Skip to content

News in Amharic

የፍርሃትና ስም ማጥፋት ፖለቲካ በኢትዮጵያ

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

2011፡ የሙስና አገዛዝ፤ ፍርሃትና ሰም ማጥፋት

በዲሴምበር 2011 ‹‹ኢትዮጵያ የደም ሃገር ወይም የንቅዘት (ሙስና) ሃገር›› በሚል ርእስ የኢትዮጵያን ሁለት ገጽታ በማመዛዘን አንድ ጦማር አስነብቤ ነበር፡፡ በዚያን ወቅት ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በተባለው ተቋም ተቀምጦ የነበረው ገጽታ ያሳየው ኢትዮጵያ ለም መሬቶች በተንኮል በተጠቀለለ ስውር ደባ እየተቸበቸቡ እንደነበር ነው፡፡በዘገባው ላይ ተቋሙ ለኢትዮጵያ ያሰፈረው ነጥብ (10 ከሙስና የፀዳ ማለት ሲሆን 0 ደግም በሙስና ንቅዘት ያጨማለቀው ማለት ነው) ኢትዮጵያ 2.7 ነበር ያገኘቸው፡፡ በሙሰና ከታወቁት የኣለም ሃገሮች ዋነኛዋ ኢትዮጵያ ናት ይል ነበር::  የግሎባል ፊናንሻል አንተግሪት ድርጅት ደግሞ ባለፉት ፲ ኣመታት ከኢትዮጵያ 11.7 ብልዖን  ያሜርካን ብር በሀገወጥ መንገድ ከኣገሪቷ ወጥቶአል ብሎ ዘገቦ ነበር::

ባልፈው ኣመት: አሁንም በስላጣን ላይ ያለው ገዢ ኣስተዳደር ኢትዮጵያን በሽብርተኞች ማነቆ ውስጥ ተወጥራ እንዳለች ሃገር አድርጎ ለማቅረብ ባወጣው የልመናና የገንዘብ መቧገቻ እቅዱ ባለሶስት ክፍል የፕሮፓጋንዳ የቅጥፈት ታሪክ ‹‹አኬልዳማ›› በማለት (ወይም የደም መሬት በማለት ከአክትስ 1፡19 በመዋስ፤ የአስቆሮቱ ይሁዳ ክርስቶስን ክዶ በመሸጥ ባገኘው ገንዘብ የተገዛ መሬት) ከልብ ወለድ የማይሪቅ ትርኢት ለሕዝብ ኣቅርቦ ነበር፡፡ ይህም ትርኢት በአትዮጵያና በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሰዎች በሚታገዝና በሃገርም ውስጥ ባሉት የሚደገፍ የሽብር ተግባር አምባ አድርጎ ለማሳመን የተሰራ ነው፡፡ አኬልዳማ ሲጀምር በኢትዮጵያ ውስጥ ሊከሰት የሚችል በማለት የደም ጎርፍ መምጣት እንደሚችልና፤ ሸብር ዓለምን በማጥፋት ላይ ነው፡፡ ‹‹አኬልዳማ›› ሲተረት: “ሽብርተኝነት የቆምንበትን መሬት እያነቃነቀ፤ ዕለታዊ እንቅስቃሴያችንንም እየገታ መሆኑን በቅጥፈታዊ ፈጠራ ለማሳየት የቀረበ ትርኢት፡፡ አሁን እየተናገርኩ ያለሁት ስለዓለም አቀፉ ሥብርተኝነት አይደለም፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት በገዢው መንግስት ለኢትዮጵያ የተቀመጠውን የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳና በዚያም ውስጥ ስለተካተተው አኬልዳማ ተብሎ ስለተቀፈቀፈው፤ ሸብርተኝነት ለኢትዮጵያ አስጊና አሳሳቢ ችግር ነው…… ስለተባለው ነው፡፡”

በአኬልዳማ ውስጥ ተቀነጫጭቦና ተቆርጦ የተቀጣጣለ የቪዲዮ ቅንጥብጣቢ፤የአልቃይዳና የአል ሸባቢ ተከታዮች የመለስ ዜናዊን መንግስት ለማፍረስና ሃገሪቱንም ለማመሰቃቀል ተነስተዋል በማለት የሕጻናት የአዛውንቶች፤ እሬሳ በመንገድ ላይ ወድቀውና በደም ተጨማልቀው በዝንቦች የተወረሩ እሬሳዎች፤ የተቆራረጡ እግሮች፤ የነደዱ ተሸከርካሪዎች፤ በቦምብ የፈራሱ ሕንጻዎች፤ የህክምና ባለሙያዎችም የተጎዱትን ሲያክሙና በኒው ዮርክ በሽብርተኞች የፈረሱት የትዊን ታወር ምስሎች በማገጣጠም የገዢውን መንግስት ስጋት አሳማኝ ለማድረግ ምስሉን አቀነባብሮ አቀረበ፡፡ በዚህም የሕብረተሰቡ ሕሊና ውስጥ የፈጠረው ስጋት ቢኖር የገዚዎች ውሸትና ተራ ፕሮፓጋንደ እንጂ ከዚያ ያለፈ ለማሳመን የቻለው የለም፡፡ ማስረጃውን እንመልከት ብሎም ያቀረበው ዘጋቢ ቁጭት በውስጡ እየነደደ የሃሰት ስሜቱን ታግሎ በማውጣት በጥፈሩ እየቆመና ቃላትን እየረገጠ በሚያስፈራና ቀፋፊ በሆነው ድምጹ ህጻናትን እያሰበረ አርጉዝ ሊያጨነግፍ በሚችል ስሜት አቀረበው፡፡ እስቲ እውነተኛውን ማስረጃ እንመልከት፤  ይላል ‹‹አኬልዳማ››: “ባለፉት ጥቂት ዓመታት፤ 131 የሽብርተኞች ጥቃት ተካሂዶ 339 ተገድለዋል 363 ቆስለዋል፤ 25 ደግሞ በሽብርተኞች ታፈነው ተገድለዋል፡፡” ቅጥፈት የተሞላበት፤ ማጭበርበሪያ የሆነ፤የተዛባ ትረካ የተካተተበት አኬልዳማ በተቃዋሚዎች ላይ ሕዝባዊ ጥላጫና ጥርጣሬ ለመንዛት ሆን ተብሎ የተዘጋጀ ነበር፡፡ውጤቱ ግን እንደታሰበውና እንደታሰበው ሳይሆን መክኖ ቀረ፡፡

2013 የሙስና አገዛዝ፤ ፍርሃትና ሰም ማጥፋት

ወደ ፌብሪዋሪ 2013 ፈጠን ብለን እንሂድ::  በቅርቡ ተጣርቶ በወጣው ባለ 448 ገጾች የዓለም ባንክ ዘገባ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ካሉት ሀገራት ሁሉ ከአናት እስከ ታች ድረስ በባለስልጣናቱና በአጃቢ አገልጋዮቻቸው ንቅዘትና ሙስና የተዘፈቀች ሃገር ናት ይላል፡፡ በዘገባው መሰረት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት የንቅዘቱ መፈልፈያ ማህጸን ነው፡፡  ገዢው ኣስተዳደር በጣሙን የገዘፈ መዋእለ ንዋይ በማፍሰስ በቴሌ ላይ ኢንቬስት ቢያደርግም፤በአፍሪካ ሁለተኛው የቴሌፎን ስርጭት ዝቅተኛ የሆነበት ሃገር ከመሆን አላዳነውም፡፡ በጣም አናሳ አግልግሎት ሰጪ ድርጅት ከመሆንም አልፎ፤ከተጠያቂነት ነጻ የሆነ የዘረፋ ማእከል ነው፡፡በሃገርም ውስጥ ሆነ በውጭ ታዛቢዎች ድርጅቱ በሙስናና በንቅዘት የተገነባ ለምዝበራ የተጋለጠ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ በየትኛውም የአገልግሎት አሰጣጥ መመዘኛ ተጎታችና እርካታ ይሉት አገልግሎት የሌለው በየጊዜው በሚነደፈው የሙስና እቅድ ውስጥ ተውተፍትፎ አገልግሎቱ እርባና ቢስ ነው፡፡ የፍትህ ስርአቱም ቢሆን ሕብረተሰቡን በነጻ እንዳያገለግልና የፖለቲካ መሳሪያ እንዲሆን ተደርጎ በገዢው ኣስተዳደር ንጹሃንን በመወንጀል ፖለቲካዊ እንቅስቃሴን በመግታት አገዛዙ ከመንበሩ ሳይለቅ የሚቀጥልበትን ሁኔታ የሚተገብር የፍትህን ስርአት የጣሰ ነው፡፡ ይህም በህጋዊ ኢፍትሃዊነት ብቻ ጉዳት ከማድረሱም ባሻገር ለጉቦና ለንቅዘት ተጋልጦ ያለ አንድ የገዢው መንግስት የጦር መሳርያ ነው፡፡ ገዢው መንግስት በስልጣን መቆየቱን እንጂ ለሃገርና ለህዝብ እድገትና ልማት ጨርሶ ደንታ የሌለው በመሆኑ ከጉቦ ውጪ አንዳችም ጉዳይ በስርአት አይከናወንም:: የዚህም ሂደት ዋናው አስፈጻሚ ሞተር ገዢው ፓርቲና ጀሌዎቹ ናቸው፡፡

በፌብሪዋሪ 5/2013 ላይ በአዲስ አበባ ያለው ገዢው ኣስተዳደር ‹‹ጂሃዳዊ ሃራካት›› (የቅዱስ ጦርነት እንቅስቃሴ) በሚል ርዕስ አንድ ዘጋቢ (ዶኩሜንታሪ) ፊልም በእኩይ አስተሳሰብና ዲያብሎሳዊ ግንዛቤው የኢትዮጵያ ሰላማዊ ሙስሊሞች ያነሱትን ሃይማኖታችንን ለኛ ተዉልን፤ ሰብአዊ መብት ይከበር፤ በማለቱና በሰላማዊ መንገድ እንሰማ በማለታቸው፤ በየቦታው ካሉና የኢትዮጵያ ሙስሊም ሕብረተሰብ ከማያውቃቸው፤ ተግባራቸውን ከማይቀበለውና ግንኙነትም ከሌለው ጋር ገዢው ኣስተዳደር በተካነበት የቅጥፈት ዘመቻው ጥያቄ  እንዳሰኘው በሚያዝበት ቴሌቪዥን ጣቢያው ላይ አሰራጭቶ ነበር፡፡

‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› በሁለንተናዊ መልኩ የ‹‹አኬልዳማ›› ግልባጭ ነው፡፡ መሰረታዊ ልዩነቱ የሙስሊሙን ማሕበረሰብ ለይቶ ለማስፈራሪያነትና ለስም ማጥፊያ ተብሎ በአንድ የሃይሞነት ተከታዮች ተነጣጥሮ መተግበሩ ነው፡፡ በአጠቃላይ ዘጋቢው ፊልም ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ሰብአዊ መብት እንዲከበር፤ ኣስተዳደሩ በእምነታቸው ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም በመጠየቃቸው፤ ያላለሙትንና ጨርሶ ያላሰቡትን ሕዝቡ ናቸው ብሎ እንዲቀበል፤ እነዚህ ደም የጠማቸው የናይጄሪያው ቦኮ ሃራም፤የማሊው አንሳር ዲን፤ አልቃይዳ አልሻባብ ሃማስ ቅርንጫፍ ተከታዮች  በማለት ያልሆኑትን ናቸው በማለት በተለመደው የፍርሃትና የመደናገጥ ዜማው ታርጋ በመለጠፍ ላይ ያተኮረ ነው፡፡  ዶኩሜንታሪው ተቆቋሪ በመምሰልና አዛኝ ቅቤ አንጓችነቱን በማጠናከር በሙስሊሙ መሃል የተሸሸጉ ጥቂት ሽብርተኞች በማለት ይኮንናል፡፡ ዘጋቢው ፊልም በየትም የአፍሪካ ያልታየ የቂመኝነትና የትእግስት ማጣት እኔ ካልኩት ውጪና ከምፈቅደው ባለፈ ንክች ያባ ቢላ ልጅ ይሉት ዓይነት ድንፋታ ብቻ ነው፡፡

ውሸት ሞልቷል፤ እርቃኑን የቆመ ውሸት አለ፤የጎደፈ ውሸት አለ፤የሆዳሞች ውሸት አለ፤የመልቲዎች ቅጥፈት አለ:: ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ደሞ እነዚህ ሁሉ ውሸቶች የተጠናወቱት ነው፡፡ ይህን የሚያቀለሸልሽ ዶኩሜንታሪ ከተመለከትኩት በኋላ፤ በቅርቡ ያለፈው መለስ ዜናዊ የሜይ 2010ን ምርጫ 99.6 በሌብነት የተገኘ ድል አስመልከተው የአውሮፓ ዩኒየን የምርጫ ታዛቢዎች ስለተከናወነው የድምጽ ሌብነቱ  ፊት ለፊት ሲጋፈጡት የሰጠው ምላሽ ታወሰኝ፡፡ መለስ እጅ ከፍንጅ በመያዙ የአውሮፓ ዩኒየነን የምርጫ ዘገባ በመኮነን ከአንድ መሪ በማይጠበቅ መልኩ ማፈሪያ የሆነውን ‹‹ዘገባው ቆሻሻ ስለሆነ ንብረቱ  ወደሆነው ወደ ቆሻሻ መጣያ ሊወረወር ይገባዋል›› ነበር መልሱ፡፡ ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ደካማ፤ አስቂኝ፤ማሰብ ከተሳነው ህሊና የወጣ፤ማስመሰያ፤ መርዘኛ፤ በጉራ ያበጠ፤ ድንፋታ ነው፡፡ ይህን መሰሉ የመለስ አባባልም የቅራ ቅንቦ ክምር ነውና ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ወደ ቆሻሻ ቱቦ ተደፍቶ ከእጥብጣቢውና ከቆሻሻው ፍሳሽ ጋር ሊቀላቀል ይገባዋል፡፡

ፈጽሙ የተባሉትን ያለ ጥያቄና ስስብእናቸውን ለጥቃቅን ጥቅም በመሸጥ ታዛዥነታቸውን የሚያረጋግጡትን አሰባስቦ ተመረጡ ብሏል፡፡ ቀድሞ ለዘመናት ከመንግስት ተጽእኖና ቁጥጥር ነጻ የነበረው አስልምና ካዉንስል አሁን በገዚዎቹ  የሚታዘዝና የገዚዎቹን ትእዛዝ በመቀበል የሚያስፈጸም የካድሬዎች መጠራቀሚያ ሰፈር ሆኗል፡፡ መያዙ፤በሽብርተኝነት ወንጅላ ካውንስሉን የመቆጣጠር ህልሙን ተግባራዊ ማድረጉ በኢትዮጵያ ውስጥ ገዚዎቹ ሃይማኖቶቹን መጠቀሚያ የማድረጉ ሂደት እየባሰ መሄዱን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ በሰላማዊ እንቅስቃሴያቸው ጊዜ በርካታ ሙስሊሞች በመላ ሃገሪቱ ለእስራት እየተዳረጉ ነው፡፡ በኦክቶበር 29 ገዢው የኢትዮጵያ መንግስት 29 ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ የነበሩ ሰዎችን በሽብርተኝነትና የሙስሊም መንግስት ለማቋቋም ተንቀሳቅሰዋል በሚል ለእስር ዳርጓል፡፡

ጂሃዲስቶች ተመልሰው እየመጡ ነው?!

‹‹ጂሃዳዊ ሃራካት›› የኢትዮጵያ መንግስት ጂሃዲስቶችን ከጓዳው እያወጣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያስፈረራ የመጀመሪያው አይደለም፡፡በ2006 ዓም የመለስ ዜናዊ ታንኮች መንገዳቸውን ወደ ሞቃሾ ከማምረታቸውና በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃን የሱማሌ ህዝቦችን ከመጨፍጨፋቸው በፊት፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩት ከቤት ንብረታቸው ከመፈናቀላቸውና ከመልቀቃቸው አስቀድሞ መለስ ዜናዊ የሶማልያን ጂሃዲስቶች፤ ሽብርን ፈጥሮ፤ በሚገዛው ሃገር ውስጥ የሚፈጽመውን ሽብር፤ ጭቆና፤ ግፍ፤ መጠን ያጣ በደል፤ የሰብአዊ መብት ገፈፋ፤ የፍትህን መዛባት ከዓለም ገጽታ ለመሰወርና አዲስ ባወጣው የሶማሌ ጂሃዲስቶችና ……… በመተካት በተለይም የአሜሪካንን መንግስት ትኩረት ከኢትዮጵያ የግፍ አመጽ በማሸሽና ወደ ሶማሊያ ላይ በማስተኮር የአሜሪካንን  መንግስት የዲፕሎማቲክ ድጋፍ ሙሉ ፈቃድ ተጎናጸፈ፡፡

‹‹ጂሃዳዊ ሃራካት›› ወይም እስልምናን ማስፈራሪያ ማድረግ ጥበብ

‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› የሚያስጠላ የሙያ አልባዎች ቅጥ የሌለው ፕሮፐጋንዳ ሲሆን ማንም ቢሆን ከተመለከተው በኋላ የዘገምተኛ መሃይም አስተሳሰብ ከማለት ቀልድ ሌላ ትርጉም አያገኝለትም፡፡  ለአዘጋጂዎቹ ግን ቁም ነገር የሌለው ተብሎ ብቻ የማይተው ሳይሆን ጠቅላላውን የሙስሊም ማሕበረሰብ ዝቅ አድርጎ የመመልከትና እንደ መሪም ሃላፊነት የጎደለው ጋጠ ወጣዊ ተግባር ሊባል ብቻ ነው የሚቻለው፡፡ ለማስተላለፍ የተፈለገውም በጥላቻ የተሞላና በሰላም የኖሩትን የአንድ ሃገር ሰዎች በማከፋፈልና ጠብ እንዲጫርና ጣልቃ ገብቶ የተለመደ የመግደል የማቁሰል ሱሱን ለመወጣት ተብሎ ‹‹ጥሩ ክርስቲያኖች›› ላይ ‹‹መጥፎ ሙስሊሞች››  ሊፈጽሙ ያሰቡት ደባ›› በማለት፤ ሁለቱ እንዲጋጩ፤ አለመግባባት ጨርሶ ሳይኖራቸው አንዱ የሌላው ችግር ደራሽ፤ አሳቢ፤ በሃዘንም ሆነ በደስታ አብረው በመቆም ዘመናት ባሳለፉት ወንድማማቾች መሃል አለመግባባት በመፍጠር በድንገት የሙስሊም ሽብርተኞች መጡብህ በሚል ስር የሰደደና የተካኑትን የማናቆር ተግባር በመተግበር የእስልምና መንግስት ለማቋቋም እየተንቀሳቀሱብህ ነው በማለት ክርስቲያኑ እንዲነሳሳ በመጨረሻም ግጭቱ እንዲሰምርላቸው ነበር ቅዠታዊ ስልት ነበር፡፡ ቀደም ሲል‹‹አኬልዳማ›› ብለው የፈጠሩት  የቆርጦ ቀጥል የማፍያ ተግባራቸው፤ ሙስሊሙን ክርስቲያኖች ሊያጠፉህ መጡብህ ለማለት ተብሎ ቢተላለፍም፤ አቅራቢውም ትንፋሽ እስኪያጥረው ቃላቱን እየረገጠና በዘጋቢው ፊልም ውስጥ የነበሩትን ንጹሃን ዜጎች፤ ከአለቆቹ በበለጠ ጥላቻው ከሮበት እስኪታይ ድረስ ቢንደፋደፍም ውጤቱና ሕዝባዊ መልሱ ግን ከ ‹‹ዶሮን ሲያታልሏት………›› አላለፈም፡፡ እንዲጠሉ የታቀደላቸው ጭርሱን የፍቅር አድባራት ሆኑ፡፡ በእዝ ማስጠላትና ማራቅ ባለመቻሉ ግለሰቦችን ከእገሌ ጋር ቢቀርብህ ይሻላል በሚል ከንቱ ተራ ማስፈራርያ መጠቀሙም ቢሆን ብዙም አልሰመረም፡፡

ገዢው መንግስት በዚህ ዱክትርናው በርከት ያሉ የፕሮፓጋንዳ ግቦችን ለመፈጸም ሞክሯል  1) የማን አለብኙ መንግስት ሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር፤በሃይሞኖቶች መሃል ጣልቃ ገብነቱን እንዲያቆምና የማይመጥናቸውን የራሱን ፍላጎት ለሟሟላት ሲል ብቻ ሽብርተኞች፤አክራሪ ጂሃዲስቶች፤ የመግደል አባዜ የተጠናወታቸው በማለት የራሱን መታወቂያ  በሙስሊማኑ ላይ ለመለጠፍ መሞከር: 2)የክርሰትና እምነት ተከታዮችን በማነሳሳትና ነገር በመቆስቆስ ጥላቻና በመዝራት በሙስሊም ወንድሞቹ ላይ ጥርጣሬና እምነት እንዲያጣ ለማድረግ መሞከር፤ 3)ሙስሊሞችን ለይቶ በማወቅና ስማቸውን በእኩይነት በማቅለም ፍርሃት እንዲያድርባቸው ማድረግ፤ ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር ማጋጨት፤ ሁሉንም የሕብረተሰብ አባል እንደሚጠሉና ለራሳቸው የሚሆን ዓለም ለመፍጠር የሚጥሩ በማስመሰል ሌላውን የሕብረተሰብ አካል በጥላቻ እንዲነሳሳባቸው ማድረግ፤እንዲሁም ለመወንጀል ለመያዝ በግፍ ለማሰርና ለማሰቃየት በመጨረሻም የሚመኘውን የሰውን ልጅ ክብር በማዋረድ ለመከራ መዳረግ፡፡ 4)መላው ሕብረተሰብ ላይ ያጠላበትን የመከራ የርሃብ የችግር የድህነት የኤኮኖሚና የፖለቲካ እጦቱን፤ሙስሊሙን ጂሃዲስቶች ናቸው በሚል ከንቱ የጉሮ ወሸባዬ ያልተቃኘ ዜማው በማደናቆር ሃሳብንና ቁጭትን ለማስለወጥ የተዘረጋ የኢህአዴግ ዲያብሎሳዊ አካሄድ ነው፡፡ 5) ጨርሶ ሙስሊሙ ሕብረተሰብ አስቦትና አንስቶት የማያውቀውን አስተሳሰብ የሙስሊም መንግስት ለማቋቋም፤ ቦምብና ሌሎች መሳርያዎች ለማንሳት እንዳቀዱ በማስመሰል ፕሮፓጋንዳውን እንደ የእድር የቀብር ጥሪ ቢያናፋም ቀብሩ የማን እንደሆነ ሕብረተሰቡ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ አልተቀበለው፡፡ እርግጥ ገዢው መንግስት የሕዝብን ቁጣና የበቃህ ስሜት በሚገባ ስለተረዳው በማድረግ ላይ ያለው አስተሳሰብንና አመለካከትን በማስቀየር ጊዜ መግዛትን ነው፡፡ የዓለም ባንክ ጥርት ያለው የ448 ገጽ ዘገባ፡፡

ይህንን የበሬ ክምር እበት በመመልከት ጊዜያቸውን ማጥፋት ለማይፈልጉ (ማየት ካለባቸህ ደግሞ አፍንጫችሁን ጠቅጥቁት) እንደዘጋቢ ፊልም ለማለፍ ቅንጫቢው እነሆ፡፡ የዶኪመንተሪ ቅልመዳ ትርኢት ሲከፈት መክፈቻውንና ማስረጃውን በጸሁፍ በማስቀደም ይጀምራል ‹‹ጥቂት ግለሰቦች የእስልምና ሃይማኖትን ከለላ በማድረግ፤የሥብር ተግባራቸውን ለመፈጸም ሲሉ ባደረጉት እንቅስቃሴ ላይ የቀረበ ማስረጃ፡፡ ከብሔራዊ ደህንነት አግልግሎት፤ ከፌዴራል ፖሊስ፤እና ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር የተቀነባበረ፡፡ ፊልሙ ማስረጃዎችን በመቅረብ እያንዳንዱ ተጠርጣሪ የእስልምና ሃይማኖትን መጋረጃ በማድረግ የአልቃይዳንና የአልሸባብን እቅድ በኢትዮጵያ ለመተግበር ያደረገውን እንቅስቃሴ ያስረዳል›› ይላል፡፡

ለ13 ሴኮንዶች ቀስ እያለ በጽሁፉ ምስል ይተካና ያለአንዳች ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ የአንድ ‹‹ሽብርተኛ›› ተብሎ የተፈረጀ ዜጋ ገጽታ በጥቁር ግድግዳ ፊት ለፊት ቀስ እያለ ተመለካቹን በሚያስደነግጥና በሚያስፈራራ መልኩ ለ8 ሴኮንዶች ብቅ ይልና እያዘገመ ወደ ቀኝ ይሄዳል፡፡ይህ በፎቶሾፕ ምስሉ የተቀነባበረውና ቆርጦ የተቀጠለው ሰው አውሬ፤በረኸኛን እንዲመስል ቃሉን በለሰለሰና በረጋ  መንፈስ ሙስሊም በሆኑና ባልሆኑ መሃል ‹‹ጂሃዲ›› ያለ ልዩነትና በሕብረተሰቡ ውስጥ የሌለ አመለካከት ለማስያዝ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ድራማ ነው፡፡ ይህን ዘጋቢ ያሉትን ማስረጃ ያዘጋጁት እርባና የለሾች እራሳቸውና የናጣቸውን የፍርሃት ድባብ በማቅረብ ለምን ሕብረተሰቡን የማይፈራውን ፍርሃት እንዲፈራ ያደርጉታል፡፡

‹‹ማስረጃ›› ተብሎ የሚደመጠው የያዘው ‹‹ኑዛዜ›› (በአብዛኛውከሁለት አለያም ከ3 አረፍ ተነገር ያልዘለለ፤ወንጀለኞች እንዲመስሉ ሆን ተብሎ የተቀነባበረባቸው ሆኖ ተከሳሦቹ የጥፋተኝነት እምነታቸውን ያረጋገጡበት ቢባልም በመርማሪው በኩል ምን እንዳለም ሆነ እንደጠየቀ አንዳችም ቃል አይሰማም) በአሜሪካን መንግስት የዓለም አቀፍ ሃይማኖቶች ነጻነት ኮሚሽን የተጠቀሱት 29 ተከሳሾች ዘገባ ግን ከተባለው አንዱንም አላካተተም፡፡ (እነዚህ ቃላቸውን ሰጡ የተባሉት ሰዎች ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያለ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ይኼው ፊልም ለሕዝብ እንዳይቀርብ ትእዛዝ ቢሰጥም ሰሚአጥቶ አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ አይነት እየተላለፈ ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ አሳፋሪ መንግስታዊ የፍትህ ጥሰት የት ይታያል? ከቃል አሰጣጡ የሙስሊም የሆኑና ሙስሊም ያልሆኑ ጂሃዲስቶች የኢ ቲ ቪ  ትርኢት ተከትሎ፤የቪዲዮ ቁራጭ ትእይንት ይከተላል፤ ወጣቶች (ሙስሊም አሸባሪዎች እንዲመስሉ ከሌላ ቪዲዮ ላይ የተቀነጨበ) ከአንድ ነገር ለማምለጥ ሲሸሽ ይታያል፡፡ ከኢንተርኔት የተለቃቀሙ ሌሎች ምስሎችም ተቆርጠው በመቀጠል፤በጭንቅላታቸው ላይ ስካርፍ ያሰሩና መሰወሪያ ፊታቸው ላይ ያከናነቡ በዓለም ላይ በተለያየ ወቅት ሽብርተኞች የተነሱትን ቪዲዮ መጠቀሚያ በማድረግ ቦታውና ጊዜው የማይታወቅ ፊልም ቀርቧል፡፡

የጽሁፍ መግለጫው ተከትሎ ይመጣና በድምጽም ‹‹ቦኮ ሃራም በኢትዮጵያ›› በሚለው ይታጀባል፡፡ ወጣት ኢትዮጵያዊያን በሰላማዊ መንገድ ለመብታቸው ተሰልፈው ይታያሉ፡፡ አንድ ወጣት ሙስሊምም በአንድ ቦታ ቆሞ ለተሰበሰቡት ‹‹ሙስሊሞች አሸባሪ፤ ወንጀለኞች፤ እና የሙስሊም መንግስት ለማቋቋም ይፈልጋሉ ተብለን ተወንጅለናል›› ይላል:: በርካታ ሰዎች ጥምጣም ያደረጉና መሳርያ ያነገቡ ሰዎች መልክና ሁለንተናቸው ጨርሶ ኢትዮጵያዊያን የማይመስሉ፤ አንድ ጢሙን ያጎፈረ ሰው ሲናገር ሌሎች ጉድጓድ ሲቆፍሩና መሳርያ ከተቀበረበት ሲያወጡ፤ ዓላማችን የሙስሊም መንግስት ለማቋቋም ነው በማለት ሲነጋገሩ ይደመጣል፡፡ ከዚሁ ጋር በመንግስት ‹‹ሽብርተኞች የሚል የማደናገሪያ ስም የተለጠፈባቸው የ29ኙ ተከሳሾች ምስል በቴሌቪዥኑ መስኮት ላይ ይመላለሳል፡፡ ይህም የሚነገረው ጉዳይ አባሎች ናቸው ብለን እኛ ተመልካቾች እንድናምን ሆን ተብሎ የተደረገ ቢሆንም ተመልካቹ ግን ከማመን ይልቅ በስህተት ልጆች ለጨዋታ ያቀነባበሩትን ፊልም መሰል ዝብርቅርቅ መጨረሻና መጀመርያ የሌለው በማለት በሚገዘው መንግስት ተራ ወንበዴነት አዝኖ ታዝቧል፡፡ በቃላትና ግድ የምታምኑትን እመኑ በሚል የማስገደጃ አካሄድ ቀረበ እንጂ ማስረጃ ተብሎ በምንም መልኩ ተቀባይነት አያገኝም፡፡ የግፍ ተከሳሾቹ ምስል ከየቦታው ተለቃቅሞ ሽብርተኞች፤ የሽብርተኞች ጥፋት በሚለው ቃል ብቻ በመታጀቡ ንጹሃኑ ያልሆኑትን ያደርጋቸዋል ብሎ የሚያምን ገዢ ዲክታተራዊ የቃዠ መንግስት ብቻ ነው፡፡

 

የሕግ የበላይነት ወይስ የመሃይሞችና የሕግ የበላይነት

የገዢው ፓርቲ ሰዎች በተደጋጋሚና አፋቸው በተከፈተ ቁጥር ምን ያህል ሕገመንግስቱን እንደሚያከብሩትና ለሕግጋቱም የቱን ያህል ታማኞችና ተገዢዎች እንደሆኑ ይቦተልካሉ፡፡ ባለፈው ሴፕቴምበር የፕሮፐጋንዳው ሂትለራዊው ሚኒስቴር በረክት ስምኦን ስለ መለስ መታመምና መሞት በየቀኑ ታላቁን የወቅቱን ውሸት ሲዋሽ ሲዋሽ ደሞ ሲቀላምድ ደሞ ሲቀላምድ፤ ችግር የሌላ መሆኑንና በሕገመንግስቱ መሰረት መተካካቱ እንዳለ ነው የሚለውን ያልተቃኘ ቱልቱላውን ሲነዛ ከረመ፡፡ እንደ መገናኛ  ሚኒስትርነቱ ስምኦን የ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት››ን መተላለፍ ያዘዘው እሱ ነው፡፡ ማንንም ሰው የሚያስገርመው ግን እነዚህ ለሕገ መንግስቱ መከበርና ልዕልና ቆመናል በማለት በየጊዜው ከበሮ የሚደልቁት ማን አለብን ባይ ዲክታተሮች እነዚህን የፈጠራ ክሳቸው በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያሉትን ንጹሃን ዜጎች ከችሎቱ አስቀድሞ እንዲህ አይነቱን ፓርቲያዊ የስልጣን ማክረሚያ ፍርዳቸውን ማስተላለፋቸው መብት መጣሳቸው መሆኑን አንገታቸው ላይ የተሰካው ቅል አያስታውሳቸው ይሆን? ድርጊታቸው የሼክስፒርን አባባል አስታወሰኝ፡፡ ‹‹ዲያቢሎስም ለራሱ መጠቀሚያ መጽሃፍ ቅዱስን ይጠቅሳል›› ያለውን፡፡ እነዚህ ሰዎች ያላዋቂ ሳሚ ናቸው ወይስ የሰይጣን ቁራጮች? ላለፉት በርካታ ዓመታት በተደጋጋሚ እንዳልኩት በኢትዮጵያ ላለው አረመኔ መንግስት ስለ ሕግ የበላይነት ማውራት ለዲያቢሎስ መጽሃፍ ቅዱስን እንደማንሳት ነው፡፡ አይግባቡምና፡፡  ሕገመንግስቱ እግር አውጥቶ እየዳመጣቸው እንዲገባቸው ሊያደርግ ቢሞክር እንኳን ጨርሶ ድንጋያማ ሕሊናቸው ተፈረካክሶ ያልቃል እንጂ አይገባቸውም፡፡

በ‹‹ሽብርተኘነት የተጠረጠሩት›› ሙስሊሞች ጉዳይ እና ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ላይ ቃላቸውን ሰጡ የተባሉት ጉዳይ ሊተኮርበት የሚገባው 3 ነጥብ አለ፡፡ 1) እነዚህ ተከሳሾ ቅድም ችሎት ታሳሪዎች ስለሆኑ በሕገመንግስቱ ላይ በተደነገገውና በሌሎችም ሃገሪቱ ከገባችባቸው ፍትሃዊ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች አኳያ መብታቸው ሊከበርላቸው ግድ ነው፡፡ 2) እነዚህ ተጠርጣሪዎች ቃላቸውን በፈቃደኝነትና በነጻ አለመስጠታቸውን የሚያረጋግጠው በካቴና ቀርቦ የነበረው ተጠርጣሪ ሲሆን ሌሎችም ቢሆኑ አያያዛቸውና ያሉበት ሁኔታ ሕጋዊ ስርአትን የተከተለ አለመሆኑ ይታወቃል፡፡ 3) ሁሉም 29 ታሳሪዎች የፖለቲካ እስረኞች ናቸው፡፡ ሕገመንህስቱን ለማክበር በሱም ለመመራት ጨርሶ ፈቃድ የሌላቸው መሪዎች፤የጣሳሪዎቹን ሰብአዊ መብት ያከብራሉ ማለት የማይሞከር ነው፡፡የሃገሪቱ መሪዎች ባላቸውና በሚያሳዩት ተግባራቸው ምን ያህል ከእውቀትና ከሰለጠነው ፖለተካ ጋር እንደማይተዋወቁ ነው በማሳየት ላይ ያሉት፡፡ እነዚህ ገዢዎች ከመሰረቱ ጀምሮ ከተንኮልና ከግፍ በደል በስተቀር አንዳችም ተግባር አለመፈጸማቸውንና ማንኛቸውንም ጉዳይ ይተገብር የነበረው የሞተው አለቃቸው እንደሆነ ሳያፍሩ በመናገር የራሳቸውን ብቃት የለሽ መሆን አውጀዋል፡፡ ማንም ተከሳሽ በፍርድ ሂደት ወንጀለኛ እስካለተባለና እስካልተፈረደበት ጊዜ ድረስ ነጻና ንጹህ ነው፡፡ በምንም መልኩ በግዳጅ የተገኘ ቃል ለማስረጃነት ሊቀርብ አይችልም፤ ድርጊቱም ዓለማቀፋዊ ድንጋጌዎችን ያልተከተለ ነው፡፡ ሰብአዊ መብትን ይገረስሳል፤ የፍትህን የበላይነት ይቃረናል:: 4) በጣም የሚያሳዝነው ቀልድ ደግሞ ፍርድ ቤቱ በኢቲቪ እና በሬዲዮ ድርጅቶች ላይ ያን የተቀነባበረና ቆርጦ የተቀጠለ የማፍያ አካሄድ ጨርሶ እንዳይተላለፍ ያስተላለፈውን ትዕዛዝ፤ እነማን አለብን ‹‹እኛው የፈጠርነው ዳኛም ሆነ ችሎት ሊከለክለን አይችልም›› በማለት ትእዛዙን ጥሰው ሲያስተላልፉት፤ በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ መሰረት ባለመፈጸሙና አግባብም ስላልሆነ የቀረቡትን ማስረጃ የተባሉትን ሁሉ አመኔታ ስለማንሰጣቸው ተቀባይነት አይኖራቸውም›› በማለት እንኳን ዋጋ ቢስ በማድረግ ፈንታ ችሎቱና በችሎቱ ወንበሮች ላይ የተጎለቱት እራሳቸው እርባና ቢስ ሆነዋል፡፡

ተስፋ የቆረጠ አምባገነንነት እና የዕጣቢ መውረጃ ቱቦ ፖለቲካ በዚህ ዶኩመንታሪ በኢትዮጵያ ያሉት ጨቋኝና ርህራሄ ቢስ ገዢዎች ከምንም በታች አዘቅዝቀው ወርደው ውረደታሞች መሆናቸውን ገሃድ ከማውጣታቸውም አልፎ የዝቃጭ መፈሰሻ  ቱቦ ፖለቲከኛነታቸውንም ይፋ አድርገዋል፡፡ አንድ ብቸኛ ሆኖ ሊታይና ሊረጋገጥ የሚችለው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሽብርተኛ እነሱ ገዢዎቹ ብቻ መሆናቸው ነው፡፡በ‹‹አኬልዳማ ገዢው መንግስት ሆነ››ባለው መሰረት በአሸባሪዎች 131 ጥቃት ተፈጽሟል፤339 ዜጎች ተገድለዋል፤363 ቆስለዋል፤25 ደግሚ ተጠልፈው ለሞት ተዳርገዋል:፡ ይሁንና በራሱ በመለስ ዜናዊ ይሁንታ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን እንዳጣራው  ምርጫ 2005ን ተከትሎ በጥቂት ቀናት ውስጥ በመለስ ዜናዊ አመራርና ትዕዛዝ መሰረት፤ 193 ሰላማዊ ዜጎች አንዳችም መሳርያ ያልነበራቸው 193 ሲገደሉ፤763ቱ ደግሞ ለከፍተኛ ቁስለት ተዳርገዋል፡፡ ኮሚሽኑ ባረጋገጠው መሰረት የስለላ ሰራተኞችና የመንግስት ጦር አባላት አተኳኮሳቸው ሰልፉን ለመበተን ሳይሆን ለመግደል በመሆኑ ሁሉም አናታቸውንና ደረታቸውን እየተመቱ ነው የሞቱት፡፡ በሴፕቴምበር 2011 ዓለም በሙሉ የኢትዮጵያ የደህንነት ሰዎች፤ በሴፕቴምበር 16 2006 በአዲስ አበባ ከተማ 3 ቦምቦች አጥምደው ካፈነዱ በኋላ ፍንዳታውን የፈጸሙት ኤርትራዊያንና የኦሮሞ ነጻ አውጪ ድርጅት አባላት ናቸው በማለት ሰበብ አድረጓቸዋል:: በዚህም ፍንዳታው የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ለስብሰባ በመጡበት ወቅት መከናወኑ የጉዳዩን ተአማኒነት አጣጥሎታል፡፡  አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ጉዳዩን በራሱ ባለሙያዎች ካስመረመረውና ካጣራ በኋላ ጣቱ የጠቆመው ወደ ኢትዮጵያ መንግስት ሆኗል፡፡ ገዢዎቹ ስልጣን ወንበር ላይ ከተፈናጠጡ ጀምሮ የተካሄዱት ግድያዎች ቢቆጠሩ ከብዙ ሺሆች በላይ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ መንግስት ነኝ ባዩ በራሱ አፈንድቶ፤ አጥምዶ፤ ደብቆ፤ አግኝቶ ያፈነዳውን አድራጊዎቹ ሌሎች ናቸው ብሎ አመልካች ጣቱን ወደ ሌሎች ሰዎች ሲዘረጋ ሌሎቹ ሶስቱ ያቶች ወደ ራሱ ማመልታቸውን መገንዘብ አልቻለም፡፡

ጂሃዳዊ ሃረካት የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ስም ለማጥፋት፤ለመኮነን፤ለማዋረድ፤ለመከፋፈል፤ ሆን ተብሎ የተፈበረከ ነው፡፡ ለዘመናት ጸንቶ በፍቅርና በመተሳሰብ የኖረውን የሁለቱን ሃይሞኖቶች ሂደት ለመበጥበጥ የተቀመመ መርዝ ነው፡፡ እዚህ ግባ የማይባል ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ በዚህም ሊፈጠር የተሞከረው በሙስሊሙና በእስልምና ሃይሞኖት ተከታዮች መሀላ መለያያት ለማስረጽ ነው፡፡ ከዚህም ሙስሊሙን ዳግም ወደ ፖለቲካና መብት ጥየቃ እንዳይነሳ፤ በፍርሃት ለማሰር፤ለመወንጀልና ለማሰር መንገድ ለመክፈት ከኤኮኖሚ፤ ህብረተሰባዊ ግንኙነት፤ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለመለየት የታቀደ ማስደንበሪያ ነው፡፡‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት እስልምናን የመፍራትና ደንብሮ የማስደንበር፤ ፈርቶ የመስፈራራት፤ ያለቀንና የበቃውን የገዢነት ስልጣን የማቆያ ዘይቤ ነው፡፡ አይሆንም አልሆነም ይልቅስ ሁሉንም ያስተባበረ የገዢዎች ግፍ ሆኗል!

በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ!

*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):

http://open.salon.com/blog/almariam/2013/02/15/ethiopia_the_politics_of_fear_and_smear

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::) ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

ኢትዮጵያ፡ ከዚህ በኋላ ቀጣዩ ጉዟችን (ወይም መቆሚያችን) ወዴት ነው?

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

በዴሞክራሲ የአንድነት ጎዳና ላይ?

በጁን 2012 ‹‹ኢትዮጵያ፡ በሕገ መንግስታዊ ዴሞክራሲ ጎዳና ላይ›› የሚል ጦማር አቅርቤ ነበር፡፡ ‹‹በርካታማ ሕበረሰቦች ከጭቆና ወደ ዴሞክራሲ ሽግግርን ሲያስቡና ሲንቀሳቀሱ፤ እንቅስቃሴያቸውን የሚገቱ በርካታ ፈተናዎች›› እንደገጠሟቸው በማስረጃ የተደገፉ ታሪካዊ እውነታዎችን ጠቅሼ ነበር:-

ከአረብ ‹‹መነሳሳት››ከታየው ልምድ በመነሳት ሕገ መንግስታዊ ቅድመ ውይይት እንደሚያስፈልግ ጠቁሜ አንዳንድ ሃሳቦችም ሰንዝሬ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ሕገ መንግስት ፍለጋና የዴሞክራሲያዊ ሕገ መንግስት ግቡ ዙርያ ጥምጥም መንገድ፤ አድካሚና ተስፋ ሞጋች ይሆናል፡፡ይም ሆኖ የማይቻል አይደለም………..ግጭትን አስወግዶ ሰላማዊ ሽግግርን ተግባራዊ ለማድረግ፤ተፎካካሪ አለያም በተናጠል ያሉት ሁሉ በአንድ ላይ መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ ይሄ ደግሞ በዋናው ግብ ላይስምምነትንና መቻቻልን መግባባትን ይጠይቃል፡፡ በዚህ የሽግግር ወቅት ሕዝባዊ የሲቪክ ማሕበረሰብን በአዲሱ ሕገ መንግስት ዙርያ ማስተማርን ያካትታል፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች፤ ድርጅቶች፤ አመራሮች፤ ምሁራን፤ ሰብአዊመብት ተሟጋቾች፤ እና ሌሎችም የጉዳዩ አካላት፤ ስርአት ባለው ፕሮግራም ተካተው ትምህርትና አስተባብሮ ማሰለፍን መውሰድና ማዳረስ በዚህም ለዴሞክራሲ ሽግግር የሚጠቅመውን ሁሉ ተግባራዊ ማድረግ  ይኖርባቸዋል፡፡ ከጭቆና ስርአት ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ስኬታማ የሆነ ሂደት ለማድረግ ኢትዮጵያዊያን የመነጋገርንና የመመደራደርን ጥበብ ሊማሩ ይገባል…….››

እነሱ በታችኛው የጭቆና ጎዳና ላይ የኋሊት እየተዘወሩ ነው፤ እኛስ በዴሞክራሲ አውራጎዳና ላይ ወደፊት እየተጓዝን ነው?

ለአንዳንድ ሰዎች ለገዢዎች ባለስልጣኖች ወይንም ለመጪው እውነቱን መንገር ቀላል ነው፡፡ ያለምንም ችግር እነዚህን ስልጣንን አላግባብ የሚጠቀሙትን ጥፋት መስራታቸውንና ልክ አለመሆናቸውን ማሳወቅ፤ ጥፋታቸው ምን እንደሆነ፤ጥፋታቸውን እንዴት ማረም እንደሚችሉና ጥፋት ለፈጸሙባቸውም ትክክል በማደረግ ማሳረም አንደሚችሉ፡፡ ነገር ግን ‹‹ማንነታቸውን›› መለየት በማይቻልበት “ተቃዋሚዎች” እውነትን ማሳወቁ ቀላል አይደለም፡፡ ስለዚህም ላልታወቁት “ተቃዋሚዎች” ለማስረዳት ከሞመከር ይልቅ: “እነሱ በታችኛው  የጭቆና ጎዳና ላይ የኋሊት እየተዘወሩ ነው፤ እኛስ በዴሞክራሲ አውራጎዳና ላይ ወደፊት እየተጓዝን ነው? ከዚህ በኋላ ቀጣዩ ጉዟችን (ወይም መቆሚያችን) ወዴት ነው? የሚል ጥያቄ ማንሳት እመርጣለሁ፡፡ ይህን መሰሉ ጥያቄ መሰንዘር ያለበት ‹‹ለተቃዋሚ አመራሮች ነው››:: ግን ለጥቂትጊዜያትም እነዚህ አመራሮች እንማንናቸው እንማንስ አይደሉም በሚል ግራ መጋባት ውስጥ ነበርኩ፡፡

ባለፈው ሴፕቴምበር ‹‹የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች በዴሞክራሲ ማለዳ ወቅት?››  በሚል ርእስ አንድ ጦማር አቅርቤ ነበር፡፡ ድምጼን ከፍ አድርጌ (እስካሁን መልስ ባላገኝም) ‹‹በኢትዮጵያ ተቃዋሚው ማነው?›› ብዬ ጠይቄ ነበር፡፡ አሁንም ሆነ ያንጊዜ ግራ እንደተጋባሁ መሆኔን መናዘዝ እወዳለሁ፡፡ ‹‹በአግባቡ የተደራጀና የማያወላውል አስተማማኝ ተቃዋሚ ፓርቲ እንደሌለ እረዳለሁ:: አንድም ጠንካራና ግንባር የፈጠረ የህብረት ፓርቲ  የገዢውንመንግስት ፖለቲካም ሆነ ፍልስፍና የሚሞግት የለም፡፡ በምሑራን ግንባር ቀደምትነት የተቀናጀና የተጠናከረ አንድም ፓርቲ ያለ አይመስልም፡፡ ሁሉንም ሙያዎችና ማሕበራት፤ሃይማኖቶችን ያቀፈ የሲቪል ማሕበረሰብ ስብስብም የለም፡፡ ለወጥ ባለ አባባል፤ ‹‹ተቃዋሚው ያው ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው ደካማ፤ ልፍስፍስ፤ ቅርጽ ያልወጣለት፤ ተጣምሮ አሁንም ከነድክመቱ፤ተከፋፍሎ፤ እርስ በርስ ለመናቆር የሚሽቀዳደሙትና ለገዢውፓርቲ የመጠናከርያና የግዛት ማራዘም አስተዋጽኦ የሚያደርጉት ናቸው? ያው አሁንም በማጉረምረም ብቻ ሰብአዊ መብትን ለማስከበር የሚጥሩት፤ የሲቪክ ማሕበረሰቡን የሚያደራጁት፤ጋዤጠኞች ተብዬዎቹ አገልጋዮች፤ እና ፈራ ተባ የሚሉት ምሁራን ናቸው? በመሳርያ ገዢውን ሃይል ገርስሰው የሚጥሉት ናቸው ተቃዋሚዎች? እራሱን በተቃዋሚነት ፈርጆና ሰይሞ ያስቀመጠችው/ው ሁሉ ናቸው ተቃዋሚዎች:  ወይስ ከላይ የተዘረዘሩት አንዳቸውም አይደሉም?

የመጨረሻዋን እንጥፍጣፊ ብሬን ለውርርድ የማቀርብበት ጉዳይ ግን የመለስ ዜናዊ አምላኪ ደቀመዝሙራን ከዚህ በኋላ ወዴት ወዴት ነው የምትሄዱት ቢባሉ ለማስረዳት አንዳችም ችግር የለባቸውም፡፡ በእርግጠኛነትም: ሰማይና መሬት ቢደበላለቁም፤ በመለስ ‹‹ዘልዓለማዊ አሸብራቂ ኮቴ ፈለግ›› እየተመራን አሸሸ ገዳሜያችንን እያስነካን፤ ጮቤ አየረገጥን የሀደሰና ግድብ ሥር የተቀበረልንን ወርቅ ለማፈስና በየዓመቱም 10. 12. 15 በመቶ የኤኮኖሚ እድገት እያልን ከፍ ከፍ ብለን በመብረር መንገዳችንን እንቀጥላለን ይሉናል……….›› እኔም የጉዞ አውራ ጎዳና ቀይሶ ወደ የህልም  መንገድ መሄዱ  ክእጅና እግርን አጣጥፎ ማፋጨት ለእናት ሃገር ከመቆዘሙይሻላል ባይ ነኝ፡፡

ለመሆኑ ጥያቄው ተቃዋሚ መሆን ወይም አለመሆን ነው እንዴ? በተቃዋሚ ጎራስ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? በተቃዋሚ ጎራ ውስጥስ ለመካተት አንድ ሰው ምን ሊያከናውን ወይም ሊያደርግ ይገባዋል? ተቃዋሚ መሆንስ ገዢውን ፓርቲና በውስጡ የተካተቱትን በመሳደብ በማጥላላት፤ በመፎከር፤ጥርስ በመንከስ፤ ስልጣንን አለአግባብ የሚጠቀሙትን በመውቀስና በመተቸት በስድብ ላይ ስድብ መከመር ነው? ስልጣንን አለአግባብ የሚጠቀሙበትንስ በመቃወም በተቃውሟችን የሞራል የበላይነትስ ማግኘት? እነዚህን አለአግባብ ማንኛውንም ጉዳይ የሚጠቀሙበትን ያለ እቅድ ያለግብ መቃወምስ ተቃዋሚነት ነው?

በተደጋጋሚ እንዳስቀመጥኩት የመለስ እምነቱ ‹‹ተቃዋሚዎች እራሳቸውን ከሚያውቁት በላይ መለስ ተቃዋሚዎችን ማወቁ ነው››::

መለስ በተቃዋሚዎቹ ከምር የስቅባቸው ነበር፡፡ የተቃዋሚዎችን አመራሮች የእውቀታቸው ደረጃ ከሱ ታች አድርጎ ነበር የሚገምተው፡፡ባስፈለገው ወቅትና ጊዜ፤ ሊያፌዝባቸው፤ሃሳባቸውን ሊያጣጥል፤ ሊበልጣቸው፤ማንም ከማንማ ሳይል ሊያላግጥባቸው እንደሚችል ያምን ነበር፡፡እርባና ቢስ ብሎ ስለሚያስባቸው፤ ለስልጣኑ አስጊና ተቀናቃኝ ይሆናሉ የሚል ስጋት አልነበረውም፡፡ በሚያደርጋቸው ሕዝባዊ ዲስኩሮቹ ሁሉ እንዳፌዘባቸው፤ እንዳዋረዳቸው፤መሳቂያ መሳለቂያ ሊደርጋቸው እንደሞከር ነበር፡፡ ተቃዋሚዎቹን የዕለት ተዕለት ክትትልና ቁጥጥር  ከጥፋታቸው እንዲመለሱም ቁንጥጫና ትንሽም በሳማ ለብ ለብ እንደሚያስፈልጋቸው ጨቅላ ሕጻናት ነበር የሚያያቸው፡፡ እንደእውነቱ ከሆነም ባለፉት የግዛት ዘመኑ መለስ ተቃዋሚዎቹን እንዳለውም በሁሉም መልኩ ቀድሟቸው በልጧቸው፤ ቀልዶባቸው፤ መሳቂያ አድረጓቸው ነበር፡፡አሁንም የመለስ ደቀመዝሙሮችና እሱ የፈጠራቸው በፈጠረላቸው ብቻ የሚመሩት የራሳቸው የሆነ አንዳችም ነገር የሌላቸው ‹‹ሰብ ግዑዛን›› በመራቸው መንገድ የውርየድንብራቸውን ለመጓዝ ነው እቅዳቸው፡፡

‹‹ተቃዋሚዎች›› አሁን የት ናቸው? 

ምናልባት በኢትዮጵያ ያሉትን ‹‹ተቃዋሚዎች›› ከእንግዲህ ጉዟችን ወዴት ነው የሚለውን ጥያቄ ማንሻ ጊዜው አማካኝ ላይሆን ይችላል፡፡ይልቁንስ አሁን ተቃዋሚዎች የት አሉ (የትም የሉም) የሚለውን መጠየቁ አግባብ ሊሆን ይችላል፡፡ ለኔ አመቺው ነጥብ፤‹‹ተቃዋሚው በአሁኑ ጊዜ፤ ወደ በቃኝ፤ አጉራህ ጠኛኝ፤ ወደ ተስፋ መቁረጡ፤ ወደ መሳቀቁ፤  ገለል ወደ ማለቱ ነው፡፡ ‹‹ተቃዋሚውን›› እንደተደገመበት አይነት ፈዝዞ ስልጣንን አለአግባብ ተከተለ ነው ማለት እችላለሁ፡፡ ‹‹ተቃዋሚው›› ደህንነት ያጣ፤ አጀንዳ ቢስ፤ አቅመ ቢስ፤ አቅጣጫ ቢስ፤ ራዕይ የሌሌለው ሆኖ ነው የሚታየኝ፡፡ ‹‹ተቃዋሚው›› ግራ የተጋባ፤ ተሸመድምዶ ያለ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ‹‹ተቃዋሚው›› አንድ ላይ የሆነበት፤ በአንድ የቆመበት፤ጠላትን በአንድ ላይ የተጋፈጠበት፤እና በአንድ ላይ ለወህኒ የበቃበትም ጊዜ ነበር፡፡ የ2005 ምልሰት! ያኔ ‹‹ተቃዋሚው›› የዘርን፤ የጎሳን፤ የሃይማኖትን፤ የቋንቋን፤ የዓላማን እና ሌሎችንም ልዩነቶች ወደ ጎን አሽቀንጥሮ ጥሎ ለነጻነትና ለዴሞክራሲ በአንድነት የቆመበት ወቅት ነበር፡፡ ያ ራዕይ ደግሞ ተቃዋሚዎችን በወንድማማችነትና እህትማማችነት መንፈስ አስተሳሰራቸው፡፡ ‹‹ተቃዋሚው›› አንድ ሆኖ መለያየትን ትቶ በቅንጅት፤ ውስጣዊ መቆራቆስን በመተው ሊከፋፍሉትና ሊያለያዩትበሚጥሩት ላይ በአንድነት ቆሞ አሸነፋቸው፡፡

ባለፉት ሰባት ዓመታት፤ ‹‹የተቃዋሚዎች›› የነጻነትና የዴሞክራሲ ራዕይ ቀስ በቀስ ባለመግባባትና በመወነጃጀል እየከሰመ ሄዷል፡፡በተቃዋሚው ጎራ መወያየት በመነታረክ ተተክቷል፤ ተግባርም ወደ ባዶነት፤ ሕብረት ወደመለያየት፤ መቀናጀት ወደ ግላዊነት፤ መሰባሰብ ወደ መለያየት፤ መፈቃቀር ወደ መጠላላት፤ መቻቻል ወደ አለመግባባት ተለውጧል፡፡ ‹‹ተቃዋሚው›› ለውጥን ይፈልጋል:: በለውጡም ኢትዮጵያን ከጭቆና በማላቀቅ የዴሞክራሲ ባለቤት ሊያደርጋትይመኛል፡፡ ግን ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር እንዳሉት፤ ‹‹ለውጥ በመንኮራኩር ተጭኖ የማይቀር ነገር አይደለም: ሊገኝ አይችልም፤በማያቋርጥ የነጻነት ትግል እንጂ፡፡ ወገባችንን ጠበቅ አድርገን ለነጻነታችን መጣር አለብን፡፡ ወገብህ ለመጥ ካላለ ጠላትህ ሊጋልብህ አይችልም… ከልምድ እንዳየነው ጨቋኝ ገዢ ነጻነትን በፍቃደኛነት አይሰጥምበተጨቋኞች መገደድ ይኖርበታል››

የኢትዮጵያ ‹‹ተቃዋሚ›› ሃይሎች፤ ወገቡን ጠበቅ አድርጎና ጥርሱን ነክሶ ፍላጎቱን ማሳወቅና ማግኘት አለበት፡፡ ወገብን ማጥበቂያዎች በርካታ መንገዶች አሉ፡፡ስለሰብአዊ መብት መከበር መናገርና፤ ገዢዎች የሚያደርሱትን በደል ግፍና ጭቆና መናገርም ወገብን ማጠንከር ነው፡፡ ጥፋቶች መስተካከል እንዳለባቸው መሞገትም ቀበቶን ማጥበቅ ነው፡፡ በእኩዮች ፊት ዓይን መግለጥና የተደፈነ ጆሮን እንዲሰማ ማድረግ ጠንክሮ መቆም ነው፡፡ ለማንም ቢሆን አግባብነት ከሌለው አሻፈረኝ ማለት መቻል ብርታት ነው፡፡ ለገዢ ባለስልጣናት ስህተታቸውን ማሳወቅ ጥንካሬ ነው፡፡ ዶ/ር ኪንግ እንዳሉት ‹‹የፍፁምነት ሕግ አለያም ምሉዕ ሕግ ከሰው ሰራሽ ደንብ ጋር የሚጣጣም የሞራል ሕግ ወይም የፈጣሪ ሕግ ነው፡፡ ሕጋዊነት ያጣ ሕግ ደሞ ከሞራላዊ ሕግ ጋር የማይጣጣም ነው::››  በጃንዋሪ 2011 ሳምንታዊ የሆነ ጦማር ‹‹ከአፍሪካ ጨቋኝና ግፈኛ ገዢዎች ውድቀት በኋላ›› አቅርቤ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አንስቼ ነበር፡፡‹‹በአሸዋ የተገነባው የፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ግንብ ሲደረመስና የቅዠት ቤተ መንግስታቸው ፍርስረሱ ሲወጣ አፍሪካ ምን ትሆናለች? አፍሪካ መላቅጡ የጠፋ ትሆንና መልሶ ለመገንባት የምታስቸግር ፍርስራሽ ትሆናለች? የፈላጭ ቆራጮቹስ መጨረሻስ ምን ይሆናል?

ባለፈው በጋ ወራት ያለፈው የጨቋኞች ስርአት ገንቢው መለስ ዜናዊ ካለፈ በኋላ በኢትዮጵያ ያለው የጭቃ ግንብ መስፋፋትን እያስመሰከረ ነው:: የታሪክ ሚስጥራዊነት ግን አሁን ያለው ጥያቄ እኩይ ገዢዎች ላለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት ሊያደርጓት እንደሞከሩትና ኢትዮጵያ ትፈራርሳለች ወይስ ትጠነክራለች የሚለው አይደለም፡፡ እነዚያ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ቀና ማሰብ የሚጎመዝዛቸው የእርኩስ መናፍስት ስሪቶች ከሚያመልኩትና አንቀጥቅጦ ሲያምሳቸው ከነበረው የቅዠት ሳጥን ሞት በኋላ እርስ በርሳቸው ወደ ፍርስራሽነት በመንደርደር ላይ

ናቸው፡፡ ባለሕልም እንጀራቸው ሲሞት የነሱም እንጀራቸው እያረረና እየሻገተ ነው፡፡ አባባሉ እንደሚያስረዳው‹‹በዕውራን አምባ አንድ አይና ብርቅ ነው›› አሁን እንግዲህ አይነ ብርሃናቸው የለም ከዚሁ ጋርም በራሳቸው ጥፋት፤ ተንኮል፤ ድክመትና መሰሪነት የሚይዙት የሚጨብጡት ጠፍቷቸው በመደነባበር ላይ ናቸው፡፡

አሁን ‹‹አጣዳፊው ጉዳይ›› ኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚ መሪዎች ለዴሞክራሲ ያላቸውን እቅዳቸውንና ራዕያቸውን በአስቸኳይ ማዘጋጀት ነው፡፡ኢትዮጵያዊያን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በሕግ የበላይነት የሚመራ ሕብረተሰብ ለመፍጠር ራዕያቸውን ማቀድ ያለባቸው አሁን ነው፡፡ኢትዮጵያዊያን የተቃዋሚ መሪዎችም የመገናኛ መረቦቻቸውን በጥንቃቄና በእርጋታ በመዘርጋት ከየአቅጣጫው ያለውን የሕብረተሰብ ክፍል በማሰባሰብና በመረቡ ግለሰቦችንም ሆነ ማሕበረሰቡን፤ በአንድ የማሰለፉ ወቅት አሁን ነው፡፡ ከጭቆና አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት የሚደረገውን ሽግግር ምሁራን ማመቻቸት ያለባቸው አሁን ነው፡፡ ሁሉም ነጻነትና ዴሞክራሲን የሕግ የበላይነትን የሚፈልግ ሁሉ አሁን ነው በአንድ ላይ ለመቆም ስምምነታቸውን ይፋ በማድረግ መንቀሳቀስ ያለባቸው፡፡ ካለፈው የግፍ ሰንሰለት ማነቆ እራሳችንን ማለቀቂያው ጊዜ አሁን ነው፡፡ ለሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ስንል የተጫነብንን የዘርና የጎሳ ፖለቲካ አሽቀንጥረን መጣያው ወቅት አሁን ነው፡፡ ለብሔራዊ አንድነት መቆሚያና መሰባሰቢያችን አሁን ነው፡፡ ለሃቅና ለይቅር ባይነት መወሰኛችን አሁን ነው፡፡ እራሳችንን ከጭቆና እኩይ ምግባርተኞች አላቀን፤ሰብአዊ ክብራችንን የምናረጋግጥበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ አሁን እርስ በርስ የመወነጃጀያና የመለያያ የጣት መቀሰርያ የእልህ መወጫና የእርስ በርስ መናቆሪያ ወቅት አይደለም፡፡ አሁን እስቲ ይሁና በማለት አፋችንን የምንለጉምበት ጊዜ አይደለም፡፡ አሁን አይናችን እያየ አላይም የሚልበት ጊዜ አይደለም:: ጆሯችን አሁን አይደለም አልሰማም ማለት ያለበት ሊከፈት ሊያዳምጥ ሊሰማ የግድ ወቅቱ ነውና፡፡

ከዚህስ በኋላ ጉዟችን ወዴት ነው? ከዚህ በኋላ የራሴን ጥያቄ እኔ አጠር አጠር እያደረግሁ ለመመለስ እሞክራለሁ፡፡ ተቃዋሚው ሃይል ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለመምራት በጎዳናው ላይ መሆን አለበት፡፡ በቅድመ ዴሞክራሲ ጭቆና የነበረችውን ኢትዮጵያን ለመገንባት

ተቃዋሚው ሃይል የዴሞክራሲ ድርጊት እቅዱን በአግባቡ መንደፍ አለበት፡፡ ዋነኛው ካለፉት ሰባት ዓመታት ልንማርና መስወገድ ያለብን ለመቃወም በሚል ብቻ ዝም ብሎ መቃወም መቃወም መቃወም ያለግብና ዓላማ ሊሆን አይችልም፡፡ የተቃዋሚዎች ሚና በስልጣናቸው የሚባልጉትን መቃወም ከሚለው ባለፈ ሊሆን ይገባል፡፡ የተቃዋሚዎች ድርሻ በሃገሪቱ ላይ በሚመሰረተው ዴሞክራሲያዊ ስርአት እቅድና ራዕይ ላይ መሆን ይኖርበታል፡፡ የጨቋኞች የተጠያቂነትን ጉዳይ ሰምተው እንዳልሰሙ ሊያስመስሉ ይጥራሉ::  ያ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ዋናው ነገር ተጠያቂነትን መቼ አምነውይቀበላሉ ነው፡፡ ለተቃዋሚዎች ጨቋኞች ያደረሱትን ግፍና በደል መቁጠርና በዚያ ላይ ማላዘኑ በቂ አይደለም፡፡ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በአግባቡ በጥንቃቄ ታስበበትና ተመክሮበት ሊወጣ የግድ ነው፡፡

እንደ መግቢያ ተቃዋሚው ስለተጠያቂነትና ግልጽነት ጥርት ያለ አቋሙን ለሕዝቡ በማያዳግምና በማያወላዉል መልኩ ማስቀመጥ አለበት፡፡ለምሳሌ ስር ሰዶ ኢትዮጵያንና ሕዘቦቿን እየቦረቦረ በማጥፋት ላይ ያለውን የጨቋኞች ስሪት የሆነውን ሙስና ለማጥፋት ተቃዋሚዎች ምን ለማድረግ ነው ያቀዱት፡፡ የዓለም ባንክ በጥንቃቄ የተዳሰሰ 448 ገጽ ያለው ዘገባ ኢትዮጵያ በዓለም አሉ ከሚባሉት በሙስና የዘቀጡ ሃገሮች አንዷ እንደሆነች አስነብቧል፡፡ ከተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዎችም አለያም ከአባሎቻቸው ይህን ዘገባ ምን ያህሉ እንዳነበቡት አለያም በሙስናና በብክነት ላይ የራሳቸውን ዳሰሳ እንዳደረጉ መናገር ባልችልም፤ ይህን ዘገባ ያነበበ ማንም ቢሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ስር የሰደደ የሙስና ነቀርሳ ጥርጣሬ ሊኖረው አይችልም፡፡

ለሥልጣን ለሚበቃው እውነትን ማሳወቅ 

ይህ የጻፍኩት አንዳንዶቹን ሊያበሳጫቸው ሌሎቹን ደሞ ሊያንድዳቸው ይችላል፡፡ ብዙዎችን ደግሞ የሚያበረታታቸውና ጠንካራና ደፋር እርምጃ ነው እንደሚሉ እርግጠኛ ነኝ፡፡ አንዳንድ አቃቂር አውጪዎች እኔ በምቾት ፈረሴ ላይ ተኮፍሼ ‹‹ተቃዋሚውን እንደተሳደብኩ አድርገው በመውሰድ ምላሳቸውን ሊሰብቁ ይቃጣታቸው ይችላል፡፡ ተቃዋሚውን እያዳከምኩና ዝቅ አድርጌ እየተመለከትክ ነው ሊሉኝ ይችላሉ፡፡ሌሎችም የተቃዋሚውን ሚና አጋነንክ ሊሉ ይችላሉ፡፡ ከዚህ ባለፈም ለ‹‹ተቃዋሚዎች›› ባደረጉት መስዋእትነትና እኔ ከማደርገው በበለጠ ለሰብአዊ መብት መሟገታቸውን በማሳነስ የሚገባቸውን ከበሬታ አልሰጠሃቸውም ነፍገሃቸዋል ሊሉኝም ይችላሉ፡፡ እኔ የማደርገው ጨቋኝ የሆኑት አምባገነን ገዢዎች ከሚያደርጉት ጋር ተመሳሳይ ነው ሊሉም ይዳዳቸዋል፡፡ እኔ በተመቻቸ የምሁር ወንበሬ ላይ ተቀምጬ ያለሁ የተቃዋሚዎች ተግባርና አካሄድ ሊገባህ አይችልም ብለው ሊወቅሱኝ ይችላሉ፡፡ የሆነውይሁን!

ምንም እንኳን እነዚህ አባባሎች አቅጣጫ ማስለወጫ ቢሆኑም ሁላችንም ‹‹በተቃዋሚ›› ጎራ ነን የምንል ሁሉ ልንመልሳቸው የሚያስፈልጉን ሁለት ጥያቄዎች አሉ፡፡ ጨቋኞችና አምባገነን እኩዮች በጨቋኞች ጎዳና ላይ እንደግመልሽንት የኋሊት እየተዘወሩ ነው እኛስ በዴሞክራሲ አውራ ጎዳና ላይ ወደፊት አየገሰገስን ነው? የተቃዋሚው ጎራ ከ2005ቱ ከነበረበት ሁኔታ ዛሬ በተሸለ ደራጃ ላይ ነው?

*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):

http://open.salon.com/blog/almariam/2013/02/10/ethiopia_where_do_we_go_or_not_go_from_here

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::) ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

 

የኢትዮጵያ አምባገነኖች ጉም ይጨብጣሉ አውሎ ነፋስን ይዎርሳሉ!

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

የአፍሪካ አምባገነኖች የዉሃ ላይ ቤተመንግስተና የዉሃ ገደብ: ለዘላለም  ለስማቸው መጠሪያ ይሆናል ብለው ሲገነቡና ሲያስገነቡ ኖረዋል:: ትተው ያለፉት በሕያውነት ጀግነውና ሲወደሱ መኖርን ነበር፡፡ ውጤቱ ግን ጉምን መጨበጥ ነፋስን መውረስ ሆኗል፡፡

የጋናው  ክዋሚ ንክሩማ በ1957 ዓም የመጀመሪያዋን የጥቁር  አፍሪካ ሃገር ከቅኝ ገዢዎች በማላቀቅ፤ወደ ነጻነት መራት፡፡ በመንግስት በሚመራ ንኩርማኒዝም በተባለ ፀንሰ ሃሳብ  ኢንዱስትሪ በማዳበር ዘመናዊ ሶሻሊስት ሃገር ለመገንባት አሰበ፡፡ በቮልታ ወንዝም ላይ አኮሶምቦ ግድብን ገነባ:: ያም በወቅቱ ‹‹ታላቁ የጋና የኤኮኖሚ ግንባታ›› ተብሎ ተወደሰ፡፡ የግልን ዝናም በማሰራጨት በሃገሩ ‹‹መሲህ››፤ ‹‹የጋናና የፓን አፍሪካኒዝም አባት›› “የአፍሪካ ብሔርተኝነት አባት›› አያስባለ አራሱን ሰየመ ፡፡ ነጻ ማሕበራትንና የተቃዋሚዎችን ጎራ አፈራረሰ፤ ዳኞችን ለወህኒ ዳረገ፤ የአንድ ሰው አንድ ፓርቲ ስርአትን በመፍጠር እራሱን ‹‹የዕድሜ ልክ ፕሬዜዳንት›› አደረገ፡፡ በ1966 የወታደራዊውን ሃይል እርግጫ ቀመሰ፡፡ እስካሁን ድረስም በሥራ ላይ ያለውን የአፍሪካን አምባገነኖች መመርያ የሆነውን የአንድ ሰው አንድ ፓርቲ ስርአት አዋቅሮላቸው አለፈ፡፡ በዚህም ንከሩማ ባዶ አየር ወርሶ፤ ጉም ዘግኖ በግዞት ዓለም ሞተ፡፡

የግብፅ ጋማል አብድል ናስርም ራሱ ያተረፈው የአረብ ሶሻሊዝምና ብሔርተኝነትን የተቀደሰ “የፓን አረብ” (መላው አረብ) ፍልስፍና በማለት እያስተጋባ አስተዋወቀ፡፡ በርካታ የደህንነት መረቦችና  የፕሮፓጋንዳ ጦር አሰማርቶ እራሱን የ‹‹ሕዝብ ሰው›› በሚል እራሰ አምልኮ ገንባ፡፡ በሶቭየቶች እርዳታም የአሰዋንን ግድብ ገደበ፡፡ በሃገሪቱ ላይ የአንድ ሰው አንድ ፖርቲ ስርአትን ለማቅቆቃም የስለላ መረቡን ዘርግቶ፤ ከሱ ፓርቲ ጋር ስምምነት የሌላቸውን በተለይም የሙስሊም ብራዘር ሁድ አባላትን አጠፋ፡፡ አሁን ባለንበት ዘመንም እንደምናየው የሙስሊም ብራዘርሁድ (የስላም ወንደማማቾች ፓርቲ)  በሥላጥኑ ወንበር ላይ ሲፈናጠጥ “ናሲሪዝም” የቆሻሻ መጣያ  ዉስጥ ወድቁአል፡፡ ናስር ለግብጽ ወታደራዊ አምባገነንትን ትቶ ሲያልፍ፤እራሱም ባዶ አየር ወርሶ፤ ጉም ዘግኖ አልፏል፡፡

ሞአመር ጋዳፊ ‹‹የሊቢያ ሶሻሊስት አረብ ጃምሂሪያ››ን በማወጅ፤የብዙሃን መንግሥት ዘመን (ጃምሂሪያ) ደረሰ አለ፡፡ የሊቢያን ሕብረተሰብ  ‹‹ሕዝባዊ ኮሚቴ›› በሚባል ስብስብ አቀናጅቶ ለጭቆናው አደራጀ፡፡ ከመሰረተው እርባና ቢስ አደረጃጀት ጋር ያልተስማሙትን ሁሉ በግፍ ጭቆና ውስጥ ከትቶ፤ የሃገሪቱን ብሔራዊ ሃብት እንዳሻው አዘዘበት በከንቱ አባከነው፡፡ ታላቁን ሰውሰራሽ ወንዝ በመቀየስ፤በዓለም ታላቁ የመስኖ ፕሮጄክት ‹‹የዓለም ስምንተኛው አስደናቂ ነገር›› በማለት ሰየመው፡፡ ከኣራት አሰርት ዓመታት አገዛዝ በኋላ ‹‹ወንድም መሪው››  ‹‹የአረንጓዴው መጽሃፍ ደራሲ›› ለፉካ አይጥ ሞት ተዳርጎ አለፈ፡፡ የመከፋፈልና የጥፋት ውርስ ትቶ ሲያልፍ፤ለራሱ ግን ባዶ አየር ወርሶ፤ ጉም ዘገነ፡፡

ኢዲ አሚን ዳዳ ከሁሉም አፍሪካውያን ግፈኛ ገዢዎች የከፋው ‹‹የኡጋንዳው ሰው በላ››  በኡኡጋንዳ ሕዝብ ላይ የሽብር ዘመን በመጫን፤ በጭካኔያዊ ስሜት ለዓለም መገናኛ ብዙሃን አምባገነናዊ ስልጣኑን በይፋ አሳየ፡፡ ጉራ በተመላበት ድንፋታም እራሱን ‹‹የተከበሩ የዘልዓለም ፕሬዜዳንት፤ ፊልድ ማርሻል፤አል ሃጂ ዶክተር  ኢዲ አሚን ዳዳ  VC, DSO, MC,  የምድር አራዊትና የባህር አሳዎች ጌታ ፤ በአጠቃላይ የአፍሪካ የብሪቲሽ (አንግሊዝ )ግዛት ድል አድራጊ፤ በተለይም የኡጋንዳ ነኝ አለ::‹‹ ግድብ አልገነባም ግን የኡጋንዳን ሕዝብ ለ8 ዓመታት ለኩነኔ በመዳረግ በመጨረሻው ተባሮ ለስደት ተዳርጓል፡፡ የሞት ውርስ ካወረሰ በኋላ ለራሱ ግን፤ ባዶ አየር ወርሶ፤ ጉም ዘገነ፡፡

ያ ‹‹ታላቁ መሪ››?

እንደማንኛቸውም የአፍሪካ ግፈኛ ገዢዎች በቅርቡ ያለፈው መለስ ዜናዊም፤ እራሱን ከሕይወት ባሻገር አድርጎ በማግዘፍ አስቀምጦ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ መዳኛ  (መድሃኔ ዓለም) ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ጭምር ነኝ እያለ ያስፎከር ነበር፡፡ እራሱን ‹‹ሕልመኛ መሪ፤ የአፍሪካ መኩሪያ አፈ ጉባኤ፤ እና የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ከፍተኛው ተግባሪ›› አድርጎ አስቀምጦም ነበር፡፡ ባለፈው  በጋ ወቅት ህልፈቱን ተከትሎ መነዛት የጀመረው ቅጥፈተ ፕሮፓጋንዳ፤ ጥንታዊነትን፤ ውዳሴን፤ አይረሳነትን፤ ተመላኪነት፤ የዘበት ተውኔት (የቀልድ ትያትር) ሆኖ አየታየ ነው፡፡ በመለስ ዜናዊ ፍቃድና ምርጫ የተሰየመው፤ የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ፤ ታማኞች በተሰገሰጉበት ፓርላማ ባደረገው ንግግር መለስን ከክርስቶስ በታች ብቸኛ በማድረግ ምርቃቱንና የራሱንም ታማኝነት መግለጫ መካቢያ ንግግሩን ሲያደርግ: ‹‹ዘልዓለማዊ ክብር ለታላቁ መሪያችን›› በማለት ነበር፡፡ ዋነኛው ታላቁ መሪ የሚባለው የሰሜን ኮርያው ኪም ኢልሱንግ እንኳ፤ ‹‹የሕዝብ ልጅ›› ከመባል ያለፈ ከበሬታ አልተቸረውም ነበር፡፡ ሃይለማርያም የተጣለበትን የፍጥምጥሞሽ መለኮታዊ ውክልና ተልእኮ እንደሃይማኖት ሰባኪ ለመወጣት ከፍተኛ ጉጉት እንዳለው በንግግሩ ቃለ መሃላ ሰጥቷል፡፡ ‹‹ አሁን ያለብኝ ሃላፊነት፤ ……. የማይረሳውን ታላቁን መሪያችንን ዓላማ፤ ምኞት፤ በተሳካ ሁኔታ መፈጸም ነው፡፡……….የታላቁ መሪያችን የእግር ኮቴ በመከተል፤ በአህጉር፤በዓለም አቀፍ ደረጃ ያን ተደማጭነት ያለውን ድምጽ ቀጣይ ማድረግ ነው፡፡ ታላቁ መሪያችን ተደናቂ የሃሳብ አፍላቂያችን ሞተር ብቻ ሳይሆን  እራሱን በመሰዋት አርአያነትን ያስተማረም መሪ ነበር…….››

ታዲያ ሃይለማርያም ደሳለኝ ይሀን ሲናገር የተናገረው ስለመለስ ነበር ወይስ ስለ ገሊላው ሰው?

‹‹የሕልመኛው ታላቅ መሪ›› ሕልምና ውርስ

ከሱ በፊት እንደነበሩት የአፍሪካ አምባገነን ጨቋኝ ገዢዎች መለስም ቅዠት ነበረው፡፡ ከንቱ ስሜት፤ምስጠትም ነበረው፡፡ ታላቅ ሕልም ግን አልነበረውም:: የነበረው፤እራስን የማግዘፍ ራዕይ ነበር፡፡ ከሱ ቀደም ብሎ እንደነበረው ሞቡቱ ሴ ሴ ሴኮ በአፍሪካ ትልቁን ግድብ የመገንባት ሕልም ነበረው፡፡ ታላቁ የተሃድሶ ግድብ የሚባለው፤በአባይ ላይ በቀዳሚ ባጀት ሂሳብ (ላልተጠበቁ አጋጣሚዎች በጀት ሳይቀመጥለት) በ 5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የመገንባት (ላም አለኝ  በሰማይ) ሕልም ነበረው፡፡ ባለሙያዎች እንዳስቀመጡት፤ይህን መሰሉ ግድብ ከተገነባ፤ ‹‹በሰሜናዊ ምአራብ ኢትዮጵያ ላይ ያለውን  1680 ካሬ ኪሎሜትር ደን፤ በሱዳን ድንበር የሚገኘውን ቦታ ከአባይ ሁለት ጊዜ በሚበልጥ መጠን ሰው ሰራሽ ሀይቅ ይፈጥራል፡፡ ከዚህ ባሸገርም ‹‹ግድቡ፤ወደ ግብጽ የሚፈሰውን የውሃ መጠን በግድቡ ሙሌት ጊዜ በ25 በመቶ በመቀነስ የአስዋን ግድብን የውሃ ማከማቸት አቅም ያዳክመዋል፡፡ ሱዳኑ መሪ ኦማር አል በሺር ለግብጽ የዓየር ማረፊያ ጣቢያ በሃገራቸው ደቡብ ግዛት ለመገንባት  ተስማምተዋል፡፡የግድቡ ሁኔታ በዲፕሎማቲክ ንግግሩ ደረጃ የማይፈታ ሆኖ ከተገኘ ግድቡን ባየር ጦር ሃይል ላማጥቃት የሚያስችል ጣቢያ ይሆናል::››  የመለስ ችሮታ ከጎረቤት አገር ሁከትና ጦርነት?

መለስ የዕድገት ትራንስፎረሜሽን እቅድ አልነበረውም:: ይልቅስ ከንቱና ስሜታዊ የሆነ የማይጨበጥ የኤኮኖሚ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ቅዠት ነበረው፡፡ ቀደም ሲል፤ ‹‹የመለስ ዜናዊ የጥንቆላ ኤኮኖሚ›› በሚል ጦማሬ ላይ እንዳስገነዘብኩት፡ መለስ በኢትዮጵያ ስላለው የኤኮኖሚ እድገት ሆን ብሎ በተጋነነ መልኩ በተፈጠረና፤ በታገመ እምነት ያወራ ነበር፡፡ በሃገሪቱ ያለውን የኑሮ ውድነት ለማጥፋትና በመካከለኛ ኤኮኖሚ ውስጥ ያሉትን ሃገራት በመቅደም ሕዝቡም ኑሮውን በማሻሻል ደረጃ ሃገሪቱ ከችግር ለመላቀቅ ክፍተኛ ጉዞ ላይ ነች በማለት ያውጅ ነበር፡፡ (የመለስ ሙት ዓመት ገና ሳይከበር የመለስ ስሪት የሆነው አዲሱ ሰም ብቻ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም እድገቱን ወደ ታች አዘቅዝቆ መግለጫ መስጠት ጀምሯል:: አይገርምም!) የአሜሪካን መንግስት አማካይ የዋጋ ግሽበትን አስመልክቶ 36 በመቶ ሆነ ሲል፤ መለስ በ2009/10 በጥንቆላው የኤኮኖሚ ስሌቱ 3.9 በመቶ ብቻ ነው ብሏል፡፡ የዕድገትና ትራንስፎረሜሽን እቅዱ (እኔ ዜናዊኖሚክስ የምለው) በ ጁን 2011 አስተያቴ እንደገለጽኩት ‹‹የመለስ ዜናዊ ቅጥፈኮኖሚክስ›› የይሁንልኝ ምኞት ዝባዝንኬ ነው፡፡  ‹‹በረጂም ወቅት ማይጨበጥ ተስፋ ላይ የተገነባ ኢትዮጵያን የዴሞክራሲ፤ የመልካም አስተዳደር፤ የህግ የበላይነት የተከበረባት ሃገር የማድረግ የማስመሰያና የማወናበጅያ ሃሳብ ነው፡፡ የመለስ የኤኮኖሚ ተረት: ‹‹ዘመናዊና ውጤታማ ኤኮኖሚ በመገንባት የእርሻውን የኤኮኖሚ ዘርፍ፤በአዲስ ቴክኖሎጂ በማገዝ ልማቱን አፋጥኖ የሕዝቡን የኑሮ ደራጃ ከፍተኛ ቦታ ላይ ለማድረስ የሚል የማይጨበጥ ሕልም››  ‹‹የእርሻውን ክፍለ ኤኮኖሚ መሰረት ያደረገ›› የኢንዱስትሪውን ክፍል ለማጎልበት አመቺ ሁኔታ በመፍጠር፤በኢኮኖሚው ላይ ወሳኝ ሚና እንዲኖረው ማድረግ: የአቅም ግንባታን በማሳደግ፤ ወጣቱን፤ ሴቶችን፤ በማሳተፍና ተጠቃሚ በማድረግ መልካም አስተዳደርን መገንባት ነው፡፡ የትራንስፎርሜሽን እቅዱ ‹‹ማስመሰያ ኤኮኖሚክስ›› (sham-o-nomics) ብቻ ነው፡፡  የመለስ ችሮታው የዋጋ ግሽበት፤የኤኮኖሚ ብልሹ አስተዳደር፤የውጭ እዳን መከመርና አካባባዊ ጥፋት?

መለስ ብሔራዊ ራዕይ ጨርሶ አልነበረውም፡፡ ሕልሙና ቅዠቱ የጎሳ መከፋፈልና ማበጣበጥ ነበር፡፡‹‹የብሔር ፌዴራሊዝም›› በሚል የመርዝ መጠቅለያ የተዋጠው ሃሳቡ የሞተውን የአፓርታይድ ስርአት አለሳልሶ በኢትዮጵያ ትንሳኤውን ለማምጣት የታቀደ ቅዠቱ ነበር፡፡ ላለፉት ዓመታት የመለስ ጭንቀትና ጥበት፤ እንቅልፍ አልባው ጥረቱ ወጥ የሆነውን የኢትዮጵያን የአንድነት አቋም አፈራርሶ፤በብሔር፤ዘር፤ ጎሳ የመከፋፈያ ቅርጽ መሰረት ለማደራጀት ነበር፡፡ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 46 (2) ላይ ‹‹ክልሎች የሚገነቡት እንደአቀማመጣቸው ሁኔታ በቋንቋቸው፤ በማንነታቸው፤ በተመሳሳይነታቸው፤ እና በሕዝቡ ፈቃደኛነት ላይ በመመስረት›› ይላል፡፡ ማለትም ‹‹ክልሎች›› (በውስጡ የሚኖሩት ሕዝቦች) ልክ በደቡብ አፍሪካ በአፓርታይድ ዘመን እንደነበረው ስርአት በባንቱስታን ላይ ያደርግ እንነበረው፤ ከከብት ባልተለየ ሁኔታ በአይነታቸው ለይቶ በጋጣ ውስጥ እንደማጎር ያለ ስርአት መፍጠር ነው፡፡ እነዚህ የጎሳዎች መኖርያዎች በአፓርታይድ አጠራር ባንቱስታን ወይም በኢትዮጵያ ደግሞ ክልል  (ክልእስታን) ይባላሉ፡፡ በአጠቃላይ የመለስ ምኞት አንድ የነበረውን ሕዝብ በዘር፤ በብሔር፤ በጎሳ፤ በቋንቋ በማለይየት በባብሎንያውያን በቋንቋ ባለመግባባት እንደፈራረሱት አይነት ለመበታተንና ሰላምና አንድነት በማጥፋት እርስ በእርስ በማቆራቆስ ኢትዮጵያ የምትባለውን መሰረቷ የጸናውን ሃገር እንዳልነበረች ለማድረግና ታሪኳን ሕዝቧን የመከራ ገፊት ቀማሾች አድርጎ ማጠፋፋት ነበር፡፡ የመለስ ችሮታ በፖለቲካ፤በተጻራሪ ቡድን፤በጭካኔና  በወገንተኝነት በመበታተን የሁከት አምባ መፍጠር?

በመለስ ሥር ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ምጽዋትና ችሮታ ጠባቂ የለማኝ ለማኝ ሃገር ሆነች፡፡ በሁለቱ አሰርት ዓመታት ኢትዮጵያዊያኖች ቁጥር አንድ የዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ እርደታ፤ የልማት እርዳታ፤ የወታደራዊ እርዳታ፤ ኤድስ መከላከያ እርዳታ፤በዓለም ቀዳሚ ተመጽዋች ሆነች፡፡ ‹‹ የኢትዮጵያ ቦንድአይድ›› በሚለው ጦማሬ ላይ እንዳስቀመጥኩት: መለስ በተሳካለት መልኩ የዓለም አቀፉን ችሮታና ምጽዋት፤ብድር በተለይም የአሜሪካንን መንግስት እርዳታ፤የራሱን የጭቆናና  የግፍ አገዛዝ መረብ ለማጠናከሪያነት በተሳካ ስልት አውሎታል፡፡ የዓለም አቀፍ እርዳታ ሱሰኝነት እና የልመና ባህል የመለስ ችሮታ?

በመለስ ዜናዊ አገዛዝ ዘመን ሙስና ኢትዮጵያን በሞት አፋፍ ላይ ጥሏታል፡፡ በቅርቡ የዓለም ባንክ 448 ገጽ ያለው የኢትዮጵያን የሙስና ሁኔታ  መመርመር (“የኢትዮጵያን የሙሴና ህመም  ምርመራ”) በሚል ርእስ ዘገባ አውጥቷል፡፡ የዓለም ባንክ አንደሚለው: ሙስና የኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልገሎት ቦርቡሮ በልቶታል:: “በቅርቡ በሰፊው ከተደረገው የቴሌኮሙኒኬሽን ማጠናከሪያ ወጪ ፍሰት አኳያ ሲታይም በአፍሪካ በጣም ዝቀተኛ የቴሌፎን አገልግሎት ፍሰት ያለባት ሀገር ነች፡፡ አንድ ወቅት ላይ ዘመነኛውን የፋይበር ኦብቲክ ገመዶች በማስገባቱ ረገድ ቀደምት ለመሆን በቅታ የነበረች ቢሆንም በአነስተኛና ደካማ ባንድ ዊድዝ፤ አስተማማኝነት ማጣት ችግር ውስጥ ኢትዮጵያ ተዘፍቃለች፡፡ ተጠያቂነት የሌለበት ሁኔታ በመደርጀቱና መንግስትም ጥቅሙን እንጂ ግልጋሎቱ ላይ እጅግም አይኑን ስለጋረደ፤ በሃገርም ውስጥ ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሙስና የተዘፈቀ ድርጅት ሆኗል፡፡”

በግንባታውም (ኮንስትረክሽን) ዘርፍ፤ ያለው ሙስና ‹‹ኢትዮጵያ በሙስና ችግር፤ ደረጃው ዝቅ ባለ ግንባታ፤የተጋነነ የግንባታ ዋጋ ተመን፤ ተግባራዊ ማድረጊያው ዘመን የተጓተተ›› ነው ብሏል ያለም ባንክ፡፡

በፍርድ ስርአቱም ዘርፍ ሙስና “(ሀ) በፍርዱ ሂደትና በተጓዳኝ ዘርፎቹ የፖለቲካው ጣልቃ ገብነት (ለ) ውሳኔዎችን ለማስገልበጥ የጉቦ መቀባበል አጠያየቁ መናር›› ከሁለቱ በአንደኛው ሳቢያ ይመራል፡፡ በማንኛውም ዘረፍ ቢሆን ስለ እድገት፤ ስለልማት፤ ስለ ጤና ስለትምህርት ለፖለቲካ መጠቀሚያ ሲባል ይታወጃል ይለፈፋል እንጂ ማናኛቸውም ተግባር ለሃገርና ለሕዝብ ሊያገኝ ከሚችለው ጠቀሜታ ይልቅ ለስልጣን፤ ለግል መጠቀሚያነት፤ አገልጋዮች ለመግዣ እንዲሆን ተብሎ የሚተገበር ብቻ ነው፡፡  መቋጫ የሌለው የመለስ የሙስና በሽታ ችሮታና ልግስና ?

የመለስ ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ከመፈክርነትና ከቃላት ማጭበርበሪያነት ያለፈ አይደለም፡፡ ምንግዜም የአብዮተኛነት ዛሩ ሲነሳበት የሚያውጠነጥነውና የሚደሰኩረው ብቻ ነው፡፡ በቦርዶ ፈረንሳይ ነዋሪ የሆነው ምሁር ጃን-ኒኮላስ ባህ ሲጥፍ: ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ አብዮታዊም ያልሆነ አለያም ዴሞክራሲያዊም ለመሆን የማይችል የሌኒኒስት፤ የማርክሲስት፤ ማኦኢስት፤ እና የሊብራሊዝም ቅንጭብጫቢ በመለስ ዙርያ በሚገኙ የፓርቲ ፖለቲካ ዘይቤኞች እና በጥቂት ኤጀንሲዎች የተፈጠረ ‹‹ዝባዝንኬና ትርኪምርኪ›› ብሎታል፡፡ አብዮታዊ ዴሞክራሲ እንደ የፖለቲካ ዘይቤ አገልጋይነቱ በኢህአዴግ በሚመራው የአገዛዝ ስርአት ውስጥ የሚከናወነውን ሕገ ወጥነት፤ ስርአት አልበኝነት፤የኤኮኖሚ ሃይlን ማጠናከሪያነትን ሕጋዊ ለማድረጊያነት መገልገያ ብቻ ነው፡፡ የተለያዩ ፓርቲዎች ልሳኖችና በራሪ ወረቀቶች አብዮታዊ ዴሞክራሲን የሊበራሊዝም  አሻሚ ሕግ በመሆኑ የውስጥንም የውጭንም ተቃዋሚዎች ከጨዋታው ውጪ ለማድረጊያ በመሳሪያነት የሚያገለግል ነው፡፡” በአንድ ወቅት  አንድ አስተያየት ሰጪ አብዮታዊ ዴሞክራሲን ከኮሚኒዝምና ፋሺዝም ጋር የተቆራኝ ብሎታል::

አብዮታዊ ዴሞክራሲ በ2010 በተካሄደው ምርጫ ወቅት 99.6 በመቶ ድል ለመለስ ለማስረከብ ያገለገለ ነው፡፡ ለተጭበረበረና፤ ለተሰረቀ ሕገወጥ ምርጫና መጥፎ አስተዳደር የመለስ  ልግስና?

መለሲዝሞ (መለሳዊነት) ፡ የመለስ ታላቁ ውርስ

የመለስ ዋናው ውርስ ቅርስ መለሳዊነት ብቻ ነው፡፡ ጥሬው የጉልበት ትምክህተኝነት በሚለው በዲሴምበር 2009 ባቀረብኩት ጽሁፌ ላይ እንዳስቀመጥኩት ነው፡፡ መለስ መለሳዊነትን በሚገባ ተክኖታል አስልቶ ተግብሮታል፡፡ የሱም የፖለቲካ ቅያሱና አካሄዱ፤ ‹‹የኔ መንገድ፤ የአውራ ጎዳና፤ መንገድ አልባ……አለያም ወህኒ!” ነው::

መለስ የሚያረጋግጠው ጀብደኝነት ትክክለኛ ያደርጋል የሚለውን አካሄዱን ነው፡፡ ልክ የገሊላው ሰው ደቀ መዝሙሮች እንደሚሉት ሁሉ የመለስም ተከታይ አገልጋዮች አምላኪዎቹ፤ በመለስ የእግር ኮቴ  ላይ እንደሚረማመዱና ያን ብቻ እንደሚከተሉ ይደሰኩራሉ፡፡  የመለስን መለኮታዊ ሃይል ጉልበታቸውን ለማጠናከር ያልማሉ ይሰግዳሉ፡፡ ከነገሥታት መለኮታዊ ሃይል ልግስና ወደ አነስተኛ አምላክነት መለኮታዊ አመራር! ሆኗል የኢትዮጵያ ዕድል (አያሳዝንም!)::

የመለስ አምላኪዎች ማምለኪያ ጣኦት ሙት ማወደሻነት፤ ፈጣሪነት ሊያሳድጉትና ሊያሳልሙን ይዳዳቸዋል፡፡ የሆነው ቢሆን ያሻቸውን ያህል ቢደነባበሩና ቢፍጨረጨሩ መለስን መመለስ አይቻልም፡፡ እንኳን መለስ ታላቁ ኔልሰን ማንዴላም ለእርገትና ሞቶ ለመነሳት ምኞትም ሃሳብም የላቸው፡፡ ማንዴላ ስለራሳቸው ሲናገሩ ‹‹እኔ እናንተ ደጋግሞ ሃጢአተኛዉን  መልአክ ማደረግ ካልፈለጋችሁ በስተቀር እኔ መልአክ አይደለሁም››  ነው ያሉት፡፡ ጻድቃንም ሆኑ  ዲያቢሎሶች ‹‹ዘልአለማዊ ሕይወት›› አይገባቸውም፡፡  መለስም በስተመጨረሻው እንደማንኛውም የአፍሪካ ከንቱ  አምባገነን መቀመጫው የቆሻሻ መጣያ ነው የሚሆነው፡፡   የመለስ ታላቁ ልግስናው ሊሆን ይችል የነበረው፤ ልግስናዬ ብሎ የሚመኘው ነበር፡፡ በ2007 መለስ ሲናገር ‹‹ተስፋዬና ፍላጎቴ፤ የኔ ችሮታ የተስተካከለና የተረጋጋ የልማት አድገት ኢትዮጵያን ከድህነት የሚያላቅቅና ኢትዮጵያውያንን ከተዘፈቁበት የችጋር አረንቋ ማውጣት ብቻ ሳይሆን፤ በሃገሪቱ ላይ አፋጣኝ መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲን በአውን ማስፈን ነው›› ብሎ ነበር፡፡ በመለስ አምላኪዎች አፋጣኝ የዴሞክራሲ ግንባታ ካልተጣለ በስተቀር መለስ ለወደፊቱ በታሪክ የሚታወሰው እንደ መላ ቢስ የአፍሪካ ግፈኛ የለውጥና የእድገት ተቃዋሚ ሰው ብቻ ነው፡፡ ከመለስስ በኋላ መለሳዊያኖች መቆሚያቸው መሰረት ያለው ይሆናል? መለሳውያንስ መለስን ሊተኩት ይችላሉ?

ዛሬ በኢትዮጵያ ያለው የፕሬስ ነጻነት መመልከቻ ተምሳሌት የሆነውና  በመለስ ለወህኒ የተዳረገው ወዳጄ እስክንድር ነጋ የኢህአዴግን ክስረት ሲተነብይ አንደዚህ ብሎ ነበር:: ‹‹ ከሚታየው በስተጀርባ ያለውን ፋቅ ፋቅ አድርገን መመልከት ብንችል ኢህአዴግ እንደሚተረክለትና የማይለወጥ ሃሳብ ያለውና ትልቁ “ዳይናሶርም” (ከድንጋይ ጊዜ በፊት የኖረ አራዊት) አይደለም:: ተዋቅረዋል ከሚባሉት አራቱ አንጃዎች ጋርም ቢሆን የሕወሃት የበላይ ገዢነት ግራ መጋባትና መደነባበር ቅሬታ እንዳቋጠረ ነው፡፡ የአማራ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አስቸጋሪና ስር የሰደደ ጥርጣሬ፤ የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አፍራሽ ባህሪ፤  ያዘለ ስብስብ ነው::››

መለስ ራዕይን ከተልእኮ ጋር ግራ ያጋባ ተልእኮ ነበረው፡፡ ያን ተልእኮውንም ጨርሷል፡፡ ታሪክም ልግስናውን ከሰብአዊ መብት ገፈፋ ጋር፤ የፕሬስ ነጻነትን ከማፈን ጋር፤ የዘር መከፋፈልን፤ የማይድን የሙስና በሽታን፤ ከማሰራጭት ጋር አዛምዶ፤ በደሙ ውስጥ በተሰራጨው የተጠያቂነት ሽሽት፤ግልጽነትን በመፍራቱ ያስታውሳዋል፡፡ ሼክስፒር እንዳለው ‹‹ሰዎች የሚፈጽሙት ጥፋት ተንኮላቸው  ከመቃብር  በላይ ይኖራል: መልካሙስራቸው ከአጥንታቸው ጋር ይቀበራል::››  ጸሃፍት እንደሚያስተምሩትም ‹‹የራሱን ቤት ሰላም የነሳ፤ በምልሰቱ ነፋስን ከመጨበጥ አያልፍም፡ ሞኝ ለልበ ብልሁ አገልጋይ ይሆናል::›› መለስና አምላኪዎቹ የኢትዮጵያን ቤቶች ሁላ በጥብጠዋልና ጉም ይጨብጣሉ አውሎ ነፋስን ይዎርሳሉ!

*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):

http://open.salon.com/blog/almariam/2013/02/03/ethiopia_they_shall_inherit_the_wind

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::) ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

ፕሬዜዳንት ኦባማ በሁለተኛው ዙር ምርጫ ምን ይጠበቅባቸዋል

ከፕሮፌሰር  ዓለማየሁ  ገብረማርያም

ትርጉም  ከነጻነት ለሃገሬ

ፕሬዜዳንት ኦባማ ሁለተኛውን ዙር የፕሬዜዳንትነት ምርጫ በማሸነፋቸው እንኳን ደስ ያለዎት ማለቱ አግባብ ነው፡፡ የአሜሪካንን መራጮች አብላጫ ድምጽ አግኝቶ ለማሸነፍ ብቃት ባለው አካሄድ ለድል በቅተዋል፡፡ ሚት ሮምኒም ለማይናቀው የምርጫ ግብግባቸው ሊመሰገኑ ተገቢ ነው፡፡ በማጠቃለያው የመለያያ ንግግራቸው ላይ ሚት ሩምኒ ግሩም የሆነ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ‹‹በእንደዚህ አይነቱ ወቅት የደጋፊዎቻችንን ስሜታዊ ጫጫታ ማዳመጥ፤የፖለቲካ አካኪ ዘራፍ ባይነትን ለማስተናገድ ጊዜው አይደለም፡፡ መሪዎቻችን የሕዝቡን ፍላጎትና ምኞት ለማሳካት መንቀሳቀስ ሲኖርባቸው እኛ ሕዝቦች ደግሞ ለዚህ ሂደት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር ለማድረግ በቀናነት መነሳሳት ይገባናል” ብለዋል::

ባለፈው ሳምንት በተከናወነው የምርጫ ሂደት ወቅት አንዳንድ ኢትዮጵያዊያን አሜሪካውያን በቁጭትና በምሬት ጣቶቻቸው እየጠቆሙ ሮሮ ምሬታቸውን አሰምተዋል:: ጥርሳቸውን በማቀጫቀጭ ንዴታቸውን አሳይተዋል:: ፤አይናቸው በቁጭት ቀልቷል፡፡ከፊሎቹ በፕሬዜዳንት ኦባማ ተግባር አዝነው ለተቃዋሚዋው አቻቸው ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር፡፡ በአፍሪካና በኢትዮጵያ ስለሰብአዊ መብት ቀደም ሲሉ የተናገሩትን አጓጊና ተስፋ ያዘለ ዲስኩራቸውን ወደ ተግባር ለውጥው አንዳች ለውጥ ባለማምጣታቸው በኢትዮ አሜሪካውያን ዘንድ ክህደት አለያም ድክመት ሆኖ ታይቶባቸዋል፡፡ ከፊሎች ደግሞ ፕሬዜዳንቱ በአፍሪካ ላሉ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ደጋፊና ረዳት በመሆናቸው ተቀይመዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ ፕሬዜዳንቱ ስላጋጠማቸው ሃገራዊ ችግርና ስለነበረባቸው ውጥረት አዝነውላቸዋል፡፡ የአሜሪካንን ዓለም አቀፋዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያስችለውን የአሜሪካንን የውጭ ፖሊሲ ማስተካከልና መቅረጽ ነበረባቸው፡፡ ለአሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የተከሰተው ሽብርተኛነት አሳሳቢ ነበርና ኦባማ ደግሞ ሽብርተኝነትን ለማክሰም ሰብአዊ መብትን ከጸረ ሽብርተኝነት ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ጋር ማቀናጀት ነበረባቸው፡፡

እኔም ፕሬዜዳንቱ በመጠኑም ቢሆን ሰብአዊ መብትን በተመለከተ አጀንዳ ለመቅረጽ ባለመቻላቸው በምር ቅር ተሰኝቼባቸዋለሁ፡፡ ከዚሁ ጋር ደግሞ በአሜሪካ ውስጥ ስለአለው የኤኮኖሚ ችግር፤አንዳንድ አጣዳፊ የሆኑ ሶሻል ፖሊሲዎችን መንደፍ፤ስለነበረባቸው ሁለት ጦርነቶችን በማካሄድና በዓለም ዙርያ የተነሱና የተካረሩ ግጭቶችን ጦዘው ችግር ከማባባሳቸው አስቀድሞ ማስታገስ ስለነበረባቸው ነው በሚል አልፋቸዋለሁ፡፡ በደቡብ ሱዳን ሬፈረንደም ላይ ስለወሰዱት አቋምና ስለተገኘውም ድል አንድ ሌላ አፍሪካዊ ሃገር እንዲፈጠር በመቻላቸው አደንቃቸዋለሁ፡፡

ፕሬዜዳንት ኦባማ ጥቂት የአሜሪካ ወታደሮች ሃይል እንዲዘምትና ያን የደም ጥማት አራራው አናቱ ላይ የወጣበትን ጆሴፍ ኮኒንና የደም ጥማት ጓደኞቹን እንዲይዟቸው ካልተቻለም እንዲገሏቸው ማዘዛቸው ታላቅ ድርጊት ነው፡፡ እንደኔ እምንት በጣም ትልቅ የሚባል ክሌፕቶክራሲ ፕሮጄክት ፕሮጄክት (ወሮበላአገር በዝባዞች) ተግባራዊ ማድረጋቸውም ታላቅ ተግባር ነው፡፡ ‹‹አፍሪካ ሙሳዊነት ብክነት›› (Africorruption, Inc.”,) በሚለው መጣጥፌ ላይ እንዳቀረብኩት፤ዋነኛው የአፍሪካ መሪዎች ተግባራቸው ሙስና ነው ብዬ ነበር፡፡ አብላጫዎቹ የአፍሪካ ገዢዎች ዋነኛ መመርያቸውና ተግባራቸው የራሳቸውን ሃገር ብሔራዊ የገንዘብ ተቋማትና ሪሶረሱን በመበዝበዝና በመስረቅ፤እጅጉን የተወሳሰበ የግድያና የወንጀል ኢንተርፕራይዝ መፍጠር ነው፡፡ እንደ ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ዘገባ በስውርና በሰበብ አስባቡ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የፈረጠጠው የሃገሪቱ ሃብት ከ2000-2009 ባለው ጊዜ  $11.7 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡ በሊቢያ ሕዝብ ላይ ላለፉት 41 ዓመታት ተንሰራፍቶ ፍዳቸውን ሲያበላቸው የነበረውን የሊቢያውን ጋዳፊን ከስር መሰረቱ ነቅሎ ለመጣልና ለሊቢያውያን የእፎይታ ዘመን ለማምጣት በተባበሩት መንግስታት መመርያ ላይ በመንተራስ የተባበሩት መንግስታት የ1973ን ውሳኔ  ሬዞሉውሽን እንዲያልፍ በማድረጋቸውና አብላጫውን የጦሩን ሂደት የኔቶ አባል ሃገራት ሃላፊነት እንዲሆን በማድረጋቸው እጅጉን አደንቃቸዋለሁ፡፡ ከዚህም ባለፈ በጠነከረ አመራር የሚስጥር የነበሩትን የሲ አይ ኤ ወህኒ ቤቶች እንዲዘጉና የነበረውም ስቃይና የመከራ አመራመር እንዲያበቃ አድርገው የጓንታኔሞ ቤዝም ተዘግቶ የፍርድ ሂደቶች ሁሉ አግባብነት ወዳለው የሲቪል ፍርድ ቤቶች እንዲዛወር በማድረጋቸው የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች እንዲከበሩ በወሰዱት እርምጃ አከብራቸዋለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ብሎም በጠቅላላው አፍሪካ አህጉር ስለ ሰብአዊ መብት ብዙ ሊያደርጉ ሲችሉ አላደረጉትም፡፡ ባለፉት ሁለ፤ት ዓመታት ስለአሜሪካ ፖሊሲ ድክመት በርካታ ጦማሮችን ጽፌያለሁ፡፡ በአፍሪካ የአሜሪካ ፖሊሲ ድክመት አሜሪካም ሆነ ሌሎች አውሮፓ ሃገሮች በአፍሪካ ያለውን ዴሞክራሲና ሰብአዊ  መብት ሁኔታ ፍላጎታቸውን እምነታቸው በስልጣን  ለመቆየትና የሃገሪቱንና የሕዝቡን ነንብረትና ሃብት በመበዝበዝ ራሳቸውንና አሽቃባጮቻቸውን ለማቶጀር የሚንደፋደፉትን  የአፍሪካን ፈላጭ ቆረጭ ገዢዎች በመንከባከብ ለውለታ ሰሪነት ሊገዙበት እንደማይገባ አሳስቤያለሁ፡፡

“ሰግታቶርሺፕ (የወሮበላ መንግስት)፡‹‹ በአፍሪካ ከፍተኛው የጦዘ የፈላጭ ቆራጭነት አገዛዝ ደረጃ›› በሚለው አምዴም ላይ እነዚህ የአፍሪካ የቀን ጅቦች ገዢዎች የዘለቀና በጥቅም ላይ የተመሰረተ የወዳጅነት ግንኙነት አላቸው በማለት ሞጋቻቸዋለሁ፡፡ በእርዳታና በንግድ ስም የምዕራቡ ዓለም በተለይም አሜሪካ እነዚህ ሰውበላ ገዢዎች በአፍሪካ ውስጥ እንዲበራከቱ ብርታት ሆነዋቸዋል፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ‹‹ኢትዮጵያ በቦንድ ኤይድ ውስጥ›› በሚለው ጽሁፌ ላይ ዓለም አቀፉ እርዳታ አፍሪካን በአፍራሽ ጎኑ እየጎዳት እንደሆነ  አሳስቤ ነበር፡፡ በ1960ዎቹ አብዛኛው የአፍሪካ ሃገራት ነጻ ከመውጣታቸው አስቀድሞ  አፍሪካውያን በኮሎኒያል ማነቆ ተወጥረው ነበር በማለት ጥፌ ነበር፡፡ በቅርቡ ባሰፈርኩት ማሳሰቢያ ጽሁፌም ኢትዮጵያ ‹‹ምግብ ለችጋር፤እና አስተሳሰብ››  በሚለው አምድ በቅርቡ በዋሽንግቶን የተደረገውን የጂ 8 ስብሰባን አስመልክቼ ስብሰባውና የሚያስተላልፈው ውሳኔ ያለፈውን ለአፍሪካ ሲደረግ የነበረውን የቅኝ ገዢዎች መቀራመት የተካ ነው በማለት አስተያየቴን አስፍሬ ነበር፡፡ የጂ 8 አባላት አዲሱ ጥምረታቸው፤ አፍሪካን ከችጋር ለማላቀቅ፤ ርሃብንና ድርቅን ለማሰወገድ በአፍሪካ ውስጥ የያሉትን ምርጥና ለም ቦታዎች ለጠገቡት የዓለም የናጠቱ ሃብታሞች በመስጠት ማቀዳቸውንም አሳውቄያለሁ፡፡

በኢትዮጵያ አልፎም በመላው አፍሪካ ውስጥ የኦባማ አስተዳደር ሊያደርግ ሲችልላ ባላደረጋቸው የአፍሪካውያን ፍላጎትና ራዕይ ላይ አንዳችም ጉዳይ ባለማድረጉ ካለኝ ቅሬታ ባሻገር  ፕሬዜዳንት ኦባማን በዳግም ምርጫው ወቅት ደግፌያቸዋለሁ፡፡ ከነስህተታቸው ተስፋ የሚጣልባቸው መሪነታቸውን አሳይተውኛልና፡፡ በ2004 ሴነተር ኦባማ ባደረጉት መሪ ንግግራቸው፤ ‹‹ጥቁር አሜሪካውያን፤ነጭ አሜሪካውያን፤ላቲና አሜሪካ፤ኤሽያ አሜሪካ ብሎ ዜጋ የለም፡፡ያለው አንድ የተባበሩት አሜሪካ ብቻ ነው፡፡›› እነዚህ ቃላቶች ምንግዜም እያነቃቁኝና ተስፋዬንም እያለመለሙት ወጣቱ የኢትዮጵያዊያን ትውልድ ወንድ ሴት ሳይል በአንድነት ተሰባስበው በመግባባትና በመፈቃቀር ‹‹ኦሮሞ ኢትዮጵያ፤አማራ ኢትዮጵያ፤ትግራይ ኢትዮጵያ፤ጉራጌ ኢትዮጵያ፤ኦጋዴን ኢትዮጵያ፤ አኝዋክ ኢትዮጵያ…… ብሎ ዜጋ የለም ያለው ፤ ፍትሕ እንደውሃ እኩል የሚፈስባት ህብትና ልማትም እንደታላቅ ምንጭ የሚፈልቅባት   አንድ የተባበረች ኢትዮጵያ እንጂ›› የሚልበት ወቅት እንደሚመጣ  ቁልጭ ብሎ ይታየኛል፡፡

ሰብአዊ መብት 2003ን ረቂቀ ህግ  (“Ethiopia Democracy and Accountability Act of 2007”) ሲካሄድ በነበረው የውይይት መድረክ ላይ በወቅቱ የሴኔተር ኦባማ የሥራ ባልደረቦች ጋር በቢሯቸውና ለበርካታ ጊዜያት ተገናኝተን ነበር፡፡ በዚያን ወቅት ቢሉ በምክር ቤቱ  አልፎ ወደ ሴኔት ሲደርስ ኦባማ ሙሉ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ምንም ጥርጣሬ አልነበረም፡፡ በፌብሪዋሪ 2008 የምክክር ስብስባችን የባሮክ ኦባማን የፕሬዜዳንትነት ውድድርን ተመራጭነት ሙሉ በሙሉ ድጋፉን ሰጥቷል፡፡ በዚህም ጊዜ አሜሪካ በአፍሪካ ላሉት ፈላጭ ቆራጭ መሰሪ ገዢዎች ድጋፍ ሙሉ በሙሉ እንደሚያቋርጥ ተስፋችን ብሩህ ሆኖ ፖሊሲውም የአፍሪካውያንን ራዕይ የሚያጠናክር ተስፋቸውንም የሚያጎላ እንሚሆን አምነን   ነበር፡፡ ወቅቱም የአሜሪካ ፕሬዜዳንት በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በማጥፋት ይህንንም ሲያደርጉ የነበሩትን ሰው በላዎች ከስልጣናቸው እንደሚያወርዳቸው የላቀ ራዕይ ሰንቀን ነበር፡፡

አፍሪካ በአሜሪካኑ የአጀንዳ ፖሊሲ አወቃቀር ላይ አንሶ በመገኘቱ፤ ባለፉት አራት ዓመታት ፕሬዜዳንቱ በሌሎች ስራዎች በመጠመድና ለሃገራቸው ቅድሚያ በመስጠት በመየያዝ አፍሪካ ከነበረችበት ለባሰ ፈላጭ ቆራጭ የቀን ጅቦች መፈንጫ ሆነች እንጂ ተስፋው አልተተገበረም፡፡ በቅርቡ በተካሄደው ‹‹የውጭ ፖሊሲ ክርክር ላይ› አፍሪካ ለይስሙላ ያህል ነው የተጠቀሰችው፡፡ በዓለም በድህነት በሶስተኛ ደረጃ ላይ ባለች ማሊ  አልቃይዳ ስለመኖሩ እግረመንገድ ገለጻ ነበር የተደረገው፡፡ (እንደ ኢኮኖሚስት መጽሔት ገለጻ፤ ኢትዮጵያ በዓለማችን የመጨረሻዋ ድሃ ሀገር ናት  ናት) ለማቻቻል ሳይሆን እርግጥ ነው ፕሬዜዳንቱ በአጀንዳቸው ላይ በርካታ ፈታኝ ጉዳዮች ነበሩባቸው፤የአረቦች መነሳሳት እንደሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ዘመን ያስቆጠሩ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች እየመነጠረ ነበር፤ በመካከለኛው ምስራቅም የኒውክሊየር ጉዳይ አሳሳቢ ሆኖ መጥቷል:: ፤ በአውሮፓም የተከሰተው የኤኮኖሚ ውድቀት አውሮፓን ሊሽመደምድ እየዳዳው ነው፡፡

ተስፋ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ምን ግዜም ዘልዓለማዊ ነው፡፡

በዚህ የፕሬዜዳንት ኦባማ ዳግም የፕሬዜዳንትነት የሥራ ዘመን በአፍሪካ ያለው የሰብአዊ መብት ጉዳይ በፕሬዜዳንት ኦባማ የውጭ ፖሊሲ አጀንዳ ላይ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ እንደሚሆን የላቀ ተስፋ አለኝ፡፡ ለዚህም አመላካች የሚሆነው በምርጫው ማግስት ፕሬዜዳቱ ማይነማርን (በርማ) ከሁለት ሳምንት በኋላ ለመጎብኘት ማቀዳቸው ነው፡፡ ፋይዳ በሌለው ከአሃምሳ ምስት አመት ወታደራዊ  አገዛዝ ዘመን በኋላ ማይነማር ቀስ በቀስ ወደ ዴሞክራሲያዎ ስርአት እያመራች ነው፡፡ ፕሬዜዳንት ቲየን ሲየን የፖለቲካ እስረኞችን ሁሉ እየለቀቁ ነው፡፡ የዜና ማሰራጫዎችን ሁሉ ማዕቀቡና ቁጥጥሩ እየተነሳላቸው:: ፤ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጥሪፎርም እየተካሄደ ነው፡፡ከሃያሁለት ዓመታት የግፍ የቤት አስር ወጥተው አውንግ ሳን ሱዊ ኪ በፓርላማው እውቅና የተሰጣቸው ሕጋዊ ተቃዋሚ ሆነዋል፡፡እንደ አሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዘገባም፤የስቴት ዲፓርትመንት አፈ ጉባኤም በኢትዮጵያ ስለሚታየው የሰብአዊ መብት ጉዳይ አጽንኦት እንደተሰጠው ተደምጸዋል፡፡ የኦባማ አስተዳደር በአፍሪካ ስላለው ጉዳይ ቆራጥ አቋም ይዞ ሰብአዊ መብትን ለሕዝቡ እንደሚያስገኝ አንዳንድ ምልክቶች እየታዩ ነው፡፡

ፕሬዜዳንት ኦባማ ለአፍሪካ ዘልዓለማዊና የማይነጥፍ የዴሞክራሲ ልዕልና የመመስረት ዓላማ አላቸው

በተለምዶ  ዳግም ምርጫ በአሜርካ አብዛኛው ትኩረቱ በውጪ ፖሊሴ ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ በዚህ ወቅትም በይበልጥ የሚያስቡበትና ሊተገብሩም የሚሹት፤ከአግልግሎታቸው ፍጻሜ በኋላ የሚተዉትንና ዘመን ሊያስታውሰው የሚችለውን መልካምና ዘላቂ ድርጊታቸውን ነው፡፡ፕሬዜዳንት ኦባም ለአፍሪካ የማይዘነጋና በቅርስነት የሚታሰብ የሰብአዊ መብት መከበር ስጦታ ትተው ማለፍ ነው ዓላማቸው፡፡በእርግጠኝነትም እሳቸው ወደ ሥልጣን ከመጡበት ጊዜ በባሰ ሁኔታ ውስጥ አፍሪካን ጥለው መሄድ አይፈልጉም ብዬ አስባለሁ፡፡ ፕሬዜዳንት ኦባማ ወደስልጣን በመጡበት ጊዜ ጦር ሰብቀው አለያም ምርጫን አጭበርብረው፤ወደስልጣን የወጡ የአፍሪካ ገዢዎች የበረከቱበት ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ  አፍሪካ ውስጥ በአብዛኛው ያሉት ገዢዎች የሕግ የበላይነት ጨረሶ የጠፋበትና ሕግ ማለት እነዚሁ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎችና ሆድ አደር አገልጋዮቻቸው የሆኑበት፤ በመሆናቸው ሁኔታው ለአእምሮ የሚሰቀጥጥ ነው፡፡ የሰብአዊ መብት ገፈፋ የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ነው፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞች፤ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤የተቃዋሚዎ ፓርቲ መሪዎች፤ሰላማዊ መብት ጠያቂዎች፤ይታሰራሉ፤አለፍርድ በየዕለቱ በገዢዎቹ በየስለላ ድርጅቶች አባላት ስቃያቸውን ያያሉ፡፡

ምንም እንኳን በአሜሪካ ተወልደው ቢያድጉም ለፕሬዜዳንት ኦባማ አፍሪካ የአባታቸው ሃገር ነው፡፡እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ አሜሪካ ኦባማም አሁጉሩን ከድህነት ማውጣት ብቻ ሳይሆን፤ በአፍሪካ ውስጥ የሰብአዊ መብት ተከብሮ፤ነጻና ፍትሐዊ ምርጫም እንዲካሄድበት፤ የሕግ የበላይነትም የሚጠበቅበት እንዲሆን ምኞት እንዳላቸው አልጠራጠርም፡፡‹‹ከአባቴ ሕልሞች ›› በተባለው መጽሃፋቸው “….በአባቴ ገጽታ ውስጥ ነበር፤ከዚያ ጥቁር ሰው፤ከአፍሪካው ልጅ፤በኔ ውስጥ የተጠራቀመውን መልካም ዋጋ ሁሉ፤የማርቲንን፤ የዱቧንና የማንዴላን ብርታት የተቸርኩት››፡፡ እነዚህ ሰዎች ባሳለፉት የትግል ጥንካሬያቸውና ብርታታቸው እንደራሴ በማየት፤ ባከብራቸውም ያ የአባቴ ድምጽ ግን ምንገግዜም ሳይለየኝ የማደርገውን ሁሉ እየፈቀደልኝና እየመራኝ አብሮኝ አለ፡፡ፕሬዜዳንት ኦባም በዚሀ የሁለተኛው ዘመን አመራራቸው አፍሪካውያን ለሰብአዊ ክብራቸው በሚያደርጉት ትገል አፍሪካውያንን እንደሚያግዙና ለድልም እንደሚያበቋቸው አልጠራጠርም፡፡

በአረብ የመነሳሳት ወቅት የአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ሁኔታ

በአረቦች መነሳሳት ወቅት የአሜሪካን መንግስት የነበረውን የሰብአዊ መብት ፖሊሲሰ ከ ደህንነትና የኤኮኖሚ ጠቀሜታ ጋር ማዋሃዱን ሂደት ከ እብሪተኞች ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ከሚያደርገው አመለካከት ጋር በድጋሚ ማጥናት፤ ሁኔታዎችን ማገናዘብ፤ መመርመር ማስተካከልም እንዳለበት ተገነዘበ፡፡ የአካባቢውን የደህንነትና የመረጋጋት ሁኔታና ዋስትና በዲክታተር መሪዎች አመኔታ ላይ በማድረግ የአረብ ዓለሙን ሕዝቦች ስቃይና መከራ፤ የሚፈጸምባቸውን ግፍ በቸልታ ማሳለፉን ታሪክ ያሳያል፡፡የአረቡ ዓለም የበቃኝ ሂደት ሲፈነዳና ሕዝቡ በእምቢታ ለነጻነት ለሰብአዊ መብት መከበር ለዴሞክራሲ እውነታ ሲነሳሳ የአሜሪካ አስተዳደርም በመደናገጥና ግራ በመጋባት የሚያደርገው ተዘበራረቀበት፡፡

የአሜሪካ መንግስት ከአፍሪካ የፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ጋር ያለውን ሁኔታ አያይዞ የሚመለከተው በአካባቢው ካለው ደህንነትና መረጋጋት ጋር ስለነበር፤የሰብአዊ መብትንና ሌሎችንም ሕዝባዊ መብቶች ማንሳቱ ከእነዚህ አረመኔ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ጋር ስለሚያጋጨው ትብብራቸውን ላለማጣት ፍርሃት አለው፡፡ከዚህም በመነሳት ሁኔታዎቹ ሲታዩ የአሜሪካን መንግስት ከዝምታ የዲፕሎማቲክ ፖሊሲና የቃላት ባዶ ተስፋ ከመቸር ያለፈ ተግባር በአፍሪካ ውስጥ አላከናወነም፡፡ ፕሬዜዳንት ኦባማ የአሜሪካ ዘላቂ ዓለም አቀፍ ፍላጎት የሞራል ማስታገሻ ድጎማ ቃላትና ድርጊትን በማውገዝ ብቻ አንዳችም እርምጃ እንደማያስኬድ እንደሚያውቁ አልጠራጠርም፡፡ የፕሬዜዳንቱ አካሄድ በቅድሚያ የዲፕሎማቲክ አካሄዱን በሚገባ ማስኬድና ውጤቱን ተመልክቶ ካልሆነ አስቀድመው ወደመጨረሻው አማራጫቸው እንደማይገቡ የታየ ነው፡፡እንዳሉትም ‹‹የሰብአዊ መብትን ተግባራዊ ማድረግ የሚቻለው በቃላት በሚሰነዘሩ ሂደቶች ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡ አንዳንድ ጊዜም እጅጉን በጠነከረ የዲፕሎማሲ ግንኙነትና ድርድር መሞከር አለበት፡፡ እርግጥ የሰብአዊ መብት ሂደትን በተመለከተ ከግፈኛ መሪዎች ጋር የሚደረግ መግባባት በጣሙን አስቸጋሪና በእምቢታና በጀብደኝነት ላይ የተመሰረተ እንደሆነ እገነዘባለሁ፡፡ ማንኛውም ጨቋኝ መንግስት መውጫ መንገድ እስካላገኘ ድረስ ከነበረበት ዝቅ ብሎ መውረድን አይቀበልም፡፡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ጥቂት የአፍሪካ መሪዎች በተከፈተላቸው በር በመውጣት የዴሞክራሲንና የሰብአዊ መብትን መከበር ተቀብለዋል፡፡ አብዛኛዎቹ  ደግሞ የተከፈተላቸውን የሠላም በር በአጉል ንቀትና በማያዋጣቸው ማንአለብኝነት በርግጫ መልሰው ዘግተውታል፡፡ በጣም እርግጠኛ ነኝ ፕሬዜዳንቱ በሁለተኛው የአስተዳደር ዘመናቸው ከቃላትና ከማስታመም አልፈው የአፍሪካን መሪዎች የእርዳታና የችሮታ ከረጢት በእጃቸው ስለያዙ ሸምቀቆውን በማጥበቅና በማላላት አካሄዳቸውን ሊያስለውጡና በአፍሪካ የተናፈቀውን የነጻነት መንገድ እንደሚያስተካክሉት እምነቴ ነው፡፡

ፕሬዜዳንት ኦባማ ፕሬዜዳንት ብቻ ሳይሆኑ የሕገመንግስታዊ ጠበቃም ናቸውና……..

ፕሬዜዳንት ኦባማ መሪ ከመሆናቸው በፊት ያካበቱት ልምድ አሁንም በአስተሳሰባቸውና በድርጊታቸው ላይ ጫና እንደሚፈጥርባቸው አምናለሁ:: እንደ ኮኒስቲቲዩሻናልና የሲቪል የሕግ ባለሙያነታቸው፤  ስለሕግ መዛባትና ስለሞራል ድክመት፤ ስለሰብአዊ ክብር መደፈርና ሌሎችም ተመሳሳይ ጉዳዮች የጠነከረ ልምድና እምነት አላቸው፡፡ ለረጂም ዓመታት በሰብአዊ አገልግሎት፤ በሕብረተሰብ ፍላጎትና ጥቃትን በመከላከል ዘርፍ ብዙ ሰርተው በርካታ ልማድ ያላቸው ናቸው፡፡ የተቸገሩትናና አቅመ ደካሞችን፤ በቤተክርስቲያናት በኩል በማደራጀትና በመርዳት ብዙ ከውነዋል፡፡ የኮሙኒቲ ተግባራቸው የታመቀ ልምድ አስጨብጧቸዋልና ያወውቁቅታል፡፡ ፕሬዜዳንት ኦባማ የሕግን የበላይነት ጥቅሙን ይረዱታል የሚል ጠንካራ እምነት አለኝ፡፡የሕግ ምሁርና የተቸገሩ ምስኪኖች ተሟጋች እንደመሆናቸውም ማንኛቸውም የችግር ምንነት በአግባቡ የገባቸው ናቸው፡፡ስለዚህም ለሕብረተሰብና ለአካባቢ ሰዎች ያላቸው ተሟጋችነት በዚህ የሁለተኛው አስተዳደር ዘመናቸው ጎልቶ ይወጣል እላለሁ፡፡

አንዳንዶቻችን ፕሬዜዳንት ኦባማ ምን ሊያደረጉልን ይችላሉ በሚለው ጥያቄ እንታለላለን፡፡ ትክክለኛው ጥያቄ ግን እኛስ በመደራጀት፤የኦባማን አስተዳደር በእውነተኛው ሁኔታ ላይ በማግባባት፤ጠንካራ የሰብአዊ መብት አጀንዳ እንዲቀርጽ ለማድረግ ምን እያደረግን ነው የሚለው መሆን አለበት፡፡ፕሬዜዳንት ኦባማ ምርጫውን ባሸነፉበት ማታ ባደረጉት ንግግር ‹‹በእኛ ዴሞክራሲ የዜጎች ሚና በሰጣችሁት ድምጽ ብቻ የሚገታ አይደለም፡፡ አሜሪካ ፈጽሞ ለኛስ ምን ይደረግልናል ሃገር ሆኖ አያውቅም፡፡ይልቅስ በእኛስ በኩል ሊደረግ የሚገባው ምንድን ነው፤በዚህ አስቸጋሪና ፈታኝ ወቅት ግን አስፈላጊና የራሳችን በሆነው መንግስት ምን ይጠበቅብናል የሚለው ነው›› ገቨርነር ሮምኒ በመጨረሻው የማክተሚያ ንግግራቸው እንዳሉት ‹‹ በእንዲህ አይነቱ ወቅት እርስ በርስ መነቃቋርና ባለፈው  ጥርስ በመንከስ መለያየት የለብንም፡፡ መሪዎቻችን ባሻገር ተጉዘው የሕዝቡን ፍላጎት ማሟላት ሲገባቸው እኛ ሕዝቦች ደግሞ ጊዜው የሚጠይቀውን ማድርግ ግዴታችን ነው፡፡››……. ይህ ነው የኢትዮጵያዊያን አሜሪካውያን እምነት ሊሆን የሚገባው፡፡ በዲያስፖራውም በሃገራችንም ውስጥ፡፡ ይህንን ነው አምነን በመቀበል መተግበር ያለብን፡፡ካለፈው ስህተታችንና ድክመታችን በመማር እራሳችንን አስተካክለንና ሂደታችንን አርመን የኦባማ አስተዳደር ተገቢውን እንዲያደርግ መጎትጎት ያለብን፡፡ የአረብ አሜሪካኖች፤ኢራንያን አሜሪካኖች፤አርሚኒያን አሜሪካኖች፤ማሲዶንያን አሜሪካኖች፤ሰርቢያን አሜሪካኖችና ሌሎችም ከአስተዳደሩ ጋር በጥንካሬያቸው በመሞገት ተግባራቸው ውጤታማ ሆኗል፡፡ እንደሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ጠበቆች፤የአሜሪካ ቀዳሚ ባለስልጣናት ጋር በመቀራረብና በመነጋገር በመግባባት ስለሰብአዊ መብት የሃገራችን ሁኔታ በማስረዳት ውጤታማ መሆን ይጠበቅብናል፡፡

የአሜሪካን መንግስት ዲክታተሮች የሆኑ  አመራሩ ላይ የተቀመጡት ወዳጆቹን ማንበርከኩን ያወቅበታል፡፡በ1980 የአሜሪካን መንግስት በፊሊፒንስ፤በቺሊ በታይዋን እና በምእራብ ኮሪያ ውስጥ በተካሄደው የዴሞክራሲ ሽግግር ቁልፍ ቦታ እንደተጫወተ ይታወሳል፡፡ በሶቭየት ዩኒየንና በሌሎቹ የሶቭየት ክልል በነበሩት ሃገራት የዴሞክራሲ ሂደትም አሜሪካ ድርድሩን በመምራት ውጤታማ እንዳደረገ ይታወሳል፡፡ጥያቄው አሜሪካ በኢትዮጵያ ወይም በአፍሪካ ውስጥ የሰብአዊ መብት አጀንዳን ያራምዳል ወይ ሳይሆን፤ ይህን ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ የፖለቲካ ፈቃደኝነቱ አለው ወይ ነው፡፡ በፕሬዜዳንት ኦባማ ሁለተኛ የአስተዳደር ዘመን ፈቃደኝነቱ ይታያል የሚልጠንካራ እምነት አለኝ፡፡

የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):

http://open.salon.com/blog/almariam/2012/11/11/what_should_ethiopians_expect_in_a_second_obama_term

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::)

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

Ethiopian Muslim & Christian solidarity in Washington: VOA

Demonstrators demand issues raised by Ethiopian Muslims be addressed

Ethiopians and people of Ethiopian origin living in the Greater Washington, D.C., area and throughout the United States staged a huge rally on Thursday, August 2, 2012, in front of the US Department of State, according to reports by the Voice of America.

Sheikh Imam Sheik Khaled Omar of Washington’s First Hejira Foundation called on the US government to put pressure on Ethiopian authorities to address the three key issues raised by Ethiopian Muslims, VOA reported.

On the Christian side, Father Philippos of the Holy Synod of the Ethiopian Orthodox Church in exile affirmed that the issues raised by Muslims are just and that the beatings and imprisonment to which they have been subjected to must be condemned, the report concluded.

Please click on link below to listen to the full VOA report in Amharic.

http://www.voanews.com/amharic/news/dc-muslims-christians-demo-164804826.html

 

Is Aiga Forum writing Meles’ obituary?

Bye, Bye Meles?

July 15, 2012

Aiga Forum, the website closely associated with Ethiopia’s intelligence services, just posted an emotional, tear-soaked, braggadocio-filled piece that appears to be the obituary of Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi.

The article titled “Meles ad Infinitum” was penned by someone using the pseudonym “Aesop.”  Aesop, incidentally, is the same author who wrote another piece a week ago calling Ethiopian Muslims mosquitoes.  That article was a prelude to the government crackdown on Ethiopian Muslims this past Friday.

In a thinly-veiled farewell to the best known son of Adwa who went on to terrorize  the nation of 90-million for the last twenty-one years, the author argues that Zenawi should be remembered for what he accomplished in “praxis” as as well as his one-time promise to step down peacefully.

You can read the full article at the following link.

http://aigaforum.com/articles/meles-ad-infinitum.php