Skip to content

የፍርሃትና ስም ማጥፋት ፖለቲካ በኢትዮጵያ

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

2011፡ የሙስና አገዛዝ፤ ፍርሃትና ሰም ማጥፋት

በዲሴምበር 2011 ‹‹ኢትዮጵያ የደም ሃገር ወይም የንቅዘት (ሙስና) ሃገር›› በሚል ርእስ የኢትዮጵያን ሁለት ገጽታ በማመዛዘን አንድ ጦማር አስነብቤ ነበር፡፡ በዚያን ወቅት ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በተባለው ተቋም ተቀምጦ የነበረው ገጽታ ያሳየው ኢትዮጵያ ለም መሬቶች በተንኮል በተጠቀለለ ስውር ደባ እየተቸበቸቡ እንደነበር ነው፡፡በዘገባው ላይ ተቋሙ ለኢትዮጵያ ያሰፈረው ነጥብ (10 ከሙስና የፀዳ ማለት ሲሆን 0 ደግም በሙስና ንቅዘት ያጨማለቀው ማለት ነው) ኢትዮጵያ 2.7 ነበር ያገኘቸው፡፡ በሙሰና ከታወቁት የኣለም ሃገሮች ዋነኛዋ ኢትዮጵያ ናት ይል ነበር::  የግሎባል ፊናንሻል አንተግሪት ድርጅት ደግሞ ባለፉት ፲ ኣመታት ከኢትዮጵያ 11.7 ብልዖን  ያሜርካን ብር በሀገወጥ መንገድ ከኣገሪቷ ወጥቶአል ብሎ ዘገቦ ነበር::

ባልፈው ኣመት: አሁንም በስላጣን ላይ ያለው ገዢ ኣስተዳደር ኢትዮጵያን በሽብርተኞች ማነቆ ውስጥ ተወጥራ እንዳለች ሃገር አድርጎ ለማቅረብ ባወጣው የልመናና የገንዘብ መቧገቻ እቅዱ ባለሶስት ክፍል የፕሮፓጋንዳ የቅጥፈት ታሪክ ‹‹አኬልዳማ›› በማለት (ወይም የደም መሬት በማለት ከአክትስ 1፡19 በመዋስ፤ የአስቆሮቱ ይሁዳ ክርስቶስን ክዶ በመሸጥ ባገኘው ገንዘብ የተገዛ መሬት) ከልብ ወለድ የማይሪቅ ትርኢት ለሕዝብ ኣቅርቦ ነበር፡፡ ይህም ትርኢት በአትዮጵያና በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሰዎች በሚታገዝና በሃገርም ውስጥ ባሉት የሚደገፍ የሽብር ተግባር አምባ አድርጎ ለማሳመን የተሰራ ነው፡፡ አኬልዳማ ሲጀምር በኢትዮጵያ ውስጥ ሊከሰት የሚችል በማለት የደም ጎርፍ መምጣት እንደሚችልና፤ ሸብር ዓለምን በማጥፋት ላይ ነው፡፡ ‹‹አኬልዳማ›› ሲተረት: “ሽብርተኝነት የቆምንበትን መሬት እያነቃነቀ፤ ዕለታዊ እንቅስቃሴያችንንም እየገታ መሆኑን በቅጥፈታዊ ፈጠራ ለማሳየት የቀረበ ትርኢት፡፡ አሁን እየተናገርኩ ያለሁት ስለዓለም አቀፉ ሥብርተኝነት አይደለም፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት በገዢው መንግስት ለኢትዮጵያ የተቀመጠውን የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳና በዚያም ውስጥ ስለተካተተው አኬልዳማ ተብሎ ስለተቀፈቀፈው፤ ሸብርተኝነት ለኢትዮጵያ አስጊና አሳሳቢ ችግር ነው…… ስለተባለው ነው፡፡”

በአኬልዳማ ውስጥ ተቀነጫጭቦና ተቆርጦ የተቀጣጣለ የቪዲዮ ቅንጥብጣቢ፤የአልቃይዳና የአል ሸባቢ ተከታዮች የመለስ ዜናዊን መንግስት ለማፍረስና ሃገሪቱንም ለማመሰቃቀል ተነስተዋል በማለት የሕጻናት የአዛውንቶች፤ እሬሳ በመንገድ ላይ ወድቀውና በደም ተጨማልቀው በዝንቦች የተወረሩ እሬሳዎች፤ የተቆራረጡ እግሮች፤ የነደዱ ተሸከርካሪዎች፤ በቦምብ የፈራሱ ሕንጻዎች፤ የህክምና ባለሙያዎችም የተጎዱትን ሲያክሙና በኒው ዮርክ በሽብርተኞች የፈረሱት የትዊን ታወር ምስሎች በማገጣጠም የገዢውን መንግስት ስጋት አሳማኝ ለማድረግ ምስሉን አቀነባብሮ አቀረበ፡፡ በዚህም የሕብረተሰቡ ሕሊና ውስጥ የፈጠረው ስጋት ቢኖር የገዚዎች ውሸትና ተራ ፕሮፓጋንደ እንጂ ከዚያ ያለፈ ለማሳመን የቻለው የለም፡፡ ማስረጃውን እንመልከት ብሎም ያቀረበው ዘጋቢ ቁጭት በውስጡ እየነደደ የሃሰት ስሜቱን ታግሎ በማውጣት በጥፈሩ እየቆመና ቃላትን እየረገጠ በሚያስፈራና ቀፋፊ በሆነው ድምጹ ህጻናትን እያሰበረ አርጉዝ ሊያጨነግፍ በሚችል ስሜት አቀረበው፡፡ እስቲ እውነተኛውን ማስረጃ እንመልከት፤  ይላል ‹‹አኬልዳማ››: “ባለፉት ጥቂት ዓመታት፤ 131 የሽብርተኞች ጥቃት ተካሂዶ 339 ተገድለዋል 363 ቆስለዋል፤ 25 ደግሞ በሽብርተኞች ታፈነው ተገድለዋል፡፡” ቅጥፈት የተሞላበት፤ ማጭበርበሪያ የሆነ፤የተዛባ ትረካ የተካተተበት አኬልዳማ በተቃዋሚዎች ላይ ሕዝባዊ ጥላጫና ጥርጣሬ ለመንዛት ሆን ተብሎ የተዘጋጀ ነበር፡፡ውጤቱ ግን እንደታሰበውና እንደታሰበው ሳይሆን መክኖ ቀረ፡፡

2013 የሙስና አገዛዝ፤ ፍርሃትና ሰም ማጥፋት

ወደ ፌብሪዋሪ 2013 ፈጠን ብለን እንሂድ::  በቅርቡ ተጣርቶ በወጣው ባለ 448 ገጾች የዓለም ባንክ ዘገባ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ካሉት ሀገራት ሁሉ ከአናት እስከ ታች ድረስ በባለስልጣናቱና በአጃቢ አገልጋዮቻቸው ንቅዘትና ሙስና የተዘፈቀች ሃገር ናት ይላል፡፡ በዘገባው መሰረት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት የንቅዘቱ መፈልፈያ ማህጸን ነው፡፡  ገዢው ኣስተዳደር በጣሙን የገዘፈ መዋእለ ንዋይ በማፍሰስ በቴሌ ላይ ኢንቬስት ቢያደርግም፤በአፍሪካ ሁለተኛው የቴሌፎን ስርጭት ዝቅተኛ የሆነበት ሃገር ከመሆን አላዳነውም፡፡ በጣም አናሳ አግልግሎት ሰጪ ድርጅት ከመሆንም አልፎ፤ከተጠያቂነት ነጻ የሆነ የዘረፋ ማእከል ነው፡፡በሃገርም ውስጥ ሆነ በውጭ ታዛቢዎች ድርጅቱ በሙስናና በንቅዘት የተገነባ ለምዝበራ የተጋለጠ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ በየትኛውም የአገልግሎት አሰጣጥ መመዘኛ ተጎታችና እርካታ ይሉት አገልግሎት የሌለው በየጊዜው በሚነደፈው የሙስና እቅድ ውስጥ ተውተፍትፎ አገልግሎቱ እርባና ቢስ ነው፡፡ የፍትህ ስርአቱም ቢሆን ሕብረተሰቡን በነጻ እንዳያገለግልና የፖለቲካ መሳሪያ እንዲሆን ተደርጎ በገዢው ኣስተዳደር ንጹሃንን በመወንጀል ፖለቲካዊ እንቅስቃሴን በመግታት አገዛዙ ከመንበሩ ሳይለቅ የሚቀጥልበትን ሁኔታ የሚተገብር የፍትህን ስርአት የጣሰ ነው፡፡ ይህም በህጋዊ ኢፍትሃዊነት ብቻ ጉዳት ከማድረሱም ባሻገር ለጉቦና ለንቅዘት ተጋልጦ ያለ አንድ የገዢው መንግስት የጦር መሳርያ ነው፡፡ ገዢው መንግስት በስልጣን መቆየቱን እንጂ ለሃገርና ለህዝብ እድገትና ልማት ጨርሶ ደንታ የሌለው በመሆኑ ከጉቦ ውጪ አንዳችም ጉዳይ በስርአት አይከናወንም:: የዚህም ሂደት ዋናው አስፈጻሚ ሞተር ገዢው ፓርቲና ጀሌዎቹ ናቸው፡፡

በፌብሪዋሪ 5/2013 ላይ በአዲስ አበባ ያለው ገዢው ኣስተዳደር ‹‹ጂሃዳዊ ሃራካት›› (የቅዱስ ጦርነት እንቅስቃሴ) በሚል ርዕስ አንድ ዘጋቢ (ዶኩሜንታሪ) ፊልም በእኩይ አስተሳሰብና ዲያብሎሳዊ ግንዛቤው የኢትዮጵያ ሰላማዊ ሙስሊሞች ያነሱትን ሃይማኖታችንን ለኛ ተዉልን፤ ሰብአዊ መብት ይከበር፤ በማለቱና በሰላማዊ መንገድ እንሰማ በማለታቸው፤ በየቦታው ካሉና የኢትዮጵያ ሙስሊም ሕብረተሰብ ከማያውቃቸው፤ ተግባራቸውን ከማይቀበለውና ግንኙነትም ከሌለው ጋር ገዢው ኣስተዳደር በተካነበት የቅጥፈት ዘመቻው ጥያቄ  እንዳሰኘው በሚያዝበት ቴሌቪዥን ጣቢያው ላይ አሰራጭቶ ነበር፡፡

‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› በሁለንተናዊ መልኩ የ‹‹አኬልዳማ›› ግልባጭ ነው፡፡ መሰረታዊ ልዩነቱ የሙስሊሙን ማሕበረሰብ ለይቶ ለማስፈራሪያነትና ለስም ማጥፊያ ተብሎ በአንድ የሃይሞነት ተከታዮች ተነጣጥሮ መተግበሩ ነው፡፡ በአጠቃላይ ዘጋቢው ፊልም ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ሰብአዊ መብት እንዲከበር፤ ኣስተዳደሩ በእምነታቸው ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም በመጠየቃቸው፤ ያላለሙትንና ጨርሶ ያላሰቡትን ሕዝቡ ናቸው ብሎ እንዲቀበል፤ እነዚህ ደም የጠማቸው የናይጄሪያው ቦኮ ሃራም፤የማሊው አንሳር ዲን፤ አልቃይዳ አልሻባብ ሃማስ ቅርንጫፍ ተከታዮች  በማለት ያልሆኑትን ናቸው በማለት በተለመደው የፍርሃትና የመደናገጥ ዜማው ታርጋ በመለጠፍ ላይ ያተኮረ ነው፡፡  ዶኩሜንታሪው ተቆቋሪ በመምሰልና አዛኝ ቅቤ አንጓችነቱን በማጠናከር በሙስሊሙ መሃል የተሸሸጉ ጥቂት ሽብርተኞች በማለት ይኮንናል፡፡ ዘጋቢው ፊልም በየትም የአፍሪካ ያልታየ የቂመኝነትና የትእግስት ማጣት እኔ ካልኩት ውጪና ከምፈቅደው ባለፈ ንክች ያባ ቢላ ልጅ ይሉት ዓይነት ድንፋታ ብቻ ነው፡፡

ውሸት ሞልቷል፤ እርቃኑን የቆመ ውሸት አለ፤የጎደፈ ውሸት አለ፤የሆዳሞች ውሸት አለ፤የመልቲዎች ቅጥፈት አለ:: ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ደሞ እነዚህ ሁሉ ውሸቶች የተጠናወቱት ነው፡፡ ይህን የሚያቀለሸልሽ ዶኩሜንታሪ ከተመለከትኩት በኋላ፤ በቅርቡ ያለፈው መለስ ዜናዊ የሜይ 2010ን ምርጫ 99.6 በሌብነት የተገኘ ድል አስመልከተው የአውሮፓ ዩኒየን የምርጫ ታዛቢዎች ስለተከናወነው የድምጽ ሌብነቱ  ፊት ለፊት ሲጋፈጡት የሰጠው ምላሽ ታወሰኝ፡፡ መለስ እጅ ከፍንጅ በመያዙ የአውሮፓ ዩኒየነን የምርጫ ዘገባ በመኮነን ከአንድ መሪ በማይጠበቅ መልኩ ማፈሪያ የሆነውን ‹‹ዘገባው ቆሻሻ ስለሆነ ንብረቱ  ወደሆነው ወደ ቆሻሻ መጣያ ሊወረወር ይገባዋል›› ነበር መልሱ፡፡ ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ደካማ፤ አስቂኝ፤ማሰብ ከተሳነው ህሊና የወጣ፤ማስመሰያ፤ መርዘኛ፤ በጉራ ያበጠ፤ ድንፋታ ነው፡፡ ይህን መሰሉ የመለስ አባባልም የቅራ ቅንቦ ክምር ነውና ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ወደ ቆሻሻ ቱቦ ተደፍቶ ከእጥብጣቢውና ከቆሻሻው ፍሳሽ ጋር ሊቀላቀል ይገባዋል፡፡

ፈጽሙ የተባሉትን ያለ ጥያቄና ስስብእናቸውን ለጥቃቅን ጥቅም በመሸጥ ታዛዥነታቸውን የሚያረጋግጡትን አሰባስቦ ተመረጡ ብሏል፡፡ ቀድሞ ለዘመናት ከመንግስት ተጽእኖና ቁጥጥር ነጻ የነበረው አስልምና ካዉንስል አሁን በገዚዎቹ  የሚታዘዝና የገዚዎቹን ትእዛዝ በመቀበል የሚያስፈጸም የካድሬዎች መጠራቀሚያ ሰፈር ሆኗል፡፡ መያዙ፤በሽብርተኝነት ወንጅላ ካውንስሉን የመቆጣጠር ህልሙን ተግባራዊ ማድረጉ በኢትዮጵያ ውስጥ ገዚዎቹ ሃይማኖቶቹን መጠቀሚያ የማድረጉ ሂደት እየባሰ መሄዱን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ በሰላማዊ እንቅስቃሴያቸው ጊዜ በርካታ ሙስሊሞች በመላ ሃገሪቱ ለእስራት እየተዳረጉ ነው፡፡ በኦክቶበር 29 ገዢው የኢትዮጵያ መንግስት 29 ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ የነበሩ ሰዎችን በሽብርተኝነትና የሙስሊም መንግስት ለማቋቋም ተንቀሳቅሰዋል በሚል ለእስር ዳርጓል፡፡

ጂሃዲስቶች ተመልሰው እየመጡ ነው?!

‹‹ጂሃዳዊ ሃራካት›› የኢትዮጵያ መንግስት ጂሃዲስቶችን ከጓዳው እያወጣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያስፈረራ የመጀመሪያው አይደለም፡፡በ2006 ዓም የመለስ ዜናዊ ታንኮች መንገዳቸውን ወደ ሞቃሾ ከማምረታቸውና በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃን የሱማሌ ህዝቦችን ከመጨፍጨፋቸው በፊት፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩት ከቤት ንብረታቸው ከመፈናቀላቸውና ከመልቀቃቸው አስቀድሞ መለስ ዜናዊ የሶማልያን ጂሃዲስቶች፤ ሽብርን ፈጥሮ፤ በሚገዛው ሃገር ውስጥ የሚፈጽመውን ሽብር፤ ጭቆና፤ ግፍ፤ መጠን ያጣ በደል፤ የሰብአዊ መብት ገፈፋ፤ የፍትህን መዛባት ከዓለም ገጽታ ለመሰወርና አዲስ ባወጣው የሶማሌ ጂሃዲስቶችና ……… በመተካት በተለይም የአሜሪካንን መንግስት ትኩረት ከኢትዮጵያ የግፍ አመጽ በማሸሽና ወደ ሶማሊያ ላይ በማስተኮር የአሜሪካንን  መንግስት የዲፕሎማቲክ ድጋፍ ሙሉ ፈቃድ ተጎናጸፈ፡፡

‹‹ጂሃዳዊ ሃራካት›› ወይም እስልምናን ማስፈራሪያ ማድረግ ጥበብ

‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› የሚያስጠላ የሙያ አልባዎች ቅጥ የሌለው ፕሮፐጋንዳ ሲሆን ማንም ቢሆን ከተመለከተው በኋላ የዘገምተኛ መሃይም አስተሳሰብ ከማለት ቀልድ ሌላ ትርጉም አያገኝለትም፡፡  ለአዘጋጂዎቹ ግን ቁም ነገር የሌለው ተብሎ ብቻ የማይተው ሳይሆን ጠቅላላውን የሙስሊም ማሕበረሰብ ዝቅ አድርጎ የመመልከትና እንደ መሪም ሃላፊነት የጎደለው ጋጠ ወጣዊ ተግባር ሊባል ብቻ ነው የሚቻለው፡፡ ለማስተላለፍ የተፈለገውም በጥላቻ የተሞላና በሰላም የኖሩትን የአንድ ሃገር ሰዎች በማከፋፈልና ጠብ እንዲጫርና ጣልቃ ገብቶ የተለመደ የመግደል የማቁሰል ሱሱን ለመወጣት ተብሎ ‹‹ጥሩ ክርስቲያኖች›› ላይ ‹‹መጥፎ ሙስሊሞች››  ሊፈጽሙ ያሰቡት ደባ›› በማለት፤ ሁለቱ እንዲጋጩ፤ አለመግባባት ጨርሶ ሳይኖራቸው አንዱ የሌላው ችግር ደራሽ፤ አሳቢ፤ በሃዘንም ሆነ በደስታ አብረው በመቆም ዘመናት ባሳለፉት ወንድማማቾች መሃል አለመግባባት በመፍጠር በድንገት የሙስሊም ሽብርተኞች መጡብህ በሚል ስር የሰደደና የተካኑትን የማናቆር ተግባር በመተግበር የእስልምና መንግስት ለማቋቋም እየተንቀሳቀሱብህ ነው በማለት ክርስቲያኑ እንዲነሳሳ በመጨረሻም ግጭቱ እንዲሰምርላቸው ነበር ቅዠታዊ ስልት ነበር፡፡ ቀደም ሲል‹‹አኬልዳማ›› ብለው የፈጠሩት  የቆርጦ ቀጥል የማፍያ ተግባራቸው፤ ሙስሊሙን ክርስቲያኖች ሊያጠፉህ መጡብህ ለማለት ተብሎ ቢተላለፍም፤ አቅራቢውም ትንፋሽ እስኪያጥረው ቃላቱን እየረገጠና በዘጋቢው ፊልም ውስጥ የነበሩትን ንጹሃን ዜጎች፤ ከአለቆቹ በበለጠ ጥላቻው ከሮበት እስኪታይ ድረስ ቢንደፋደፍም ውጤቱና ሕዝባዊ መልሱ ግን ከ ‹‹ዶሮን ሲያታልሏት………›› አላለፈም፡፡ እንዲጠሉ የታቀደላቸው ጭርሱን የፍቅር አድባራት ሆኑ፡፡ በእዝ ማስጠላትና ማራቅ ባለመቻሉ ግለሰቦችን ከእገሌ ጋር ቢቀርብህ ይሻላል በሚል ከንቱ ተራ ማስፈራርያ መጠቀሙም ቢሆን ብዙም አልሰመረም፡፡

ገዢው መንግስት በዚህ ዱክትርናው በርከት ያሉ የፕሮፓጋንዳ ግቦችን ለመፈጸም ሞክሯል  1) የማን አለብኙ መንግስት ሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር፤በሃይሞኖቶች መሃል ጣልቃ ገብነቱን እንዲያቆምና የማይመጥናቸውን የራሱን ፍላጎት ለሟሟላት ሲል ብቻ ሽብርተኞች፤አክራሪ ጂሃዲስቶች፤ የመግደል አባዜ የተጠናወታቸው በማለት የራሱን መታወቂያ  በሙስሊማኑ ላይ ለመለጠፍ መሞከር: 2)የክርሰትና እምነት ተከታዮችን በማነሳሳትና ነገር በመቆስቆስ ጥላቻና በመዝራት በሙስሊም ወንድሞቹ ላይ ጥርጣሬና እምነት እንዲያጣ ለማድረግ መሞከር፤ 3)ሙስሊሞችን ለይቶ በማወቅና ስማቸውን በእኩይነት በማቅለም ፍርሃት እንዲያድርባቸው ማድረግ፤ ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር ማጋጨት፤ ሁሉንም የሕብረተሰብ አባል እንደሚጠሉና ለራሳቸው የሚሆን ዓለም ለመፍጠር የሚጥሩ በማስመሰል ሌላውን የሕብረተሰብ አካል በጥላቻ እንዲነሳሳባቸው ማድረግ፤እንዲሁም ለመወንጀል ለመያዝ በግፍ ለማሰርና ለማሰቃየት በመጨረሻም የሚመኘውን የሰውን ልጅ ክብር በማዋረድ ለመከራ መዳረግ፡፡ 4)መላው ሕብረተሰብ ላይ ያጠላበትን የመከራ የርሃብ የችግር የድህነት የኤኮኖሚና የፖለቲካ እጦቱን፤ሙስሊሙን ጂሃዲስቶች ናቸው በሚል ከንቱ የጉሮ ወሸባዬ ያልተቃኘ ዜማው በማደናቆር ሃሳብንና ቁጭትን ለማስለወጥ የተዘረጋ የኢህአዴግ ዲያብሎሳዊ አካሄድ ነው፡፡ 5) ጨርሶ ሙስሊሙ ሕብረተሰብ አስቦትና አንስቶት የማያውቀውን አስተሳሰብ የሙስሊም መንግስት ለማቋቋም፤ ቦምብና ሌሎች መሳርያዎች ለማንሳት እንዳቀዱ በማስመሰል ፕሮፓጋንዳውን እንደ የእድር የቀብር ጥሪ ቢያናፋም ቀብሩ የማን እንደሆነ ሕብረተሰቡ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ አልተቀበለው፡፡ እርግጥ ገዢው መንግስት የሕዝብን ቁጣና የበቃህ ስሜት በሚገባ ስለተረዳው በማድረግ ላይ ያለው አስተሳሰብንና አመለካከትን በማስቀየር ጊዜ መግዛትን ነው፡፡ የዓለም ባንክ ጥርት ያለው የ448 ገጽ ዘገባ፡፡

ይህንን የበሬ ክምር እበት በመመልከት ጊዜያቸውን ማጥፋት ለማይፈልጉ (ማየት ካለባቸህ ደግሞ አፍንጫችሁን ጠቅጥቁት) እንደዘጋቢ ፊልም ለማለፍ ቅንጫቢው እነሆ፡፡ የዶኪመንተሪ ቅልመዳ ትርኢት ሲከፈት መክፈቻውንና ማስረጃውን በጸሁፍ በማስቀደም ይጀምራል ‹‹ጥቂት ግለሰቦች የእስልምና ሃይማኖትን ከለላ በማድረግ፤የሥብር ተግባራቸውን ለመፈጸም ሲሉ ባደረጉት እንቅስቃሴ ላይ የቀረበ ማስረጃ፡፡ ከብሔራዊ ደህንነት አግልግሎት፤ ከፌዴራል ፖሊስ፤እና ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር የተቀነባበረ፡፡ ፊልሙ ማስረጃዎችን በመቅረብ እያንዳንዱ ተጠርጣሪ የእስልምና ሃይማኖትን መጋረጃ በማድረግ የአልቃይዳንና የአልሸባብን እቅድ በኢትዮጵያ ለመተግበር ያደረገውን እንቅስቃሴ ያስረዳል›› ይላል፡፡

ለ13 ሴኮንዶች ቀስ እያለ በጽሁፉ ምስል ይተካና ያለአንዳች ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ የአንድ ‹‹ሽብርተኛ›› ተብሎ የተፈረጀ ዜጋ ገጽታ በጥቁር ግድግዳ ፊት ለፊት ቀስ እያለ ተመለካቹን በሚያስደነግጥና በሚያስፈራራ መልኩ ለ8 ሴኮንዶች ብቅ ይልና እያዘገመ ወደ ቀኝ ይሄዳል፡፡ይህ በፎቶሾፕ ምስሉ የተቀነባበረውና ቆርጦ የተቀጠለው ሰው አውሬ፤በረኸኛን እንዲመስል ቃሉን በለሰለሰና በረጋ  መንፈስ ሙስሊም በሆኑና ባልሆኑ መሃል ‹‹ጂሃዲ›› ያለ ልዩነትና በሕብረተሰቡ ውስጥ የሌለ አመለካከት ለማስያዝ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ድራማ ነው፡፡ ይህን ዘጋቢ ያሉትን ማስረጃ ያዘጋጁት እርባና የለሾች እራሳቸውና የናጣቸውን የፍርሃት ድባብ በማቅረብ ለምን ሕብረተሰቡን የማይፈራውን ፍርሃት እንዲፈራ ያደርጉታል፡፡

‹‹ማስረጃ›› ተብሎ የሚደመጠው የያዘው ‹‹ኑዛዜ›› (በአብዛኛውከሁለት አለያም ከ3 አረፍ ተነገር ያልዘለለ፤ወንጀለኞች እንዲመስሉ ሆን ተብሎ የተቀነባበረባቸው ሆኖ ተከሳሦቹ የጥፋተኝነት እምነታቸውን ያረጋገጡበት ቢባልም በመርማሪው በኩል ምን እንዳለም ሆነ እንደጠየቀ አንዳችም ቃል አይሰማም) በአሜሪካን መንግስት የዓለም አቀፍ ሃይማኖቶች ነጻነት ኮሚሽን የተጠቀሱት 29 ተከሳሾች ዘገባ ግን ከተባለው አንዱንም አላካተተም፡፡ (እነዚህ ቃላቸውን ሰጡ የተባሉት ሰዎች ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያለ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ይኼው ፊልም ለሕዝብ እንዳይቀርብ ትእዛዝ ቢሰጥም ሰሚአጥቶ አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ አይነት እየተላለፈ ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ አሳፋሪ መንግስታዊ የፍትህ ጥሰት የት ይታያል? ከቃል አሰጣጡ የሙስሊም የሆኑና ሙስሊም ያልሆኑ ጂሃዲስቶች የኢ ቲ ቪ  ትርኢት ተከትሎ፤የቪዲዮ ቁራጭ ትእይንት ይከተላል፤ ወጣቶች (ሙስሊም አሸባሪዎች እንዲመስሉ ከሌላ ቪዲዮ ላይ የተቀነጨበ) ከአንድ ነገር ለማምለጥ ሲሸሽ ይታያል፡፡ ከኢንተርኔት የተለቃቀሙ ሌሎች ምስሎችም ተቆርጠው በመቀጠል፤በጭንቅላታቸው ላይ ስካርፍ ያሰሩና መሰወሪያ ፊታቸው ላይ ያከናነቡ በዓለም ላይ በተለያየ ወቅት ሽብርተኞች የተነሱትን ቪዲዮ መጠቀሚያ በማድረግ ቦታውና ጊዜው የማይታወቅ ፊልም ቀርቧል፡፡

የጽሁፍ መግለጫው ተከትሎ ይመጣና በድምጽም ‹‹ቦኮ ሃራም በኢትዮጵያ›› በሚለው ይታጀባል፡፡ ወጣት ኢትዮጵያዊያን በሰላማዊ መንገድ ለመብታቸው ተሰልፈው ይታያሉ፡፡ አንድ ወጣት ሙስሊምም በአንድ ቦታ ቆሞ ለተሰበሰቡት ‹‹ሙስሊሞች አሸባሪ፤ ወንጀለኞች፤ እና የሙስሊም መንግስት ለማቋቋም ይፈልጋሉ ተብለን ተወንጅለናል›› ይላል:: በርካታ ሰዎች ጥምጣም ያደረጉና መሳርያ ያነገቡ ሰዎች መልክና ሁለንተናቸው ጨርሶ ኢትዮጵያዊያን የማይመስሉ፤ አንድ ጢሙን ያጎፈረ ሰው ሲናገር ሌሎች ጉድጓድ ሲቆፍሩና መሳርያ ከተቀበረበት ሲያወጡ፤ ዓላማችን የሙስሊም መንግስት ለማቋቋም ነው በማለት ሲነጋገሩ ይደመጣል፡፡ ከዚሁ ጋር በመንግስት ‹‹ሽብርተኞች የሚል የማደናገሪያ ስም የተለጠፈባቸው የ29ኙ ተከሳሾች ምስል በቴሌቪዥኑ መስኮት ላይ ይመላለሳል፡፡ ይህም የሚነገረው ጉዳይ አባሎች ናቸው ብለን እኛ ተመልካቾች እንድናምን ሆን ተብሎ የተደረገ ቢሆንም ተመልካቹ ግን ከማመን ይልቅ በስህተት ልጆች ለጨዋታ ያቀነባበሩትን ፊልም መሰል ዝብርቅርቅ መጨረሻና መጀመርያ የሌለው በማለት በሚገዘው መንግስት ተራ ወንበዴነት አዝኖ ታዝቧል፡፡ በቃላትና ግድ የምታምኑትን እመኑ በሚል የማስገደጃ አካሄድ ቀረበ እንጂ ማስረጃ ተብሎ በምንም መልኩ ተቀባይነት አያገኝም፡፡ የግፍ ተከሳሾቹ ምስል ከየቦታው ተለቃቅሞ ሽብርተኞች፤ የሽብርተኞች ጥፋት በሚለው ቃል ብቻ በመታጀቡ ንጹሃኑ ያልሆኑትን ያደርጋቸዋል ብሎ የሚያምን ገዢ ዲክታተራዊ የቃዠ መንግስት ብቻ ነው፡፡

 

የሕግ የበላይነት ወይስ የመሃይሞችና የሕግ የበላይነት

የገዢው ፓርቲ ሰዎች በተደጋጋሚና አፋቸው በተከፈተ ቁጥር ምን ያህል ሕገመንግስቱን እንደሚያከብሩትና ለሕግጋቱም የቱን ያህል ታማኞችና ተገዢዎች እንደሆኑ ይቦተልካሉ፡፡ ባለፈው ሴፕቴምበር የፕሮፐጋንዳው ሂትለራዊው ሚኒስቴር በረክት ስምኦን ስለ መለስ መታመምና መሞት በየቀኑ ታላቁን የወቅቱን ውሸት ሲዋሽ ሲዋሽ ደሞ ሲቀላምድ ደሞ ሲቀላምድ፤ ችግር የሌላ መሆኑንና በሕገመንግስቱ መሰረት መተካካቱ እንዳለ ነው የሚለውን ያልተቃኘ ቱልቱላውን ሲነዛ ከረመ፡፡ እንደ መገናኛ  ሚኒስትርነቱ ስምኦን የ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት››ን መተላለፍ ያዘዘው እሱ ነው፡፡ ማንንም ሰው የሚያስገርመው ግን እነዚህ ለሕገ መንግስቱ መከበርና ልዕልና ቆመናል በማለት በየጊዜው ከበሮ የሚደልቁት ማን አለብን ባይ ዲክታተሮች እነዚህን የፈጠራ ክሳቸው በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያሉትን ንጹሃን ዜጎች ከችሎቱ አስቀድሞ እንዲህ አይነቱን ፓርቲያዊ የስልጣን ማክረሚያ ፍርዳቸውን ማስተላለፋቸው መብት መጣሳቸው መሆኑን አንገታቸው ላይ የተሰካው ቅል አያስታውሳቸው ይሆን? ድርጊታቸው የሼክስፒርን አባባል አስታወሰኝ፡፡ ‹‹ዲያቢሎስም ለራሱ መጠቀሚያ መጽሃፍ ቅዱስን ይጠቅሳል›› ያለውን፡፡ እነዚህ ሰዎች ያላዋቂ ሳሚ ናቸው ወይስ የሰይጣን ቁራጮች? ላለፉት በርካታ ዓመታት በተደጋጋሚ እንዳልኩት በኢትዮጵያ ላለው አረመኔ መንግስት ስለ ሕግ የበላይነት ማውራት ለዲያቢሎስ መጽሃፍ ቅዱስን እንደማንሳት ነው፡፡ አይግባቡምና፡፡  ሕገመንግስቱ እግር አውጥቶ እየዳመጣቸው እንዲገባቸው ሊያደርግ ቢሞክር እንኳን ጨርሶ ድንጋያማ ሕሊናቸው ተፈረካክሶ ያልቃል እንጂ አይገባቸውም፡፡

በ‹‹ሽብርተኘነት የተጠረጠሩት›› ሙስሊሞች ጉዳይ እና ‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት›› ላይ ቃላቸውን ሰጡ የተባሉት ጉዳይ ሊተኮርበት የሚገባው 3 ነጥብ አለ፡፡ 1) እነዚህ ተከሳሾ ቅድም ችሎት ታሳሪዎች ስለሆኑ በሕገመንግስቱ ላይ በተደነገገውና በሌሎችም ሃገሪቱ ከገባችባቸው ፍትሃዊ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች አኳያ መብታቸው ሊከበርላቸው ግድ ነው፡፡ 2) እነዚህ ተጠርጣሪዎች ቃላቸውን በፈቃደኝነትና በነጻ አለመስጠታቸውን የሚያረጋግጠው በካቴና ቀርቦ የነበረው ተጠርጣሪ ሲሆን ሌሎችም ቢሆኑ አያያዛቸውና ያሉበት ሁኔታ ሕጋዊ ስርአትን የተከተለ አለመሆኑ ይታወቃል፡፡ 3) ሁሉም 29 ታሳሪዎች የፖለቲካ እስረኞች ናቸው፡፡ ሕገመንህስቱን ለማክበር በሱም ለመመራት ጨርሶ ፈቃድ የሌላቸው መሪዎች፤የጣሳሪዎቹን ሰብአዊ መብት ያከብራሉ ማለት የማይሞከር ነው፡፡የሃገሪቱ መሪዎች ባላቸውና በሚያሳዩት ተግባራቸው ምን ያህል ከእውቀትና ከሰለጠነው ፖለተካ ጋር እንደማይተዋወቁ ነው በማሳየት ላይ ያሉት፡፡ እነዚህ ገዢዎች ከመሰረቱ ጀምሮ ከተንኮልና ከግፍ በደል በስተቀር አንዳችም ተግባር አለመፈጸማቸውንና ማንኛቸውንም ጉዳይ ይተገብር የነበረው የሞተው አለቃቸው እንደሆነ ሳያፍሩ በመናገር የራሳቸውን ብቃት የለሽ መሆን አውጀዋል፡፡ ማንም ተከሳሽ በፍርድ ሂደት ወንጀለኛ እስካለተባለና እስካልተፈረደበት ጊዜ ድረስ ነጻና ንጹህ ነው፡፡ በምንም መልኩ በግዳጅ የተገኘ ቃል ለማስረጃነት ሊቀርብ አይችልም፤ ድርጊቱም ዓለማቀፋዊ ድንጋጌዎችን ያልተከተለ ነው፡፡ ሰብአዊ መብትን ይገረስሳል፤ የፍትህን የበላይነት ይቃረናል:: 4) በጣም የሚያሳዝነው ቀልድ ደግሞ ፍርድ ቤቱ በኢቲቪ እና በሬዲዮ ድርጅቶች ላይ ያን የተቀነባበረና ቆርጦ የተቀጠለ የማፍያ አካሄድ ጨርሶ እንዳይተላለፍ ያስተላለፈውን ትዕዛዝ፤ እነማን አለብን ‹‹እኛው የፈጠርነው ዳኛም ሆነ ችሎት ሊከለክለን አይችልም›› በማለት ትእዛዙን ጥሰው ሲያስተላልፉት፤ በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ መሰረት ባለመፈጸሙና አግባብም ስላልሆነ የቀረቡትን ማስረጃ የተባሉትን ሁሉ አመኔታ ስለማንሰጣቸው ተቀባይነት አይኖራቸውም›› በማለት እንኳን ዋጋ ቢስ በማድረግ ፈንታ ችሎቱና በችሎቱ ወንበሮች ላይ የተጎለቱት እራሳቸው እርባና ቢስ ሆነዋል፡፡

ተስፋ የቆረጠ አምባገነንነት እና የዕጣቢ መውረጃ ቱቦ ፖለቲካ በዚህ ዶኩመንታሪ በኢትዮጵያ ያሉት ጨቋኝና ርህራሄ ቢስ ገዢዎች ከምንም በታች አዘቅዝቀው ወርደው ውረደታሞች መሆናቸውን ገሃድ ከማውጣታቸውም አልፎ የዝቃጭ መፈሰሻ  ቱቦ ፖለቲከኛነታቸውንም ይፋ አድርገዋል፡፡ አንድ ብቸኛ ሆኖ ሊታይና ሊረጋገጥ የሚችለው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሽብርተኛ እነሱ ገዢዎቹ ብቻ መሆናቸው ነው፡፡በ‹‹አኬልዳማ ገዢው መንግስት ሆነ››ባለው መሰረት በአሸባሪዎች 131 ጥቃት ተፈጽሟል፤339 ዜጎች ተገድለዋል፤363 ቆስለዋል፤25 ደግሚ ተጠልፈው ለሞት ተዳርገዋል:፡ ይሁንና በራሱ በመለስ ዜናዊ ይሁንታ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን እንዳጣራው  ምርጫ 2005ን ተከትሎ በጥቂት ቀናት ውስጥ በመለስ ዜናዊ አመራርና ትዕዛዝ መሰረት፤ 193 ሰላማዊ ዜጎች አንዳችም መሳርያ ያልነበራቸው 193 ሲገደሉ፤763ቱ ደግሞ ለከፍተኛ ቁስለት ተዳርገዋል፡፡ ኮሚሽኑ ባረጋገጠው መሰረት የስለላ ሰራተኞችና የመንግስት ጦር አባላት አተኳኮሳቸው ሰልፉን ለመበተን ሳይሆን ለመግደል በመሆኑ ሁሉም አናታቸውንና ደረታቸውን እየተመቱ ነው የሞቱት፡፡ በሴፕቴምበር 2011 ዓለም በሙሉ የኢትዮጵያ የደህንነት ሰዎች፤ በሴፕቴምበር 16 2006 በአዲስ አበባ ከተማ 3 ቦምቦች አጥምደው ካፈነዱ በኋላ ፍንዳታውን የፈጸሙት ኤርትራዊያንና የኦሮሞ ነጻ አውጪ ድርጅት አባላት ናቸው በማለት ሰበብ አድረጓቸዋል:: በዚህም ፍንዳታው የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ለስብሰባ በመጡበት ወቅት መከናወኑ የጉዳዩን ተአማኒነት አጣጥሎታል፡፡  አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ጉዳዩን በራሱ ባለሙያዎች ካስመረመረውና ካጣራ በኋላ ጣቱ የጠቆመው ወደ ኢትዮጵያ መንግስት ሆኗል፡፡ ገዢዎቹ ስልጣን ወንበር ላይ ከተፈናጠጡ ጀምሮ የተካሄዱት ግድያዎች ቢቆጠሩ ከብዙ ሺሆች በላይ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ መንግስት ነኝ ባዩ በራሱ አፈንድቶ፤ አጥምዶ፤ ደብቆ፤ አግኝቶ ያፈነዳውን አድራጊዎቹ ሌሎች ናቸው ብሎ አመልካች ጣቱን ወደ ሌሎች ሰዎች ሲዘረጋ ሌሎቹ ሶስቱ ያቶች ወደ ራሱ ማመልታቸውን መገንዘብ አልቻለም፡፡

ጂሃዳዊ ሃረካት የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ስም ለማጥፋት፤ለመኮነን፤ለማዋረድ፤ለመከፋፈል፤ ሆን ተብሎ የተፈበረከ ነው፡፡ ለዘመናት ጸንቶ በፍቅርና በመተሳሰብ የኖረውን የሁለቱን ሃይሞኖቶች ሂደት ለመበጥበጥ የተቀመመ መርዝ ነው፡፡ እዚህ ግባ የማይባል ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ በዚህም ሊፈጠር የተሞከረው በሙስሊሙና በእስልምና ሃይሞኖት ተከታዮች መሀላ መለያያት ለማስረጽ ነው፡፡ ከዚህም ሙስሊሙን ዳግም ወደ ፖለቲካና መብት ጥየቃ እንዳይነሳ፤ በፍርሃት ለማሰር፤ለመወንጀልና ለማሰር መንገድ ለመክፈት ከኤኮኖሚ፤ ህብረተሰባዊ ግንኙነት፤ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለመለየት የታቀደ ማስደንበሪያ ነው፡፡‹‹ጂሃዳዊ ሃረካት እስልምናን የመፍራትና ደንብሮ የማስደንበር፤ ፈርቶ የመስፈራራት፤ ያለቀንና የበቃውን የገዢነት ስልጣን የማቆያ ዘይቤ ነው፡፡ አይሆንም አልሆነም ይልቅስ ሁሉንም ያስተባበረ የገዢዎች ግፍ ሆኗል!

በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ!

*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):

http://open.salon.com/blog/almariam/2013/02/15/ethiopia_the_politics_of_fear_and_smear

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::) ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

Leave a Reply