Skip to content

St. George Brewery workers complain about unfair treatment

Workers of the famous St. George Brewery in Ethiopia complain about unfair treatment by the management and head of their own labor union. The following report is sent to ER by Getabicha Anteneh from Addis Ababa.

PDF

የቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካና የሠራተኞቹ ማኅበር

ጌታብቻ አንተነህ – አዲስ አበባ

ከብዙ ዓመታት በፊት የተመሠረተው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ በዓለም ለታወቀው የፋብሪካ ባለቤት ለሚስተር ካስቴል (Castel Winery) ተሸጦ የግል ድርጅት ከሆነ ጊዜ ጀምሮ በታወቁ የአገር ልጆችና የውጭ አገር ባለሞያዎች እየታገዘ በጥቂት ዓመታት ውስጥ አንድ የቢራ ፋብሪካ መድረስ ወደሚችልበት ደረጃ ከመድረሱም አልፎ ኢንተርናሺናል ይዘትን የተላበሰ ምርቱን ለዓለም ገበያ በማስተዋወቅ ኤክስፖርት በማድረግ ከፍተኛ አመርቂ ውጤትን አስመዝግቦ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ ወደ ግል ሀብትነት ሲዛወር ግን በሠራተኛ መህበሩ ድክመት ብዙ ዘመን ያገለገሉ ሠራተኞችን ያለበቂ የአገልግሎት ካሣ ክፍያና ለአንዳቸውም የጡረታ መብታቸውን ሳያስከብርላቸው በቅነሳ መልክ ማሰናበቱ ቅር የሚያሰኝ ክስተት ነበር፡፡ ለጡረታ አንድ ዓመት ብቻ የቀራቸውን አንድ አዛውንት የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ አግኝቶ ሲያነጋግራቸው ለፍተን ደክመን ሜዳ ላይ ወረወሩን ያሉትን በሀዘኔታ ያስታውሰዋል፡፡ የነዚህ ሠራተኞች ጉዳይ በፍርድ ቤት ተይዞ እስከዛሬ እልባት ሳያገኝ በእንጥልጥ ላይ ነው፡፡

የሠራተኛው ማህበር ከድርጅቱ አመራር ጋር እጅና ጓንቲ ሆነው ይራመዳሉ ቢባልና በየጊዜው የሚከሰተውን የኑሮ ውድነት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ሠራተኛው አንዳንድ ጥቅማ ጥቅሞችን በተወሰነ መልኩ አልፎ አልፎ ቢያገኝም የሠራተኛ ማህበሩ ሊቀመንበር ዶክተር ብርሃኑ የድርጅቱ የሥራ አመራር አባል (የማናጅመንት አካል) ሆነው መገኘታቸው ድርጅቱ በተመቸው መልኩ የሚያቀርባቸው የማሻሻያ ሃሰቦች ምንም ክርክር ሳይገጥማቸው ይተገበራሉ፡፡ ምናልባትም ለሠራተኛው ትክክለኛው ተከራካሪ ቢኖርለት ኖሮ በደሞዝም ሆነ በሌላ ጥቅማ ጥቅሞች የበለጠ መሻሻል ሊገኝ እንደሚችል እንደማያጠያይቅ የብዙ ሠራተኞች እምነት ነው፡፡

የማህበሩ ሊቀመንበር የማናጅመንቱ አካል ሲሰበሰብ አብረው ተሰብስበው በአብዛኛው ለድርጅቱ ጥቅም በሚሆነው ላይ ተስማምተው ወስነው ይወጡና ምናልባትም ያ ውሳኔ ሠራተኛውን የሚያነጋግር ሆኖ ሲገኝ የማህበሩን ሃላፊዎች ሰብስበው እራሳቸው ተስማምተው በወሰኑት ጉዳይ ላይ ሲተቹ መገኘታቸው በጣም የሚያስገርም ነው፡፡

ልከክልህ እከክልኝ ስለሆነም ከእሳቸው ጋር የጥቅም ተጋሪ የሆኑ የሠራተኛው ማህበር አንዳንድ አካላት ምርጫ በደረሰ ቁጥር ዶክተሩ እንዲመረጡ የሚያደርጉት የቅስቀሳ ሩጫ በጣም አስገራሚ ነው፡፡

ሌላው የሚያስደንቀው ሁኔታ ደግሞ በየዓመት በዓሉ መህበሩ ለሠራተኞች ስጦታ ሲያደርግ ከኪሳቸው አምስት ሳንቲም ስንኳ መዋጮ ለማይከፍሉትና ከድርጅቱ ከፍተኛ ጠቅማ ጥቅም ለሚያገኙት የማናጅመንት አካላት በጠቅላላ በሺ ብር የሚቆጠር ስጦታ መበተኑ የብዙዎችን አንጀት የሚያበግነው ነው፡፡ ከሠራተኛው ማህበር ይህ ገንዘብ ወጪ ሆኖ መሰጠቱ መደለያ ወይንስ ርካሽ የመወደጃ ዘዴ ??? ሊገባን አይችልም፡፡

በተለይም ደግሞ የሠራተኛው ማህበር ሊቀ መንበር ከአስተዳደር መምሪያ ሃላፊው ጋር የድራፍት ቤት ከፍተው ስለሚነግዱ በሠራተኛው በኩል የሚቀርቡ የበደል አቤቱታዎች በሁለቱ አካላት አመራሮች እንዴት እንደሚገመገም ለመገመት አያዳግትም፡፡

በመሠረቱ ሊቀመንበሩ የተማሩና የማናጅመንቱ አካል እንደመሆናቸው በዚህ ስልጣን ላይ ልቀመጥ አልችልምና የሚሆናችሁን ምረጡ ብለው በፈቃዳቸው ቦታውን መልቀቅ ነበረባቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ ቦታ መቀመጣቸው በሠራተኛው ጫንቃ ላይ ተፈናጠው ከፍተኛ ጥቅም ይቀራመታሉና ይህን እርምጃ ለመውሰድ ድፍረቱም ህሊናውም ሊኖራቸው ይችላል ብለን አንገምትም፡፡

ለመሆኑ የማናጅመንት አባል የሆነ በሠራተኛው አዋጅ መሠረት የሠራተኛውን ማህበር በሊቀመንበርነት ሊመራ ይችላልን? ለዚህ ትክክለኛውን ምላሽ የሚሰጠን ከተገኘ በቅድሚያ ምስጋናችንን እንቸረዋለን፡፡

የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ጃንፖል ቢላቭየ ምንም አንኩዋን ሲቆጡ በመጮህ ይናገሩ አንጂ በሰብአዊ ርህራሄ የተሞሉ የሠራተኛን ጉዳት ፈጽሞ ለማየት የማይሹ ለማንኛም ችግር የተጋለጠን ሠራተኛ የህብረት ስምምነቱ ሕግ ቢከለክልም የብዙ ወራቶችን ደሞዝ በየወሩ በመጠኑ ከደሞዙ እየተቆረጠ በረጅም ጊዜ ክፍያ እንዲያጠናቅቅ የሚፈቅዱ ሠራተኛው በሚያከብራቸው በዓሎች ላይ እየተገኙ የሠራተኛውን ደስታ የሚካፈሉ በመሆናቸው ዶክተር ብርሃኑ የማህበራችን ሊቀመንበር ሆነው ከሚመሩን ሚስተር ጃንፖል ሊቀመንበር ቢሆኑልን ብዙ ጥቅም እናገኝ ነበር የሚለው የለበጣ አስተያየት የብዙዎች ሠራተኞች ነው፡፡ አይቻልም አንጂ፡፡

ሠራተኛው በማይገባን አይነት ፍርሀት ተሸብቦ መብቱን ማስከበር እንዳይችል ያሰረው ምን እንደሆነ ልንረዳው አልቻልንም፡፡ ሠራተኛው በፍርሃት የተሸበበው ዶክተሩ የዚያ ክልል ሰው በመሆናቸው ይሆን ? ብለን እንጠረጥራለን፡፡ ቢሆንም አመራር ላይ መቀመጥ የማይገባቸውና በጥቅም የታወሩ ግለሰቦች ተገቢ ባልሆነ መንገድ የያዙትን ቦታ እንዲለቁ የማድረጉ ትግል የእያንዳንዱ ሠራተኛ መብቱና ግዴታውም መሆኑ ታውቆ ይህ ባህል እንዲዳብር በምንችለው መንገድና ዘዴ ዲሞክራሲያዊ የሆነውን መንገድ ሁሉ መጠቀም ይኖርብናል እንላለን፡፡

ድርጅቱ ከሚሰጠው ጥቅማ ጥቅሞች መካከል ተሸጦ ብዙ ሺ ብር የሚያወጣው የገብስ ጭማቂ የሠራተኛው ማህበር ሊቀ መንበር ዶ/ር ብርሃነ ባቋቋሙት የአክሲዮን ሂሳብ ውስጥ ፈሰስ ስለሚደረግ በዚህም አብዛኛው ሠራተኛ ተጠቃሚ ባለመሆኑ ሰሞኑን በድርጅቱ ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብን አስከትሏል፡፡ ይህን በተመለከተም ወደፊት በሰፊው እንዘግብላችኋለን፡፡

ጌታብቻ አንተነህ
አዲስ አበባ
[email protected]

One thought on “St. George Brewery workers complain about unfair treatment

  1. how could it be labour union chairman from the managemant memeber? maybe the person who is the labour union chair man is TPLF memeber, that is why he is above the law.only one solutionwe have to stand together and to win TPLF by any means pls. don’t listen Pro. mesfin.he don’t know poltical struddle. pro.mesfin start poltical just now , but Ethiopian people start from Haile selasie.

Leave a Reply