Seven Political Orgs agreed to form one National Party
Seven Political Organizations from inside and outside Ethiopia reached a memorandum of understanding to merge and form one National Party. Read the Memorandum of Understanding below (pdf)
Seven Political Organizations from inside and outside Ethiopia reached a memorandum of understanding to merge and form one National Party. Read the Memorandum of Understanding below (pdf)
የተከበራችሁ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን፤ የተለያዩ ድርጅቶች አመራርና አባላት፤
በቅድሚያ ኢሳት ይህንን የመወያያ መድረክ በማዘጋጀቱ በኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት አባላትና አመራር ስም ምስጋና እናቀርባለን።
የአገራችን ሁኔታ ከጊዜ ወደጊዜ እይተባባሰ፤ ጭቆናውና አፈናው፤ የዘር ማድዳቱና ግድያው እየበረታ ህዝባችን በአንባገነኖች ቀንበር እየማቀቀ ይገኛል። የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት መልኩን እየቀያየረ ህዝብን ረግጦ ሌላ 22 አመትና ከዚያም በላይ ለመግዛት መፍጨርጨሩን ቀጥሏል። የበደሉን ጥልቀትና ክብደት በጨመረው ቁጥር ሀይልና እድሜውን የሚያራዝምለት መስሎት እየበረታበት ነው። የሀገራችንንና የህዝባችን ጉዳይ የአደጋ ጫፍ ላይ ደርሷል ስንል አድማሱን አስፍቶ ሌላ አዲስና የከፋ ጫፍ ይፈጥርልናል።
ሌላውን 21 አመት ወደጎን ተተን ባለፈው አንድ አመት ብቻ እንኳን የትፈጸሙትን ወንጀሎችና ሰቆቃዎች ብንተነትን፤ ሊስቱ ረዥም በመሆኑና፤ ኢሳትና የተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን በየእለቱ እየዘገቡት በመሆኑ በሃገራችን ያለውን ሰቆቃ ያልተረዳ ኢትዮጵያዊ ይኖራል የሚል እምነት የለንም። በመሆኑም የሽግግር ምክር ቤቱ የዘመናት ችገሮችን ከመተንተንና ማለቂያ ከሌለው በወያኔ በተደጋጋሚ የሚወረወሩ አጀንዳዎች አዙሪት በመውጣት መፍትሄን መሰረት ያደረጉ ዘላቂና ስር ነቀል ለውጥ በሚያመጡ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ምክክሮች መደረግ አለባቸው ብሎ ያምናል።
የኢትዮጵያ ህዝብና የፖለቲካ ድርጅቶች የተለያዩ የትግል ስልቶችን በመጠቀም በአገር ውስጥና በውጭ በስርአቱ ላይ ጫና በማድረግ ላይ ናቸው። በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ታጋይ ድርጅቶች፤ ተቋማትና ግለሰቦች ሁሉ ያለውን ክብርና የትግል ትስስር ያረጋግጣል። ወደፊትም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሀይሉን አቀናጅቶ ይህንን ብልሹ ስርአት ከየአቅጣጫው በማዋከብ ለመቃብር እንደሚያበቃው ቅንጣት ያክል ጥርጥር የለንም። የዚህ ቻይና ትግስተኛ ህዝብ ብሶት በጫንቃው ከሚሸከመው በላይ ሲሆን ገንፍሎ እንደሚወጣ አጠያያቂ አይሆንም። የምናያቸውም ሁኔታዎች የዚህ ጠቋሚዎች ናቸው።
ጥያቄው ይህ ክስተት ይሆናል ወይስ አይሆንም ሳይሆን፤ ህዝቡ በቃኝ ብሎ ከዳር እስክዳር በሚነሳበት ጊዜ ምንድንነው የሚፈጠረው የሚለው ነው። ድህረ-ወያኔ አገራችን አላስፈላጊ ቀውስ ውስጥ ትገባ ይሆን? ጀግኖች ህይወታቸውን ያጡበትን ትግል አንዱ ጉልበተኛ ወይም ብልጣብልጥ መጥቶ ይነጥቀው ይሆን? ዛሬ የወያኔ/ኢህአዴግ ለ22 አመት በሰራው አገር አፍራሽ የጎሳ፤ የዘር፤ የሃይማኖት፤ የሃብት ከፋፋይ እኩይ ተግባር የተነሳ በህብረተሰቡ ውስጥ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አስቸጋር አይሆንም። ያለቅድመ ዝግጅት የሚደረግ የለውጥ ሂደት ምን ሊያስከተል እንደሚችል ይሀው ዛሬ በግብጽ እያየነው ነው።
ፕሪዚደንት ኦባማ በቅርቡ ግብጽን በተመለከተ ንግግር ሲያደርጉ ‘አንድ አገር ከአምባገነን ስርዓት ወደ ዲሞክራሲ በሚሸጋገርበት ወቅት ‘false start’ ወይም ደግሞ ‘የተሳሳተ አጀማመር’ ይኖራል ሲሉ ተናግረዋል። ችግሩ ታድያ እያንዳንዱ ‘false start’ ወይም ደግሞ የተሳሳተ አጀማመር የሚያስከትለው ውድ የደም ዋጋ በመኖሩ ነው። ህዝባችን ቢያንስ ቢያንስ በዚህ ስተተኛ አጀማመር ሊከፍለው የሚችለውን ዋጋ ሲቻል ማስወገድ ካለዚያም ለመቀነስ ስለድህረ ወያኔ የሽግግር ወቅት መምከርና እቅድ ማውጣት ይገባዋል እንላለን።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክርቤት ከተነሳበት አላማው ጋር በተዛመደ ይህንን አጀንዳ በአንክሮ ሲያሳስብ ቆይቷል። የተቃዋሚ ሀይሎች ትግሉን የጋራ ድሉንም የጋራ ለማድረግ ተቀናጅተው እንዲሰሩና በተለይም ይህንን ስርዓት በተባበረ ሀይል አስወግዶ ሁሉን አቀፍ በሆነ ህዝባዊ የሽግግር መንግስት ለመተካት የሚደረገው ሂደት ላይ ከአሁኑ ጀምረን መምከር ይገባናል። ይህንን አቋም በመያዝ ባለፈው ወር የመጀመሪያውን የምክክር ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ አካሂደናል። በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ የሲቪክና የሃይማኖት ተቋማት፤ ምሁራንንና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል። ስርዓቱን አስወግዶ ወደ ዲሞክራሲ መንገድ የሚወስድ ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ የሽግግር መንግስት ማቋቋም አስፈላጊነትና ምክንያቶቹን በዚህ ታሪካዊ ጉባዔና በተለያዩ መድረኮች ላይ ካቀረብናቸው ዝርዝር ጉዳዮች ዛሬም በጥቂቱ ዕንደሚከተለው መጥቀስ እንወዳለን።
ስርአቱ መወገድ አለበት ለዚህም ተባብራችሁ ታገሉ፤ ትግሉ የጋራ ድሉም የጋራ ይሁን የሚለዉን የአብዛኛዉን ህዝብ ጥያቄ ሰለሚመልስ
ከላይ የተዘረዘሩትን መሰረት ያደርገ ስምምነትና ትብብር፤ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ አስተማማኝ አማራጭ ሆኖ መቅረብ ያስችላል። በጁላዩ የምክክር ጉባኤ ላይ የሽግግር ምክር ቤቱ ያቀረባቸው ባለ 5 ነጥብ አማራጭ proposal የጉባኤው ተሳታፊዎች ተስማምተውበት የሚከተሉትን አብይ ጉዳዮች በመወሰን የተሳካ ጉባዔ ሆኗል።
1/ የሽግግር መንግስት የቅድመዝግጅት ኮሚቴ ተቋቁሟል
2/ የሽግግር ወቅት ቻርተር የሚያረቅ ቡድን ተቋቁሟል
3/ የወያኔን ስርዓት ለማስወገደ ሀገርአቀፍና ዓለማቀፍ የህዝባዊ እምቢተኝነት ዘመጃ እነዲታወጅና የህዝባዊ እምቢተኝነት ዘመቻውን የሚያቀነባበር ግብረሃይል እንዲቋቋም ተወስኗል።
የተቋቋመውም ኮሚቴ ሃላፊነቱን ለመወጣት ዕንቅሰቀሴውን በመጀመሩ ዛሬ በዚህ ስብሰባ ላይ የተገኛችሁ ወገኖች ሁሉ ታዋቂ ምሁራንና የድርጅት ተወካዮችን ያካተተው በጁላይ የምክከር ጉባዔ ላይ የተቋቋመውን የሽግግር መንግስት የቅድመዝግጅት ኮሚቴ በመነሻነት በመውሰድ የበለጠ እንድናጠናክረው ጥሪ እናቀርባለን።
ይህንን ስራ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክርቤት በሃላፊነት ይውሰደው እንጂ እያንዳንዱ ድርጅት፤ ተቋምና አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚሳተፉበት ጉዳይ መሆን ይገባዋል። በተለያየ አቅጣጫ የሚታገሉትን የተቃዋሚ ድርጅቶችንም በዚህ አጀንዳ ዙርያ ተባብረው እንዲሰሩ ህዝቡ ግፊት ያደርግ ዘንድ በዚህ አጋጣሚ እንጠይቃለን።
የሽግግር መንግስት ምስረታ ሂደት፤ የሽግግር ወቅት መመሪያ ሰነድ ማዘጋጀት ቀላል አይደለም። ነገር ግን እንዚህ ባለጉዳይ አካላት (stakeholders) ተሰብስበውና መክረው የመግባቢያ ሰንዳቸውን መንደፍና ለኢትዮጵያ ህዝብ የምንሄድበትን አቅጣጫ መጠቆም ይጠበቅባቸዋል። ይህ ነገ ችግር ከተፈጠረ በኋላ የሚሰራ ሳይሆን፤ ዛሬ ተሰርቶ ለህዝብ ቀርቦ፤ ህዝብ ተወያይቶበትና ተስማምቶበት የሚያጸድቀው የጋራ ሰነድ መሆን ይገባዋል። አሁንም በድጋሚ የምንጠይቀው ይህንን ከፍተኛ ሃላፊነት ለመወጣት በምናደርገው ጥረት ህዝቡ የጉዳዩ ባለቤት በመሆን ከጎናችን እንዲቆም ነው። በተያያዥ የሽግግር መክር ቤቱ ተመሳሳይና ቀጣይ ጉባኤ እንደሚያዘጛጅና ስለዝርዝር ጉዳይ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደምናወጣ መግለድ እንወዳለን።
ኢትዮጵያ ከፍተኛ እውቀት፥ የስራ ልምድና የሀገር ፍቅር ያላቸው እጅግ በርካታ ዜጎች ያፈራች አገር ነች። እንዴት ታድያ ህዝባችን ለእንደዚህ አይነት ግፍ፥ ሰቆቃና ውርደት ይጋለጣል? መፍትሄውም መልሱም ያለው እኛው ጋር ነው። በመሆኑም ስርአቱን በማስወገድና በመተካትና ዘላቂ የሆነ ውጤት ለማምጣት ከብዥታ የደዳ አቋም እነዲኖረን ባፅንዖት እገለድን ኢሳት ላደረገው ዝገጅት ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት አመራር
ENTC has issued a press release denouncing the recent massacre of our Muslim brothers and sisters in Arsi region and the ongoing brutal crimes of the TPLF/EPRDF regime around Addis Ababa and other cities.
The Ethiopian National Transitional Council (ENTC) has released the video of the consultative conference that was held July 2-3. The conference was focusing on the process of removal of the brutal dictatorial regime in Ethiopia and replacing it with an all-inclusive transitional government. The conference jump started the critical issue of the process of the formation of an all-inclusive transitional government with all the stake holders participation.
While the Ethiopian National Transitional Council (ENTC) was hosting a consultative conference on transitional government during the first week of July 2013, its chapters in Ethiopia were busy spreading the organization’s message.