Skip to content

Author: Elias Kifle

Woyanne’s desperation – Analysis by Tesfaye GebreAb

Tesfaye GebreAb analyzes the recent developments inside the Woyanne regime in Ethiopia, including the alleged coup plot, desperate measures against Amhara officers in the Woyanne army, Meles Zenawi’s possible retirement next year, who may take his place, etc.

[click here for PDF]
[Source: EMF]

የግንቦት ማስታወሻ

ከተስፋዬ ገብረአብ

እነሆ! ዛሬ ቅዳሜ ነው።

እለቱም ግንቦት 9፣ 2009።

ትናንት ደግሞ ግንቦት 8 ነበር። በአበሻ የዘመን አቆጣጠር ልክ የዛሬ ሃያ አመት ግድም “ጥቂት ጄኔራሎች” ኰሎኔል መንግስቱ ላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገው ነበር። ሳይሳካላቸው በመክሸፉ ዛሬ በህይወት የሉም። ማንኛውም አጥንት – አስከሬን ሆነዋል። አምላክ የጄኔራሎቹን ነፍስ ይማር። እኒያ ሰዎች ከነሙሉ ችግራቸው ከኰሎኔል መንግስቱ የተሻሉ ዜጎች ነበሩ ብዬ አምናለሁ።

ቀደም ሲል ደግሞ ጄኔራል መንግስቱ ነዋይ ጃንሆይን ለማስወገድ በመሞከራቸው የዚያ ዘመን ወጣት ትውልድ ጃንሆይን መንካትና መድፈር እንደሚቻል ትምህርት ማግኘት መቻሉ ይታመናል። ሰሞኑን ደግሞ ታሪክ ራሱን ለመድገም ሞከረ። የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ርእሰ አጀንዳ ሆኖ ሲያነጋግረን ሰነበተ።

እኔም ታዲያ ምንም ስንኳ የፓለቲካ ተንታኝ ባልሆንም፣ እንደ ጋዜጠኛነቴ በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየቴን በጨረፍታ ለማኖር ፈቅጄያለሁ። ለነገሩ ይቺን “ብጫቂ ወረቀት” የመጫር አሳብ የመጣው ከኔው አልነበረም። በፀጥታ ተቀምጬ፣ “የደራሲው ማስታወሻ” የሚል ስም የሰጠሁትን ቀጣይ መፅሃፌን እየፃፍኩ ሳለ የethioforum.org ዋና አዘጋጅ ክንፉ አሰፋ መስመር ላይ አገኘኝና፣

“የሰሞኑ ግርግር ላይ አስተያየትህን ለምን አትፅፍም?” ሲል ጠየቀኝ።

* * *

የሰሞኑን የመፈንቅለ መንግስት ግርግር ጉዳይ ከማንሳቴ በፊት ግን በዚህ ወቅት የማንም የፖለቲካ ድርጅት አባል አለመሆኔን ከወዲሁ መግለፅ ግዴታ ሆኖ አጊንቸዋለሁ። ቀደም ሲል የወያኔ አባል ለመሆን የበቃሁትም ባልጠበቅሁት ሁኔታ ከተራራ ወደ ሸለቆ እንደ ኳስ እየተጠለዝኩ መሆኑን በ“ጋዜጠኛው ማስታወሻ” አውግቼያችሁዋለሁና እሱን እዚህ አልደግመውም። ይህን ርእሰ ጉዳይ ማንሳት ያስፈለገበት ምክንያትም በቅርቡ ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ እየታማሁ በመሆኑ ነው።

በመሰረቱ በግንቦት 7 አባልነት መታማት የሚያኮራ ነው።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የመግባት ሃሳብ ቢኖረኝ ኖሮ ግንቦት 7 ከአማራጮቼ አንዱ በሆነ ነበር። ቅሬታዬን መግለፅ የፈለግሁትም የአብርሃ በላይ ድረገፅ አትሞት የነበረው አንድ ፅሁፍ ግንቦት 7ን ለማጥቃት ሆን ተብሎ በወያኔ ካድሬዎች የተፃፈ ሊሆን ይችላል ብዬ በመገመቴ ነበር። “የአድአው ጥቁር አፈር” በሚል ርእስ ኢትዮሚዲያ ድረገፅ ላይ የታተመው ፅሁፍ ከኔ በላይ ግንቦት7ን የሚያጠቃ ሆኖ ነበር ያገኘሁት።

በዚያን ሰሞን የፀሃፊውን ማንነት ለማወቅ ብዙ ጥረት አድርጌ ነበር። ፍንጭ የሚሰጠኝ ግን ጠፋ። ‘ያያ አባ ቦር’ በሚል የብእር ስም ግንቦት 7ን ከኔ ጋር ደርቦ በቃላት መድፍ ሲደበድበኝ የከረመው ፀሃፊ ለካስ የሩቅ ወዳጄ ኦቦ በፈቃዱ ሞረዳ ኖሮአል።

በፈቃዱ ሞረዳ በፃፍው መጣጥፍ እኔን ‘ወኔ ቢስ፣ፈሪ!’ ብሎ የቻለውን ያህል በሚያጥላሉ ቃላት ሲገልፅ፣ ራሱን ደግሞ ‘የግንባር ስጋ’ ወይም ‘ጀግና’ ‘እውነተኛ ጋዜጠኛ’ ሲል ገልፆአል። እዚህ ላይ ማንበቤን በማቆም ጥቂት ተክዤ ቆየሁ። በፈቃዱ ስለራሱ ጀግናነት በአደባባይ እስኪናገር ድረስ ርግጠኛ መሆን ከቻለ በውነቱ በጣም እድለኛ ሰው ሆኖ ይሰማኛል። ጀግና መሆን መልካም ነው። ሰዎች በምርጫቸው ፈሪ ሆነው አያውቁም። ለነገሩ የጀግንነትና የፈሪነት መለኪያዎች ከቶ ምን ይሆኑ? ስንት አይነት ጀግንነቶችስ አሉ? እና በፍቃዱ ሞረዳ ራሱን ጀግና ብሎ እኔን ወደ ፈሪዎች ቀበሌ የላከኝ በየትኞቹ መለኪያዎች ይሆን?

በፍቃዱ ከ1981 ጀምሮ እንደሚያውቀኝም ፅፎአል።

እውነቱን ነው።

ግጥሞቹን በጣም ስለምወዳቸው ራሴ ነኝ ፈልጌ የተዋወቅሁት። እኔ ከዚያ በፊት በስነ -ግጥሞቹ አውቀው ነበር። እሱም እንደኔው ሃረር ላይ ያቺኑ የፉገራ ፖለቲካ ተምሮ ነበርና እኛ ስንመረቅ በፍቃዱ የኢሰፓ ጋዜጠኛና ካድሬ ሆኖ መጣ። አዲሳባን እንጂ ጦርነትን አያውቃትም። ሃረር ላይ ግማሽ ሰአት ያህል ስነፅሁፍ ነክ ወሬ ተጨዋውተን ተለያየን። በዚሁ አበቃ። በፍቃዱ ሞረዳ ወደ አዲሳባ፣ እኔ ወደ አሰቃቂው ጦርነት ተለያየን። መልአከ ሞት ደግሞ ሬሳ በዝቶበት ነው መሰለኝ፣

“አንተን ለጊዜው አንፈልግህም” ብሎ ሳይወስደኝ ቀረ።

ደርግ ወድቆ አዲሳባ ስንገባ ከበፈቃዱ ጋር በድጋሚ ተገናኘን። አሁን ደግሞ ሁለታችንም ስደተኞች ነን። ከስደቱ በሁዋላ ወያኔን በጋራ እንታገለዋለን ብዬ ስጠብቅ በፈቃዱ ሞረዳ ፊቱን ወደኔ አዙሮ በባዙቃ ይደበድበኝ ያዘ። አብርሃ በላይም፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የበፈቃዱ ሞረዳን ፅሁፍ ከድረገፁ ነቅሎ ጣለው። እንዳልኳችሁ ግን “የግንቦት 7 አምባሳደር” ሆኜ አስመራ ልጓዝ እንደተዘጋጀሁ የሚገልፀውን የፈጠራ ፅሁፍ የፃፈው በፈቃዱ ሞረዳ ሊሆን ይችላል ብዬ አልገመትኩም ነበር።

ያን ሰሞን ታዲያ ለቀጣዩ መፅሃፌ ከበፈቃዱ ሞረዳ ውብ ግጥሞች፣ “ጀጎል” የተባለችውን ልጠቀምባት በማሰብ፣ “ጀጎል’ የተባለች ግጥምህን ላክልኝ” የሚል ኢሜይል ፃፍኩለት። በጀጎል ፈንታ በኔ ላይ ያለውን ጥላቻ የሚተርከውን ፅሁፍ በፒዲፍ አስሮ ላከልኝ። “የአደአው ጥቁር አፈር” መድፈኛ እሱራሱ እንደሆነም ነገረኝ።

በእውነቱ ወያኔዎች በዚህ ነው የሚበልጡን። የራሳቸውን ሰው በመደብደብ ሃይል አያባክኑም። በፍቃዱ ሞረዳ እኔን በመደብደብ ወያኔን ብቻ ነው ማስደሰት የቻለው። በርግጥ በፍቃዱ ወደ ኦነግ ስለ መግባቱ ያልተረጋገጠ ጭምጭምታ ወሬ ሰምቻለሁ። ወሬው እውነት ከሆነ ለገጣሚው ያያ አባ ቦር መልካም ትግል እመኝለታለሁ…

በዚያን እለት ምሽት ወደ ፕሪቶሪያ ደቡብ ነዳሁ። የከተማችን ደቡባዊ አቅጣጫ ኮረብታማ ነው። ገና ሙሉ በሙሉ አልመሸም ነበር። ባቡሮች የጉልበት ሰራተኞችን እየጫኑ፣ ፕሪቶሪያን እያቋጡ፣ በውበቱ ከቶውንም ተወዳዳሪ ወደሌለው ወደ ኩዋዙሉ ናታል ከፍለሃገር ይከንፋሉ። ኮረብቶቹ በጣም ውብ ሲሆኑ ጃኪቻን የተባለው የፊልም አክተር “…” የተባለውን ፊልም ለመስራት እኒያን ኮረብቶች ተጠቅሞባቸዋል። እዚያ ኮረብታ ላይ ወጣሁና ቁጭ አልሁ። ቁጭ አልኩ ብቻዬን።

በወርቃማው ዘመን ስለ ተፈጠሩት የሩስያ ደራስያን አሰብኩና ቅናት ሰቅዞ ያዘኝ። በአንድ ወቅት ሃያስያን ወደ ቶልስቶይ ቀርበው ስለ ቼኾቭ ጠይቀውት ነበር።

ሳያመነታ እንዲህ መለሰ፣

“ወደድኩም ጠላሁም አንቶን ቼኾቭ እንደሚበልጠኝ አመኜያልሁ!!”

* * *

የሆነው ሆኖ በፈቃዱ ሞረዳ ስለ ግንቦት 7 የገመተውን እንርሳውና እንደ አንድ የስነፅሁፍ ሰው በሰሞኑ አጀንዳ ላይ የግል እይታዬን ላውጋችሁ…..

ከትናንት በስቲያ ግንቦት 7 ነበር እለቱ።

መለስና በረከት የኰሎኔል መንግስቱ ርኩስ መንፈስ ምን ሹክ እንዳላቸው ባይታወቅም፣ እንደ መርዶ ነጋሪ በጠዋት ተነስተው፣ “ግንቦት 7 ወንበራችንን ሊሰርቅ ሲል ለጥቂት ያዝነው!!” ሲሉ በጩኸት ነገሩን።

አያያዘናም በረከት፣

“ለግንቦት 20 ሲያስቡን፣ ግንቦት 7 ላይ አስቀረናቸው” አለን።

በርግጥ በረከት እንደዚህ ሲል አልሰማሁትም። አይልም ግን አይባልም።

እንደዋዛ ከጀመርኩት ወግ ወዲያ ማዶ ታዲያ አያሌ መራራ አጀንዳዎች አሉ። በአስር ሺዎች የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ እስረኞች በየማጎሪያው የከፋውን ስቃይ እየተቀበሉ ይገኛሉ። ቴዲ አፍሮ አንዱ ነው። ብርቱካን ሚደቅሳ – ሁለት። ገመቹ አባቢያ – ሶስት። ገመቹን የሚያውቀው አለ? ምናልባት የምናውቀው ጥቂቶች ሳንሆን አንቀርም። የኦነግ ታጋይ ነበር። ወያኔ አስሮታል። ከናይሮቢ አፍነው ወሰዱትና አሁን የት እንዳለ አይታወቅም።

የስንቱ ስም ተዘርዝሮ ይቻላል?

በርግጥ የሹርሹራ ጓደኛ ስለሆነው ገመቹ በቀጣዩ መፅሃፌ በስፋት አወጋችሁዋለሁ። “ሹርሹራ ደግሞ ማነው?” ትሉ ይሆናል። ለማንኛውም ሹርሹራ በህይወት የለም። የወለጋ ምድር ላይ በክብር አርፎአል። እንግዲህ በየማጎሪያው ከተወረወሩት ወገኖቻችን መካከል እነ ጄኔራል ተፈራ ማሞ የዚህ ማስታወሻ መነሻና ማእከል ናቸውና ወደዚያው ልዝለቅ….

* * *

ወያኔ አብላጫ ቁጥር ባላቸው ብሄሮች መካከል እንዴት አክሮባት እየሰራ መዝለቅ እንዳለበት የቤት ስራውን የሰራው ደርግ ከመውደቁ በፊት እንጂ ትናንት አልነበረም። ቀድሞውንም በተዳከመ የግንኙነት ማእቀፍ ውስጥ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጣራው ተደርምሶበት፣ የሚያገናኙት የጋራ የስሜት ክሮች እየተበጣጠሱ አንዱ ለሌላው ጠላት በሚሆኑበት ጎዳና ላይ ሲደነቃቀፍ ዘመናት ባጅተዋል።

ጄኔራል ከማል ገልቹ ከ150 በላይ የታጠቁ የሰራዊት አባላትን አስከትሎ የኤርትራን ድንበር ሲያቋርጥ “የወያኔ ሰራዊት ፍፃሜ ተቃረበ!” ተብሎ ነበር። የጄኔራሉን መኮብለል ተከትሎ በረከት ሰምኦን በሰጠው ቃለምልልስ “ተገላገልን!” ሲል ነበር የገለፀው። ወያኔ ራሱን የሚያጠናክርበት በር ተከፈተለት። ከ20 ሺህ ያላነሱ ኦሮሞ ወታደሮች ከየጦር ክፍሉ ተመንጥረው ትግራይ ውስጥ ታሰሩ። በመቶዎች የሚገመቱ ኦሮሞ መኮንኖች ደግሞ ደሴ አካባቢ ወደሚገኝ ወታደራዊ እስር ቤት ተላኩ። መኮንኖቹን የተረከበቻቸው የእስርቤቱ ሃላፊ፣ ኮሎኔል ብራ የተባለች ነባር የህወሃት አባል ስትሆን፣ የአሉላ ክፍለጦር ኮሚሳር ከነበረችበት ጊዜ አንስቶ በጨካኝነቷ ትታወቃለች። ኮሎኔል ብራ የሃገር መከላከያ ከፍተኛ መኮንኖችን እርቃናቸውን አስቁማ ታስገርፋለች። እንደ ወይራ በጠነከረ የጎማ ዱላ ተደብድበው፣ፓራላይዝድ ሆነው ዛሬም ድረስ ማገገሚያ ጣቢያ የተቆለፈባቸው አንድ ሁለት መኮንኖችን አውቃለሁ።

መኮንኖቹ በግርፊያው ወቅት የተጠየቁት አንድ አጭር ጥያቄ ብቻ ነበር፣

“ከኦሮሞ ጄኔራሎች መካከል ከኦነግ ጋር ግንኙነት ያለው ማነው?”

ድብደባው ሲበዛባችው የአባዱላን ስም ጠሩ።

ኮሎኔል ብራ ወቀጣው እንዲቆም አዘዘችና ያገኘችውን “ምርጥ የምርመራ ውጤት” ለአለቆቿ አቀረበች። አለቆቿ ግን አባዱላ ዝንተአለም እንደማይከዳ ያውቁ ነበር።

ጄኔራል ከማል ሰራዊቱ ውስጥ በህቡእ ካደራጀው የኦነግ ደጋፊዎች መካከል ሲሶውን እንኳ ይዞ አለመውጣቱን ገልዖ ነበር። ይህ ለወያኔ እልል በቅምጤ ሆነለት። በዚያ ሰበብ ምንጠራውን ለማካሄድ በቂ ምክንያት አገኙ። ከጠረጋው በሁዋላ በጎደለ ለመሙላት በተደረገው የስልጣን ሽግሽግ ወያኔ ከአማራ የሰራዊቱ አባላት ድጋፍ ለማግኘት ጥቂት ሞካክሮአል። በዚያን ጊዜ አፍንጫ ሲመታ አይን ሳያለቀስ ቀረ።

ይህን ዘዴ ወያኔ ደጋግሞ ይጠቀምበታል።

ቅንጅት አዲሳባ ላይ በምርጫ ሲያሸንፍ በአንድ አዳር ፊንፊኔ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ሆና አደረች። በዚሁ ሰሞንም ኢህአዴግ አዳማ ከተማ ላይ ባዘጋጀው አንድ ግብዣ ላይ የኢህአዴግ አባላት በትግርኛና በኦሮምኛ ብቻ ጨፈሩ። አባዱላም የሚያምነው ታቦት ስላልነበረው በጠመንጃ ስም እየማለ ታሪካዊ ንግግር አደረገ። ግብዣው ላይ የነበሩ እንደሚተርኩት አባዱላ እንባው ባይኑ ቸፈፍ ብሎ፣

“ፊንፊኔ ወደ እናት ክልሏ እንደምትመለስ ህልም ነበረኝ!!” ሲል እንደ ማርቲን ሉተር ኪንግ ድምፁን ቢለቀው ዝቋላና ካካ ተራሮች ደግሞ ያንን በገደል ማሚቷቸው በኩል አገማሸሩት።

አባዱላ እንባውና ህልሙን አጣጥሞ ሳያበቃ መለስ ዜናዊ ጠርቶ፣

“ህልምህን ህፃናት የማይደርሱበት ቦታ አስቀምጠው። ለጊዜው ግን አዳማ ትቆያላችሁ” አለው።

ወያኔ ሁለቱ አብላጫ ቁጥር ያላቸውን ብሄሮች በተመሳሳይ ጊዜ አጥቅቷቸው አያውቅም። አንዱን ሲያጠቃ የሌላው ድጋፍ ስለሚያስፈልገው የፈረቃ ቁማር ይቆምራል። የህወሃት አባላትም ምንጊዜም ፍርድ ሰጪ ዳኛ ሆነው መካከል ላይ ይገኛሉ። የኮሜዲያን ክበበው ገዳ “ገብረመድህን” የተባለው ገፀባህርይ ለዚህ አባባሌ እንደ መልካም ማሳያ ሊጠቀስ የሚችል ነው።

የሰሞኑ፣ “የመፈንቅለ መንግስት ድራማ” ለአየር ከበቃ በሁዋላ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በቃለመጠይቁ ሲገልፅ እንደነበረው ከጄኔራል ከማል ኩብለላ በሁዋላ በሰራዊቱ ውስጥ በተካሄደው ጠረጋ የአገዛዙ ስርአት ዘረኛ አካሄድ ላይ ጥያቄ ያሳደሩ ምርጥ የሰራዊቱ አባላት በአብዛኛው እየታፈኑ ተሰውረዋል።

ወያኔን እንቅልፍ የሚከለክሉ የሰራዊቱ አባላት አንድ ባንድ እየተመነጠሩ ጥጋቸውን ይዘዋል። ሃይሌ ጥላሁን ሊጠቀሱ ከሚችሉት መካከል ነው። በሰሞኑ “የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ” ጣት ከሾለባቸው መካከልም ሃይሌ ዋናው መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ያወጋሉ። ዳሩ ግን ወያኔ በዚህ ጊዜ በቀጥታ ጄኔራል ሃይሌን ሊነካው እንደማይፈልግ የምናውቅ ከጥቂት በላይ ነን። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ጄኔራል ሃይሌን የተመለከቱ ጥቂት አስገራሚ ወጎች ነበሩ። በዚያን ወቅት የህወሃት ጦር ኮማንደሮች በከባድ መሳሪያ ግዢ ሰበብ በሚሊዮናት ዶላር ኮሚሽን እየበሉ የመሆናቸው ወሬ አየሩን በክሎት ነበር። ጄኔራል ሃይሌ ደግሞ እዚሁ ግዢ አካባቢ የተመደበ ባለስልጣን ነበር። እና ድምፁን ከፍ አድርጎ በስብሰባ ላይ እንዲህ ሲል ተናገረ፣

“እኔ እዚህ ተቀመጬ የሃገሪቱን ገንዘብ አትበሉም! ስትዘርፉ እያየሁ ዝም አልላችሁም!”

ጄኔራል ሃይሌ ከነታምራትና በረከት ጋር ኢህዴንን ከመሰረቱት ነባር ታጋዮች አንዱ ሲሆን፣ አዲስአበባ እስክትያዝም በኢህአዴግ ደረጃ ትግሉን የመራ ሰው ነው። በስብሰባ ላይ የህወሃት ኮማንደሮችን እንዲያ ከተናገረ በሁዋላ ግን የሃይሌ ጉዳይ ያለቀለት ሆነ። “ጡረታ!” አሉና አገለሉት። ጉዳዩ ተራ የእድሜና የአስተዳደር ጉዳይ ቢሆን ኖሮ፣ ሳሞራ የኑስ ቀድሞት ጡረታ ሊወጣ በተገባ ነበር። እነደሰማሁት ጡረታ ከወጣም በሁዋላ ሃይሌ አላረፈም። ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ፣

“እንተዋወቃለን!” እያለ ይናገራል አሉ።

እነ ሳሞራም “የትም አይደርስ” በሚል ችላ ብለውት ሰንብተዋል።

እንግዲህ በዚህ መረጃ ዙሪያ አንዳንድ ፍንጮችን ማሽተት የሚገድ አይሆንም። ዛሬ በመፈንቅለ መንግስት ወይም በሽብርተኛነት ስም ተይዘው የታሰሩት ከፍተኛና ጄኔራል መኮንኖች ከሃይሌ ጥላሁን ጋር ያላቸውን የጠበቀ ግንኙነት ወያኔም ሆነ የቅርብ የብአዴን አባላት አሳምረው ያውቁታል።

የመፈንቅለ መንግስቱን ወሬ እንደሰማሁ የሚፃፉትን ዜናዎችና ዜና ትንታኔዎች ለማንበብ ሞክሬ ነበር። ወያኔ ጉዳዩን ከመፈንቅለ መንግስት ወደ ሽብርተኛነት ሊለውጠው ለምን እንደፈለገ ገልፅ ነበር። “ሽብርተኛነት ክስ ለመመስረት የሚያመች ሲሆን፣ ባንፃሩ “መፈንቅለ መንግስት” የሚለው ግንቦት 7 የተባለውን ድርጅት ዝና ይበልጥ ከፍ ሊያደርገው ይችላል የሚል ስጋት አሳድሮባቸዋል። “ከሰራዊቱ እየተመነጠሩ ያሉት አማራ መኮንኖች የግንቦት 7 አባላት ናቸው ወይስ አይደሉም?” የሚለው ጥያቄም አከራካሪ አይደለም። ቢሆኑም ብርሃኑና አንዳርጋቸው፣ “አባላቶቻችን ናቸው!” ብለው ይነግሩን ዘንድ አንጠብቅም። ይህ ለታሪክ የሚቆይ ይሆናል። እንደምንሰማው ግን ከግንቦት 7 ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያልመሰረቱ፣ በአላማው ዙሪያ በራስ አነሳሽነት የተደራጁ ወጣቶች የክፍለ ሃገር ከተሞችን እያጥለቀለቁ ይገኛሉ። በየአካባቢው “ወንድም ጋሻ!” የመሆን የአርበኛነት ስሜት ተቀስቅሷል። ብርቱካን ሚደቅሳ እንደገለፀችው፣ አንድ አላማ በህዝብ ተቀባይነት ካገኘ የሚያደራጀውን አካል ሳይጠብቅ እንደ መንፈስ ይሰራጫል። ቀደም ሲል ለቅንጅት አላማዎች ህይወታቸውን የሰጡት አብዛኞቹ ወጣቶች በአባልነት የተመዘገቡ እንዳልነበሩ እናስታውሳለን። የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ሰለባ የሆነውን ሰፊ ህዝብ እንተወውና በዚህ ቀውጢ ወቅት ተፈራ ዋልዋ ራሱ የግንቦት 7 ደጋፊ ሆኖ ቢገኝ አይደንቀኝም።

ከመነሻው ብአዴኖች ውስጣቸው ጥሩ አለመሆኑን የውስጥ መረጃዎች አሉኝ። ከኢህአዴግ አራት አባል ድርጅቶች መካከል ክፉኛ ሞራሉ ተነክቶ በቀውስ ላይ የሚገኘው ብአዴን ነው።

ኦህዴድን በቀላል ቋንቋ ላስቀምጥላችሁ!

አመራሩ ንፁህ ወያኔ ሲሆን፣ አባላቶቹ ደግሞ በአብዛኛው የስራ እድል ለማግኘት ድርጅቱን የተቀላቀሉ በአመለካከት ወደ ኦነግ የሚቀርቡ ናቸው።

“ደቡብ ህዝቦች” በሚል ስም አባይ ፀሃዬ ያቋቋመው ድርጅት “አለ ይባላል በሳይንስ ግን አልተረጋገጠም” እየተባለ የሚቀለድበት፣ ዶክተር ካሱ ይላላ እንደፈለገ የሚያንገላታው ከሞቱት በላይ ያለ እቁብተኛ ነው።

ወደ ብአዴን ስንመጣ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ወድቀዋል። መለስ ዜናዊ እንደሚለውም ቀዩን የፈንጂ መስመር ረግጠዋል።

አመራሩን በጨረፍታ ላስጎብኛችሁ…

አዲሱ ለገሰ ከጤንነቱ መበላሸት ሁኔታ ጋር ተደማምሮ ስልጣን ላይ መቆየት እንደማይፈልግ ማመልከት የጀመረው ከሚሊኒየሙ ዋዜማ ጀምሮ ነበር። ተፈራ ዋልዋ፣ “የታገልነው ለዚህ አልነበረም!” እና “መምራት አቅቶናል!” የተባሉ ሁለት ነጠላ ዘፈኖችን ውስጥ ውስጡን ማንጎራጎር መጀመሩን በምሰማበት መንገድ ሰምቻለሁ። ህላዌ ዮሴፍ ቀድሞውንም “ከኢህአፓ መንፈስ አልተላቀቁም!” እየተባሉ ከሚታወቁት አንዱ ነበር። ህላዌ “ኢትዮጵያዊነት!” የሚል መንፈሳቸው ጠንካራ ከነበሩ የቀድሞ የኢህአፓ ትንታጎች አንዱ ነበር። የሽግግር መንግስቱ ስራ ከጀመረ በሁዋላ መለስ ዜናዊ፣

“ህላዌ ዮሴፍ ሆይ! አንተ አማራ ብቻ ነበርክ፣ አማራ ብቻ ሆነህም ትኖራለህ!! ስለሌላው አያገባህም!” ብሎት ሲያበቃ አረንጓዴዋን ቀንሶ በቀይና ቢጫ ቀለማት ያማረች ክራቫት አሰረለት። ከኢህዴን ላይ የተቀነሰችው አረንጓዴ ቀለም ሁመራ መሆኗም በሹክሹክታ ተናፈሰ። ጄኔራል ሃይሌ ጥላሁን ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ለይቶለታል። መኮንኖች ክበብ ብቅ ሲል፣ “እነዚህ የቀን ሌቦች፣ ተጫወቱብን!” ማለቱን ቀጥሎአል።

ከምርጫ 97 አንድ ወር ቀደም ብሎ መኮንኖች ክበብ ላይ በተደረገ አንድ ግብዣ ላይ ስብሃት ነጋ፣

“ነፍጠኛው ወደ ስልጣን ይመጣል ብሎ የሚያልም ካለ የዋህ ነው!” ብሎ ሲናገር ህላዌ ዮሴፍ የሚጠጣው ትን ብሎት ወደ መፀዳጃ ቤት መሄዱ ተሰምቶአል።

ብአዴን ማለት እንግዲህ እነዚሁ ናችው። ያልተጠቀሱ ቢኖሩ ታደሰ ጥንቅሹና በረከት ስምኦን ናችው። ታደሰ ብአዴን ውስጥ የህወሃት ትክል መሆኑ ነው የሚነገርለት። በረከት ያው በረከት ነው። በወያኔ ዘረኛ ፖለቲካ ውስጥ ገብቶ የወገኖቹን የስቃይ ጊዜ ከሚያራዝም፣ አንዴ ጎንደር ሌላ ጊዜ ቡግና ከሚንከራተት፣ “አማራ ነኝ!” እያለ በምድረበዳ ከሚጮህ፣ የጎንደር ልጅነቱን አክብሮ፣ በኢትዮጵያዊነቱ ቢፀና እንዴት ባማረበት?

የሆነው ሆኖ ከመነሻው ብአዴኖች ውስጣቸው ጥሩ አለመሆኑን ገልጫለሁ። ከአባላቶቻቸውና ከህዝቡ የሚመጣውን ግፊት ከቶውንም ሊቋቋሙት ተቸግረዋል። ብአዴኖች በህወሃት ላይ የቆየ ቅሬታ እንዳላቸውም “የጋዜጠኛው ማስታወሻ” ላይ መግለፄ አይዘነጋም። ብርሃኑ ነጋ ጠቁሞት እንዳለፈውም ሰራዊቱ ውስጥ ቁጣ አለ። የሰሞነኛው ግርግር ከግንቦት 7 ባሻገር የብአዴን ውስጣዊ ሁኔታ ላይ እንዳተኩር ያደረገኝም ብአዴን የወያኔን ዘረኛ ፖሊሲ እያስፈፀመ መቀጠል ከማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱ ይበልጥ ግልፅ እየሆነ በመምጣቱ ነው። ከበረከትና ከታደሰ ጥንቅሹ ባሻገር ያሉት የብአዴን የአመራር አባላት የጄኔራል ሃይሌ ጥላሁንን ቁጣ ቢጋሩ አይደንቀኝም።

“የጋዜጠኛው ማስታወሻ” የተባለውን መፅሃፍ በረከትና ተፈራ ዋልዋ እነዳነበቡት ሰምቻለሁ። በረከት ጠረጴዛ እየደበደበ፣ “ውሸታም!! የውሸት ክምር!!” አለ ተባለ። ተፈራ ግን፣ “የሚያውቀውን ፅፎአል” ማለቱን ሰማሁ። እኔን የሳበኝ ሁለቱ የጥንት ጓደኛሞች የሁለት አለም ሰው መሆን የመጀመራቸው ፍንጭ ነው።

ተፈራ አይኑን መግለጥ ጀምሮ ይሆን?

በርግጥም ሚስቱን እስከ ማሰር ሊደፍሩት የበቁበትን ምክንያት እንደ ተራ ስህተት የሚታይ ሊሆን አይችልም። ተፈራና አዲሱ ያሻውን ያህል የስልጣን ጥመኞች ቢሆኑም፣ የመከላከያ አባላቶቻቸውና የቀድሞ የትግል ጓዶቻቸው እንደ አይጥ እየተለቀሙ ወደ ኮሎኔል ብራ ሲላኩ ድርጊቱን በደስታ ሊያስተናገዱት ከቶ አይችሉም። ለዘመናት ውስጥ ውስጡን ሲበላላ የባጀው የብአዴንና የህወሃት ሽኩቻ ካለፉት ጊዜያት በላቀ ደረጃ ወደ ግጭት አምርቶአል።

ህወሃት ብአዴንን ለማዳከም ይህን ጊዜ ለምን እንደመረጠ መረዳትም ከባድ አይደለም።

ምርጫ 2010 እየቀረበ ነው።

የማጭበርበሪያ ሜዳው ከወዲሁ መደልደል እንዳለበት ግልፅ ነው። “ኢትዮጵያዊነት” የሚል ባንዲራ የሚያስቀድሙ ሃይሎችና የትጥቅ ትግል ያወጁ፣ ኦነግ፣አርበኞች፣የኦጋዴን ነፃ አውጪ የመሳሰሉ አማፅያን “የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች!” ተብለው ተፈርጀዋል። ወያኔ “የግንቦት 7” እና “የአንድነት” ፓርቲዎችን ሁለትነት አለማመኑም ግልፅ ነው። በቀጣዩ ምርጫ ወያኔ እንደለመደው ሊያጭበረብርና ጠመንጃ ሊጠቀም ሲሞክር የግንቦት 7 ትንታጎች መብረቅ እንዳያወርዱበት ሰግቶአል። ብአዴን ለግንቦት 7 የመፈልፈያ ጫካ ሊሆን እንደሚችልም ወያኔ ከምርጫ 97 በቂ ትምህርት አጊኝቶአል። እና ግንቦት 7 ወጣት ወታደሮቹን ይዞ የማይቀርለትን ፍልሚያ የሚጋፈጥ ከሆነ በርግጥም ማእከሉ መከላከያ ነው የሚሆን። የሰሞኑ የመፈንቅለ መንግስት ድራማ እንዲህ ሰፊና አሻገሮ የተመለከተ ስለመሆኑ ከቶ ምን ጥያቄ አለውና?

የብአዴን አመራር በበረከት ሰንሰለት ተጠፍሮ የታሰረ ተስፋ የቆረጠ አካል እንደመሆኑ በህወሃት የሚታዘዘውን የጎጥ አስተሳሰብ ተፈፃሚ የማድረግ ብቃቱን አጥቶአል። ይህ ማለት ግን ህወሃት አልቆለታል ማለት አይደለም። “ኢትዮጵያዊነት” የሚል ባንዲራ ያስቀደሙ ሃይሎች ሲበረቱበት አባዱላ ገመዳን ጠርቶ አንድ የቤት ስራ እንደሚሰጠው ከወዲሁ የሚጠበቅ ነው። አሁንም አፍንጫ ሲመታ አይን ካላለቀሰ ወያኔ ሊሳካለት ይችላል።

ወገኖቼ ሆይ!

ምን ቀረ?

ቀሪው ግልፅ ነው….

በቀጣዩ ምርጫ መለስ ዜናዊ ስልጣኑን እንደሚለቅ ነግሮናል። መለስ ቃሉ አይታመንም። አሳ የላሰው ድንጋይ ነው። በአሁኑ ንግግሩ “አሁንስ በቃኝ! እለቅላችሁዋለሁ!!” ማለቱን ግን እኔ በበኩሌ አምኜዋለሁ። መለስ በርግጥም ስልጣኑን ሊለቅ ወስኖአል። አማራጭም የለውም። ሁኔታዎችንና እድሜውን አስለቶ የቤት ስራውን ሰርቶ አብቅቶአል። ሆኖም ብቻውን እንደማይለቅም አስባለሁ። የፖሊት ቢሮ አባላቱን ሁሉ በትልቅ ዘንቢል ሸክፎ ዘወር ይል ዘንድ እንጠብቃለን። ይሁን እነጂ የዚህች ሃገር መከራ እዚህ ላይ ያበቃል ብላችሁ አትጠበቁ። የሚወራው እውነት ከሆነ አስመራ የተማረው ባለመነፅሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም መለስን ተክቶ ኢህአዴግን ሊመራ እጅጌውን ሰብስቦአል። የቅንጅት መሪዎች ከመፈታታቸው ቀደም ብሎ ስዬ አብርሃ ከእስር የተለቀቀበት የስምምነት ምስጢርም ያልተነካ ወሬ ነው። ህወሃት አንድ አስገራሚ ጠባይ አለው። ጥንካሬ ሲሰማው ርስበራስ ይባላሉ። ጠላት ሲበረታባቸው ደግሞ ልዩነታቸውን መሳቢያ ውስጥ አስቀመጠው ባንድ ሰልፍ ለውጊያ ይዘጋጃሉ። የስዬ አብርሃ በድንገት የመፈታትና የተቃዋሚ ንቅናቄ ውስጥ መገኘት የህወሃት ራስን የማዳን ስትራቴጂ አካል ስለመሆኑ የሚጠራጠር ካለም የዋህ ፖለቲከኛ መሆን ይኖርበታል።

ባጭሩ ቀጣዩ የሃይል አሰላለፍ በአንድ ወገን መለስና ቡድኑን የሚተካው ሃይል፣ በሌላ ወገን ደግሞ በስዬና በገብሩ የሚመራው ሃይል ይሆናሉ። ከዚህ ባሻገር ያሉ ሃይሎች እጣ ፈንታ ገብሩና ስዬን መቀላቀል አለያም መጥፋት ይሆናል። ስልጣን ከሁለቱ ሃይሎች እጅ እስካልወጣች ድረስም የህወሃት አላማዎች እንደተጠበቁ ይቆያሉ። ከዚህ ባሻገር መለስ ለግሉ የሚመኛቸው ጥቂት ነገሮች አይጠፉም። የሞ ኢብራሂም ሽልማት ቀዳሚው ይሆናል። ለገንዘቡ ሳይሆን ለክብሩ።

ይህ የወያኔ ሂሳብ ይሳካ ይሆን? ለማንኛውም ትግሉ ቀጥሎአል!…

* * *

እነሆ! ዛሬ ቅዳሜ ነው…

እለቱም ግንቦት 9፣ 2009።

ፕሪቶሪያ ቁጭ ብዬ እኔም ይቺን እጫጭራለሁ። የደቡብ አፍሪቃ ክረምት ከነጓዙ ገብቶአል። ዛሬ ጠዋት ከቤት ስወጣ ቆፈኑና ዝናቡ ፕሪቶሪያ ላይ እንደጉድ እየወረደባት ነበር። ያፍሪቃ መሪዎች አብዛኞቹ ፕሪቶሪያ ገብተዋል። ጃኮብ ዙማ መንበረ ስልጣኑን የሚረከብበት እለት ዛሬ ነው። የኛው አዛውንት ጋሽ ግርማም ገብተዋል። መኖሪያ ቤቴ ከቤተመንግስቱ ብዙም አይርቅ። እንደምንም እየተሹለከለክሁ ወደ ሰኒሳይድ አቅጣጫ ነዳሁ። አብዛኞቹ አበሾች እዚያ ቀበሌ ይኖራሉ። ሰኒሳይድ ውብ ናት። ሰኒፓርክ የተባለ አንድ ትልቅ የገበያ አዳራሽ አለ። እዚያ ገባሁና በረንዳው ላይ ቁጭ አልኩ።

ሰኒሳይድ በደስታ አብዳለች።

የዙሉ ጎሳ አባላት የቆዳ ልብስ ለብሰው ባህላዊ ጭፈራቸውን ያስነኩታል። እኔም ደስ አለኝ። ይህቺን መጣጥፍም መጫጫር ጀመርኩ። ሰጫጭር ቆየሁና ቀና ስል ለካስ አጠገቤ ካለ ጠረጴዛ ላይ አንዲት ነጭ ደቡብ አፍሪቃዊት ብቻዋን ቁጭ ብላለች፣

“ጋዜጠኛ ነህ እንዴ?” ስትል ጠየቀቺኝ።

ለማሳጠር ያህል፣

“ነኝ አዎ!” አልኩ።

“በምርጫው ስራ በዝቶባችሁ ከረመ?”

“እኔ እንኳ ደስተኛ አይደለሁም” አልኳት “….ምንም ስራ የለም። ምርጫው ቢጭበረበርና ግርግር ቢኖር ስራ ይኖረን ነበር..”

ቀልዱ ገብቶአት ሳቀች። እናም፣

“እናንተ ስራ ብታጡ ይሻላል” አለች።

በርግጥም ደቡብ አፍሪቃውያን ዛሬ ተደስተዋል። በጣም ተደስተዋል። ምርጫው በሰላም አለቀ። አልተጭበረበረም። እና ፕሪቶሪያ ደስ ብሎአታል። እንኳን ደስ ያላት።

አዲሳባስ ለዚህ አይነቱ የደስታ እለት የምትበቃው መቼ ይሆን?

(Tesfaye GebreAb can be reached at [email protected])

Ethiopia’s patriots wage a comeback

Elias Kifle (center) with officials of the Ethiopan People’s Patriotic Front, Arbegna Meazaw, chairman (left), Shambel Zewdu (right), Arbegna Mengistu (sitting).

By Elias Kifle

After being buried for several years, Ethiopia’s patriots, those who speak the kind of language anti-Ethiopia forces such as Woyanne understand, are slowly waging a comeback. I have been privileged to visit some of them when I went to Eritrea this month to interview President Isaias Afwerki. Due to scheduling conflicts, I could not go to their camp in the field this time, so they drove several hundreds kilometers to meet with me in Asmara.

After spending a few minutes with these patriots, I was more inspired than ever, and left with more determination and sense of responsibility to help free Ethiopia from the Woyanne tribal mafia that is pillaging and plundering our country.

One of those patriots I met is Shambel Zewdu. He is an elected member of the federal parliament from the Gaynt Woreda of “Killil 3” (the so-called “Amhara Killil”). Following the 2005 elections, when Meles Zenawi unleashed his killers on civilians, Shambel Zewdu told then Kinijit Chairman Hailu Shawel about his intention to join resistance fighters. He said I cannot bring myself to sit down in that ‘parliament’ and allow the murderers who gunned down 12-year-olds go unpunished. He also urged Ato Hailu Shawel to leave the country and lead the struggle from exile.

Shambel Zewdu then went on a 4-month journey through northern Ethiopian jungles and mountains to arrive at the Eritrean border. When Eritrean soldiers saw him, they hugged him with tears in their eyes, gave him food, clothes, medical treatment and shelter. After he recuperated, he asked them to take him to the Ethiopian People’s Patriotic Front (EPPF) camp. They tried to talk him out of it because of his old age. But he told them that he would kill himself if they don’t take him to EPPF.

For the past 4 years, Shambel Zewdu has been with the EPPF, first as a rank-and-file member and now a member of the central committee. Two months ago, the EPPF leadership transferred him to Asmara to run the newly opened office.

EPPF has numerous genuine Ethiopian patriots such as Shambel Zewdu who refuse to betray their people and country like those who are currently sitting in the Woyanne parliament and eat crumb. Their stories have not been told so far for various reasons. Ethiopian Review is determined to change that. Ethiopia is indeed blessed with heroes. We still have them. We just need to give them the chance to shine.

Ethiopia’s capital Addis Ababa turns dark

Most parts of Addis Ababa are currently out of electric light three days a week, according to Ethiopian Review sources. Several business are forced to shut down their operations.

Addis Ababa is also hit with shortage of water. Tens of thousands of houses are with out tap water. People are seen carrying water jugs in the streets.

Ethiopia’s capital is run by Meles Zenawi’s puppet named Kuma Demeksa who is busy doing his own business and taking money out of the country rather than administering the city. He is too dumb to administer a city any way.

Asmara, the cleanest city in Africa

We hope translation of the interview with President Isaias Afwerki will be completed by next Monday or Tuesday. The interview is 4 hours long and we want to make sure that the translation is as accurate as possible. Until then, here are more photos from the beautiful city of Asmara, the cleanest city in Africa. It is more clean and safe than Washington DC. By contrast, the savage Woyannes turned Addis Ababa, Ethiopia’s once beautiful and vibrant capital, into the 6th dirtiest city in the world, according to Forbes Magazine.

Roma Cinima, Asmara. It is amazing how clean Asmara is, even by Western standard

Asmara’s Merkato

Despite the military preparedness due to the ongoing state of war with the Woyanne regime in Ethiopia, there is a massive residential housing development in Asmara. This construction site is at the outskirt of Asmara. Many of the houses are being built by Eritreans residing in Europe and the U.S. and some of them look like mansions.

More housing development.

Elias Kifle of Ethiopian Review (middle), Sileshi Tilahun of EPPF (left), and Arbegna Mengistu of EPPF Radio (right) at a cafe in Asmara, May 12, 2009. Arbegna Mengistu joined EPPF 5 years ago as a fighter. Before that, he was a reporter for Wonchif Newspaper in Addis Ababa. He joined EPPF when Woyanne tried to arrest him for reporting about EPPF activities. After serving as a fighter and political officer for several years, he was recently transferred to the EPPF press office to work on producing a radio program. In one of the many gun battles with the Woyanne army he was hit with a bullet that now causes him to limp when he walks. EPPF is full of patriotic Ethiopians like Arbegna Mengistu who are shedding their blood to free Ethiopia from the Woyanne fascist regime.

Two indicted in killing of an Ethiopian businessman in Atlanta

Posted on

By Josh Green | Gwinnett Daily Post

ATLANTA – A Gwinnett County grand jury has indicted the second half of an alleged four-person robbing crew accused of killing an Ethiopian businessman in Lilburn, a suburb of Atlanta, Georgia.

Prosecutors say Marshae Brooks and Demarcus “Money Marc” Crawford played roles in the home-invasion murder of Tedla Lemma, 51. They allegedly beat, gagged and hog-tied the victim, leaving him for dead in March last year.

Unable to breathe through the gag, Lemma suffocated.

Brooks and Crawford face counts of murder, felony murder, burglary and false imprisonment. Brooks is also charged with armed robbery, kidnapping with bodily injury and aggravated assault stemming from three other incidents.

Last month, a jury convicted Brooks’ former roommate in Riverdale, Quincy Jackson, of murder and related charges in Lemma’s death. A judge sentenced Jackson to life plus 30 years. He plans to appeal.

Jackson, who had filed a speedy trial demand, was the first to face the charges in court.

A key witness in Jackson’s trial, Lorna Araya, is accused of masterminding the home invasions against members of the Ethiopian community she grew up in. Prosecutors agreed to not seek a life sentence for Araya in exchange for her testimony.

Brooks and Crawford were arrested earlier this year after Araya, incarcerated since July, told authorities they were involved.

As for the victim, Lemma lived in an upscale Lilburn home with his brother, after the two had fled their native Ethiopia and built a small fortune in the convenience store business. He was paralyzed from a store robbery and shooting several years prior.

Brooks and Crawford remain without bond at the Gwinnett County Jail. Their arraignments, wherein they could enter pleas, are expected within a month.

A fifth co-defendant, Ramon Ferguson, is charged in a December 2007 robbery and kidnapping in Stone Mountain. All but Crawford are said to have taken part in that hit, which involved owners of a Buckhead jewelry store.