By JERÉ LONGMAN, The New York Times
BEIJING — The women’s 5,000 meters has become less of an open race than a personal tug of war between Ethiopia’s Tirunesh Dibaba and Meseret Defar.
The women are neither enemies nor friends, but they are rivals. They trade Olympic gold medals and world records. They are in the same events, at the apex of their careers. There are only so many baubles to go around. Gold medals are not like pizza that can be divided into slices.
The rivalry turned decidedly in Dibaba’s favor Friday night as she completed a historic double, winning the 5,000 in 15 minutes 41.40 seconds and becoming the first woman to win the 5,000 and 10,000 in the same Summer Games.
As fast as the 10,000 meters was a week ago, the 5,000 was slow. The second lap took 92 seconds. A couple of 80-second laps were tossed into the middle of the sluggish 12 ½-lap race. At times, the runners seemed almost to be jogging in place.
Perhaps it would have been smart to challenge Dibaba early, to see if she had anything left in her legs after running the second-fastest 10,000 ever last week in 29:54.66.
But neither Defar, the 2004 Olympic champion in the 5,000, nor anyone took a chance. And the race played into Dibaba’s hands.
As usual, she won with her final-lap sprint, finishing ahead of Elvan Abeylegesse of Turkey, who took the silver in 15:42.74, and Defar, who said she was left in pain after being bumped and settled for bronze in 15:44.12.
“This was totally contrary to my thinking,” Dibaba, 23, said of the torpid pace. “I was expecting a faster pace. They didn’t do it. I can outkick them anytime, so I waited.”
Anyone expecting a thrilling duel would have been disappointed with the tactical dullness. But Dibaba did not apologize on this hot, humid night for running a minute and a half slower than her world record of 14:11.15, set in Oslo, Norway, in early June.
“I came here to represent my country,” Dibaba said. “The major object is to win.”
With two Olympic gold medals, a world record at 5,000 meters, four world track titles and four in the world-cross country championships, Dibaba can now lay claim to the mantle of world’s greatest female distance runner.
Perhaps she even deserves the title ahead of her cousin Derartu Tulu, a two-time Olympic champion at 10,000 meters who in 1992 became the first black African woman to win a gold medal at the Winter or Summer Games.
“I really don’t know, but I’m fighting for it,” Dibaba said.
Yet it is Tulu who commands a greater presence in Ethiopia. She is a pioneer who inspired many young runners, including Dibaba, and she has a more open, public persona, while Dibaba appears reserved and unforthcoming.
“In terms of achievement, yes, she might have surpassed Tulu,” said Elshadai Negash, a prominent Ethiopian track and field journalist. “But given that Tirunesh is so shy and withdrawn, she hasn’t been getting all the credit she deserves.”
Four years ago, Defar won the 5,000 at the Athens Games and Dibaba took the bronze. They train together before major international competitions. They both seem to have a social conscience. Defar is a goodwill ambassador to the United Nations Population Fund and has previously given her world-record bonuses to children’s charities. Dibaba supports a voluntary counseling and testing program for HIV/AIDS, which has ravaged Ethiopia.
Despite their common purpose, or because of it, the two runners keep a competitive distance between them. Even on the Web site of the International Associations of Athletics Federations, track and field’s world governing body, Defar insisted, “I only speak about myself and will only answer questions about myself.”
Two weeks after Dibaba set the 5,000 world record in June, Defar countered with a personal best of 14:12.88 in Stockholm, the second-fastest time ever run.
That set up what seemed to be an engaging Olympic final in the 5,000, which has been open to women since the 1996 Atlanta Games. But Defar was reluctant to set a fast pace, and so was everyone else.
“I was shocked,” said Kara Goucher of the United States, who finished ninth in 15.49.39.
The pace quickened in the later laps, but Defar never applied any real threat, saying that she had been bumped, leaving her limping and unable to unleash a kick. Dibaba ran the bell lap in 59 seconds and strolled home with the victory.
“She’s a sprinter, she’s beautiful to watch,” said Shalane Flanagan of the United States, who took 10th in 15:50.80, running on tired legs after winning a bronze in the 10,000. “And she’s got an innate ability to read everything on the track.”
2 thoughts on “Ethiopia’s Tirunesh outkicks rival to historic victory”
i love you trye.
አሳሳቢው የማራቶን ውጤት
Source: Reporter
እስከ አሁን ከተከናወኑ ኦሊምፒያዶች ከዝግጅቱ ጀምሮ ለየት ባለ ሁኔታ እየተካሄደ የሚገኘው ቤጂንግ ኦሊምፒክ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶችና ደጋፊዎች አስደሳችም አሳዛኝም እየሆነ ነው፡፡
አስደሳቹ በአስር ሺህ ሜትር ሴትና ወንዶች የተገኘው ውጤት ሲሆን፣ በዚሁ ርቀት ነገስን ስንል አሳዛኙን እንድናስብ እንገደዳለን፡፡
በአስር ሺህ ሜትር ወንድም ሆነ ሴት በተገኘው ውጤትና ለውጤቱ መገኘት ተጠቃሾች ጥሩነሽ ዲባባ፣ ቀነኒሳ በቀለና ስለሺ ስህን አያድርገውና ችግር ቢገጥማቸው ምን እንደምንሆን ስናስብ መልሱን ለጊዜው እንተዋለን፡፡
ለአንዳንዶች ስጋቱ ላይገባን የሚችል እንኖር ይሆናል፡፡ ነገር ግን ውጤቱ እንዲህ አምሮ እያየን ስለ 10ሺህ ሜትር ስጋት ስናስብ አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ ሮጦ ለአፍሪካውያን የአልሸነፍ ባይነትን መንፈስ እንዳጎናጸፈ፣ ውጤት ደረጃ ደግሞ ኢትዮጵያውያን እንደ ባህል እንደሚመለከቱት የከፈተው በር በአሁኑ ሰዓት እየተዘጋ መሆኑን ስናስብ በ10ሺህና አምስት ሺህምን ይህ ታሪክ እንዳይደገም ስለምንሰጋ ነው፡፡
ለኦሊምፒክ ጨዋታዎች ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ማራቶን ነው፡፡ በቤጂንግ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 29ኛው ኦሊምፒያድ የሴቶች ማራቶን ባፈለው ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ተካሂዷል፡፡ ኢትዮጵያን በመወከል ታዋቂዎቹ ጌጤ ዋሚና ብርሃኔ አደሬ እንዲሁም አትሌት ድሬ ቱኔ ተሳትፈዋል፡፡ ድሬ ቱኔ ውድድሩን 15ኛ ሆና ስታጠናቅቅ፣ ሲጠበቁ የነበሩት ጌጤና ብርሃኔ ግን እስከ 30ኛው ኪሎ ሜትር እይታ ውስጥ ገብተው፣ ከዚያን የአጨራረሳቸው ሚስጢር እንኳ በውል ሳይታወቅ ቀርቷል፡፡
ከቡድኑ ዝግጅት ጀምሮ በተለይ አትሌት ጌጤ ዋሚና ብርሃኔ አደሬ በግል አሰልጣኝ ከመሰልጠናቸው ጋር ተያይዞ ከዋናው ኦሊምፒክ ቡድን ጋር የተቀላቀሉት ቤጂንግ ኦሊምፒክ ሊጀመር አንድ ወር ሲቀረው እንደነበርና በፌዴሬሸኑ አሰልጣኞች ለረጅም ጊዜ ሰልጥነው በመጨረሻው ሰዓት እንዲቀነሱ የተደረጉ አትሌቶች ጉዳይ አይነተኛ መነጋገሪያ እየሆነ ይገኛል፡፡
በተለይ ከቤጂንግ አየር ጋር በተያያዘ ችግር እንዳይከሰት በሚል ተመሳሳይ አየር ወዳላቸው አገሮች አትሌቶቹ ሄደው እንዲሰለጥኑ ከተወሰነ በኋላ በአትሌቶቹ ፍላጎት ጉዞው መስተጓጎሉ ከሙያ አኳያ አነጋጋሪነቱ ትኩረትን ስቧል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ኦሊምፒኩን በበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንደ አገር ምንም ዓይነት የአሰራር መስመር እንዳልነበራቸው ሲነገር፣ በሁለቱም አካላት የቤት ሥራ የነበረው የቤጂንግ ልዑካን አባላት እነማን ይሁኑ” የሚለው እንጂ ስለዝግጅቱ ጉዳያቸው እንዳልነበረ ነው እየተነገረ የሚገኘው፡፡
ዶ/ር ሳምሶን ባዩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አባልና የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሲሆኑ፣ መቶ አለቃ መገርሳ ሁንዴ የ10ሺህና አምስት ሺህ ሜትር ረዳት አሰልጣኝ፣ የመከላከያ ክለብ አሰልጣኝና የመብራት ኃይል ክለብ አሰልጣኝ መቶ አለቃ ግርማ ወልደሃና ባለፈው እሁድ ማለዳ በተጠናቀቀው የሴቶች ማራቶን ውጤትና የአትሌቲክስ አሰራርን በተመለከተ አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል፡፡
በሙያተኞች የተጠና ጥናትን መነሻ ያደረገ ልምምድ መደረግ የሚኖርበትን ቦታ መወሰን የአትሌቶች ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሲሆን፣ ከዚያ በላይ የሚመለከተው አሰልጣኞችን እንደሆነ የሚናገሩት ዶ/ር ሳምሶን ለአስተያየታቸው መነሻ ያደረጉት ብቸኛውን የቦክስ ተወዳዳሪ የነበረውን ጌታቸው ሞላን ነው፡፡ “አትሌቱን የሚከታተለው የሕክምና ሙያተኛ አብሮ መሄድ ሲገባው የማይመለከታቸው ወገኖች የቤጂንግ ልዑካን ሆነ በመጓዛቸው ተወዳዳሪው ከክብደት በላይ ሆኖ በመገኘቱ ከውድድር ውጭ ሊሆን በቃ፡፡
ይህ የሚያመለክተው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የቦክስ ፌዴሬሽኑ ከውድድሩ በፊት ምን መስራት እንደሚገባቸው እንኳ አለማወቃቸውን የሚያመላክት ነው”፡፡
የኢትዮጵያ ማራቶን ቡድን ከአመራረጡ ጀምሮ ችግር እንደነበረው የተናገሩት ዶ/ር ሳምሶን “ሁለቱ ታዋቂ አትሌቶች ጌጤ ዋሚና ብርሃኔ አደሬ ከዋናው ኦሊምፒክ ቡድን ጋር የተቀላቀሉት ቤጂንግ ኦሊምፒክ አንድ ወር ሲቀረው ነው፡፡ ከእነሱ ቀደም ሲል ከቡድኑ ጋር ልምምድ ሲያደርጉ የቆዩ አትሌቶች በመጨረሻው ሰዓት እንዲቀነሱ ተደርጓል፡፡ ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ችግሩ ከዚህ ይጀምራል፡፡ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ቡድኑ ከቤጂንሽግ አየር ጋር ተመሳሳይነት ወዳላቸው አገሮች ለልምምድ እንዲሄድ ተወስኖ በአትሌቶቹ ፍላጎት መቅረቱን ከሚዲያ ውጭ በግሌ የማውቀው ነገር የለም፡፡ ይህም የኦሊምፒክ ኮሚቴውንና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑን ግንኙነት መስመር የሌለው መሆኑን ያመለክታል” ብለዋል፡፡ አጠቃላይ አስሩም ሊገመገምና ሊጠና እንደሚገባው ገልፀዋል፡፡
በማራቶን ውጤት እየጠፋ ያለው የአትሌቶች መጥፋት ሳይሆነ አሰልጣኙና አትሌቶቹ የሚተዋወቁበት ጊዜ አጭር መሆኑ አንዱ ችግር ሲሆን፣ የዓለም ዋንጫና ኦሊምፒክ በደረሰ ቁጥር የይድረስ፣ ይድረስ መሆኑ ዋነኞቹ ችግሮች ናቸው የሚሉት መቶ አለቃ መገርሣ ሁንዴ በበኩላቸው፣ ባለፈ ነገር ከመወቃቀስ፣ ድክመቱ እንዳይደገምና በቀጣይ የተሻለ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በግልጽ መነጋገር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡
እየታየ ያለው ድክመት በማራቶን ብቻ እንዳልሆነ የሚናገሩት መቶ አለቃ መገርሣ “ማራቶን ከኦሊምፒክ እስከ ኦሊምፒክ ዝግጅት ያስፈልገዋል፡፡ በአገራችን እየተደረገ ያለው ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው፡፡ የልምምድ ጊዜው እጥረት እንዳለ ሆኖ ከአተሌቶቹ ጋር ረዘም ያለ የልምምድ ጊዜን የሚጠቀም አሰልጣኝ የለም” ብለዋል፡፡
እንደ መቶ አለቃ መገርሣ አስተያየት እንደየ አገሩ የውድድርና አየር ፀባይ ልምምድ መስራቱ ተገቢ ቢሆንም፣ የውስጥ አሰራሩ ከተስተካከለና ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አየር በጥናት ከተሰራበት ለአትሌቲክስ ውጤት ከየትኛውም አገር አየር የተሻለው አገር ውስጥ መስራቱ እንደሚሻል ገልፀዋል፡፡
አትሌቶች ከቤጂንግ አየር ፀባይ ጋር ተመሳሳይነት ወዳላቸው አገሮች ኮሪያና ጃፓን ሄደው ልምምድ እንዲያደርጉ ከተወሰነ በኋላ በአትሌቶቹ ፍላጎት እዚሁ እንዲሰሩ መደረጉ ከሙያ አኳያ ያላቸውን አስተያየትም ሲገልፁ “ጥናቱ የተደረገው በሙያተኞች እስከሆነ ድረስ ለልምምድ የተመረጡ ቦታዎች ያዋጡናል፤ አያዋጡንም የሚለውን መወሰን ያለበት አትሌቶቹ ሳይሆኑ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና አሰልጣኞቹ ናቸው፡፡”
የሆነ ሆኖ ግን አትሌቶቹ ወደ ኮከሪያና ጃፓን ሄደው ልምምድ ባለማድረጋቸው ውጤቱ ተበላሸ ወደሚለው ድምዳሜ ከመሄድ ይልቅ በቀጣይ ስለሚያከናውነው፣ አሰራሩ ምን መሆን አለበት በሚለው ላይ ማተኮሩ የተሻለ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
ከሙያተኞች ጋር በተያያዘ ስለሚነሳው ጥያቄና የአሰልጣኞች ምደባን በተመለከተ “አሰልጣኞችን የሚመድበው የፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ኮሚቴ ሲሆን፣ ምደባውን የሚያፀድቀው ስራ አስፈፃሚው ነው፡፡ ብቃት ወደሚለው ስንመጣ ደግሞ ጉዳዩ የሚመለከተው ቴክኒክ ኮሚቴው በመሆኑ ጥያቄውን አይመለከተኝም” ብለዋል፡፡
እንደ ግል አስተያየታቸው ግን አሰልጣኞች ሲመደቡ ቢያንስ በዘርፉ ያለፉ ቢሆኑ እንደሚመረጡ ገልፀዋል፡፡
በየውድድር ዓይነቱ እየተነሱ ለሚገኙ የተተኪ አትሌቶች ጉዳይ ሊታሰብበት እንደሚገባ የሚናገሩት አሰልጣኙ “አዲስ አበባን ብቻ ማዕቀፍ ያደረገው የአትሌቲክስ ስልጠና ወደ ክልሎች መውጣት አለበት፡፡ ብዙዎቹ አሰልጣኞች ወደ ክልል መውጣት አንፈልግም፡፡ የተተኪ አትሌቶች መገኛ ክልሎች መሆናቸው እየታወቀ አሰልጣኞች ጊዜያችንን የምናጠፋው፣ በራሳቸው ጥረት ደክመውና ጥረው ለብሔራዊ የሚመረጡ አትሌቶችን አሰልጣኝ ለመሆን ነው፡፡ እውነቱን መነጋገር ካስፈለገ አብዛኛው ተተኪ አትሌት በግሉ ጫካ ውስጥ በባዶ እግሩ ሲሮጡ ነው የሚውሉት፡፡
እነዚህ ነገሮች በፌዴሬሽኑም ሆነ አሰልጣኞች ትኩረት ከተሰጣቸው ብቻ ነው የተተኪዎች እጥረት ሊቃለል የሚችለው” ሲሉ አስተያየታቸውን አጠቃለዋል፡፡
በሴቶች ማራቶን የተመዘገበው ውጤት እጅግ እንዳሳዘናቸው የሚገልፁት የመብራት ኃይል ክለብ አሰልጣኝ መቶ አለቃ ግርማ ወልደሃና በበኩላቸው፣ ለውጤቱ አሰልጣኞቹ ብቻ ሊጠየቁ እንደማይገባ ይገልፃሉ፡፡
የቤጂንግ የመጨረሻው ቡድን ከመታወቁ ቀደም ሲል በርካታ ወጣት አትሌቶች ዝግጅት ሲያደርጉ ከቆዩ በኋላ ውድድሩ አንድ ወር ሲቀረው ከቡድኑ ጋር እንዲቀላቀሉ የተደረጉት አትሌቶች እድሉ ለወጣቶቹ እንዲሰጥ ጫና መፍጠር ሲችሉ ዝም ብለው ኃላፊነቱን ተቀብለው መሄድ እንዳልነበራቸው ይናገራሉ፡፡
“ቤተ መንግስት ገብቶ የ80 ሚሊዮን ሕዝብ አደራ መቀበል በቀላሉ ሊታይ አይገባም” ካሉ በኋላ፣ በተለይ የማራቶን አትሌቶች ምርጫ ወቅት ችግሮች እንደነበሩ ሲነገር የነበረውን አስተያየት እንደመነሻ ወስዶ ግልጽ ውይይት ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በአስር ሺህ ሜትር የተመዘገበው ውጤት አስደሳች ቢሆንም፣ የውጤቱ ተጠቃሾች ባይኖሩ የሚለው ትኩረት የሚያስፈልገው ጉዳይ መሆኑን የሚገልፁት አሰልጣኙ “ችግሩ ሊቃለል የሚችለው ክልሎችን መሠረት ያደረገ ሥራ መስራት ሲቻል ብቻ ነው” ብለዋል፡፡
በሴቶች ማራቶን ለተመዘገበው ውጤት ከዝግጅቱ እስከ አትሌቶች ምርጫ የነበረው ችግር ተጠቃሽነቱ ቅድሚያ ቢሰጠውም፣ የፌዴሬሽኑ አሰራር ከመነሻው ሊገመገመና ሊጠራ የሚገባው ተቋም እንደሆነ ነው በርካታ የዘርፉ ሙያተኞች አስተያየት ያመለከተው፡፡