Skip to content

Aleqa Ayalew Tamiru remembered

Today is the 3rd anniversary of the passing away of Ethiopia’s preeminent Orthodox Church scholar and religious father. His absence is deeply felt these days as Ethiopians are left with few leaders who dare to speak the truth and take stand against evil.

Click here to read a message from Aleqa Ayalew’s family and his brief biography.

Please also visit the web site his family has launched to make information about him accessible to every one: aleqayalewtamiru.org It contains some of the published and unpublished documents of Aleqa Ayalew.

Aleqa Ayalew was engaged in a running battle with Aba Gebre-Medhin (formerly Aba Paulos) over fundamental teachings of the Church. He had served as chairman of YeLiqawnt Gubae (council of scholars) until he was forced out by Aba Gebre-Medhin, the gun-totting illegitimate patriarch of the Ethiopian Orthodox Church.

8 thoughts on “Aleqa Ayalew Tamiru remembered

  1. This guy is unique, probably the last of Ethiopian great men. As a result of the greed in the Ethiopian Orthodox, he ended up being unsung heroe.
    Any one who wants to understand the division with in the Ethiopian Orthodox church and the participation of each high priest including those outside the country, You better find his tapes and listen to them. You will benefit by understanding what, why, when, where, which and all the question you have. Until you hear it, I wouldn’t give you a clue but it is a thriller.

  2. Let Aleka Ayalew’s soul rest in peace. He was a true child of the EOTC.

    By the way, recently we heard about the death of Megabi Biluy Sefe Silassie, also a member of ye-Likawunt Gubae of the EOTC. However, these two men left this world in a very different way. Aleka Ayalew was denied even the “Fitihate Tselot” service by Aba Paulos whereas Megabe Bily Seife S. departed while serving Aba Paulos. Can anyone explain to us the depth of the matter.

    Thanks.

  3. Aleqa Ayaleiw missed nothing by his last rite (fthat) done by poulos we dabilos. Aba dabilos sold his soul to lucefer. At this point of time aba dabilos is a test sent by God to Ehiopia Orthodox Church. Believe me this man’s (G/Medhn)soul is burning in side his body. Probably he is most remembered here in LA’s Vagabon Inn where he used to eat beccon cheese burger.

  4. ውድ የኢትዮጵያ ልጅ፤
    ለጥያቄህ በአጭሩ የማውቀውን ያህል ልገልጽልህ ወደድሁ። አለቃ አያሌው ታምሩ መላው ዕድሜያቸውውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለገሉ አባት ናቸው።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን የሊቃውንት ጉባኤ ለረጅም ዓመታት የመሩ ናቸው። የቤተክርስቲያኒቱን ህግና ሥርዓትም ጠንቅቀው የሚያውቁ፤ ቤተክርስቲያናችን ካፈራቻቸው ታላላቅ መምህራን መካከልም አንዱ ነበሩ። በዚህም ምክንያት የአባ ጳውሎስ አስተዳደር በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የሚያደርሰውን ጥፋት ለማለፍ አልቻሉም። በተደጋጋሚ ጥፋቱን ጥፋት ነው ብለው በግልጽ መናገራቸው ደግሞ ከሥራ ገበታቸው ያለጡረታ እንዲገለሉ አደረጋቸው።
    በምትካቸውም መጋቢ ብሉይ ሰይፈ ስላሴ ቦታውን እንዲይዙ ተደረገ። እንግዲህ እኔ እንደሚመስለኝ ዛሬ በኢትዮጵያ ወስጥ በቤተክርስቲያን አካባቢ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ቦታ መስለህ ከኖርክ መኖር ትችላህ። በመሆኑም መጋቢ ህሩይ በተሰጣቸው ቦታ ላይ ችግር የገጠማቸው አይመስለኝም። ለዚህም ነው በአሜሪካን ሀገር ይደረግ ወደነበረው የሁለቱ ሲኖዶሶች የሰላም ጉባኤ ላይ የሀገርቤቱን የአባ ጳውሎስን ሲኖዶስ ለመወከል ከተጓዙት ውስጥ አንዱ የነበሩት። ለዚህም ነው የቀብር ሥነሥርዓቱ ከአለቃ አያሌው የተለየ የሆነው። ለዚህም ነው በቀብራቸው ሥነሥርዓት ላይ አቡነ ጳውሎስ ስለ መጋቢ ብሉይ ሰይፈስላሴ ጠባየ ሸጋነት በሰፈው እንደገለጡ የተዘገበው።

  5. ትንቢተ አያሌው

    ከኢትዮጵያ በላይ

    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የነበራትን ክብርና ማዕረግ ጥላ ቁልቁል መሄድ ከጀመረችበት የደርግ ዘመን አንስቶ እስከዛሬ ድረስ ያለውን ታሪኳን ብንመለከት በየዕለቱ ዝቅ እያለች ክብሯንና ማዕረጓን ለሌሎች እያስረከበች ልጆቿን እየበላችና እያስበላች ከማየት በስተቀር ምንም አዲስ ያየነው ለቤተክርስቲያኒቱ የሚጠቅም ለውጥ ወይም ዕድገት የለም። ለዚህም ነው ቤተክርስቲያኒቱን ወደ እድገት ጎዳና ከመምራት ይልቅ፤ ክርስትናን ከማስፋፋት በተለይም በተለያየ የእምነትና የበሽታ ወረርሽኝ የተከበበውን ወጣት ወደ ኃይማኖቱ ከመመለስ ይልቅ ወደኋላ ተመልሰን የጣዖት ምስል ለማየት የበቃነው። በነዚህ ዓመታት ውስጥ ብቅ ያሉት መሪዎቿም ከኃይማኖት ይልቅ ፖለቲካን፤ ከአንድነት ይልቅ በዘር መለያየትን፤ ከኃይማኖት ክብር ይልቅ ለራስ ክብር መቆምን ለቤተክርስቲያኒቱና ለምዕመናኑ ያወረሱ ናቸው ብንል ማጋነን አይሆንም።

    የክርስትና ኃይማኖት የተመሰረተው ራስን ለሌሎች አሳልፎ በመስጠት ላይ ነው። ሆኖም ግን የቤተክርስቲያናችን መሪዎች ይህንን ዓላማ መከተል ትተው ጠቦቶቻቸውን መጠበቅ ዘንግተው “አብዮት ልጆቿን ትበላለች” በተባለበት በዚያ ክፉ የጭንቀት ዘመን እናት ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ወርቃማ ልጆች በአውሬ ሲበሉ ዝምታን መረጡ። እንደውም ብዙዎቹ ከኮሚኒስት ካድሬነት አልፈው ተርፈው እጃቸውም በደም ታጠቡ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክክሳዊት ቤተክርስቲያን ለብዙዎች መምህርና አስተማሪ መሆን ሲገባት የቤተክርስቲያኒቱ መብት ሲገፈፍ ምንድነው የሚል ጠፋ። ንብረቷን በወታደራዊው መንግስት ተቀምታ ወደ ልመና ጉዞ ስትመለስ የሚናገርላት አፍና የሚቆምላት ተከራካሪ ጠበቃ አጣች።

    ዛሬ ደግሞ በዘረኛው የወያኔ አስተዳደር ጥላ ሥር በቁንጮነት የቆሙት አባ ጳውሎስና አባ ገሪማ በደርግ ዘመን በህመም ላይ የነበረችውን ቤተክርስቲያን ታማ አስታመዋት፤ ሞታ ገንዘዋት፤ ወይም ፍታት አድርገውላት ሳይሆን ዛሬ ጠላቶቻችን ናቸው ብለው በሚሏቸው ግለሰቦች ላይ እንደሚያደርጉት ሁሉ እናት ቤተክርስቲያናችንንም በቁሟ ቀበሯት። ታሪክ የማይፍቀውና የማይሽረው ወንጀል ሰሩ። ታሪኳ፤ ሥርዓቷ ተፋቀ ተሻረ። የቤተክርስቲያኒቱ ጥንታዊ ቅርሶች ተዘረፉ። ብዙ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ተዘግተው እንዲውሉ ሆነ። ብዙዎች በዘራቸው ምክንያት፤ እውነትን ለመሸሽ ባለመፈለጋቸውና፤ እውነትን በመናገራቸው ከስራ ገበታቸው ላይ ተገልለው ከነቤተሰባቸው በረሃብ አለንጋ እንዲሰቃዩ ተደረገ። ሌሎችም እራሳቸውና የቤተሰብ አባላቶቻቸው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ የቤተክህነቱን ቁንጮዎች ይቅርታ ካልጠየቁ በስተቀረ ሙታናቸውን እንደማይቀብሩ ተነገራቸው።

    ወድ አንባቢያን “ሙታን እንዳይቀበሩ መከልከል” የሚባል ነገር፤ ወይም የሚባል ወንጀል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? ከዚህ የከፋ ወንጀልስ በዓለማችን ላይ ተፈፅሞ ይሆን? ደግሞስ ይህ ነገር በቤተክርስቲያን መሪዎች መፈጸሙ ወንጀሉን ምን ያህል የከፋ ያደርገዋል? ይህ አጸያፊ ወንጀል ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሪዎች ነን በሚሉት ግለሰቦች ተፈፀመ። የዚህ ፍርድ ፅዋ ቀማሽ ከሆኑት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባላት መካከል አንዱ ታላቁ መምህር አለቃ አያሌው ታምሩ ናቸው። አለቃ አያሌው ታምሩ በህይወታቸው በነበሩበት ጊዜም የነዚህን ወንጀለኛ መሪዎች ጥፋት በመናገራቸውና በማውገዛቸው ብቻ ለአስራ ሦስት ዓመታት ከስራ እንዲገለሉና፤ የጡረታ መብታቸውም በካንግሩ ፍርድ ቤት እንዲታገድ ሆነ ። አለቃ አያሌው ታምሩ በህይወት በነበሩበት ጊዜ ብዙ የሚያውቋቸው ሰዎች በእድሜ መግፋታቸውንና በአካባቢያቸው ያለውን ችግር በመመልከት የመቃብር ቦታቸው የት ቢሆን እንደሚመርጡ ይጠይቋቸው ነበር። የእሳቸው መልስ ግን “እኔ ከሞትኩ በኋላ ያለው ነገር አያሳስበኝም” የሚል ነበር። ስለዚህ ጊዜ ሥልጣኑን የሰጣቸው የዛሬይቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች አለቃ አያሌው ታምሩ በህይወት በነበሩበት ጊዜ እንኳ “የመቀበር ሰብዓዊ መብታቸውን መገፈፋቸውን” ቢንግሯቸውም ኖሮ ፀንተው ከቆሙበት ዓላማቸው የሚነቀንቃቸው ምንም ኃይል እንደማይኖር ቀድመው ይረዱት ነበር።

    የአለቃ አያሌው ታምሩ ከዚህ ዓለም በሞት የመለየትን ዜና መስማት ለቤተክርስቲያኒቱ የዛሬ ቁንጮዎች ታላቅ ደስታ ነበር። ከዚህ በኋላ ይህች ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ታመመች፤ ቆሰለች፤ ደማች፤ ተበደለች፤ ፈረሰች፤ ሥርዓቷ ጠፋ፤ ተበላሸ ብሎ የሚናገር ስለማይኖር እረፍት ያገኙ መስሎ ተሰማቸው። ስለዚህ ለዓመታት ያደረሱባቸውን በደል ለመሸፈንና እውነተኛ የቤተክርስቲያን መሪዎች መስሎ ለመታየት አጋጣሚውን ለመጠቀም ሞከሩ። ብዙዎች የአለቃ አያሌው ተከታዮች፤ ብዙዎችና ተማሪዎቻቸው እነዚያን የመከራ ሰዓታት ያውቋቸው ስለነበርና፤ ይደርሱባቸው የነበሩትን መከራዎች ለመመልከት እድሉ የገጠማቸው ስለነበሩ የዛሬውን የማስመሰል ግርግር አልተቀበሉትም ነበር። ስለዚህም በህይወት እያሉ በቁም በረሃብ እንዲሞቱ የዳረጓቸው ነፍሰገዳዮች የማስመሰል የጸሎት ሥርዓቱን እንዲያካሂዱ አልተፈቀደላቸውም ዕድሉንም አልሰጧቸውም ነበር።

    “ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም “ እንዲሉ አለቃ አያሌው ታምሩን በቁማቸው የገደሏቸው የቤተክርስቲያኒቱ ባለሥልጣናት በፀሎት ፕርግራሙ ላይ እንዲገኙ ስላልተፈቀደላቸው በየትም ቦታ በዓለም ዙርያ ተፈፅሞ የማያውቅ ወንጀል እንደገና ሰሩ። በዚህ ጊዜ የአለቃ አያሌው ታምሩ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የሰብዓዊ ፍጡር መብት ተጣሰ። በከፍተኛ የክፋት ስራው በዓለም ዙሪያ የሚታወቀው ሂትለር እንኳ አይሁዶችን ከመግደሉ በፊት የመቃብር ቦታቸውን ያስቆፍራቸው እንደነበር አንብቤአለሁ አንጂ “ሞቶ መቀበርን ከለከለ” የሚል ታሪክ አላየሁም። በጥላቻ ተሞልተው አምላካቸውን ጌታቸውን የገደሉት አይሁድ እንኳ የአርማትያሱ ዮሴፍ ኢየሱስን ለመቅበር ሲጠይቅ አልከለከሉትም ነበር። እንግዲህ እንስሳ እንኳ ሲሞት በሥርዓት በሚቀበርበት ዛሬ ባለንበት ዘመን የዛሬይቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሪዎች ግን እየተቆፈረ ያለው የመቃብር ጉድጓድ እንዲቆም አዘዙ ። ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ለሥርዓቱ በቂ ባልሆነው እየተቆፈረ እያለ ሳያልቅ በቆመው ጉድጓድ ታላቁ መምህር አረፉ። በህይወታቸው እያሉ ብቻ ሳይሆን በድን ሰውነታቸው ሳይቀር እንደሚያስፈራቸው ምስክር ሆነ። በግራና በቀኝ፡ዘበኛዎች አካባቢውንና የመቃብሩን ቦታ ይቆጣጠሩት ጀመር። እስከዛሬም ድረስ ይህ እየተደረገ ይገኛል። ምዕመናን መቃብሩን ለማየት ሲሄዱ በተለይም ትንሽ ቆም ብለው ከቆዩ ምን እንደሚሰሩ ይጠየቃሉ። ከእረፍታቸውም በኋላ በቀሉ ቀጥሎ የአለቃ አያሌው ታምሩ አፅም ያረፈበት ቦታ ላይ የመታሰቢያ ምልክት እንዳይሰራ በመከልከሉ ተማሪዎቻቸውና እውነተኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ያችን የነፃነት ቀን እየጠበቁ የአያሌው ታምሩን ትምህርት እየተከተሉ ተአምሩንም እያዩ ይገኛሉ። ትላንትና በትምህርቱ ትላንትና በትንቢቱ የተናገረውም እየተፈጸመ ነው።

    በህይወት በነበሩበት ጊዜ ብዙ ጋዜጠኞችና ምዕመናን ስለቤተክርስቲያን መከፋፈል እየተጨነቁ እየተቆጩ ሲጠይቋቸው አለቃ አያሌው ታምሩ የሚሰጡት መልስ ይህ ነበር። “ቤተክርስቲያን አንድ ናት፤ ሲኖዶስም አንድ ነው። ስለዚህ በቤተክርስቲያናችን ዙሪያ ያለውን ችግር በአንድነት በመቆም መፍታት አለብን እንጂ መፍትሄው ሌላ ሲኖዶስ ማቋቋም አይደለም የሚል ነበር”። ይህ ደግሞ በሌላ በኩል የቆመውን ወገን አላስደሰተም። ስለዚህ አለቃ አያሌው ታምሩ እውነት የመሰላቸውንና በተደጋጋሚም “አምላኬ ንገር ያለኝን ነው የምናገረው” በሚሉት መሰረት ለሰዎች ጥላቻ ቦታ ባለመስጠት እውነት የመሰላቸውን እንደተናገሩ አለፉ። በዚህም ምክንያት ለቤተክርስቲያኒቱ የሰጡት የሃምሳ ዓመት አገልግሎት ሳይሆን በዚህች ምድር ላይ በነበሩበት ጊዜ በተለይም በትምህርታቸው እነማንን ነበር ያስደሰቱ? እነማንን ነበር ያስከፉ በሚለው መሠረት በደጅ ያለው ሲኖዶስም በሚያሳዝንና በሚያሳፍር ሁኔታ(በተወሰኑ አብያተ ክርስቲያናት በምዕመናን ጥያቄ) ከተደረጉት በስተቀር ፀሎትና ፍትሃት ሳያደርግላቸው፤ ስማቸውንም እንኳ ሳይጠራ ቀረ። ነገር ግን የአለቃ አያሌው ታምሩ ትምህርትና ለቤተክርስቲያናቸው የነበራቸው ህልምና ትንቢት ከላይ እንደተገለፀው አንድ አምላክ፤አንዲት ቤተክርስቲያንና አንድ ሲኖዶስ የሚለው ተሳክቶ ሳያዩት ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም እንኳ በግራና በቀኝ የቆሙት የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች ለሰላም ድርድር አንድ ወንበር ለይ ለመቀመጥ ማሰባቸውና ብሎም መስማማታቸው ትንቢተ አያሌው ተፈጸመ እንድንል ያደርገናል።

    ቤተክርስቲያናችን የታነፀችው የሰላም ንጉስ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነውና በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ ለመነጋገር መዘጋጀቱ እሰየው የሚያሰኝ ነው። ግን ይህ እርቅና ሰላም ከምን ተነስቶ እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል። ለምን እንደሚደረግም ማመዛዘን ይገባል። ዛሬ የታላቁን መምህር የአለቃ አያሌው ታምሩን ዕረፍት ሦስተኛ ዓመት ስናከብር አስተላልፈውልን የሄዱትንም ትምህርት በማሰብ ነው። ለታላቁ መምህር ኢትዮጵያ ማለት ቤተክርስቲያን ናት። ቤተክርስቲያንም ኢትዮጵያ ናት። ታዲያ ታሪካችንን ስንመለከት ጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ጠላት፤ ወራሪ መጣ ሲባል አብራ ስትሰለፍ በፀሎት በሱባዔ አብራ ስትቆም ምዕመናንንም ስትረዳ መኖሯን ለማወቅ የታሪክ መፃህፍትን ከማገላበጥ ሌላ ምስክር ሊኖር አይችልም።

    ዛሬ ደግሞ ኢትዮጵያ ከአብራኳ በወጡ የጠላት ክንድ ተይዛ ግዛትዋ ተደፍሮና ጠባቂ አጥቶ እይተሸጠች፤ ልጆቿ በእናትና በእንጀራ እናት እጅ እንደሚያድጉ ልጆች ተለያይተው አንዱ እርቦት ሌላው ደግሞ ጠግቦ እያደረ፤ ህፃናት ልጆቿ በዓለም ዙሪያ የመንግስት የገቢ ምንጭ ሆነው እንደሸቀጥ እቃ እየተቸረቸሩ እያሉ፤ ደረሱልኝ እያለች የምታያቸው ወጣት ልጆቿ በዓለም ዙሪያ በስደት ተበትነው፤ ለመብት ለነፃነታችን የቆሙ ወንድሞችና እህቶች ወደ እስር ቤት ተወርውረው፤ ሌሎቹ ደግሞ በመናገራቸው ብቻ በያሉበት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው እያሉ ከሁሉም በላይ ደግሞ የወያኔው አስተዳደር ከሌለ እሳቸውም እንደማይኖሩ የሚያውቁት በዕብሪት የተሞሉት አባ ጳውሎስ ወደማይቀረው ሞት ከመሄዳቸው በፊት ለጥፋታቸው ማስታወሻ የሚሆን የጣዖት ምስል ባቆሙ ማግስት፤ በስደት ላይ ያሉት የኃይማኖት መሪዎቻችን ራሳቸውን ለሀገራቸው ምድር ለማብቃት ከሚያስችል ድርድር አልፈው፤ ለሀገር ለወገን የሚበጅ ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነው።

    ስለዚህ ኢትዮጵያውያን በያለንበት አያሌው ታምሩ የሞተላትንና የወደቀላትን ታላቂቱን ቤተክርስቲያን ለማንሳት፤ በብዙ ችግር ተከባ ያለችውን ሀገራችንን ከማጥ ለማውጣት በአንድነት እንነሳ።

    አለቃ አያሌው ታምሩ እንደፃፉት “በእግዚአብሔር አትጠራጠር፤ የነበረህን ኃይማኖት ፤ትምህርት፤ ሥርዓት፤ ባህል፤ አፅና። የቅልውጡን ተወው አያገለግልህም። በተለይ ወጣቱና ትኩሱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ኃይልም ጉልበትም አንተ ነህና የኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ደምና ቀለም ይኑርህ። ይህ ልዩ ምልክትህ ከአንተ ጋር ይኑር። ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉርነቱን አይለውጥምና” (“ተአምርና መፅሐፍ ቅዱስ”፤ ገፅ 7)።

    ለሶስተኛው የሙት ዓመታቸው መታሰቢያ

    (ጸሀፊውን በዚህ ኢሜይል አድራሻ ማግኘት ይቻላል፤ [email protected])

Leave a Reply