Ethiopians in Switzerland will commemorate May 15 by holding a rally in Geneva in front of the United Nations building starting at 2:00 PM.
On May 15, 2005, millions of Ethiopians voted for change. The ruling Tigray People’s Liberation Front (Woyanne) reacted by unleashing its death squads killing thousands, throwing over 50,000 civilians in concentration camps, shutting down the independent media, and arrested all the top leaders of the opposition party.
Similar activities are being organized to commemorate this day in Washington DC and other cities around the world.
ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሠልፍ ጥሪ በስዊዘርላንድና አካባቢ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ
ለተከበራችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ
የህዝብ ድምጽ የተቀማበትና በአደባባይ የህዝብ ልጆች በአጋዚ ጦር የተጨፈጨፉበት ቀን በማስታወስ ለሚደረገው አለም አቀፋዊ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመገኘት ጥሪአችንን እናቀርባለን።
የሰላማዊ ሰልፉ ዓላማ በሃገራችን ላይ የተጣለው የጥፋት ደመናን ለማርገብም ታስቦ ነው።
ይሄዉም ፡-
* በሃገራችን ፍትህና ዲሞክራሲ ከምንጊዜዉም የበለጠ ታፍኖአል
* ህዝባችን ሰብአዊና መሰረታዊ የመኖር መብቱ ተነፍጓል
* መለስና ግብረ-አበሮቹ በህዝባችን ላይ ቀጥተኛ የሆነ ብቀላ እየፈጸሙበት ነው
* የአምባገነኑ መለስ አስተዳደር የዕለት ጉርስን የፖለቲካ መሳርያ በማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለረሃብ ተዳርገዋል
* የባህረ ነጋሽ ቁስል ሳይደርቅ የሰሜን ምዕራብ የድንበር መሬታችን ቆርሰው ለሱዳን ሰጥተዋል
* መለስና ግብረ አበሮቹ በኢትዮጵያ ላይ እና በህዝቧ ላይ የማያልቅ ጦርነት በመጫር ላይ ናቸው
* የሃገርን ሉዖላዊነት፤ታሪክንና ቅርስን ማጥፋታቸዉን ከጥለዉበታል
* በህዝባችን ላይ አፈናዉና ግድያው በአስከፊ ሁነታ ቀጥሎአል
* በብዙ ሺህ የሚቆተሩ የኢትዮጵያ ልጆች በሃገሪቱ ዙሪያ እየማቀቁ ነው
* ኢትዮጵያዊ መሆንና ስለኢትዮጵያዊነት መናገር ወንጀል ሆኗል ለዚህም እንደ ትልቅ ምሳሌ ኢትዮጵያዊው አርቲስት ቴዲአፍሮ መጥቀስ ይቻላል
* በቴዲ አፍሮ ላይ የሚወሰደዉ ኢ-ፍትሃዊ ድርጊት በኢትዮጵያዊነት ላይ ብሎም የአዲሱን ትውልድ ልብ ለማቁሰል ሆን ብሎ የሚፈጸም ድርጊት ነው
ስለኢትዮጵያዊነትና ለኢትዮጵያ ለመቆም ከእኛ ከኢትዮጵያውያን ሌላ ማንም ሊቆምና ሊቆረቆር አይችልም ።ስለዚህ ህዝባችንና ሃገራችን ካሉበት አጣብቂኝ ችግር ለማዉጣት የዘር የሃይማኖትና የፖለቲካ ልዩነት ሳይገድበን የዜግነት ድርሻችንን እንወጣ።
ስለዚህ ግንቦት 7 ቀን ወይም 15 May 2008 በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላ እንድትገኙ ጥሪአችንን እንቀርባለን
ቦታው ጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ነው
ከ14 ሠዓት ጀምሮ
ኢትዮጵያ ለዘልዓለም ትኖራለች!
የፖለቲካ እስረኞች ባስቸኳይ ይፈቱ!
ቴዲ አፍሮ ባስቸኳይ ይለቀቅ!
ጊዜአዊ አስተባባሪ ተግባር ኮሚቴ
ለበለጠ ኢንፎርሜሽን በዚህ ስልክ ይደዉሉ 0041 79 672 42 87
One thought on “Ethiopians in Switzerland to commemorate May 15”
እጅግ በጣም አስፈላጊ እና አንገብጋቢ ጉዳይ በመሆኑ ሁላችንም ወጥተን ተቃውሞአችንን ማሰማት ታሪካዊ ግዴታችን ነው!!!!!!!!