Kinijit North America will host a press conference with officials of the Unity for Democracy and Justice Party (Andinet) on Saturday, April 5, at 2 PM EDT. The press conference will be aired live via Ethiopian Review Radio Network.

2 thoughts on “Interview with Andinet Party officials, Saturday 2 PM”
የቱን ታቦት ላምጣ፣
እኔ እበልጥ እኔ በልጥ ዘራፍን ትታችሁ
ከቀን እንቅልፋችሁ ከቅዠት ነቅታችሁ
ለናንተ ለሞተው ለሕዝቡ ብላችሁ
ነፃነት አንድነት ሆኖ ውጥናችሁ
እርስ በርስ መባላት መብለጥለጥ ትታችሁ፣
የሞተን አወዳሽ የቓሚ ባላንጣ
ከኔ በላይ ላሳር የፖለቲክ ቓንጣ
ለከፋፍለህ ግዛው ለወያኔ ብዥት
ለጎጥ አጋፋሪ ለዘረኛ ቅዠት
ለ”አዋቂ እኔ ብቻ” ለደደቢት ቅኝት፣
የራሳችሁ ጠላት ከመሆን አልፋችሁ
ግለኝነት ቀርቶ እውነትን ይዛችሁ
ላገር እንድትበጁ እንድንኮራባችሁ፣
የቱን ታቦት ላምጣ እንዳስታርቃችሁ
ለየትኛው ልሳል አንድ እንዲያደርጋችሁ።
Ras Dargie
01/01/08
ምን ነካብኝ ታዬን፣
የህዝብ ድምፅ ብለን ነፃነትን ጓጉተን
አገር እንደሌለው ተሳደን ተባረን
አርነት ወይም ሞት ብለን ተማምለን፣
ለግል ቅዠት ጥንስስ ለግል ህይወት መድህን
ወዲህ ወድያ ብንል ጠብ ላይልልን
ግራ ቀኝ ሳንማትብ በጠዋት ተነስተን፣
በአደረው አፋቺን እህል ሳይገባበት
በተናገርንው ልክ ፍሬ ሳናይበት
በአክብረኝ አታክብር የፊውዳሎች ቅሌት
አንዴም ሳይጥማችሁ የኔ ድሃው ስሜት
አሁን ምን ይሉታል ሰራዊትን መክትት
ይቅር ለግዜር ሳለ በባለጌ ምላስ መጎሰም ነጋሪት
ለቅሶዬ እንዳያምር እንዳይፈስ እንባዬ
የነፃነት እርሜ ሳይወጣ መርዶዬ
የቁርጡ ሳይመጣ ገና ሳልታመም ሳይፈርስ ገላዬ
ምን አጣደፋችሁ አፈር ለመመለስ ለማቡነን በላዬ
ባሉት አለመርጋት መላበስ ክደትን
ህዝብን ከል ማልበስ መገነዝ አገርን
ሆድ ሲያውቅ ዶሮማታ መግደል ህልውናን
ችግር አሳልፈን ያን ሁሉ ተወጥተን
አሁን ወደህኋላ ምን አንሽራተተን?
የምን እርግማን ነው እንዲህ ያለ ሰይጣን
የሃይሉን አላውቅም ምን ነካብኝ ታዬን?
Ras Dargie
01/01/08