Skip to content

የአቶ አባይነህ ልኡካን የቅንጅትን ተ/ም ሊቀመንበር ሊያነጋግሩ ነው

በመላ አገሪቱ ያሉ ደጋፊዎቻችንን እናነጋግር በሚል ከቀድሞው የመኢአድ ቢሮ ተልከው የነበሩት የአቶ አባይነህ ብርሀኑ ልኡካን በየሄዱበት ተቃውሞ ሲገጥማቸው ቆይቶ ከተመለሱ በኋሏ አቋማቸውን በመመርመር የቅንጅትን ተ/ም ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ሊያነጋግሩ ቀጠሮ መያዛቸውን ሪፖርተራችን ዘገበ፡፡

ልኡኩ በተጓዘባቸው ክልሎች ሁሉ የስራ አስፈጻሚው ያለ ፓርቲው ህገ ደንብ በአንድ ግለሰብ መታገዱ ተቃውሞ አስነስቶበት የነበረ ሲሆን ባለፈው እሁድ የቃል ሪፖርት ከተሰማ በኋላ አቶ ሃይሉ ሻውልን በማፈስቀድ አጠቃላይ ጉባኤ ለመጥራት የታቀደ ቢሆንም አብዛኛው አባል አካሄዱ አያዋጣም በማለቱ ጉዳዩ የተለየ አቅጣጫ ይዟል፡፡

ከአቶ አባይነህ ጋር በጥፋቱ ጎዳና ያን ያህል የተጓዙት አባላት አቋማቸውን ቀይረው በአገር ውስጥ ያለችውን መሪያችንን እናነጋግር ማለታቸው ጊዜ ከመግዛት አንጻር የተደረገ ስልት ነው የሚሉ ወገኖች ያሉ ቢሆንም ሃሳባቸውን ለመረዳት ወ/ት ብርቱካን ለሰኞ ቀጠሮ እንዲያዝ ማዘዛቸውን ሪፖርተራችን ዘግቧል፡፡

Leave a Reply