Skip to content

'Erm' – by Kesis Asteraye Tsige

ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ወገኖቼ! የተጻፈ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ነውና ከመንፈሳውያን መጽሐፍቶቻችንም ሆነ ከአለማውያን መጻሕፍት የምንጠቅሳቸው እድሜአችን እስኪያልቅ ብንናግራቸው የማያልቁ ብዙ ብዙ ትዝታዎች አሉን፡፡ በቤተ መንግስትም ሆነ በቤተ ክህነታችን ተዝቆ በማያልቀው
እርማችን የገደልናቸው፤ ነገር ግን ምላሳችንን ገልብጠን ዛሬ ለምንዘራው እርም ይረዳን ዘንድ በበጎ ምግባር በገዛ አፋችን የምንጠቅሳቸው ቅዱሳን አባቶች ደም እየከሰሰን ነው፡፡ ይሁን እንጅ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው፤ እኔም ስለገዳይነትና ስለገደልናቸው ወገኖቻችን አይደለም ማለት የምፈልገው፡፡ ማተኮር የምፈልገው ከዚህ በፊት በፈጸምነው በደል ስለተሸከምነው እርም፤ አሁን በዚች ደቂቃም እያቦካን እንደቂጣ ስለምንጋግረው እርም፤ ከዚህ እርም ልንጸዳበት ስለምንችልበት መንገድና ሌላ እርም ከመፈጸም እድንቆጠብ ሊረዳን ስለሚችለው ሃይማኖታዊና ባህላዊ ሐብታችን ነው፡፡ እንዲሆን የምፍለገውም ከዚህ ቀደም ከገባንበት እርም ሕሊናቸን ሳይጸዳ በሌላ እርም ውስጥ ገብተን በመዋኘት መላ ሕይወታችንን በከንቱ እንዳናባክን፤ የተጠጋንበትን ጉባኤ ሁሉም እየበከልን እርምን እንደወረርሽኝ በሽታ ማሰራጨቱን እንድናቆም ነው… ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

(You can download Amharic font here)

2 thoughts on “'Erm' – by Kesis Asteraye Tsige

  1. ቀሲስ፦
    እርሙን አልበላሁም ይሉ ይሆናል።ነገር ግን መረቁን ሳይጠጡ የቀሩ አይመስለኝም። መረቁን የጠጣም ቢሆን ንስሐ መግባት ያለበት ይመስለኛል። ከትህምርት ቤት ጓደኛዎ ጋር ዲሲ ምን ሲሰሩ እንደነበረ እናውቃለን። በተረፈ ስለ አቡነ ቴዎፍሎስም ሆነ ስለ አቡነ መርቆርዮስ ከመንበረ ፕትርክና አወራረድ የሰጡትን ማብራርያ አደንቃለሁ። “እነቄስና አባ ስም አይጠሬ” ዛሬ በአሜሪካ የገለልተኝነት ካባ ለብሰው የአንድ ክፍለ ህገርን የበላይነት ለማስፋፋት አንዴ በማህበረ ካህናት አንዴ በማህበረ… ስም ሲደራጁ እያየን ነው። ጊዜን ስለማይዋጁ እንደ ኖኅ ዘመን ሰዎች የንፍር ውሃ ይወስዳቸዋል እንጂ የትም አይደርሱም። ሁላችንም ነቅተናል፣ ሁኔታዎችን ሁሉ በትኩረት ነው የምንከታተለው።
    ዛሬ ዳሩ መሃል እንደሆነ አላወቁም።
    እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ

  2. What is this guy saying? For how long will these people continue distorting the Gospel and Paul’s messages, and ramble with their misleading noise.

    Here is what Paul wrote to the Corinthians: 12 እንግዲያስ የጻፍሁላችሁ ብሆን እንኳ፥ ስለ እኛ ያላችሁ ትጋታችሁ ከእናንተ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እንዲገለጥ እንጂ፥ ስለ በዳዩ ወይም ስለ ተበዳዩ አልጻፍሁም። ስለዚህ ተጽናንተናል። 13 በመጽናናታችንም ስለ ቲቶ ደስታ አብልጦ ደስ አለን፥ መንፈሱ በሁላችሁ ዐርፎአልና፤ 14 ለእርሱ በምንም ስለ እናንተ የተመካሁ እንደ ሆነ አላፈርሁምና፥ ነገር ግን ሁሉን ለእናንተ በእውነት እንደ ተናገርን፥ እንደዚህ ደግሞ ትምክህታችን በቲቶ ፊት እውነት ሆነ። 15 ስለዚህም በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ እንዴት እንደተቀበላችሁት፥ የሁላችሁን መታዘዝ እያሰበ ፍቅሩ በእናንተ ላይ እጅግ በዝቶአል። 16 በነገር ሁሉ ተማምኜባችኋለሁና ደስ ይለኛል። 2 Corinthians 7:12

    What is this fabrication of እርም erm? If Paul reads this rambling I wonder what he might say. He probably would say, “that is not what I wrote – go back and read my letter”. One should not start preaching from a false premise.
    Please do not think you can fool people by quoting Geez version? This people who were preaching us “the king is anointed by God, the bishop is God’s spokesman” are all discredited. They are not preaching The Gospel of Jesus Christ and are far from the orthodox teaching. All of them who we are the claiming to lead a legal synod or those back home who claim to have been chosen – their days are numbered and it will not be long before we get to choose true church leaders and reclaimed our church.
    Because of the falseness of such teaching, Jesus warned people to beware of the doctrines of the Pharisees (Mat 16:11-12).
    ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ እንድትጠበቁ ብዬ ስለ እንጀራ እንዳልተናገርኋችሁ እንዴት አታስተውሉምን? 12 እነርሱም ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት እንጂ ከእንጀራ እርሾ እንዲጠበቁ እንዳላላቸው ያን ጊዜ አስተዋሉ። የማቴዎስ ወንጌል 16 (11-12)
    READ PAUL’S LETTER IN ALL THE AVAILABLE ENGLISH TRANSLATIONS AS WELL.
    Bible in Basic English
 So though I sent you a letter, it was not only because of the man who did the wrong, or because of him to whom the wrong was done, but so that your true care for us might be made clear in the eyes of God.
    King James Bible
Wherefore, though I wrote unto you, I did it not for his cause that had done the wrong, nor for his cause that suffered wrong, but that our care for you in the sight of God might appear unto you.
    New American Standard Bible (©1995)
    So although I wrote to you, it was not for the sake of the offender nor for the sake of the one offended, but that your earnestness on our behalf might be made known to you in the sight of God.

Leave a Reply