Skip to content

Message from Tesfaye GebreAb

ይድረስ ካንባቢዎቼ [pdf]
እኔ ደህና ነኝ!
እናንተስ እንዴት ሰነበታችሁ?

“የጋዜጠኛው ማስታወሻ” የመጀመሪያው እትም ተሸጦ አልቆአል። መፅሃፉን ለገዛችሁ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ሁለተኛው እትምም ታትሞ ለስርጭት ዝግጁ ሆኖአል። ከመጪው ህዳር ወር ማብቂያ ጀምሮም በሁሉም ክፍለአለማትና ከተሞች ይሰራጫል። “የጋዜጠኛው ማስታወሻ” ሁለተኛ እትም የጀርባ ሽፋን ላይ የፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ፤ የተክለሚካኤል አበበ እና የነአምን ዘለቀ ቅንጫቢ አስተያየቶች ታትመውበታል። መፅሃፉን ለማከፋፈል የምትሹ ወደ [email protected] ደብዳቤ በመፃፍ ፍላጎታችሁን መግለፅ ትችላላችሁ።

“የደራሲው ማስታወሻ”ን ቃል በገባሁት መሰረት ፅፌ ጨርሻለሁ። 21 ምእራፋትና 406 ገፆች ላይ ተጠናቆአል። ይህ አዲሱ መፅሃፍ፤ “ቀዳሚው ውሃ ነበር!” የሚለውን ብሂል ያስታውሳል። ጥቂት የማረም ስራ እና ቀሪ ቴክኒካዊ ተግባራት ብቻ ነው የቀሩኝ። በመጪው የፈረንጆች አዲስ አመት ማግስት ለስርጭት ይበቃል ብዬ ተስፋ አድርጌያለሁ።

በመጨረሻ፤ ኢሜይል ለላካችሁልኝ ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ። ምላሽ ላልላኩላችሁ በጊዜ እጥረት ነውና ከይቅርታ ጋር የክብር ምስጋና ተቀበሉኝ። አብዛኞቻችሁ እንደተመኛችሁልኝ እንደ ከዋክብት ባልራቀ ጊዜ ውስጥ ተያይዘን ወደ ቢሾፍቱ እንገማሸራለን። የወንዛችንን ዘፈን እየዘፈንን ወደ ጣና፤ ወደ አባይ፤ ወደ አዳባይ፤ ወደ ጨንቻ፤ ወደ አኝዋክ፤ ወደ ሌቃ ዱለቻ፤ ወደ አይሳኢታ፤ ባገራችን ዋሽንት ታጅበን እንዋባለን። ይህ ህልምም ቅዠትም አይደለም። የአገዛዝ ስርአቱ የቆመበት መሰረት ውስጡ የተበላ ነው። ምሰሶው ቀፎውን ቀርቶአል። ጠጋ ብለው የልብ ትርታውን ሲያዳምጡት የጭንቀት ኡኡታው ጆሮ ይበጠርቃል። ዝርዝሩን “የደራሲው ማስታወሻ” ያወጋችሁዋል። በሰላም ያገናኘን።

ተስፋዬ ገብረአብ
[email protected]

13 thoughts on “Message from Tesfaye GebreAb

  1. ብራቮ ተስፍሽ፣
    መጽሃፍህን በጉጉት እየጠበቅን ነው፣ አሁን ደሞ ምን ጉድ ልታስኮመኩመን እንደምትችል ከበፊቱ አንተም ዳር ዳር ብትለንም እንደው ዝም ብሎ ግን ታሪከኛ እንደሚሆን ይታየኛል፡፡
    አቤት አጻጻፍ….
    ከአሁኑ አይኔን በላኝ….

    እንጻፍ ከተባለ፣ የነዚህ ምስጦች ታሪክ መቼ ተጽፎ ያልቅና፣ በተለይ አንተን ከመሳሰሉት ዉስጥ አዋቂዎች፣ አይዞህ፣ እድሜ ይስጠን እንጂ ማስታወሻህን እስከ አስረኛ እትም መኮምኮማችን አይቀርም፣ ታዲያ ከዚህኛው ቀጣዮቹን ከቀዩ ዛፍ ስር…

    ተስፍሽ፣ መቼም በአዲሱ ማስታወሻ ከሚወጡት ሚስጥሮችና ጉዶች አንባቢዎችህ ብዙ እንደምንማር ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ለነዛ አለቃዎቻቸዉን እንደ መላዕክ ለሚያዩና ሆዳቸው አልቆረጥ ብሏቸው እዚያው ከነሱ ጋር እጃቸዉን በደም የሚታጠቡና ኪሳቸዉን ከወገን በተዘረፈ ገንዘብ በሚወጥሩ ወያኔዎች ልቦና ይሰጥልኝ ይሆናል…

    ሞት ለወያኔ!!!
    ድል ለሁላችን!!!

    በርታ ወንድሜ…

    ሳምሶን…

  2. Yes! There is only one true! Say it Tesfaye and we are ready to hear. God bless and protect you! You did your share and our share must follow!Put your brick on the building and everybody including me should contribute to put our brick to build the freedom and democracy to all of us. Thank you Tesfaye! Berta!

  3. Ato Tesfaye,

    You mentioned Bishoftu, Tana, Abay, Chencha, etc in your letter. I am currious if you also wish for us to go to Asmara, Dahlak, Mitsewa, etc without the need to have or show a passport – you see, as Ethiopian brothers and sisters – as it used to be for generations. How about that?

    Selam ke America

  4. Tesfaye ! whatever people are talking about you i like your writings very very much. I really appreciate your art and talent specially your Amaregna. No one can deprive you your ethiopiawinet!
    Good job! God bless you!

  5. I like your books. try to speak your mind and tell the generation what you know from your past experience…..for those who are talking shi….tell them gimelochu yiedalu wushochum yichohalu…be blessed

Leave a Reply