Skip to content

Wolqait-Tegede Ethiopians in Ohio resolution – Amharic

The following is a resolution passed on Aug 18, 2007, by Ethiopians of the Wolqait-Tegede region currently residing in Ohio. 

የወልቃይት-ጠገዴ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞና የአቋም መግለጫ

በ 8/18/2007 በትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር ተውካዮች (ትውልዳቸው ወልቃይት የሆኑ) የትግራይ ክልል የፀጥታ/ደህንነት ሃላፊ አቶ ፀጋይ አስማማውና የወልቃይት ጠገዴ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ፈረደ የሺወንድም “ልማት ለወልቃይት” በሚል ስም በተጠራው ስብሰባ ላይ በርካታ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ተገኝተዋል።

የስብሰባው ተሳታፊ በወቅቱ የቀረበለትን ተአማኒነት የሌለው የወያኔ የፕሮፕጋንዳ ሪፖርት ካዳመጠ በኋላ እጅጉን ከሃቅ የራቀ ሆኖ በማግኘቱ በተጠቅሱት አክባቢዎች ያለው ተጨባጭ ችግሮች ፊት ለፊት አጋልጧል። በማስከተልም የሚከተሉትን የውሳኔ ሀሳቦችን አስተላልፏል።

1. የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (ሕወሓት) ያለወልቃይት ጠገዴና ሁመራ ተወላጆች ፍላጎት መሬቱ ወደ ትግራይ ክልል ማስገባቱ አጥብቆ በመቃወምና ይህ ቋንቋን ብቻ መሰረት ያደረገው የማካለል ስርዓት ለኢትዮጵያችን ጎጂ መሆኑን በማስገንዘብ የጎንደር ታሪካው መሬቶች (ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሁመራና ጠለምት) ወደ ቀድሞው አስተዳደራቸው እንዲመለሱ በአፅንዖት ጠይቋል፤

2. ሕወሓት በወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ላይ ከሃያ አመታት በላይ ለፈፀመችውና በመፈፀም ላይ ያለችውን አሰቃቂ ግዲያዎችና እስራት በመቃውም ባልበቃቃ ምክንያት የታሰሩትን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በአስቸኳይ እንዲፈቱ አሳስቧል፤

3. ኢትዮጵያውያን የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ሆን ብሎ ከለም መሬታቸው በማስለቀቅ በምትኩ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ብቻ አምጥቶ መሬቱን እንዲይዙ ማድረግ ከቅንነት የመነጨ ስላልሆነ ድርጊቱን በፅኑ አውግዟል፤

4. በሰበብ አስባቡ ያለ አግባብ ከአቅሙ በላይ ቅጣትና ግብር በነዚሁ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ላይ መጫኑና ከባድ የኢኮኖሚ ትፅዕኖ እንዲደርስበት መደረጉን በመቃወም ይህ አስከፊ ተግባር እንዲቆም ጠይቋል።

5. በነዚህ አካባቢዎች ተውላጅ ኢትዮጵያዊያን ላይ ከረጅም አመታት በፊት ጀምሮ በተለያዩ ኢ-ሰብዓዊ መንገዶች እየተደረገ ያለውን የስነ ልቦና ሰለባ በአስችኳይ እንዲቆም አሳስቧል፤

6. በሃገረ ሱዳን የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ባለፈው (ጁላይ) ወር በእጅ አዙር በሱዳን መንግሥት እንዲታሰሩ መደረጉን አጋልጦ፤ ሕወሓት በስደት በሚገኙት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ የምታደርገውን ጣልቃ ገብነት እንድታቆም ጠይቋል፤

7. በጎንደርና በትግራይ ሕዝብ መካከል የነበረውን የረጅም ዘመናት ትስስር ወያኔ ስልጣን ከያዘችበት ጊዜ ጀምሮ የወልቃይት ጠገዴ እንዲሁም የጠለምት መሬቶችን በመውሰድና በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ ከፍተኛ በደል በመፈፀም በሁለቱ ህዝብ መካከል ስር የሰደደ ጥላቻ እንዲፈጠር መደረጉ እንዳሳስበው ገልጿል፤

8. በመጨረሻም በአያትና በቅድመ-አያቶች አጥንትና ደም ተከብሮ የኖረውን የኢትዮጵያ ዳር ድንበር እንዲከበርና ተቆርሶ ለሱዳን የተሰጡት መሬቶች እንዲመለሱ ለወደፊቱም እዲህ አይነቱ ተንኳሻና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚስደፍሩ ተግባራት እንዳይሞከሩ አጥብቆ በማሳሰብ ስብሰባው ተገባዷል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
በኮለምበስ ኦሃዮ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን
ኦገስት 18፣ 2007

Leave a Reply