Skip to content

Author: Negash

የቻይኖች የታክስ ማጭበርበር መበራከቱ የንግድ ማኅበረሰቡን አሳሰበ

Posted on

በ 

June 19, 2013

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሳምንት በቻይና ጉብኝት አድርገው ነበር፡፡ ቻይና በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ተፈላጊነቷ እየጨመረ ከመጣባቸው ምክንያቶች ውስጥ ያለፖለቲካዊ ቅድመ ሁኔታና ከጣልቃ ገብነት ነፃ በሆነ መንገድ የምትሰጠው ድጋፍ፣ የምታካሂደው የግንባታ ሥራ እንዲሁም የምትሰጠው የረጅም ጊዜ ብድር ተደማምሮ አጋርነቷን የማይፈልገው አገርም መንግሥትም የለም፡፡

ከዚያም በላይ በዓለም ላይ ልዕለ ኃያልነቷ እየጨመረ በመምጣቱ ቻይናን ወዳጁ የማያደርግ አገርም ሆነ መንግሥት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስሌቱ ላይ የስህተት መስመር እንዳሰመረ የሚቆጠርበት ጊዜ ይመስላል፡፡ የአፍሪካ ድሃ አገሮችን ብቻም ሳይሆን የአውሮፓ ሀብታም አገሮችም ጭምር ከገቡበበት ማጥ እንድታላቅቃቸው ቻይናን መማጸን የያዙበት የዓለም ታሪክ የቻይናን የበላይነት እያሳየ ነው፡፡

እንዲህ ያለው አቋሟ ግን እንደኢትዮጵያ ላሉት አገሮች ያስከተለው ጫና ጥቂት የሚባል እንዳልሆነ የሚናገሩ አሉ፡፡ ‹‹ገና ለገና ብድርና ዕርዳታ ይሰጡናልና  በአገራችን ውስጥ እንዳሻቸው ሲሆኑ ዝም ማለት ተገቢ አይደለም፤›› የሚሉና ሌሎችም ትችቶች ከሚቀርቡባቸው ተቋማት አንዱ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከፍተኛ ኃላፊዎቹ በእስር ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት ከምሥራቅና ከምዕራብ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ግብር ከፋዮች ጋር ‹‹ግብዓት ለመሰብሰብ›› በማለት ባለሥልጣኑ በጠራው ስብሰባ ላይ ከተደመጡ በርካታ የግብር ከፋዩ ችግሮችና እሮሮዎች ውስጥ ያልተለመደና አዲስ ሆኖ የቀረበው ይኸው የቻይኖቹ አጭበርባሪነት ነበር፡፡ ቻይኖችን ብቻ ሳይሆን ቋንቋና ባህላቸውን እንደሚያውቅ፣ ለሰባት ዓመታትም በቻይና ትምህርቱን እንደተከታተለ የገለጸው ወጣት (ስሙን እንዳንገልጽ ጠይቋል)፣ ኢንቨስተር ተብለው ከሚመጡት ቻይኖች ውስጥ አብዛኞቹ አቅም ሳይኖራቸው፣ በአገራቸው መሥራትም ሆነ የሥራ ጫናውን መቋቋም ሳይችሉ የሚመጡ መሆናቸውን ተናግሯል፡፡ አቅም እንኳ ኖሯቸው ሲመጡ ቋንቋ የማይችሉ በመሆናቸው (ቢያንስ እንግሊዝኛ መናገር የማይችሉ) ቀድመው በመጡ የራሳቸው ወገኖች ሳቢያ ወደአጭበርባሪነቱ ጎራ እንዲገቡ ይደረጋሉ ይላል፡፡

ለቻይኖቹ ብቻ ሳይሆን ለባለሥልጣኑም ቻይንኛን (ማንዳሪን) በማስተርጎም ሲሠራ የቆየው ወጣት እንዳስረዳው፣ ለአገሩ እንግዳ፣ ለሕዝቡ ባዳ የሆኑ ቻይኖች ወደአገር ውስጥ ሲገቡ ካለባቸው የቋንቋ ችግር ሳቢያ ነባር ቻይኖችን ለመጠቀም ይሞክራሉ፡፡ ነባሮቹ ደግሞ በማጭበርና ጉቦ በመስጠት የተካኑ በመሆናቸው መጤዎቹን በዚያው መንገድ ያሰለጥናሉ፡፡

ከባለሥልጣኑ የሒሳብና የኦዲት ባለሙዎች ጋር በመመሳጠር፣ ጉቦ በመስጠት የታክስ ክፍያ ያስቀራሉ፣ አለያም ያሳንሳሉ፡፡ ለዚህ ውለታቸው ኦዲተሮቹና አካውንታንቶቹ ጠቀም ያለገንዘብ ይቸራቸዋል፡፡ እንዲህ ያለውን መመሳጠር ተክነውበት በቅርቡ ሦስት ቻይኖች የሐሰት የቫት ደረሰኝ አትመው ሲጠቀሙ መያዛቸውን ወጣቱ ለሪፖርተር ተናግሯል፡፡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ሌላ ግለሰብም የሐሰት ቫት ደረሰኝ ከሚታተምባቸው የአዲስ አበባ መንደሮች ውስጥ ንግድ ሥራ ኮሌጅ አካባቢ አንዱ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ባለሥልጣኑ በአካባቢው በተሠሩ አዳዲስ ሕንፃዎች ውስጥ ድንገተኛ ጉብኝትና ፍተሻ ቢያካሂድ በቀላሉ ሊደርስበት እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ከ600 ያላነሱ ቻይኖች ‹‹ቢዝነስ›› እየሠሩ እንደሚገኙ መንግሥት አስታውቋል፡፡ ሆኖም ከእነዚህ ውስጥ ምን ያህሉ ትክክለኛና የተፈቀደላቸው መስክ ላይ እየሠሩ እንደሚገኙ፣ ምን ያህሉ በትክክል ታክስ እንደሚከፍሉ መንግሥት ከመናገር ይቆጠባል፡፡ አይከታተላቸውም፡፡ ከዚህ በከፋ ሁኔታ በቻይና ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው በሚሠሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ቻይኖቹ የሚያደርሱትን የጉልበት ብዝበዛም ሆነ አካላዊ ጥቃት አይቶ እንዳላየ፣ በማስረጃም ሲቀርብለት እንዳልሰማና እንዳላወቀ ማለፉ ክፉኛ ቢያስተቸውም ዝምታን ይመርጣል የሚባለው መንግሥት፣ አሁን ደግሞ ቻይኖቹ በሙስና አገሩን ከማበላሸት አልፈዋል የሚል ስሞታ እየቀረበለት ይገኛል፡፡

መጤዎቹ ቻይኖች ወደተለያዩ የመንግሥት መሥርያ ቤቶች ጉዳያቸውን ለማፈጸም ሲያቀኑ፣ የመንግሥት ኃላፊዎች ጉቦ ካልተሰጣቸው በቀር ጉዳያቸውን እንደማያስፈጽሙላቸው በአስተርጓሚ ስለሚነገራቸው፣ ለባለሥልጣኑ ሁሉ ገንዘብ ይሰጣሉ የተባሉት ቻይኖች ከዚህም የከፋ ሥራ ይሠራሉ፡፡ አብዛኞቹ ቻይኖች የባንክ ሒሳብ መግለጫ የሌላቸው ስለመሆኑ የአደባባይ ሚስጥር እንደሆነም ሪፖርተር ያነጋገራቸው ይናገራሉ፡፡ ቻይኖቹ አዘውትረው ገንዘባቸውን  ወደአገራቸው የሚልኩት በባንክ በኩል ሳይሆን በከተማው ውስጥ የቻይና ሬስቶራንቶች ባለቤት ከሆኑት ጋር በመመሳጠር፣ በእነሱ በኩል በጥቁር ገበያ አማካይነት ገንዘብ የሚያስወጡ መሆኑን አጥብቀው የሚያውቋቸው ይናገራሉ፡፡ ጠጠር አምርተው የሚሸጡ ሁለት የቻይና ኩባንያዎች ሹዋን ሎንግ እና ጁ ሎንግ እንደሚባሉ ጭምር ተገልጿል፡፡ እነዚህ እንግዲህ ጠጠር ለማምረት ፈቃድ ያልተሰጣቸው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከአትክልትና ፍራፍሬ ጀምሮ እስከ ራቁት ዳንስ ቤት ሳይቀር የሚቸረችሩ ቻይኖች በአዲስ አበባ መበራከታቸው እየታየ፣ በየጓዳው ያልተፈቀደላቸውን ሥራ በድብቅ ከመሥራት አልፈው በኢትዮጵያውያን ስም ፈቃድ በማውጣት የሚነገዱ እንዳሉም ወጣቱ በስብሰባው ወቅት ተናግሯል፡፡ በዘበኞቻቸውና በሾፌሮቻቸው ስም ንግድ ፈቃድ እያወጡ ለውጭ አገር ዜጎች የተከለከሉ መስኮች ላይ በመሠማራት እንደሚሠሩ ሲነገር የቆየ ቢሆንም፣ አንድም የመንግሥት አካል ዕርምጃ ስለመውሰዱ አስታውቆ አያውቅም፡፡ የቻይና መንግሥት እንዳይቀየም የሰጉ ይመስላሉ የሚል ስሞታ ለመንግሥት ባለሥልጣናት እየቀረበባቸው ይገኛል፡፡

የቻይኖቹን የገንዘብ መንገድ የሚያውቁት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ኦዲተሮችና አካውንታንቶች፣ በአንድ ወቅት በቡድን ሆነው የባለሥልጣኑን ማኅተም በማስቀረፅ በየቻይኖቹ ደጅ እየሄዱ ከባለሥልጣኑ የተላኩ በማስመሰል ከፍተኛ ገንዘብ ይቀበሉ እንደነበር፣ ይህንንም ጉዳይ ለባለሥልጣኑ ኃላፊዎች አቤት ብሎ እንደነበር ወጣቱ የሪፖርተር ምንጭ አስታውቋል፡፡

ባለሥልጣኑ ከውስጥም ከውጭም እንዲህ ለሙስናና ለማጭበርበር መጋለጡ ብቻ ሳይሆን በእውነት ለመሥራት ብለው የሚመጡት ቻይኖች የአገሪቱን ገጽታ በመጥፎ መልኩ እንዲገነዘቡት የሚያደርግ መሆኑ እንደሚያሳስበው ወጣቱ ተናግሯል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ በቻይናውያን ዘንድ በሙስና የታወቀች ሆና ተገኝታለች፤›› ያለው ወጣት፣ በትክክለኛው መንገድ ቢዝነስ ለመሥራት የሚመጡ ቻይኖች  በየቦታው ሲሄዱ ገንዘብ እየተጠየቁ ደንግጠው እንደሚጠፉ ተናግሯል፡፡ በቅርቡ የዓለም ባንክ ይፋ ያደረገው ጥናት ሙስና በአገሪቱ ሕዝብ ዘንድ እንደሚሰጠው ግዙፍ ሥዕል የገዘፈ አይደለም ማለቱ ቢታወቅም፣ ዋናውን የመንግሥት ገቢ ሰብሳቢው አካል በከባድ ሙስና ወንጀል የሚጠረጠሩ ባለሥልጣናት ሲመሩት እንደቆየ ከሰሞኑ ግርግር ለመረዳት ተችሏል፡፡

እንዲህ ያሉ ወቅታዊ የቻይኖችን አሳሳቢ እንቅስቃሴ ይፋ ያደረገው ስብሰባ፣ የተለመዱና ባለሥልጣኑ ላይ ሲሰነዘሩ የከረሙ ሌሎች ትችቶችንም ያስተናገደ ነበር፡፡ የማዕድን ዘርፍ እየተቀለደበት ነው ያሉት ከምሥራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ግብር ከፋይ የሆኑ ነጋዴ ናቸው፡፡ ምንም እንኳ የከበረ ድንጋይ አገር ውስጥ የማይሸጥ ቢሆንም 20 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ እንደተጣለበት፣ ይህም ሳያንስ ለሚያመጡት ማሽን ቀረጥና ታክስ ክፈሉ መባሉ (መንግሥት ቅርፅ ያልወጣለት የከበረ ድንጋይ ለውጭ ገበያ እንዳይቀርብ ዕገዳ ጥሏል) መስኩ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የሚመደብ ቢሆንም፣ ባለሀብቶች እንደማይበረታቱበት ሲናገሩ ለውጤቱ ማሳያ ያደረጉት አገሪቱ በየዓመቱ ከዘርፉ የምታገኘውን የ4.5 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በመጥቀስ ነበር፡፡ በአንጻሩ እንደህንድ ያሉ አገሮች ከኢትዮጵያ በጥሬው የሚረከቡትን የከበረ ድንጋይ (ከራሳቸውም ጭምር) በማስዋብና በቅርፅ በማበጀት በዓመት እስከ 35 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚያገኙበት ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ሁሉ ባሻገር ሙስና ሲሠራ ያየና የጠቆመ ሰው ‹‹አንተን ብሎ ጠቋሚ›› ተብሎ መታሰሩን እንደሚያውቁ የገለጹት እኒህ ባለሀብት፣ ሥጋታቸውንና ምክራቸውን ጨማምረው ተናግረዋል፡፡ ‹‹ግድ የላችሁም እንተማመን ወንጀል ሠርተን የትም አናመልጥም፡፡ እናንተም የትም አታመልጡም ሰሞኑን እያየነው ነው፡፡ ለአንድ ዓላማ ከቆምን (የአንድ ዓላማ እኩል ባለድረቦች ነን የሚለውን የባለሥልጣኑን መፈክር በመንተራስ) ባለማወቅ የሚፈጸሙ ስህተቶችን ሆነ ተብለው ከሚፈጸሙት ጋር ለይታችሁ ተመልከቱ፤›› በማለት አስተያየታቸውን ያቀረቡት ጋስ የተባለውን የግል ኩባንያ ወክለው እንደመጡ የገለጹ ነጋዴ ሲሆኑ፣ ይህንን ቅሬታቸውን ያቀረቡትም ከሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ ቀላል ስህተቶችን ባለሥልጣኑ አክብዶ በማየት ለከፍተኛ ቅጣትና እስር እንደሚያበቃ በማስታወስ ነው፡፡

ግብር ከፍለው የማያውቁ ሰዎች ግብር በመክፈል አበሳውን ከሚያየው ዜጋ እኩል፣ አንዳንዴም ከዚያም በላይ የጥቅም ድርሻ እንዲያገኙ መንግሥትም ዕድሉን እንደሚፈጥርላቸው የገለጹት ደግሞ ሚካኤል መኮንን የተባሉ ነጋዴ ናቸው፡፡ ከኪነ ጥበብ ሙያ ጋር የተገናኙ ሥራዎችን የሚያካሂዱት እኒህ ግለሰብ እንደገለጹት፣ መንግሥት በቅርቡ እንኳ ገቢያቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ሰዎች በማለት የቤት ልማት ፕሮግራሙ ላይ ማለትም የ20/80 አሠራርን ምሳሌ ሲያደርጉ በዚህ የቤት ባለቤት ለመሆን ከሚመዘገቡ ሰዎች ውስጥ ግብር ከፍለው የማያውቁና ቅድሚያ ሁሉ የተሰጣቸው ሰዎች የሚያገኙትን ገቢ ጠቅሰው እንዲመዘገቡ ማድረጉን በመግለጽ  ተችተዋል፡፡ በአንጻሩ ግን ከ151 ብር ጀምሮ ገቢ ያላቸው ሰዎች ግብር የሚከፍሉ ሰዎች ከማይከፍሉት ጋር እኩል እንዲጋፉ መደረጉን በመጥቀስ የመንግሥትን አሠራር ነቅፈዋል፡፡ ለግብር ከፋይ ቅድሚያ የማይሰጥ ብቻ ሳይሆን ማግኘት የሚገባው ጥቅምም በመንግሥት ዕውቅና ግብር ከፋይ ላልሆኑ ሰዎች ተላልፎ እንደሚሰሰጥበት ተናግረዋል፡፡ ባልተከፋፈለ የትርፍ ድርሻ ላይ የተከማቸ ፍሬ ግብር ከነመቀጫውና ወለዱ እንድንከፍል ተደርገናል (ምንም እንኳ መቀጫው ተነስቷል ቢባልም)፣ የጉምሩክ ዋጋ አሰቃይቶናል፣ የግብር ከፋይነት መለያ ኖሮት የፌደራል ግብር ከፋይ ያልሆነ ነጋዴ በክልሎች አሠራር መቸገሩን የሚተቹና ሌሎችም ስሞታዎችን ያደመጠው የባለስልጣኑ ስብሰባ በለውጥና ሞደርናይዜሽን ሥራዎች ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አብርሃም ንጉሤ፣ እንዲሁም በምሥራቅና በምዕራብ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ መሥርያ ቤቶች ኃላፊዎች ታጅቦ የተካሄደ ሲሆን፣ ከሌሎቹ ጊዜያት የባለሥልጣኑ ስብሰባዎች በተለየ መልኩ የተካሄደም ነበር፡፡ እነዚህ ኃላፊዎች ለተሰነዘሩባቸው ተችቶችና ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ያልፈለጉበት፣ ይልቁንም የቀረቡትን ሐሳቦች እንደሚቀበሉና በቀጣዩ ጊዜ ሲገናኙ ምላሽ የሚያቀርቡ መሆናቸው ገልጸው፣ ግብር ከፋዩን ያሰናበቱበት መድረክ ነበር፡፡ ከአንዳንድ ታዛቢዎች እንደሚደመጠው፣ በአሁኑ ወቅት ያሉት ኃላፊዎች በእስር ላይ ከሚገኙት የቀድሞ ባለሥልጣናት መታሰር ጋር በተያያዘ ድንጋጤ ብቻ ሳይሆን በቀጥታ ውሳኔ መስጠቱን እየፈሩ እንደሚታዩ፣ አንዳንዴም በአደባባይ ‹‹በሕግና በመመርያ ብቻ እንሠራለን እስር ቤት የሚወረወርላችሁ የለም›› እስከማለት መድረሳቸውን የታዘቡ አካላት የሚናገሩት ነው፡፡

 

Seeds of Change in Ethiopia

Posted on

Organizing the Determined:  Thousands march in the capital

by Graham Peebles | Counterpunch.org

June 19, 2013

The people of Ethiopia have been suppressed and controlled for generations. Under the current EPRDF government, freedom of expression has been curtailed and an atmosphere of fear and intimidation fostered. Peaceful assembly has not been allowed, contrary to the constitution, and all political dissent stamped on.

In 2005, after parliamentary elections that many, including the European observers, deemed to be unfair, students took to the streets in the capital Addis Ababa to demonstrate against what they saw as electoral fraud. The regime responded to this democratic display by deploying armed security personnel who killed, Human Rights Watch (14/06/2005) reported, “dozens of protesters and arbitrarily detained thousands of people across the country.” Some estimate that up to 200 people were killed by government forces.

Unsurprisingly, since then the streets of Addis Ababa and other major towns and cities have been quiet, and people have felt unable to protest, until Sunday 2nd June 2013, when the relatively new Smayawi (Blue) Party, to their credit, organized demonstrations at various sites across the capital. Reuters report that around 10,000 people participated, although local people put the figure much higher. Throngs of mainly young people marched through the city, demanding, The Guardian (2/06/2013) state, that the “government releases political leaders and journalists, and tackles corruption and economic problems”. Protesters carried banners reading “Justice! Justice! Justice!” Some held “pictures of imprisoned opposition figures,” others chanted: “We call for respect of the constitution.”

Members of opposition parties and journalists critical of the government are amongst those who have been falsely arrested and charged under the universally condemned Anti-Terrorism Proclamation. Human Rights Watch (HRW) report that “thirty journalists and opposition members were convicted” in 2012 under, the “vague” law introduced in 2009, granting the Ethiopian authorities what Amnesty International (7/07/2009) described as “unnecessarily far-reaching powers”. They went on to make clear that the legislation “restrict[s] freedom of expression, peaceful assembly and the right to fair trial.” It contains an easily distorted, ambiguous definition of terrorism, covering legitimate political dissent and “damage to property and disruption to any public service, for which an individual could be sentenced to 15 years in prison or even the death penalty.” (Ibid)

Under this draconian law that is being used, HRW says, “to target perceived opponents, stifle dissent, and silence journalists… freedom of expression, assembly, and association have been increasingly restricted.” Allied to the Charities and Societies Proclamation, which regulates nongovernmental organisations and “the government’s widespread and persistent harassment, threats, and intimidation of civil society activists, journalists, and others who comment on sensitive issues or express views critical of government policy”, a cocktail of suppression and fear has been created, the effects of which have “been severe”. Human rights workers have been forced to flee the country, groups have closed down and/or “scaled-down” their operations to exclude human rights work. Independent media have also been effected “more journalists have fled Ethiopia than any other country in the world due to threats and intimidation in the last decade—at least 79, according to the Committee to Protect Journalists (CPJ)”. Such unjust laws have been employed by the EPRDF government to control the people, who are at long last demanding such means of repression be repealed.

The time for change is now

 2011 saw the rise and pragmatic, peaceful expression of ‘people power’, as mainly young people across Northern Africa rose up against injustice, demanding freedom and an end to war. It was the year Time magazine named ‘The Protestor’ their person of the year, people they said, “dissented; they demanded… they embodied the idea that individual action can bring collective, colossal change.” Since what became known as the ‘Arab Spring’, Greece, Spain, Russia, Syria of course, currently Turkey, even Iran, have all seen popular uprisings against injustice, corruption and suppression. Unified actions, consistently spearheaded by young people, the occupy movement in America, Britain and elsewhere, calling for economic justice, sharing and social equality.

Extraordinary events, in what seems to be a unique time, “unlike anything in any of our lifetimes” as Time magazine described the historic happenings of 2011. A time in which it is not only possible to imagine the realisation of perennial ideals of old: the brotherhood of man, universal happiness and peace but a growing necessity. Such perennial jewels, held firmly within the hearts and minds of many throughout the world and dependent upon the inculcation of pure democratic principles: sharing, (social) justice and freedom, require new and inclusive political/economic/social forms to be built in order to accommodate the demands for change. The old structures, built on divisive foundations, are worn out and inadequate, and they do not serve the needs of the vast majority of people (“the 99.9%”). Governments like the EPRDF, that reinforce injustice, violate human rights and deny their citizens freedoms are out of step with the times and must be swept aside.

With over 65% of the population of Ethiopia under 25 years of age, and a median age of just 17, the young are an army; peaceful, unified and motivated, these young men and women are the great hope for the country. They know well that sharing and justice are the keys to peace and freedom, common-sense truths that the men of the past, acting from narrow ideological positions that distort and corrupt, do not understand. They cling to power and privilege, fearful of the changes that the people demand.

Unity is the key

The need for unity is a worldwide need; in a country where over 70 different ethnic tribal groups speaking dozens of dialects, make up a population of 85 million, unity is essential if there is to be fundamental social change in Ethiopia.

A single demonstration as seen in Addis Ababa on Sunday 2nd June, rightfully calling for justice – long overdue and the release of political prisoners, whilst highly significant and encouraging, will have little effect unless it serves as the beginning of a coordinated, strategic movement. Dictatorships such as the one enthroned in Addis do not suddenly renounce brutality and, seeing the light, embrace democratic ideals of freedom and participation. Relentless, orchestrated peaceful calls for liberty, for justice and the observation of human rights need to be made by the people of Ethiopia, establishing an unstoppable movement, a peoples tsunami, that will wash away all opposition to change. Let Meskel square in Addis Ababa become the Ethiopian Tahrir Square of Egypt’s protests.  A unified, inspired response to the impulse for change is needed, led by the young people of Ethiopia, organised and determined, uniting under one banner; justice, freedom and peace for all.

Graham Peebles is director of the Create Trust. He can be reached at: [email protected]

የሙስና ምርመራ እየተወሳሰበ ነው

Posted on

መበላላት እንዳይጀመር ስጋት አለ

By Goolgule.com

June 18, 2013

Sheraton Addis
Sheraton Addis

በጉምሩክና ገቢዎች ባለስልጣን የተጀመረው የጸረ ሙስና ዘመቻ ተከትሎ እየተካሄደ ያለው ምርመራ እየተወሳሰበ መሔዱ ተሰማ። በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ተከሳሾች የሚሰጡት መረጃ መበላላት ያስነሳል የሚል ፍርሃቻ እያስነሳ ነው። “ሰፈር የለየው” የጸረ ሙስና ዘመቻ የፈጠረው ስጋት የሃይል ሚዛን የያዙትንም ስጋት ውስጥ ከትቷል።

በኢትዮጵያ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ የታየው የውስን ሰዎች በድንገት በመበልጸግ ከባለስልጣኖችና ከከፍተኛ የስርዓቱ ሰዎች ቤተሰቦች ጋር በሚከናወን መተሳሰር አማካይነት እንደሆነ ከህዝብ የተሰወረ አይደለም። ሰሞኑንን ይፋ የተደረገው የባንክና የንብረት እግድ እንዳመለከተው የዝርፊያው ሰንሰለት በቤተሰብ የታጠረ መሆኑን ነው።

አቶ መለስ ከድነው ያቆዩትና የሳቸውን ሞት ተከትሎ ከፖለቲካው ልዩነት ጋር በተያያዘ እንደተጀመረ የሚነገርለት የጸረ ሙስና ዘመቻ፣ በመንግስት በኩል “ቆራጥ” አቋም የተያዘበት እንደሆነ ቢነገርም አስጊ ሁኔታ እየተፈጠረ ስለመሆኑ የጎልጉል የጸረ ሙስና ኮሚሽን ምንጮች ይናገራሉ።

እየተካሄደ ካለው ምርመራ በተገኙ ጭብጦች መታሰር የሚገባቸው ባለስልጣናት እንዳሉ የሚጠቁሙት እነዚሁ ክፍሎች፣ ምርመራው እየሰፋና እየጠለቀ ሲሄድ ችግር ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ማሳደሩን አይሸሽጉም።

“የመጨረሻው መጠፋፋት መጀመሪያ ላይ እንዳሉ የሚሰማቸው አሉ” በማለት ለጎልጉል መረጃ የሰጡት ክፍሎች “እየሰፋ የሄደውንና መጨረሻው ወዴት እንደሚያመራ የሚታወቀውን የጸረ ሙስና ዘመቻ የማስቆም ፍላጎት እንዳለ የሚያመላክቱ ሁኔታዎች በቢሮ ደረጃ እየሰማን ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ዘመቻው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት የሚሉ ክፍሎች ስላሉ በሙስና የሚጠረጠሩ ፕሮጀክቶችና ከፍተኛ ግንባታዎችን አስመልክቶ በስፋት መረጃ የሚደርሰው ኮሚሽኑ፣ ከነገ ዛሬ ይመጣብናል በሚል የተፈጠረው መደናገጥ በህገወጥ ሃብት የሰበሰቡትን በሙሉ ስጋት ላይ ጥሏቸዋል። በባንኮች አካባቢ ገንዘብ የማሸሽ፣ ከዶላር ገበያ ራስን የማግለልና የሃይል ሚዛን በመመልከት የመተጣጠፍ ሩጫ በስፋት እንደሚስተዋል የጎልጉል ሰዎች ተናግረዋል።

በሙስናው ሰለባ የሆኑት ቡድኖች አቅማቸውና ትስስራቸው ቀላል ባለመሆኑ፣ የታጠቁ ሃይሎችም ስላሉበት የርስ በርስ መተላለቅ ሊከተል ይችላል በሚል ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚደረግ ያመለከቱት ምንጮች “አቶ መለስ የዘረጉትን ሰንሰለት ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠር ችግር እየታየ ነው። መተላለቁ በዚህ ክፍተት ውስጥ ሊከሰት ይችላል” የሚል ስጋት መንገሱን አመልክተዋል።

የሚታወቁ ባለስልጣናትና የክልል አመራሮች “ልማታዊ” ከሚባሉት ኢህአዴግ ሰራሽ ባለሃብቶች ጀርባ ሆነው ፕሮጀክትና ጨረታ በማጸደቅ ምዝበራውን እንደሚመሩ መረጃ ስለመኖሩ የሚናገሩት ምንጮች፣ “በቅርብ ተመስርተው ከፍተኛ ሃብት በሰበሰቡ ሪል ስቴት፣ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች፣ አስመጪና ላኪዎች፣ ሰፋፊ መሬት ለአረብ አገር ባለሃብቶች በማስማማት አየር በአየር የሚጫወቱ፣ በአገሪቱ ከሚታዩት ታላላቅ ግንባታዎች ጋር በተያያዘ ወዘተ ዋናዎቹ ባለስልጣኖችና ቤተሰቦቻቸው ተዋናይ መሆናቸው ይታወቃል። የህወሃት ሰዎች ግንባር ቀደም ናቸው” በማለት የስጋቱን መጠን ይገልጻሉ።

ከአገር ውስጥ በተጨማሪ በአፍሪካና በተለያዩ አገራት የሽርክና ንግድ የከፈቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዳሉ የሚገልጹት የኢህአዴግ የቅርብ ሰዎች “አሁን አመራር ላይ ያሉት የህወሃት ሰዎች የእነዚህን ባለስልጣናት በቤተሰብና ከፍተኛ አቋም በገነቡ ድርጅቶች አማካይነት የተበተቡት ሰንሰለት በቀላሉ መበጠስ ስለማይችሉ የሙስናው ዘመቻ አደጋ ይገጥመዋል። አለያም እርስ በርስ መበታበት ሊከተል ይችላል” በሚል ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቀረጥ ነጻ በማስገባት ከፍተኛ የመንግስት ገቢ ለግል ተጠቅመዋል በሚል በተከሰሱት ሰዎች ላይ እየተካሄደ ባለው ምርመራ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ በከፍተኛ ባለስልጣናት ትዕዛዝ አማካይነት የቀረጥ ነጻ ፈቃድ መስጠታቸውን ለምርመራ መኮንኖች መናገራቸውን የጎልጉል ምንጮች አመልክተዋል።

በዚህም የተነሳ ሸራተንን ተገን ያደረጉት የባለሃብቱ ወኪል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መውደቃቸው ተሰምቷል። በነባር የህወሃት ሰዎች የማይወደዱት እኚሁ የባለሃብቱ ወኪል፣ ወ/ሮ አዜብን፣ አቶ አዲሱ ለገሰና የባለሃብቱ ዋና ሸሪክ የሆኑትን አቶ በረከትን ቢተማመኑም ምርመራው ወደእርሳቸው ሊሄድ እንደሚችል የጎልጉል ምንጮች ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል። አንዳንዶቹ የቀድሞ ሸሪኮቻቸው ስልካቸውን ስለማያነሱላቸው ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውና ከወትሮው የተለየ ያለመረጋጋት እንደሚታይባቸው የቅርብ ሰዎቻቸውን ሳይቀር ሰላም እንደነሳ ለማወቅ መቻላቸውንም ተናግረዋል።

አብዛኛውን የንግድ በሮች በስጋ ዘመዶቻቸውና በአገር ልጆች ተብትበው የያዙት የባለሃብቱ የኢትዮጵያ ወኪል ምርመራ ዙሪያ የሚነሱትን ጉዳዮች ከመጥቀስ የተቆጠቡት ምንጮች፣ በቅርቡ አዲስ ነገር እንደሚሰማ መረጃዎች እንዳሏቸው አመልክተዋል። ለሸራተኑ ሰውና ለሸራተኑ ቡድኖች እጅግ ቅርብ ነን የሚሉ በበኩላቸው “ወ/ሮ አዜብ መስፍንና አቶ አዲሱ ለገሰ እስካልተነኩ ድረስ ሸራተን ሰላም ነው። አቶ ጌታቸውም እዛው ናቸው” ሲሉ የለበጣ ቀልድ ቀልደዋል። እነዚሁ ክፍሎች ቢያንስ “የኤች አይ ቪ/ኤድስ እድሜ ማራዘሚያ እናመርታለን፣ ለወገን እንደርሳለን በሚል ሰበብ በከፍተኛ ማጭበርበር የተፈጸመውን ወንጀል ጉዳይ ዝም አይበሉት” ሲሉ ለጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ አደራቸውን አስተላልፈዋል።

አቶ ተስፋዬ ኢሬሣ በሙስና ላይ ምስክር ለመሆን ሲዘጋጁ ተገደሉ

ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ

By Goolgule.com

June 17, 2013

murder

በነበራቸው የስራ ሃላፊነት በድብቅ መረጃ ሲያሰባስቡ ቆይተው ለመንግስት ካጋለጡ በኋላ ራሳቸውን ደብቀው የነበሩት አቶ ተስፋዬ
ኢሬሣ ምሳ እየተመገቡ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። አቶ ተስፋዬ ሰኞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት
ከኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ቀጠሮ ይዘው ነበር።

በቅርቡ ወደ ፌደራል መንግስት የተዛወሩት የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኡሞት ኦባንግ፣ ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ
አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን
የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር በማደራጀት ለኢህአዴግ ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ አሟሟታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ ከፍተኛ ምስጢር ያላቸውን ሰነዶች በመያዝ ከመታሰራቸው በፊት መሰወራቸውን፤ “የቢሮ ሃላፊው ይዘው
የተሰወሩት መረጃ አቶ ኦሞት የፈረሙባቸው ከፍተኛ የገንዘብ ሰነዶችና ሙስና የተከናወነባቸው የኮንስትራክሽንና የተለያዩ
መረጃዎች ናቸው። መረጃዎቹ አንድ ቀን ህዝብ ፍርዱን ይሰጥ ዘንድ ይፋ ይሆናሉ” በሚል ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ በ (ጥቅምት
19፤2005/October 29, 2012) መዘገቡ ይታወሳል።

ቀደም ሲል የጋምቤላ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ከላይ የተጠቀሰውን የሙስና ወንጀል በማጋለጣቸው ጋምቤላ
መኖር ሳይችሉ ቀርተው ራሳቸውን ሸሽገው ለመኖር ተገደው እንደነበር የሚያውቋቸው ለጎልጉል አስረድተዋል።

“አቶ ተስፋዬ ሙስናን በማጋለጣቸው በፍርሃቻ ራሳቸውን ደብቀው ሊኖሩ አይገባም” በማለት ኢህአዴግ ከለላ እንደሚሰጣቸው ቃል
በገባላቸው መሰረት ከተሸሸጉበት የወጡት አቶ ተስፋዬ ሰንጋተራ ትንሳዔ ሆቴል ከጋምቤላ ልጆች ጋር መገናኘት ይጀምራሉ።

ባለፈው ሳምንት ከፌዴራል የጸረ ሙስና ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ ከያዙ በኋላ ኮሚሽነሩ በድንገት ለለቅሶ ወደ
ጎንደር በመሄዳቸው ቀጠሮው ለሳምንት ይራዘማል። ለሰኞ (ሰኔ10፤2005) አዲስ ቀጠሮ ይይዛሉ።

በስልክ ያነጋገርናቸው ትንሳዔ ሆቴል አካባቢ እንደነበሩና ለጉዳዩ ቅርበት እንዳላቸው የሚገልጹ የጋምቤላ ተወላጅ የስራ ሃላፊ
እንዳሉት አቶ ኦሞት ኦባንግ ለአቶ ተስፋዬ ስልክ ደውለው ነበር። አቶ ተስፋዬ ህይወታቸው ከማለፉ ሁለት ቀን በፊት የቀድሞው
የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኦሞት በስልክ ተማጽንዖ አቅርበው ነበር።

አቶ ኦሞት “እውነት ነው ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀጠሮ የያዝከው?” በማለት ይጠይቃሉ

“አዎ! እውነት ነው” በማለት አቶ ተስፋዬ መልስ ይሰጣሉ።

አቶ ኦሞት መልሰው “እንግዲያውስ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከመግባትህና ከማነጋገርህ በፊት ሁለታችን መገናኘት አለብን።
የምንነጋገረው ነገር አለ” የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ። አቶ ተስፋዬ ስለ ስልክ ልውውጡ እንደነገሯቸው የተናገሩት እኚሁ ሰው፣ አቶ ኦሞት
በስልክ ደጋግመው በመደወል ያቀረቡትን የ”እንነጋገር” ጥያቄ አቶ ተስፋዬ አልቀበልም ይላሉ።

ጋምቤላ ስራቸውን ለቀው ራሳቸውን ደብቀው የኖሩት በእርሳቸው ምክንያት መሆኑን፣ ፍትህ እንደሚፈልጉ፣ አሁን ለመነጋገር ጊዜው
እንዳልሆነ፣ ዘርዝረው ለአቶ ኦሞት መናገራቸውን ያወሱት የጎልጉል ምንጭ፣ ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው አቶ ኦሞት በንዴት
ተዛልፈው ነበር።

ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው እንግዲህ አቶ ተስፋዬ ትንሳዔ ሆቴል ሰዎችን በመላላክና በመታዘዝ ከሚኖር አንድ የጋምቤላ ሰው /አቶ
ተስፋዬ የሚረዱት በምግባር ጉዳይ የሚታማና ጸበኛ የሚባል ሰው ነው/ አብረው ተቀምጠው ምሳ እየበሉ ሳለ አቶ ተስፋዬ አረፋ
ይደፍቃቸዋል።

ወዲያው ከተቀመጡበት ተንሸራተው መሬት ይወድቃሉ። ቀጥሎም ሰውነታቸው ይዝልና ኮማ ውስጥ ይገባሉ። ከአፋቸው
እየተዝለገለገ የሚወጣው ፈሳሽ በመጨመሩና የተለያየ ርዳታ ቢደረግላቸውም ሊተርፉ ስላልቻሉ ሆስፒታል ተወስደው ህይወታቸው
ማለፉ ተረጋግጧል።

አቶ ተስፋዬ ሆስፒታል ከመድረሳቸው በፊት እንደሞቱ የሚናገሩት የጎልጉል ምንጭ አሟሟታቸው ከመርዝ ጋር የተያያዘ እንደሆነ
ተናግረዋል። አቶ ተስፋዬ በሙስና ወንጀል ላይ ያሰባሱትን መረጃ ለተለያዩ አካላት የበተኑ ስለሆነ እሳቸውን በመግደል ማድበስበስ
እንደማይቻል አስታውቀዋል።

አቶ ተስፋዬ ሙስና ካጋለጡ በኋላ መሰወራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው። በተያያዘ በጋምቤላ ኢንቨስትመንት ላይ ከተሰማሩ
ባለሃብቶች ውስጥ ከ70በመቶ በላይ የሆኑት የህወሓት የቀድሞ ታጋዮች የነበሩና የክልል አንድ ተወላጆች መሆናቸው የአቶ ተስፋዬን
አሟሟት ይበልጥ ውስብስብ እንዳደረገው አስተያየት እየተሰጠ ነው፡፡

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ “የአቶ ተስፋዬ ሞት አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው። ብዙ ሳይታወቅ
የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ” በማለት ስለ አቶ ተስፋዬ ሞትና አሟሟት መረጃ እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።

“አቶ ተስፋዬ ለእውነት ሲል ሞቷል። ኢህአዴግ ውስጥ በርካታ የወንጀል መረጃ ያላቸው ወገኖች አሉ። እንዲህ ያሉ ዜጎች
በየትኛውም ዘመን አይረሱም። የቀን ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ስማቸውና ታሪካቸው ከጨዋነታቸው ጋር ተመልሶ ህያው ይሆናል።

ሌቦችና ነፍሰገዳዮች ወደ ህግ ሲያመሩ፣ እንደ አቶ ተስፋዬ አይነቶቹ የመጪው ትውልድ ታላቅ ምሳሌ ሆነው እየተወደሱ ህያው
ሆነው ይኖራሉ” የሚል አስተያየት የሰጡት አቶ ኦባንግ፤ አቶ ተስፋዬ ያሰባሰቧቸው የሙስናና ተመሳሳይ ወንጀሎች ማሳያ ሰነዶች
እጃቸው ላይ ስላለ አቶ ተስፋዬን በመግደልና በማስገደል ወንጀል ማድበስበስ እንደማይቻል ተናግረዋል።

የአቶ ተስፋዬ የቀብር ስነስርዓት ጋምቤላ መፈጸሙን ለመረዳት ተችሏል። ቤተሰቦቻቸውን በማግኘት ሆስፒታሉ ስለ አሟሟታቸው
የሰጠውን አስተያየት ጠይቀን ለመረዳት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም።

World Cup: Fifa investigation puts Ethiopia progress in doubt

Posted on

Ethiopia’s progress to the final round of African World Cup qualifying is in doubt after Fifa opened disciplinary proceedings  against them on Sunday.

By BBC

June 16, 2013

Ethiopian National Team

Earlier in the day, the East Africans beat South Africa 2-1 in Addis Ababa to seemingly reach the African play-offs.

However, they now face accusations they fielded an ineligible player in the 2-1 win over Botswana on 8 June.

Fifa rules state any team found guilty of that offence “will be sanctioned by forfeiting the match”.

Ethiopian Football Federation president Sehilu Gebremariam is still confident his side can progress.

“This is shocking news – but the point is that we are still leading the group, we believe that we shall still qualify for the next stage,” he told the BBC’s Newsday programme.

“We are scrutinizing the situation and we will give information to Fifa and to the public.”

He said they would be consulting the coaching staff to get their views on the situation before reacting further.

Football’s world governing body is also investigating Togo and Equatorial Guinea for the same reason.

A guilty verdict against all the sides would have serious ramifications in three of the qualifying groups for next year’s World Cup in Brazil.

Fifa rules on player ineligibility

Article 55 of the FIFA Disciplinary Code states:

  • If a player takes part in an official match despite being ineligible, his team will be sanctioned by forfeiting the match and paying a minimum fine of CHF 6,000

The case against the Ethiopians is pressing, as a guilty verdict would hand a lifeline back to 2010 World Cup hosts South Africa.

Currently five points off the top of Group A, South Africa would only be two points behind if the Ethiopians have to forfeit their victory against Botswana – and receive a technical defeat instead.

The announcement of Fifa’s probes will not only encourage South African football fans, but also those of Cameroon and Cape Verde.

Cameroon were beaten 2-0 by Togo on 9 June but the six-time World Cup qualifiers now stand to gain the three points should the Togolese be found guilty.

Such a scenario would move Cameroon, who currently trail Group I leaders Libya by two points, a point clear in the table.

The West Africans host Libya in what is both sides’ final encounter in September.

Equatorial Guinea allegedly fielded an ineligible player in their 4-3 defeat of island nation Cape Verde in March.

Fifa says they recently ruled on that matter and that the 2012 Africa Cup of Nations co-hosts have appealed the decision.

Should island nation Cape Verde receive the points from a match they originally lost, the passage of Tunisia to the African play-offs would also be in question.

The Carthage Eagles drew 1-1 in Equatorial Guinea on Sunday to seemingly book their place, but a technical victory for Cape Verde would lift the islanders up to nine points – just two behind the North Africans.

Tunisia host Cape Verde on the final day of the current qualifying stage.

አገር በቤተሰብ ስትዘረፍ ኢህአዴግ የት ነበር?

አዲስ አበባ የተገተሩት ህንጻዎችስ?

By Goolgule.com

June 15, 2013

ethio_poverty

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለስልጣናት፣ ባለሃብት፣ ደላሎችና ባለድርጅቶች በልጆቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም “ዘርፈው አስቀመጡት” የተባለው ንብረታቸውና የባንክ ሂሳባቸው መታገዱ ታወቀ። የዜናውን ይፋ መሆን ተከትሎ አዲስ አበባን ያጥለቀለቋት ህንጻዎችና የንግድ ድርጅቶች ጉዳይ ለምን ዝም ተባሉ የሚል ጥያቄ እየተሰነዘረ ነው።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር 54 ተሽከርካሪዎች ተይዘውባቸዋል። ገንዘቡን ሳይጨምር 54 ተሽከርካሪዎች በስማቸው ተመዝግበው የተያዙባቸው አቶ ነጋ ፣ የወ/ሮ አዜብ መስፍን የንግድ ሽሪክ እንደሆኑ የሚያውቋቸው ይገልጻሉ። በኢህአዴግ ጉባኤዎች ላይ የማይቀሩት አቶ ነጋ በየስብሰባው ወቅት ሻይና ቡና ሲሉ ከወ/ሮ አዜብ ጋር አብረው እንደሆነ የሚገልጹት ታዛቢዎች፣ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን “አትሌት ናቸው” በሚል ወደ ውጪ በጉቦ የላካቸው ሰዎች ጉዳይም ከሳቸው ጋር እንደሚያያዝ ይጠቁማሉ።

ከጨው ንግድ፣ ከካሜራ ፊልም ብቸኛ አስመጪነት ሌላ በአሁኑ ወቅት ሂልተን ጀርባ፣ አዲስ አበባ ስታዲየም ቪክ ሬስቶራንት ጎን ግዙፍ ህንጻ ያስገነቡት አቶ ነጋ ቃሊቲ ባላቸው የነዳጅ ማደያ የከፈቱት ብቸኛ የክብደት መለኪያ/የከባድ የጭነት መኪኖች የክብደት መለኪያ “የገንዘብ ማምረቻ ማሽን” አግባብነት የሌለው ቢዝነስ እንደሆነ ቅሬታ ሲቀርብበት የቆየ የግል የንግድ ተቋማቸው ነው። ቀደም ሲል ከኤርትራዊያን ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩት አቶ ነጋ ሃብታቸው በድንገት የተመነጠቀው ከ1991 ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጀምሮ እንደሆነ የሚያውቋቸው ይናገራሉ።

አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ ከኢህአዴግ የቀድሞው የኦዲት ኮሚሽን ጸሐፊ ከነበሩት አቶ አማኑኤል አብርሃና ከቴክኒክ ክፍል ሃለፊው መቶ አለቃ ዱቤ ጁሎ ጋር በጋራ ይሰሩ እንደነበር ለጸረ ሙስና ኮሚሽን ማስረጃ እንደደረሰው የገለጸ የጎልጉል ምንጮች፣ የፌዴሬሽኑ የውጪ ምንዛሬ ሂሳብና በአትሌቶች ስም ወደ ውጪ የተላኩ በርካታ ወጣቶች ጉዳይ እንደሚመመረመር ጠቁመዋል። ኮሚሽኑ ከበቂ በላይ መረጃ ቢኖረውም ማህበራትንና የርዳታ ድርጅቶችን መመርመር የሚያስችል ህጋዊ ውክልና ስለሌለው ሙስና አለባቸው በሚባሉት ማህበራትና ርዳታ ተቋማት ላይ ምርመራ ለማድረግ አዲስ ህግ ለማውጣት በዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል። የኢህአዴግ የንግድ ተቋም የሆነው ፋና ብሮድ ካስቲንግ ከዚህ የሚከተለውን አስፍሯል። በቤተሰብ ተዘረፈ የተባለው ሃብት በስም ዝርዝር ባለቤቶቹም ይፋ ሆነዋል።

በሙስና ቤተሰብ ስም የተከማቸ ሃብት ንብረቶች ታገዱ

በእነ አቶ መላኩ ፈንታ መዝገብ ተፈፀመ በተባለው የሙስና ወንጀል በ544 ተጠርጣሪዎች ድርጅቶችና በቤተሰቦቻቸው ስም በመንግስትና በግል ባንኮች የተቀመጡ ጥሬ ገንዘብ ፣ አክሲዮኖች እንዲሁም የከበሩ ማእድናት ታገዱ።

በሌላ በኩል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች እስካሁን 92 ተሽከርካሪዎች እገዳ ተጥሎባቸዋል።

ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ በአቶ ገብረዋህድ ባለቤት ኮረኔል ሃይማኖት ተስፋይ ስም የተመዘገቡ ሲሆኑ ፥ 54 የሚሆኑት ደግሞ በአቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄር ስም የተያዙ ናቸው።

ከተሽከርካሪዎች አራቱ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን የአዳማ ቅርንጫፍ ስራ አሰኪያጅ በነበሩት አቶ አሞኘ ታገለ ስም የተመዘገቡ ሲሆን ፥ ከውጭ የሚመጡ ባለሃብቶች ወደ ሃገር ቤት እቃዎቻቸውን ሳያስፈትሹ እንዲያስገቡ በማድረግ በእነርሱና በጉሙሩክ የስራ ሃላፊዎች መካከል ጉቦ በማቀባበል መንግስትን ጎድቶ ራሳቸውን ጠቅመዋል በሚል በተጠረጠሩት በአቶ ዳዊት መኮንን ስም  እንዲሁ አራት ተሽከርካሪዎች ተይዘዋል።

ሌሎች ሰባት ተሽከርካሪዎች በአልቲሜት ፕላን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲመዘገቡ ፥ ስድስት የሚሆኑት ተሽከርካሪዎች ደግሞ በኢትባ ኮንስትራክሽን ማሽነሪ አከራይ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ተመዝግበው ይገኛሉ።

የፌደራሉ የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ቡድን በተጠቀሱ ግለሰቦች ፣ ድርጅቶች እና ሌሎች አካላት እግድ የተጣለባቸው ተሽከርካሪዎች እንዳይሸጡ ፣ እንዳይለወጡ እና ለሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፉ አስደርጓል።

የእነ አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ እና ሌሎች መዝገቦችን ሳያካትት በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ በተዘረዘሩ ተጠርጣሪዎች ፥ ተፈጸመ በተባለው የሙስና ወንጀል  ከቀረጥና ታክስ ጋር በተያያዘ ከተገኙ ሰነዶች ብቻ መንግስት ከ 230 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት እንደደረሰበት ነው የሚለው የኮሚሽኑ መረጃ የሚያመለክተው። አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ)

በፌስቡክ “የኮንዶሚኒየም ዕድለኞች ስም ዝርዝር ይፋ ወጣ” እየተባለ የተዘበተባቸው የባንክ ሂሳባቸው የታገደባቸው ሙስ ስም ዝርዝር

አባቡ አለሙ ገብሩ
ምስጋናው ይስሃቅ እጅባ
በረከት ይስሃቅ እጅባ
ታደሉ አለምነው ተፈራ
ፀጋነሽ አለምነው ተፈራ
አባተ ጋሻው ቦጋለ
ጌጤ ጋሻው ቦጋለ
ዘርፌ ጋሻው ቦጋለ
ፀሐይ ጋሻው ቦጋለ
ትዕግስት ጋሻው ቦጋለ
አስፋው ጋሻው ቦጋለ
መብራት አበበ አብርሃ
ቤቴልሄም አማኑኤል ሰይፈ
እቁባይ ተከለ አርአያ
ብሌን አማኑኤል ሰይፈ
ሊዲያ አማኑኤል ሰይፈ
እየሩሳሌም ስማቸው ከበደ
መቅደላዊ ስማቸው ከበደ
ኤልሻዳይ ስማቸው ከበደ
ኢቫና ስማቸው ከበደ
አያልነሽ ይመር ጌታሁን
ሠለሞን ከበደ ካሳ
ምንትዋብ ከበደ ካሳ
ዳንኤል ደባሽ ሀገሩ
ናኑ ደባሽ ሀገሩ
ሰላማዊት ደባሽ ሀገሩ
ሣራ ደባሽ ሀገሩ
ኤፍሬም ነጋ ገ/እግዚአብሄር
ሄኖክ ነጋ ገ/እግዚአብሔር
ይትባረክ ነጋ ገ/እግዚአባሄር
ሠላም ነጋ ገ/እግዚአብሔር
ራሄል ነጋ ገ/እግዚአብሄር
ዮርዳኖስ ደሣለኝ ገ/እግዚአብሄር
ቅድስት ድጉማ ዋቅጅራ
አናኒያ ብርሃኔ እጅጉ
ተዋበች ወርቁ ወልፃዲቅ
ብሩክ ከበደ ታደሰ
ፍቅረማርያም ከበደ ታደሰ
ክብነሽ ከበደ ታደሰ
ዳኝነት ከበደ ታደሰ
ትዕግስት ከበደ ታደሰ
ሙሉነህ ከበደ ታደሰ
ትዕዛዙ ከበደ ታደሰ
ቴዎድሮስ ማዕረግ አዱኛ
አይንአዲስ በረከት ኃ/ጊዮርጊስ
ወይንሸት ወርቁ አንጋሶ
መብራቱ እጅጉ አበራ
የማነ ብርሃን እጅጉ አበራ
መሀሪ እጅጉ አበራ
ዮሐንስ እጅጉ አበራ
ለምለም እጅጉ አበራ
ሠናይት እጅጉ አበራ
ካሰች አምደመስቀል መገርሳ
ዮናታ ማርክነህ አለማየሁ
ኤልሻዳይ ማርክነህ አለማየሁ
ባልጊቴ አለማየሁ ወዳቦ
ባፋነ አለማየሁ ወዳቦ
አየለ አለማየሁ ወዳቦ
ብርሃኑ ዓለማየሁ ወዳቦ
አበራ አለማየሁ ወዳቦ
እጀትግስት ዓለማየሁ ወዳቦ
ሚካኤል አምደመስቀል መገርሳ
ዳኛቸው አምደመስቀል መገርሳ
ተረፈ አምደመስቀል መገርሳ
ተክሉ አምደመስቀል መገርሳ
ደርባቸው አምደመስቀል መገርሳ
መቅደስ አምደመስቀል መገርሳ
ትዝታ አምደመስቀል መገርሳ
ሙሉጸጋ አምደመስቀል መገርሳ
ውቢት ኃይለገብርኤል አስፋው
ያዕቆብ ደጉ ሆቢቾ
ዮናታል ደጉ ሆቢቾ
ዳግማዊ ደጉ ሆቢቾ
ኡፋይሴ ሆቢቾ አልቤ
ዲቃም ቤቢሶ አልቤ
ካሳሁን ኃይለገብርኤል አስፋው
አምሃ ኃይለገብርኤል አስፋው
ዝናሽ ኃይለገብርኤል አስፋው
ምሳዬ ኃይለገብርኤል አስፋው
አበባ ኃይለገብርኤል አስፋው
ፍሬህይወት ጌታቸው ሀብቴ
ጌታቸው ምስጋና ተፈሪ
ዮሴፍ ጌታቸው ምስጋና
ዮናታን ጌታቸው ምስጋና
ጌታቸው ሀብቴ ተክለሃይማኖት
አብረኸት ገብረመድህን ጣሰው
አበባው ጌታቸው ሀብቴ
ገስጥ ጌታቸው ሀብቴ
ደሳለኝ ጌታቸው ሀብቴ
ቤተልሄም ጌታቸው ሃብቴ
ዜና ጌታቸው ሀብቴ
ሳህሌ ገላው ፈንቴ
ላይኩን ውብየ ተሰማ
አበባው ላይኩን ውብየ
በትረወርቅ ላይኩን ውብየ
ዳዊት ላይኩን ውብየ
አብርሃም ለይኩን ውብየ
ህሉፍ አብርሃ ሐጎስ
አስመለሻ አብርሃ ሐጎስ
ስዬ አብርሃ ሐጎስ
አሰፋ አብርሃ ሐጎስ
ወ/ስላልሴ አብርሃ ሐጎስ
ትምኒት አብርሃ ሐጎስ
ፀሐይነሽ ገ/ሚካኤል ገብሩ
ንግስቲ ሳመሶነ ብሩ
እጅግጋየሁ ሳምሶን ብሩ
ኢትዮጵያ ሳምሶን ብሩ
ያለም መብራት ሳምሶን ብሩ
ቢተወደድ ሳምሶን ብሩ
ሚዛን ሳምሶን ብሩ
በእግዚአብሔር አለበል ኃይሉ
ኤልሳ ታደለ ኃይሉ
ናአምን በእግዚአብሔር አለበል
ቅዱስ በእግዚአብሄር አለበል
በረኽት በእግዚአብሄር አለበል
አለበል ኃይሉ አዱኛ
እቴነሽ ብሩክ ደስታ
ዘላለም አለበል ኃይሉ
ነፃነት አለበል ኃይሉ
የሰውዘር አለበል ኃይሉ
በሁሉም አለበል ኃይሉ
ሰላም አለበል ኃይሉ
ዮናስ ታደለ ኃይሉ
ሚካኤል ታዳለ ኃይሉ
ዮሴፍ አዳዩ ገብሩ
ሃና በርሄ ሀጎስ
ግሎሪ ዮሴፍ አዳዩ
ሊዮ ዮሴፍ አዳዩ
አዳዩ ገብሩ ዲኒ
አብርሃ አዳዩ ገብሩ
ራህዋ አዳዩ ገብሩ
ብርክቲ አዳዩ ገብሩ
ኢንዲሪያስ አዳዩ ገብሩ
ፋና አዳዩ ገብሩ
ታበቱ አዳዩ ገብሩ
ስላስ አውዓለ ሐጎስ
ኃ/ስላሰ በርሄ ሀጎስ
ተስፋይ በርሄ ሀጎስ
ብሩር በርሄ ሀጎስ
ዘቢብ በርሄ ሀጎስ
ጌታነህ ግደይ ንርኤ
ኤደን ብርሃነ ገ/ህይወት
አበባ ግደይ ንርኤ
ዙፋን ግደይ ንርኤ
ደስታ ግደይ ንርኤ
ዮሐንስ ግደይ ንርኤ
መንግስቱ ግደይ ንርኤ
ሀብቶም ግደይ ንርኤ
ቢኒያም ብርሃነ ገ/ህይወት
ኤልሻዳይ ብርሃነ ገ/ሕይወት
ብርክታዊት ብርሃን ገ/ህይወት
ገ/መድህን ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ገ/ህይወት ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ኪዳን ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ሱራፌል ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ብርያ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
እግዜሄሩ ወ/ጊዮርጌስ ወ/ሚካኤል
ግደይ ተስፋ ገ/ስላሴ
ስላስ ተስፋይ ገ/ስላሴ
ለተመስቀል ተስፋይ ገ/ስላሴ
ማህተመሥላሴ ጥሩነህ በርታ
ማሞ በርታ ባቦ
ታደሰ በርታ ባቦ
ዳዊት በርታ ባቦ
ብሩክ በርታ ባቦ
አበበች በርታ ባቦ
አመለወርቅ በርታ ባቦ
እመቤት በርታ ባቦ
ፍቅርተ በርታ ባቦ
ይልማ ፈንታ ቻይ
አንጋች ፈንታ ቻይ
ሸዋዬ ፈንታ ቻይ
ፈጠነ ታገለ አወቀ
ቻለ ታገለ አወቀ
እማዋ ታገለ አወቀ
አልጋነሽ ታጋለ አወቀ
እመቤት ታጋለ አወቀ
ዳዊት አሰፋ ዘውዱ
ትዕግስት አሰፋ ዘውዱ
ጥሩወርቅ አሰፋ ዘውዱ
ተወዳጅ አሰፋ ዘውዱ
መልካም አሰፋ ዘውዱ
ማህሌት አሰፋ ዘውዱ
ዝናሽ ብርሃኑ በሻህ
ነፃነት ብርሃኑ በሻህ
ፍሬህይወት ብርሃኑ በሻህ
አብዮት ብርሃኑ በሻህ
ግልነሽ ብርሃኑ በሻህ
ሰለሞን ብርሃኑ በሻህ
አዲስ ብርሃኑ በሻህ
ካህሳይ ጉላል አለመ
ዘውዲቱ ለምለም ገ/ማርያም
ብስራት ገ/መድህን ተስፋይ
ግርማይ ብስራት ገ/መድህን
ዮሀንስ ብስራት ገ/መድህን
አበባ ብስራት ገ/መድህን
ለተመስቀል ብስራት ገ/መድህን
ሚዛን ብስራት ገ/መድህን
አክበረት ብስራት ገ/መድህን
ገ/መድህን ሀጎስ ንጉሴ
ጌቱ ገ/መድህን ሀጎስ
ሳራ ገ/መድህን ሃጎስ
ፍፁም ገ/መድህን አብርሃ
ነፃነት ብርሃኑ በሻህ
አለም ስንሻው አማረ
ሐጎስ ፍፁም ገ/መድህን
ኃይሌ ፍፁም ገ/መድህን
ኤርሚያስ ፍፁም ገ/መድህን
ደሊና ፍፁም ገ/መድህን
ገነት ገ/መድህን ሀጎስ
ኮነ ምህረቱ እሸቱ
መንበረ ታምራት በየነ
ፍስሐ ኮነ ምህረቱ
ፍረህይወት ኮነ ምህረቱ
መስከረም ኮነ ምህረቱ
ቅድስት ኮነ ምህረቱ
ዘይሰድ ኢሳ አወል
ተስፋዬ ወልዱ ፍስሃ
ሰብለወንጌል ዘውዴ ዋለ
ዳንኤል ዘውዴ ዋለ
ሙሉቀን ዘውዴ ዋለ
ብርሃኑ ዘውዴ ዋለ
ጌትነት ዘውዴ ዋለ
ታምራት ዘውዴ ዋለ
አምባው ሰገድ አብርሃ
ብርነሽ ሐጎስ ካህሳይ
ህሊና አምባው ሰገድ
ብሩክ አምባው ሰገድ
ሜሮን ገ/ስላሴ ገብሩ
ሳባ ኪሮስ ወ/ገብርኤል
አፀደ ገ/ስላሴ ገብሩ
አብርሃ ገ/ስላሴ ገብሩ
ያሬድ ሰገድ አብርሃ
ክብሮም ሰገድ አብርሃ
ፀዳለ ሰገድ አብርሃ
ፅጌ ሰገድ አብርሃ
ፀሐይነሽ ሰገድ አብርሃ
ተክለአብ ዘርአብሩክ ዘማርያም
ፅጌረዳ ደርበው አዳነ
ዘርአብሩክ ዘማርያም ረዳ
ሂሩት ፀጋዬ ገ/መድህን
አቤል ተክለአብ ዘርአብሩክ
ምህረትአብ ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ሠላማዊት ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ፀጋዘአብ ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ሣምራዊት ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ዳንኤል ደርበው አዳነ
ሠላዊት ደርበው አዳነ
ሄሳን ደርበው አዳነ
ኤደን ደርበው አዳነ
ጌታሁን ቱጂ ደበላ
ምኞት ብርሃኑ አበራ
ሮዳስ ጌታሁን ቱጂ
አዴራት ጌታሁን ቱጂ
ሲሳይ ቱጂ ደበላ
እመቤት ቱጂ ደበላ
ጋሻው ብርሃኑ አበራ
አዲሱ ብርሃኑ አበራ
ሠላም ብርሃኑ አበራ
ክብረወሰን ብርሃኑ አበራ
ዘለቀ ልየው ካሳ
ግንቻየው አድሮ ኃይሉ
ዮሐንስ ዘለቀ ልየው
ሊዲያ ዘለቀ ልየው
ጥሩአለም አድሮ ኃይሉ
ዮሴፍ አድሮ ኃይሉ
ያዴሳ ሚዴቅሳ ዲባባ
ተናኜ እሸቴ አዳፍሬ
ሠላማዊት ያዴሳ ሚዴቅሳ
ገመቺሳ ያዴሳ ሚዴቅሳ
ብልሴ ያዴሳ ሚዴቅሳ
መኮንን ሚዴቅሳ ዲባባ
በጂጌ ሜዴቅሳ ዲባባ
ሽታዬ ሚዲቅሳ ዲባባ
ፅጌ ሚዴቅሳ ዲባባ
ልኪቱ ሞሲሳ ቦኮ
ከበደ ደጀኔ ገለታ
ፍስሐ ደጀኔ ገለታ
የሻነው ደጀኔ ገለታ
ዘላለም ደጀኔ ገለታ
ትዕግስት ደጀኔ ገለታ
መታሰቢያ ደጀኔ ገለታ
ሠናይት ደጀኔ ገለታ
መላኩ ግርማ ገብሬ
እህተ ቱኒ ኦርጋጋ
ብርሃኑ ግርማ ገብሬ
ጌትነት ግርማ ገብሬ
አብርሃም ግርማ ገብሬ
ዳዊት መኮንን ተመስገን
እሴታ ባረጋ ሽራጋ
አሚን ዳዊት መኮንን
ዘሪሁን ዳዊት መኮንን
ዜና መኮንን ተመስገን
ማርታ መኮንን ተመስገን
መኮንን ተመስገን የሽታ
ፍሬሕይወት ማሞ አና
መቅደስ ባረጋ ሽራጋ
ብርሃኑ ባረጋ ሽረጋ
ቅጣው ባረጋ ሽራጋ
ባረጋ ሽራጋ ሽራጋ
አስፋው ስዩም ታፈረ
ማርታ የማነህ ተስፈሚካኤል
መስፍን ስዩም ታፈረ
መንገሻ ስዩም ታፈረ
አንባቸው ስዩም ታፈረ
ሂሩት ስዩም ታፈረ
ሠላማዊት ግርማ ፈለቀ
በፀሎት አበበልኝ ተስፋዬ
ኪሮስ ገ/መድህን ገ/ተክለ
ትዕግስት ተስፋዬ ፊታሞ
ሊዲያ ተስፋዬ ፊታሞ
ሐዲያወርቅ ተስፋዬ ፊታሞ
ታሪኩ አበበ ፊታሞ
ፍስሃ አበበ ፊታሞ
ማርክስ አበበ ፊታሞ
ምንአለ አበበ ፊታሞ
ዘይነባ እሸቱ ኃይሌ
ኑርሃን ጌታቸው አሰፋ
ሐይመን ጌታቸው አሰፋ
ሰሚሩ ጌታቸው አሰፋ
ኢምራን ጌታቸው አሰፋ
የንጉስነሽ አሰፋ ሀምዛ
መንገሻ አሰፋ ሃምዛ
መሰለ አሰፋ ሃምዛ
ልዑልሰገድ አሰፋ ሀምዛ
መሐመድ አሰፋ ሀምዛ
ናስር እሸቱ ሃይሌ
ዛህር እሸቱ ሃይሌ
መሐመድ እሸቱ ሀይሌ
ራቢያ እሸቱ ሃይሌ
ምፅላል ሃይሉ አለማየሁ
ጌጤ ማቲዮስ ገ/ኪዳን
ትዕግስት በላቸው በየነ
ሱራፌል በላቸው በየነ
ሰላማዊት በላቸው በየነ
አበባየሁ ዘበነ ተኮላ
ማሚቱ በየነ ገ/ዮሐንስ
አዳነ ተሰማ በረሳ
ታሪኩ ተሰማ በረሳ
ሲሳይ ተሰማ በረሳ
ተፈሪ ተሰማ በረሳ
ዜና ተሰማ በረሳ
ሙሉጌታ ተሰማ በረሳ
እመቤት ተሰማ በረሳ
ጠጅነሽ ጎሳዬ በረሳ
አንለይ አሳምነው ተሰማ
ራሄል ገበደ ኃ/ማርያም
ናርዶስ አንለይ አሳምነው
ፍፁም አሳምነው ተሰማ
ማናዬ አሳምነው ተሰማ
ይርጋለም አሳምነው ተሰማ
ፍፁም ከበደ ኃ/ማርያም
በኃይሉ ከበደ ኃ/ማርያም
ሱራፌል ከበደ ኃ/ማርያም
ቢኒያም ከበደ ኃ/ማርያም
መስፍን ከበደ ኃ/ማርያም
እመቤት ከበደ ኃ/ማርያም
መሰረት መንግስቱ በየነ
ሠላማዊት ማሩ ፍቅሩ
ፍቅርተ ማሩ ፍቅሩ
ስንታየሁ ወይም አሰለፈች ማሩ ወርዶፋ
በቀለች ማሩ ወርዶፋ
ጥሩወርቅ መንግስቴ በየነ
ገ/መድህን ገ/የሱስ ስብሃት
ትርሃስ ገ/መድህን ገ/የሱስ
ንብረት ገ/መድህን ገ/የሱስ
ማሞ ኪሮስ በዛብህ
ራሄል አስረስ መኮንን
አዶኒያስ ማሞ ኪሮስ
ብሩክ ማሞ ኪሮስ
ዳግም ማሞ ኪሮስ
ኢዮስያስ ማሞ ኪሮስ
ናሆም ማሞ ኪሮስ
ደሳዊ ማሞ ኪሮስ
ኪሮስ ገ/ህይወት በርሄ
አለም ኪሮስ በዛብህ
ፅጌ ኪሮስ በዛብህ
ፋና ኪሮስ በዛብህ
አፀደ ኪሮስ በዛብህ
አብይ አስረስ መኮንን
ቤተልሄም አስረስ መኮንን
ሂሩት አስረስ መኮንን
ፀደይ አስረስ መኮንን
ሸዋዬ መስፍን አበራ
ኤልዳና ስንሻው አለምነህ
አርሴማ ስንሻው አለምነህ
ምስጋና ይሳቅ ገድባ
በረከት ይሳቅ ገድባ
የመከረ መኮንን ተሰማ
ማራማዊት ዳዊት ኢትዮጵያ
መቅደላዊት ዳዊት ኢትዮጵያ
ቤተል ዳዊት ኢትዮጵያ
ወለላ ተስፋዬ ብሩ
ተፈሪ ኢትዮጵያ መኮንን
ፍሪው ኢትዮጵያ መኮንን
ግሩም ኢትዮጵያ መኮንን
ትዕግስት ኢትዮጵያ መኮንን
ውቢቱ ኢትዮጵያ መኮንን
ለምለም ኢትዮጵያ መኮንን
ፀሐይነሽ መንግስቱ አዳል
መቅደስ መኮንን ተሰማ
እሸቱ ግረፍ አስታክል
ብስኩት ደመቀ ታከለ
ማየት እሸቱ ግረፍ
ቤተል እሸቱ ግረፍ
ኢዮስያስ እሸቱ ግረፍ
ታደሰ ደመቀ ታከለ
በኃይሉ ደመቀ ታከለ
ብርሃኑ ደመቀ ታከለ
ልፍነሽ ገለታ ዳዲ
እቴነሽ ግረፍ አስታክል
በላይነሽ ግረፍ አስታክል
ዘውዱ ግደይ ካህሲ
በረከት ተመስገን ስዩም
ሚሚ ተመስገን ስዩም
ካህሳይ ጉልላት አለመ
ሰመረ ግደይ ካህሲ
ኢሊኑ ግደይ ካህሲ
ምህረት ገ/መድህን ገ/የስ
ትርሃስ ገ/መድህን ገ/የስ
ሀብቶም ገ/መድህን ገ/የስ
ኬኬ ኃ/የተ/የግ/ማ
ኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል
አዲስ የልብ ህክምና ክሊኒክ
ምፍአም ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ነፃ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ዎው ትራንዚት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ኤምዲ ትራንዚት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ዲ ኤች ሲሚክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
የስም ዝርዝሩን የወሰድነው ከኢሳት ነው።