Skip to content

በሀገራችን በአስደንጋጭ ሁኔታ በመስፋፋት ላይ ያለው ግብረሰዶማዊነትና ሴራው

Posted on

አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው | ጎልጉል  ድረገድ

July 24, 2013

one-man-620x233

 

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አስቀድሞ የተናቁና የተዘነጉ አንዳንድ ዘመን አመጣሽ ከባዕድ የገቡ ችግሮች እጅግ አሳሳቢ አደጋ እየጋረጡ እንደመጡ በተለይ በዚህ ወቅት በግልጽ ዕየታዩ ነው፡፡ ነገር ግን ሁኔታው ቀስ እያለ የሞቀና እያላመደ የተባባሰ የመባባስም ባሕርይ ስላለው የህልውና አደጋ የመጋረጥ ደረጃ (boiling point) ሲደርስ ሁሉ እዛ ደረጃ መድረሱን ሳናስተውለው በፍላት ኃይሉ ተቀቅለን ልንፈራርስ የምንችልበት አጋጣሚ ሰፊ ሆኗል፡፡ ይሄንን አዚማም የችግሩን ባሕርይ ከወዲሁ የተረዱ ግለሰቦችና አንድ ማኅበር በሀገራችን ግብረሰዶማዊነትና የጋረጠውን አደጋ፣ የደረሰበትን አሳሳቢ ደረጃ ለሕዝብ የማሳወቅ እንቅስቃሴ በዜግነታቸው ለሀገራቸው ወይም ለሕዝባቸው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ከመወጣት አንጻር ማንም ምንም ሳይላቸው ለሀገርና ለሕዝብ ባላቸው ፍቅር በግል ተነሣሽነት ብቻ በመንቀሳቀስ አቅማቸው የፈቀደላቸውን ያህል አስመስጋኝ ሥራን በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ይህ እንቅስቃሴ የሁላችንንም ንቁ ተሳትፎ የግድ የሚጠይቅ ነውና ሀገሬ ሕዝቤ ማንነቴ የምትሉ ሁሉ ሳትዘናጉና ሳይመሽ ተመሳሳይ ተግባር ለመሥራት ትተጉ ዘንድ በጥብቅ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡

ግብረሰዶም ማለት ምን ማለት ነው? ግብረሰዶም ማለት የሰዶም ሥራ ማለት ነው ሰዶም የሰዶማውያን ሀገር ናት ሰዶም በጥንት ዘመን ከ4ሺ ዓመታት በፊት በዮርዳኖስ ሸለቆ ከተቆረቆሩ ከተሞች አንዷ ነች፡፡ ቢጤዋ ጎሞራም እንዲሁ በዚህ ሸለቆ በሰዶም አቅራቢያ የተቆረቆረች ከተማ ነበረች እነዚህ ሁለት ከተሞች ተቃጥለው ከጠፉ በኋላ በአሁኑ ሰዓት በጨው ባሕር ተሸፍነው እንዳሉ ይገመታል፡፡

የእነዚህ ሁለት ከተሞች ሰዎች ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ በዘፍጥረት 19፡1-22 ተቀምጧል፡፡ ባጭሩ ስናስቀምጠው ግን የሰዶምና የገሞራ ሰዎች ተፈጥሮና ሃይማኖት ከሚፈቅዱት ወይም ከሚያዙት ተስማሚ ከሆነው የተቃራኒ ፆታዎች የወሲብ ተራክቦ የተለየና አጸያፊ በሆነ የተመሳሳይ ፆታ ወሲባዊ ተራክቦ የረከሱ የጎደፉ በዚህ አጸያፊ ግብራቸውም እግዚአብሔርን ያስከፉ ያሳዘኑ በአመፃ ሥራ ያበዱ ርኩስ መንፈስ የሰለጠነባቸው የነገሠባቸው እግዚአብሔርም በዚህ ኃጢአታቸው ተቆጥቶ ከሰማይ እሳትና ዲንን አዝንቦ ያጠፋቸው የሁለት ከተሞተ ሰዎች ናቸው፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮም የዚያ አጸያፊ የተመሳሳይ ፆታ ወሲባዊ ግንኙነት መጠሪያ ሊሆኑ ቻሉ፡፡

ከዚያም በኋላ በሙሴ ሕግ ይሄንን ኃጢአት የሚፈጽሙ ሁሉ ያለ ምሕረት ይገደሉ ነበር፡፡ ዘሌዋዊያን 20፡10፣ ዘዳግም 23፡17 ሰዎች እግዚአብሔር መፍራትና ማምለክ ሲተው ለጣዖታትም ሲሰግዱ የዚህ ዓይነት ርኩስ መንፈስ እንደሚያድርባቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራ፡፡ በመሆኑም ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንረዳው ይሄ ኃጢአት በአሕዛብና በእስራኤል የተለመደ ነበር፡፡ በዚህ ዘመን ግን ግብረሰዶማዊያን የሌሉበት አንድም ሀገር እንደሌለ ይነገራል፡፡

እንደሚታወቀው በሚታወቅም በማይታወቅም ምክንያት ምዕራባዊያን በሀገራችን ላይ ጥርሳቸውን ከነከሱ ዘመናት አልፏል፡፡ አንደኛው ምክንያታቸው በቅርብ ጊዜው ታሪካችን ሀገራችን ኢትዮጵያ ለወንድም ሕዝቦች ማለትም ለተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች ከዘር መድሎ(apartheid) አስተዳደርና ከቅኝ ግዛት ነጻ እንዲወጡና ቅኝ ግዛት እንዲያከትምለት እንደ ኔልሰን ማንዴላ ያሉ ተዋጊዎቻቸውንና መሪዎቻቸውን ከማሰልጠን አንሥቶ የራሷን የጦር መሪዎችንም በማሰለፍ ጭምር እጅግ ከባድ ኃላፊነትን ወስዳ፣ ለዚህ ላመነችበት ዓላማም እራሷን በግልጽ አውጥታ በማጋፈጥ የተለየ ትዕግስት ጽናት ጥረትና ቁርጠኝነት ጠይቋት በነበረውና ከባባድ ዋጋ ባስከፈላት  በዲፕሎማሲውም (በአቅንኦተ ግንኙነት) እንዲሁ ያደረገችው የማይተካ ሚና ነው፡፡ ይህ ተግባራችን የምዕራባዊያንን ጥርስ አስነክሶ ከትናንት እስከ ዛሬ ለተለያዩ ዘርፈ ብዙ ስውርና ግልጽ የበቀል እርምጃዎች ዳርጎናል፡፡ በአጭር ጊዜ የሀገራችንን መሬት ያዳረሰውን  ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ከሚቀንስ ታይቶ የማይታወቅ ፀረ-አዝርዕት አረም ከእርዳታ እህል ጋር ቀላቅሎ ከማስገባት አንሥቶ ካለን የተፈጥሮ ሀብትና አቅም አንፃር በትንሽ ድጋፍ ማለትም እንደ ማርሻል ፕላን በመሰለ ድጋፍ ያም ባይሆን ብድር ለመነሣትና ራሳችንን ለመቻል ዕድሉ እንዳለን ሁሉ ጠቀም ያለ ብድር ከቶውንም እንዳናገኝ በመከልከል ስንራብ ብቻ አዛኝ መስሎ ለመታየት ቢዘራ የማይበቅል የተቀቀለ እህል እስከ መወርወር ድረስ ለደረሰ ሴራ ለተሞላበት በቀል ሊዳርገን ችሏል፡፡ መራር ዋጋ አስከፍሎናል ወደፊትም ያስከፍለናል፡፡ የሚያሳዝነው ለዚህ ሁሉ ጣጣ የተዳረግንባቸው ወንድሞቻችን አፍሪካዊያን ስለ እነሱ ስንል ለዚሁ ሁሉ የበቀል እርምጃ እንደተዳረግን የሚገባውን ያህል አለማወቃቸውና ዋጋና ክብር አለመስጠታቸው ነው፡፡

ይህ ከባድ ማኅበራዊ ቀውስ የሚፈጥረው ግብረሰዶማዊነትን በሀገራችን የማስፋፋት ዓላማም ከዚሁ ሀገራችንን ከመበቀያ ድርጊቶች አንዱ ነው፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታም በከፍተኛ ደረጃ እየተሳካላቸው እንደሆነ ማየት ይቻላል፡፡

እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ይህ ርኩሰት ወይም ችግር በሀገራችን አይታወቅም ወይም እንግዳ ነበር ይህ ማለት ግን ይሄ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ጨርሶ በሀገሪቱ አልነበሩም ማለት አይደለም ነገር ግን ያሉን (የነበሩን) አሁን እየተሸረሸሩ ያሉ ጠንካራ ባሕሎቻችን የወግ የሥነ-ምግባር የግብረ-ገብ ድንጋጌዎቻችንና ሃይማኖት ይህ በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ይሄንን ድርጊት እንዳይሞክሩት አስሯቸው ኖሯል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በዋናነት ሆን ብለው ባሴሩ ባዕዳን በተለይም የቱሪስት (የጎብኚ) መዳረሻ በሆኑ የሀገራችን ከተሞች በጎብኝዎች (በቱሪስቶች) አማካኝነትና በተራድኦ ድርጅቶች ሳቢያ ወደ ሀገራችን በሚገቡ ባዕዳን በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡

ከዚህ ቀደም ይህን ግብረሰዶማዊነትን በሀገራችን የማስፋፋት ሴራ ይከወን የነበረው በሥውር ነበረ ይህ በሥውር ይሠራ የነበው ሴራ ከሚፈልጉት ውጤት እንደደረሰ ካወቁ በኋላ ግን በተለይ የእንግሊዝ መንግሥት የእኛን ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ የአፍሪካ መንግሥታትን በግልጽ በይፋ በየሀገሮቻቸው ያሉ የግብረሰዶማውያንን እንቅስቃሴና ተግባር ሕገወጥና ወንጀል መሆኑን ሽረው ሕጋዊ ካላደረጉ በስተቀር ከእንግዲህ እርዳታም ሆነ ብድር እንደማይሰጡ ይፋ አድርገዋል፡፡ እስከአሁን ለዚህ ከቅኝ ግዛት ላልተናነሰ አዋጅ ምላሽ የሰጠችው ጋና ብቻ ናት “እርዳታና ብድራቹህ በአፍንጫችን ይውጣ ለእርዳታና ብድር ብለን ከባሕላችንና ሃይማኖታችን ውጭ የሆነና የሚቃረንን ፀያፍ ድርጊት አንቀበልም” በማለት፡፡ ምዕራባዊያን ዛሬ በሥውርና በይፋ አስገዳጅ ጫና ከማሳደራቸው በፊት አስቀድመው መደላድል ሲፈጥሩ እንደነበሩ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ከሠሯቸው ተንኮል የተሞላባቸው የመደላድል ሥራዎች አንዱ የሴት ልጅ ግርዛትን ጎጅ ባሕል አሰኝቶ ማስቀረት ነበር፡፡ መቶ በመቶም ተሳክቶላቸው የሴትልጅ ግርዛት “ልብ በሉ እያወራሁ ያለሁት ስለሴት ልጅ ግርዛት እንጂ ስለ ብልት ትልተላ አይደለም” እናም የሴት ልጅ ግርዛትን እነሱ ከሚያወሩት አንፃር እውነት ይሁን አይሁን ወይም ጉዳትና ጥቅሙን ትርፍና ኪሳራውን በቅጡ ለመረዳት ሳንሞክርና ሳናጠና በየዋሕነት እነሱ ያሉትን ብቻ አምነን በመቀበል የሴትልጅ ግርዛት ሕገ ወጥ እንዲሆንና እንዲቀር ተደረገ፡፡ ይህ ጉዳይ ለግብረሰዶማዊነት ቀጥተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡ በሴት ልጅ ግርዛት ጉዳይ ላይ በሠነድ ደረጃ ያዘጋጀሁት ሰፊና ጥልቅ ጥናት ነበር፡፡ ከ4 ዓመታት በፊት ጀምሮ በተለያዩ መድረኮች ቀርቤ ግርዛት እንዲቀር ከሚሠሩ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ለመከራከር ያቀረብኩት ጥያቄ የመንግሥት አካላት መንግሥት አቋም የያዘበት ጉዳይ ነው በማለታቸው ምክንያት ተቀባይነት በማጣቱ ወደ ሕዝቡ ማድረስ ሳልችል ቀርቻለሁ፡፡ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ አሁን ወደ ቀደመው ነገራችን እንመለስና፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት ማለትም እንደ ሀገረ እግዚአብሔርነቷ ለዚህ አስነዋሪ የምዕራባዊያን አዋጅ አቋም በመውሰድና ምላሽ በመስጠት የሚቀድማት ሊኖር ባልተገባ ነበር፡፡ እንዲያውም ጽድቁ ቀርቶ እንዲሉ ጭራሹኑ አምና የሃይማኖት መሪዎች ግብረሰዶማዊያንንና ድርጊታቸውን በማውገዝ ሊሰጡት የነበረውን ጋዜጣዊ መግለጫ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ መግለጫውን ሳይሰጡ እንደተለጎሙ እንዲበተኑ ማድረጉ ለእነዚሁ ምዕራባዊያን የጥፋት አዋጅ እጅ መስጠቱ ወይም መንበርከኩ ይሆን የሚል ሥጋት ፈጥሯል፡፡ መንግሥት ተጠቃሚ የሚሆን መስሎት ለእርዳታና ብድር ብሎ በይፋም ባይሆን በስውር የእነ እንግሊዝን አዋጅ ከተቀበለና ሥራ ላይም ካዋለ ከእነሱ እጅ በእርዳታና ብድር ስም አንድ ሚሊዮን ብር አግኝቶ ከሆነ በዚህች አንድ ሚሊዮን ብር ሰበብ በገባው ጦስ ሕዝቡን በመቶ ቢሊዮን ብር ከማይመለስ ከማይፈወስ ከማይጠገን ከማይቀረፍ የማኅበራዊ ቀውስ አዘቅት ውስጥ እንዳሰመጠው ይወቀው፡፡ ሀገር የምትለማውና የምትገነባው የማኅበረሰቡን ሁለንተናዊ ጤና በመጠበቅ፣ የሰው ልጆችን ሰብእና ሥነ-ልቦናና ኅሊና በሚያንጹ በማይቀፉና በማይኮሰኩሱ እሴቶችና አዎንታዊ ግብሮች እንጅ ኅሊናን በሚጎዱ ሥነ-ልቡናን በሚያቃውሱ ሰብእናን በሚያረክሱ በሚያዘቅጡ ከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስ በሚፈጥሩ ርኩስ ዘግናኝና አጸያፊ ግብሮች አይደለም፡፡ መንግሥት ማለት የሕዝቡን ሁለንተናዊ ጤና የሚጠብቅ ወይም የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት አካል ማለት እንጂ የገዛ ሕዝቡን ለማያውቀው አደጋ ጥቃት አጋልጦና አሳልፎ የሚሰጥ የሚያስጠቃ አካል ማለት አይደለም ማልማትና ማጥፋት ምን ማለት እንደሆነ ለይተን ልናውቅ ያስፈልጋል፡፡ አንድ አካል ሁለት ዓይነት ሰብእና ሊኖረው አይችልም፡፡ አልያም አንደኛው የማስመሰል ወይም የውሸት ነው፡፡ ባለሥልጣኖቻችን የዚህን ችግር ጉዳት እንደራሳቸው አድርገው እንዲያዩት ያስፈልጋል፡፡ በእኛና በልጆቻችንስ ላይ ቢደርስ በሚል እሳቤ የሰለባዎች ሕመም ሊሰማቸው ስለእነሱም ሊገዳቸው ያስፈልጋል፡፡ የመሪነት ትርጉምም ወይም ሰብእና ይሄው ነው፡፡ ከእኛ አይድረስ እንጅ የራሱ ጉዳይ ነው መባል የለበትም፡፡

ከኢትዮጵያ ሕዝብ 97%ቱ ሃይማኖተኛ ነው 3%ቱ ብቻ ሃይማኖት አልባ ነው፡፡ 97%ቱ ሕዝብ ሃይማኖቱ ግብረ ሰዶማዊነትን አጥብቆ ያወግዛል 3%ቱ ሃይማኖት አልባ ቢሆንምና በሃይማኖቱ ምክንያት የሚያወግዘው ባይሆንም ይሄንን ርኩስ ጸያፍ ግብር የሚጸየፍና የሚያወግዝ ጽድት ያለ እኩሪ ባሕል አለው፡፡ በመሆኑም 100% ይሄንን አጸያፊ ግብር የሚጸየፍ ሕዝብ ባለበት ሀገር በምዕራባዊያን ተጽእኖ ወንጀልነቱና ወጉዝነቱ ቀርቶ መንግሥታዊ ፈቃድና ይሁንታ እንዲኖረው ማድረግ ጨርሶ የማይታሰብና እብደትም ነው፡፡ የምዕራቡን ዓለም ሕዝብ የባሕልና ሃይማኖት እሴት ይዘት ያየን እንደሆነ በተለይ በዚህ ዘመን ሃይማኖት አልባነትን እንደዘመናዊነት እየቆጠሩ በመሆኑ ሃይማኖተኛነት በሸመገሉ ሰዎች ብቻ የተወሰነና  የሃይማኖተኛው ቁጥር እጅግ አነስተኛ ሃይማኖት አልባው ሕዝብ ቁጥር ደግሞ እጅግ በርካታውን ቁጥር የያዘ ሆኗል፡፡ ከባሕላቸውም ጋራ ከተቆራረጡና ዘመናዊነትን ባሕላቸው አድርገው ከያዙም ዘመናትን አስቆጥረዋል፡፡ በመሆኑም ይሄንን ርኩስና ጸያፍ ግብር ሊጸየፉ፣ ሊያርቁ፣ ሊያወግዙ የሚያስችላቸው የአስተሳሰብ አጥር የላቸውም ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ነው ያለ አንዳች ሀፍረትና መሸማቀቅ ሳይቸገሩ በመንግሥቶቻቸው ደረጃ ሳይቀር በይፋ ለመቀበልና ሕጋዊ ለማድርግ የበቁት፡፡

kids2

የሚገርመውና እጅግ የሚያሳዝነው ግን መንግሥቶቻቸው ወይም ሃይማኖት አልባው የሕዝባቸው ክፍል ይሄን መቀበሉ ሳይሆን በሃይማኖት ተቋሞቻቸው ደረጃም ክርስትናን እንቀበላለን እያሉ ክርስትና በግልጽና በጽኑ የሚያወግዘውን ይሄንን ርኩስና ውጉዝ ግብር በዓለም ዓቀፍ ባሉ ቅርንጫፎቻቸው ደረጃም ጭምር በይፋ ተቀብለው ወይም ሕጋዊ አድርገው ወንድን ከወንድ ሴትን ከሴት ጋራ ሥርዓት እየፈጸሙ ማጋባታቸው ነው፡፡ የሃይማኖት መሪዎቻቸውም ግብረ ሰዶማዊያን እንደሆኑ በየጊዜው የሚወጡ ይፋዊ የብዙኃን መገናኛ የዜና መረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡ እዚህ ሀገራችን ውስጥ ያሉ በእነሱ የሚደገፉና የእነሱ ቅርንጫፍ የሆኑ የሃይማኖት ተቋማት የተባሉትም ከ10 ዓመታት በፊት ተቀብለዋል ተብሎ ውዝግብ ተነሥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

የዚህ ችግር ተጠቂ የሆኑ ሰዎች የችግሩ ተጠቂ በመሆናቸው በሚደርስባቸው ሥነ-ልቡናዊ ቀውስ መታወክ ሕመም የሞራል(የቅስም) ሥብራትና ውድቀት የተነሣ ለሀገርና ሕዝብ እርባና ቢስ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ተግተው ከተገኙም ባሉበት ወይም በያዙት ቦታ ሆነው የሚያገላቸውንና ያልተቀበላቸውን ማኅበረሰብ በመበቀል እሴቶቹን በማፈራረስ ተግባር ላይ እራሳቸውን ጠምደው ፀረ-ማኅበረሰብ ሆነው ነው፡፡ እንግዲህ እንዲህ ዓይነት ግለሰቦች እንዲበራከቱ ከዚያም እንዲህ ዓይነት ማኅበረሰብ እንዲፈጠር ዕድል መስጠት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለእናንተው እተወዋለሁ፡፡

ለመሆኑ የዚህ ችግር መንስኤው ምንድን ነው? ብንል መንስኤው የህክምና ሰዎች በሽታ ነው ሲሉት መንፈሳዊያኑ ወይም የሃይማኖት ሰዎች ደግሞ ጋኔን ወይም ርኩስ መንፈስ ነው ይላሉ፡፡ እንዴት መሰላቹህ ነገሩ እንዲህ ነው ይህ በሽታ ወይም ርኩስ መንፈስ ያደረባቸው ሰዎች ያላቸውና መፈጸም የሚፈልጉት ወሲብ ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ማለትም ወንድ ከሴት ሴት ከወንድ ጋር መራቢያ አካሎቻቸውን በመጠቀም ሳይሆን በተፈጥሮ ምንም ዓይነት ወሲባዊ ስሜት ከማይገኝባቸውና ለዚህ አገልግሎት ካልተፈጠሩት ከመጸዳጃ ጀምሮ ሌሎች ቀዳዳ ወይም ጎድጓዳ የሰውነት ክፍሎችን በመጠቀም ከዚህ ወጣ ሲልም እራሳቸውን ለገራፊ በመስጠትና በማስገረፍ የወሲብ ፍላጎታቸውን የማርካት ጤነኛና ትክክለኛ ያልሆነ ፍላጎት ነው፡፡ ይህ በሽታ ወይም ርኩስ መንፈስ ያለባቸው ሰዎች ናቸው እንግዲህ ከሕፃናት ጀምሮ እስከ ዐዋቂዎች ድረስ ወንዶችን በመድፈር ከዚያም በገንዘብ ኃይልና በተለያዩ ሐሰተኛ ማጥመጃወች የደፈሯቸውን ሰዎች ከዚያ ሕይወት እንዳይወጡና በሂደትም ሱስ እንዲሆናቸው በማድረግ የእነሱ ርኩሳዊና ጸያፍ የወሲብ ባሪያ እያደረጉ የግብረሰዶማዊያን ጥቃት ሰለባዎችን ተጠቂዎችን ወይም እራስን እስከማጥፋት በሚደርሰ የሥነ-ልቡና ቀውስ ዘወትር የሚታወኩ የሚረበሹ የሚጨነቁ ዜጎችን ከቀን ወደቀን በአስደንጋጭ አኃዝ እያበራከቱ የሚገኙት፡፡

ይህ በሽታ ያለባቸው ወንዶችም ሆነ ሴቶች በበሽታው ወይም በመንፈሱ ምክንያት ከውስጣቸው በሚፈጠር አስገዳጅ ስሜት የወሲብ ሕይዎትን ማለትም ወንድና ሴት በመራቢያ አካሎቻቸው የሚፈጽሙትን ተፈጥሯዊና ትክክለኛውን የወሲብ አፈጻጸም የሚጀምሩት በጣም በልጅነት የእድሜ ዘመናቸው ነው፡፡ ወደዚህኛው ማለትም ጸያፉና ተፈጥሯዊ ወዳልሆነው የወሲብ አፈጻጸም ተሻግረው ሰዎችን ወደማጥቃት የሚቀየሩት ወደ አቅመ ሔዋንና አቅመ አዳም ደረጃ እየደረሱ ሲሄዱና ከበሽታቸው የተነሣ በተፈጥሯዊው የወሲብ አፈጻጸም ካለመደሰት ችግራቸው የተነሣ ነው፡፡ እንደ የሕክምና ባለሙያዎች አባባል ይህ በሽታ እንደ ማንኛውም ሕክምና እንዳለው በሽታ መዳን የሚችል እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ መንፈሳዊያኑም እንዲሁ ይህ ርኩስ መንፈስ የተጠናወታቸውን ሰዎች እንደማንኛውም የርኩስ መንፈስ በሽታ ማዳን እንደሚቻል ይናገራሉ፡፡ የዚህ በሽታ ተጠቂዎች ግን በእነኝህ ሁለት የመፍትሔ ተቋማት መፍትሔ እንደሚያገኙ ቢያውቁም በሽተኞቹ ወይም ሕመምተኞቹ ከግል ስድ ሰብእናቸው የተነሣ መፍትሔውን ባለመፈለጋቸው በየጊዜውና በየቦታው ሰለባዎቻቸውን በማጥመድና በማጥቃት ወይም በመድፈር የወንጀል ተግባር በመጠመድ የብዙ ሕፃናትና ወጣቶችን ሕይዎት ያበላሻሉ፡፡

ምዕራባዊያን መንግሥታት የሦስተኛውን ዓለም መንግሥታት ለማስገደድ የሚጠቀሙበት የሕጋዊነት ሽፋን አንዱና ዋነኛው የሰብአዊ መብት ወይም የግለሰቦችን ወይም የአናሳ ቡድኖችን መብት ከማስከበር አንፃር እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ሰብአዊ መብት ይበሉ እንጅ እንዲሠራ እንዲደረግ የሚፈልጉት ግን ኢሰብአዊ ሥራ ነው፡፡ በመሆኑም ሰብአዊ መብት የሚለውን ቃል ፍጹም ያለቦታው እየተጠቀሙበት እንደሆነ ማየት ይቻላል፡፡ ይህች “ሰብአዊ መብት” (human right) የምትባል ቃል ጋጠወጦችና ደጋፊወቻቸው ለጸያፍ ድርጊቶቻቸውና አስተሳሰቦቻቸው መሸፋፈኛ ሲጠቀሙበት በሰፊው ይስተዋላል፡፡ ጠልቆ ለመረመረው ግን የሚጠቅሱት ቃልና ድርጊታቸው ፍጹም ተቃራኒ እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ “ሰብአዊ መብት” ማለት ሰው የመሆን መብት ማለት ነው ይሄም ማለት የሰውን ልጅ እንደሰውነቱና እንደ ማኅበራዊ ፍጡርነቱ ከሌሎቹ ፍጡራን የሚለየውንና የሚያልቀውን ኅሊናውን ለጸጸትና ለጉዳት የማይዳርጉ ተስማሚ አስተሳሰቡንና የጋራ ጥቅሙን ማለትም ማኅበራዊነቱን ጠብቆ ለማኖር ያስችለኛል ብሎ በጋራ ስምምነት የቀረጻቸውን ባሕል፣ ወግ፣ የግብረ-ገብ(የሞራል) ድንጋጌዎችን፣ ሃይማኖት ወዘተ. መጠበቅ መንከባከብ ማክበር ማለት እንጅ የአዕምሮ ጤና ዕክል ያለባቸው ሰዎች እንደሚሉት የሰው ልጅ ጤናማ ኅሊና የሚጸየፈውን የሚቀፈውን ሥነ-ልቡናን የሚጎዳውን ከሰውነት አንጻር ተቃርኖ ያለውን የተለየ ሐሳብና ድርጊት ያለ ሀፍረት በድፍረት የትም ቦታ በነጻነት መፈጸምና አፈንጋጭ ድርጊት ማለት አይደለም፡፡ እነዚህ የጋራ መተዳደሪያ ደገኛ ሥርዓት ማዕዘናቱን ለድርድር ማቅረብና አለማቅረብ፣ ለመጠበቅ ለማክበር የመፈለግንና ያለመፈለግን ጉዳይ የሰዎችን የአዕምሮ ጤና ደረጃና ደኅንነት መለኪያ መመዘኛውም ናቸው፡፡ አቤት! ደኅና የመሰለ ነገር ግን ያበደ የኅብረተሰብ ክፍል አለ ማለት ነው ጃል? አዬ ስምንተኛው ሽህ፡፡

የግለሰብ ወይም የአናሳ ቡድኖች መብት ማለትስ ምን ማለት ነው? የሚከበረውስ እስከምን ድረስ ነው? የሚለውን ወሳኝ ጥያቄ ለመመለስ ሌላ ቦታ ሳንሄድ በየሀገሮቻቸው ግብረሰዶማዊነትና ግብረሰዶማዊያን እንደዛሬው ሳይስፋፋና የወሳኝነት ቦታና ሥልጣን ሳይቆጣጠሩ የያዙትንም ኃይል ተጠቅመው በፈጠሩት ጫና ግብረ ሰዶምንና ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያወግዙና ሕገ ወጥ የሚያደርጉ የቀደሙ ሕግና ደንቦቻቸውን አስለውጠው አሽረው አስቀይረው ግብረ ሰዶማዊነትን ሕጋዊ ሳያደርጉ በፊት የነበሩ የየሀገሮቻቸውን ሕጎችና ደንቦችን መለስ ብሎ ማየት በቂ ማስረጃ ነው፡፡ በግብረ ሰዶማዊያኑ ብርታት ድራሻቸው የጠፋ የእነዚህ ሀገሮች የቀደሙት ሕጎች የግለሰብ ወይም የአናሳ ቡድኖች መብት የሚከበረው ከብዙኃኑ ወይም ከኅብረተሰቡ የጋራ ጥቅም ሰላም ደኅንነት ጋር እስካልተቃረነና ኅብረተሰቡ ተቀብሎት የሚኖረውን ባሕል ወግና ሃይማኖት እስካለተፃረረ ድረስ ነው ይሉ እንደነበረ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ዛሬ እነዚህ ግብረ ሰዶማዊያን ከሀገሮቻቸውም አልፈው በሌሎች ሀገሮች ጫና በመፍጠር በሀገሮቻቸው ላይ ያደረሱትን የሞራል (የግብረ-ገብ) ድንጋጌዎችንና ጠቃሚ ሃይማኖታዊ እሴቶችን ውድቀት በሌሎች ሀገሮችም ላይ ለማድረስ በከፍተኛ ጥረት ላይ ናቸው፡፡

ለእነዚህ መንግሥታት አንድ አመክንዮአዊ (Logical) ጥያቄ ማቅረብ እወዳለሁ፡፡ እነሱም በግልጽ እንደሚያውቁት ሁሉ ማንም የግብረ ሰዶም ጥቃት ሰለባ የሆነ ሰው ወዶና ፈቅዶ ወደዚህ ሕይወት የገባ ከዜጎቻቸው አንድ እንኳ አይኖርም፡፡ ነገር ግን በልጅነት ወይም በወጣትነት ዘመናቸው በደረሰባቸው የመደፈር አደጋ እንጂ፡፡ ከዚያም በኋላ ሁኔታው በሚፈጥርባቸው የሥነ ልቦና ቀውስ ራስን የመጣል ከሰዎች ራስን የማግለልና ብቸኝነት ለአጥቂዎቻቸው ምቹ ሁኔታን በመፍጠሩ ፣ በተጨማሪም አጥቂዎቹ ተጠቂዎቹን ከዚያ ሕይወት እንዳይወጡ በሚፈጥሩት የማጥመጃ ሴራ ታሥረው የዚህ ችግር ሰለባ እንደሆኑ ይቀራሉ እንጂ፡፡ በመሆኑም እነኝህን ወንጀል የተፈጸመባቸው ሰለባዎች ከዚህ ከማይፈልጉትና እራስን እስከማጥፋት ከሚያደርስ የሥነ-ልቡና ቀውስ ከፈጠረባቸው ጥቃት ችግር ለማውጣትና ወደ ጤናማው ሕይወት እንዲመለሱ የሚያስችላቸውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ከማድረግና የሠቀቀን እንባቸውን ከማበስ ይልቅ ግብረ ሰዶማዊነትን ፈቅደውና ሕጋዊ አድርገው እነዚህን ተጠቂዎች በዚያ የሥነልቦናና አካላዊ ሕመም ስቃይ ውስጥ ሆነው የእነዚያ ወንጀለኞች ደፋሪዎቻቸው የዘለዓለም የወሲብ ባሪያ እንዲሆኑ ማድረግ ፍጹም የለየለት ኢሰብአዊነትና አረመኔያዊነት መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም የሰብአዊነትና የፍትሕ ጥያቄና እሴት በውስጣቹህ ሞቶ ተቀብሯል፡፡ ከዚህ በኋላም ስለ ፍትሕና ሰብአዊነት(justice and humanity) የምትናገሩበት አንደበት ከቶውንም ሊኖራችሁ አይችልም በአንባ ገነኖቹም ላይ የወቀሳ ጣታችሁን ለመቀሰር የሚያበቃ የሞራል (የግብረገብ) ብቃት የላቹህም ምክንያቱም በግልጽ ማየት እንደሚቻለው መንግሥቶቻቹህ በቁርጠኝነት እየሠሩት ያለው ሥራ የወንጀለኞችን ግፈኛና ጸያፍ ጥቅም የሚንከባከብ የሚያበረታታና አስነዋሪ አጸያፊ ሥራቸውንም የሚባርክ ይሁንታ የሚሰጥ የሚያስፋፋ ሰለባዎችን ወይም ተጠቂዎችን ለከፋ ግፍ ያልተጠቁ ወገኖችንም ለዚህ አደጋ የሚዳርግ ነውና፡፡ እናስ? ይሄንን ግልጽ ሀቅ ሊያስተባብል የሚችል አንዳች የመከራከሪያ ነጥብ (argument) ሊኖራቹህ ይችላልን? ሚዛኑ ፍትሕና ሰብአዊነት ከሆነ ከቶውንም ሊኖራቹህ አይችልም፡፡ በመሆኑም እናንት  የምትሠሩትን ሳታውቁ  የግብረሰዶማዊነት (የወንጀለኝነት)እንቅስቃሴ ቃፊር የሆናቹህ ሀገራት መንግሥታት ሆይ ከእንቅልፋቹህ ንቁ ምን እየሠራቹህ እንደሆነም ልብ ብላቹህ ተመልከቱና ተመለሱ፡፡ ለተበዳዮችና የግፍሰለባ ለሆኑትም ቁሙ፡፡ ያኔ ለሰብአዊነትና ለፍትሕ ቆሞናል ለማለት የሞራል ብቃቱ ይኖራቹሃል፡፡ ይሄንን ስታደርጉ እንደ ፖለቲከኛና እንደ ሕዝብ መሪ የተሸለ ማሰብ መቻላችሁንም ታስመሰክራላቹህ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ያላችሁን ብስለት(maturity) ግብረ-ገብነት(morality) ሰብእና(personality) በሕዝብና በታሪክ ፊት ለትዝብት ትዳርጋላቹህ፡፡

በሀገራችን በቀደመው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ይሄንን ወንጀል ፈጽሞ የተገኘን ወንጀለኛ የቅጣት ጣሪያ 15 ዓመታት ነበር በአዲሱ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ደግሞ ይህ የጽኑ እሥራት ዘመን ወደ 25 ዓመታት ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡ ይሁን እንጅ ይሄንን ወንጀል እየፈጸሙ ያሉ ወንጀለኞችን እያደኑ ለፍርድ የማቅረቡ ሥራ አበረታች እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ በሌሎች ሀገሮች የማረሚያ ቤቶች ተሞክሮዎችና በሀገራችንም እንዳለ እንደሚወራው ሁሉ በዚህ ወንጀል ወይም በሌላ ተገኝተው የተፈረደባቸው ወንጀለኞች ማረሚያ ቤት ገብተውም እዛ ውስጥ ያሉትን ታራሚዎች እንደሚደፍሩ ይነገራል፡፡ በመሆኑም እነዚህ ግብረሰዶማዊያን የሚያደርሱትን ጥቃት ከመግታት ወይም ከመቆጣጠርና ምስኪን ሰለባዎችንም ከመታደግ አኳያ በሕጉ የተጣለባቸው ፍርድ እንደገና ተከልሶ ከእሥራቱ በተጨማሪ እንዲኮላሹ ማድረግ ብቸኛ መፍትሔ መሆኑን መገንዘብና እንዲስተካከል ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

እናም እንግዲህ ይህ ችግር ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ተረድተን ከግለሰብ እስከ ተቋማት በተለይም የብዙኃን መገናኛዎች የማይመለከተው አይኖርምና ሁሉም በቆራጥነት ይሄንን ርኩሰት መዋጋት ይኖርበታል፡፡ ጉዳዩን ተጸይፎ ዝም ማለትና ራስን ማግለል ጭራሽም ላለመስማትና የጋረጠብንን አደጋም ላለመነጋገር መፈለግ መሸሽ ለችግሩ መስፋፋት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርና እንደሚረዳ አንጅ ምንም  የሚፈይደው ነገር እንደሌለ ጊዜ ሳናጠፋ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ ካለሆነ ግን ሩቅ በማይባል ጊዜ ልጅ ወልዶ ማሳደግና ማስተማር እንደ አንዳንድ ይህ ችግር ሥር እንደሰደደባቸው ሀገሮች ከወጣንበትና ከሄድንበት በሰላም ለመመለሳችንም እርግጠኛ የማንሆንበት የመሳሪያ ድምጽ ጩኸት አልባ የሰላም እጦትና ሁከት ችግር ውስጥ እንደርሳለን፡፡ ማንም የዚህ ችግር ሰለባ ላለመሆኑ ምንም ዓይነት ዋስትና ሊኖረው አይችልም፡፡ ሀገርና ማንነት የሚጠፉት በአጥፊዎች የጥፋት ሥራና ብርታት ሳይሆን በዜጎች፣ በሚያገባቸው፣ ወይም በተቆርቋሪዎች ዝምታ ነው፡፡ ይህ ችግር ምንም እንኳ በእንጭጩ የምንልበት ጊዜ ያለፈ ቢሆንምና በየአቅጣጫው በየትምህርት ቤቱና በሌሎችም ቦታዎች በሚዘገንን ሁኔታ እንዲህ ተደረገ እየተባለ እንደምንሰማው ሁሉ ማናችንም ከምንገምተው በላይ ውስጥ ውስጡን ተጋግሞ የተስፋፋ ችግር በመሆኑ ጠንከር ያለ እንቅስቃሴና ዘመቻ ካላደረግን በስተቀር በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሊቀለበስ ከማይችልበት ደረጃ መድረሱ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ እረገድ ከሃይማኖት መሪዎች፣ ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች እስከ ባሕላዊና ማኅበራዊ አደረጃጀቶች ድረስ ያሉ ሁሉ ግንባር ቀደምና ንቁ የተሳትፎ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን ነገ ሳይሆን ዛሬ ከዛሬም አሁን፡፡

ዕድሉ ያላቸው አጋጣሚዎች የሚፈቅዱላቸው የግብረገባዊ እሴት አቀንቃኝ (moralist) የሆኑ ዜጎች ሁሉ እዚህ ጽሑፍ ውስጥ ለምዕራባዊያን መንግሥታት የቀረቡትን የመከራከሪያ ነጥቦች(arguments) እንዲደርሳቸው በፈለጓቸው መንግሥታት ቋንቋዎች በመተርጎም ለእነኝህ ተሳስተው ለማሳሳት ለሚጣጣሩት መንግሥታትና የብዙኃን መገናኛዎቻቸውም ለማድረስ የሚፈልጉ ቢኖሩ በእጅጉ ይበረታታሉ፡፡

[email protected]

Leave a Reply