Skip to content

የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎችና አባ ዝምታዎች ትንሣኤ

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

በአቦሸማኔዎች ምድር የጉማሬዎች (አባ ዝምታዎች) ዓለም

በአዲስ ዓት መግቢያ ጦማሬ ላይ 2013ን ‹‹የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ዓመት››(የወጣቶቹ)  ብዬው ነበር፡፡ በዚህ ዓመትም የኢትዮጵያን ወጣቶች ለማስተማር፤ባሉበት ለመድረስ፤ለማሳሰብም ቃል ገብቼ ነበር:: የኢትዮጵያም የምሁራን አምባ ይህንኑ ለማድረግ ጥረት እንዲያደርጉ ተማጽኜ ነበር (በተለይም በከፍተኛው ጣርያ ላይ ያለነውን ምሁራን)፡፡ በተመሳሳይ ወጣቱን እንዲደርሱት አሳስቤም ነበር፡፡ ከዚህ ባለፈም ተማጽኖዬ ከሰፊው የጉማሬ ትውልድ ጋር (መንገዱ የጠፋው ትውልድ) እራሱን በማግኘት መስመሩን አስተካክሎ ጉዞውን እንዲያሳምርና ወጣቱን እንዲረዳ  ምኞቴን አስታዉቄ  ነበር ፡፡

በጁን 2010 በግልጽ ባሰማሁት (የኢትዮጵያን ምሁራን ምን በላቸው?) የእንዳዳን ጥሪ (S.O.S)  እና አሁን ደሞ ‹‹የተሳካላቸውን ግድ የለሽ ምሁራን›› ጥሪው ጥሩ አቀባበል አላገኘም:: በተለይም በ‹‹ጉማሬያዊያን›› ላይ ያቀረብኩት ጥያቄ: በጨካኞች ሰው አጥፊዎች ላይ በሰብአዊ መብት ግፍ ፈጻሚዎች ላይ፤የአብረን እንሁን  እንስራ ተማጽኖዬ  በጣሙን የከረረ እምቢታና ጆሮ ዳባ ልበስ መልስ ነው የተሰጠው፡፡ ከአንዳንድ ጉማሬዎች ተረት መሰል አባባል እንደተረዳሁት እራሳቸውን በማመጻደቅ ከጳጳሱ ቄሱ እንዲሉ አይነት፤‹‹እከሳለሁ›› በሚል መልኩ ጣታቸውን ወደ ሌላው መቀሰርንነው፡፡ አንዳንዶች ሲተቹ እንዲያውም እራሴን በከፍተኛው ቦታ ላይ በማስቀመጥ፤ ለታይታ ብቻ በመጻፍ፤ እራሴን ለማስተዋወቅና ተወዳጅነትን ለማግኘት እንደምንቀሳቀስ አይነት ሃሳብ ሰንዘረዋል፡፡ በጉማሬዎች መሃል የተፈጠረው ድንጋጤና ስጋት፤እኔ ጉዳዩን ማንሳት እንዳልነበረብኝና ያደረግሁትም ሕዝባዊ ጥረቱን ክህደት፤ ስም ማጥፋትና የሚያሳፍር በመሆኑ፤ በራሳቸው የፈጠሩትን ሽባነትና ፍርሃት ጨርሶ ማንሳት እንዳልነበረብኝ አትተዋል፡፡ አንዳንዶችም ይህን አቦሸማኔና ጉማሬ የሚለውን  ዘይቤያዊ አነጋገር በመጠቀም፤ በወጣቱን በባለዕድሜው መሃል ልዩነትን ፈጠርክ ብለው ይኮንኑኛል፡፡ በኔ እምነት ግን ከሼክስፒር አባባል ልዋስና ‹‹ሁለቱም ወገኖች የምሬታቸው ሚዛን እኩልነው››::

የኔ እምነትና ፍላጎት ያንን ጥንታዊ የዝምታ ባህል ሽፋን ለመግለጥና አውነትን ብቻ ለገዢዎች ተብሎ ሳይወሰን፤እራሳቸውንም ለዝምታ መዳረግን ለመረጡትም ጭምር ነው፡፡ በዝምታ፤ ትክክለኛውን በስህተቱ መተካትም ትክክል አይደለም ብዬ አበክሬ አምናለሁ፡፡ በጸጥታ እኩይ ደባን እንደ ድል ማመንም፤በራሱ እኩይ ደባ መፈጸም ነው፡፡ ግፍን በዝምታ መመልከትም የለየለት የሞራል ሕገወጥነት ነው፡፡ ጥላቻን ተግባራቸው ካደረጉም ጋር መወገን በራሱ የጥላቻውአካል መሆን ነው፡፡ የሕግ ምሳሌያዊ አባባልም ‹‹ዝምታ ፈቃድ አለያም መስማማት ነው››፡፡ በይሉኝታ ብቻ በዝምተኞች የሚረጨው ውሃ በተጨቋኞች ልብና ሕሊና ውስጥ የሚፈላውን መከራና ቁጣ የሚያቀዘቅዝ አይሆንም፡፡ ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ እንዳለው፤ ‹‹እንደ ዝምታ የባለስልጣናትን ጉልበት የሚያጠናክር ምንም የለም››፡፡ እኔ ደግሞ‹‹አምባገነናዊ አስተዳደርን እንደ ዝምታ የሚያጠናክረው የለም እላለሁ፡፡ ማንም ቢሆን ጨቋኞችን በዝምታ ቋንቋ ሊያነጋግራቸው አይሆንለትምና፤  እውነት በሆነ የእምቢተኛነት ቋንቋ ሊያነጋግራቸው ይገባል፡፡ ዝምታ በምንም መልኩ የግብዞችና የአጭበርባሪዎች የመጨረሻው መሸሸጊያ ሊሆን አይገባም፡፡

አንዳንድ አበረታች የእድገት አዝማሚያዎች ይታያሉ፡፡ ባለፉት ሳምንታት በርካታ የነጻነት ብርሃን የፈነጠቁ አስተዋጽኦዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ጨቋኝ ሥርአት ላይ እየታዩ ናቸው፡፡ ሙክታር ኦማር ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› በሚለው የሃሰት ጽነሰ ሃሳብ ላይ፤ አውዳሚ ወይም አጥፊ የሆነ ግን እውነት ሂስ አስነብቦን ነበር፡፡ ‹‹በወቅቱ በኢትዮጵያ ውስጥ አለ የሚባለው እድገት በተገቢው አስተሳሰብ ሲመዘን ከውጭ መንግሥታት በሚቸር ዳረጎት እንጂ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ በሚጮኸው የመፈክር ጋጋት አይደለም::በትክክለኛው አስተሳሰብ የማርክሲዝም ኮሚኒዝምን ግንኙነት እና የአብዮታዊ ዴሞክራሲን ትስስር በሚገባ ያሳየናል፡፡” ሙክታር ሲያጠቃልል፤ “ከመለስ ዜናዊ  አስተሳሰብ ጋር ፍቅር ያላቸው ምሁራን ምክንያታዊ በማድረግ አስደንጋጫ የሆነውን የሰብአዊ መብት ሬኮርዱን ለመዘንጋት ካሰቡ እነሱም በፈቃደኝነት አለማወቅ ወንጀለኞች ናቸው፤ አለያም ከፕሮፌሰር ጆን ግሬይ ‹‹መሰራታዊ እኩይነት ከእድገት ክትትል ይወለዳል›› ከሚለው ምሁራዊ ማሳሰቢያ ጋር አይስማሙም፡፡

የኢትዮ ፎረም ድሕረ ገፅ  ዋና አዘጋጅ ‹‹ልማታዊው ኪስ አውላቂ ›› በሚል የአማርኛ ፅሁፍ፤ የአባይን ግድብ ለመጨረሻ ተብሎ በቢሊዮን ዶላር የሚሰበሰብለት፤በከንቱነት የሚነገርለት የሬኔሳንስ ቦንድ ግልባጭ መሆኑን በማስረጃ ያቀርብልናል፡፡ ሕዝቡ በችጋር እየተቆላና በጨቋኞች አለ አግባብ  እየተኮነነ የልማት ግድብ አለ ማለት ከንቱ ነው፡፡

ከእኔ በበለጠ ብልሆች የሆኑት የምከተለው ፍሬ ቢስ አቅጣጫ እንደሆነ ይነግሩኛል፡፡ ፊትህ ደም እስኪመስል መጮህ፤ማሳሰብ ትችላለህ፤ያም ሆኖም ግን ከኢትዮጵያ ጉማሬዎች ሰፋ ያለ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ፤ ጥብቅና፤ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ ብለህ ማመን ግን፤ ከቀይ ስር ደም አንደመጭመቅ የሚቆጠር ነው፡፡ ብልሆቹ እንደሚሉኝም፤ እነ አባ ዝምታን የዝምታ ዓለም ዝም ብሎ በአቦሸማኔዎች መሬት መጻፍ ይሻላል ነው::  እነሱን ከመጨቅጨቅ ዝም ብሎ ፤ እኩይነትን ላለመስማት ክፋትን ላለማየት፤ክፉ ላለመናገር በፈጠሩት የማስመሰያ አስደሳች መኖሪያቸው ዓለም እንዲኖሩ መተው ይሻላል ይሉኛል፡፡

እና እንደዚያ ላድርግ?

ከአቦሸማኔዎች ጋር ዕምንትን መልሶ መገንባት

ትልቅ ችግር አለን! በጣም ትልቅ፡፡ ‹‹እኛ›› ሁላችንም አቦሸማኔዎችና ጉማሬዎች ነን፡፡ እውነት እውነቱን እንነጋገር፡፡ ጉማሬዎች ከአቦ ሸማኔዎች ጋር የነበራቸውን እምነት አፍርሰዋል፡፡ አቦሸማኔዎች በጉማሬዎች ክህደትተፈጽሞብናል ይላሉ፡፡ አቦሸማኔዎች ተገፍተናል ጫና ተደርጎብናል ይላሉ፡፡ አቦሸማኔዎች ታማኝነታቸውና መስዋእትነታቸውበጉማሬዎች ተንኮል ተተክቶብናል ይላሉ፡፡ የአክብሮታችንና የታዛዥነታችን መልሱ ማንቋሸሽና ድፍረት ሆኗል ይላሉ፡፡ አቦሸማኔዎች፤ ጉማሬዎች ትህትናቸውን በአድርባይነት፤ ሃሳብ ተቀባይነታቸውን በግትርነት፤ ሰብአዊነታቸውን በክብረነክነት መልሰውልናል ይላሉ፡፡ አቦሸማኔዎች፤ ክህደት፤ ለእስራት ፤ተንኮል፤ውሸት፤መደናገር በጉማሬዎችተፈጸመብን ይላሉ፡፡ አቦሸማኔዎች የጉማሬዎችን ተጠያቂነት በማንሳታችን ተኮንነናል ይላሉ፡፡ እራሳቸውን በነጻ በመግለጻቸው ሰበብ በጉማሬዎች ዝምታ ለግፍ ስራ ተዳርገናል ይላሉ፡፡ አቦሸማኔዎች በጉማሬዎች ላይ እምነታቸውን አጥተዋል፡፡ ከበርካታ ኢትዮጵያዊያን አቦሸማኔዎች የምሰማው የስሞታ መግለጫ ይህን የመሰለ ነው፡፡ አቦሸማኔዎችይህን ማንሳታቸው፤ ቅሬታቸው፤ ስሜታቸው ትክክል ነው? ጉማሬዎችስ ይህን ያህል ደባ ፈጽመዋል?

ስለ መተማመን መልሶ ግንባታ ከመነጋገራችን በፊት በቅድሚያ ወጣቱ ከባለእድሜዎቹ ጋር ስላለው አለመግባባት ትንሽ እናንሳ፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች በየቀኑ በግዴታ የንስሃ ጸሎት በሚሰሙበትና የሚመዘኑትም በተፈጥሮ ስብእናቸው ሳይሆን በዘራቸው እንዲሆን በሚገደዱበት ቦታ ነው፡፡ ግላዊነት፤ዜግነት፤ሰብአዊነት የሌላቸው ዘረኝነት ብቻ የነገሰበትነው፡፡ ለዚህም ነው ‹‹የዘር ፌዴራሊዝም›› የሚባል መኖርያ የፈጠሩላቸው፡፡ ወጣቶቹ በሕይወት የመኖርያቸው ጣቢያ የተወሰነው በአእምሮ ብስለታቸው ችሎታ ሳይሆን፤ በነዚያ ማሰብ በተሳናቸው የግፍ አምባ ገዢዎች ፈቃድ መሆኑን በሚገባ ተረድተዋል፡፡ከአጋሮቻቸው ጋር በእኩል ከሚያስተሳስራቸው ሁኔታ ጋር ሳይሆን በሚያለያያቸው ላይ በይበልጥ እንዲያተኩሩ ተገድደዋል፡፡በዚህ እጅጉን እኩይ በሆነ ሰይጣናዊ አስተሳሰብና አካሄድ የሚያዳምጡት ነገር ቢኖር በዝምታ ከታገዱት የሚወጣውን የዝምታ ዱለታ ብቻ ነው፡፡ ከኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ጋር አመኔታን መልሶ ለመገንባት በቅድሚያ ዝምታችንን በአምቢተኛነት በመለወጥ፤ እራሳችንን ከተለጎመበት በማላቀቅ፤ በማያወላውል ቆራጥ አቋም ላይ ማሰለፍ አለብን፡፡

ከወጣቶቹ ጋር እምንት ከመገንባታችን በፊት ከራሳችን ጋር መተማመን መቻል ይኖርብናል፡፡ ማለትም ወጣቱን ወገናችንን ከማዳናችን አስቀድሞ እራሳችንን ማዳን መቻል፡፡ ከራሳችን ጋር መተማመን ከመገንባታችን በፊት፤ ስለፈፀምነው ስህተትና ቸል ስላልነው ጉዳይ እራሳችንን ይቅር ማለት መቻል፡፡ በራሳችንና ትክክለኛነት በመተማመን፤ የነጻነትንና የሰብአዊ መብትን አስፈላጊነት አምነን መቀበል፡፡ ወጣቱ ወኔውን እንዲያጠናክር ከመንገራችን በፊት እኛ እራሳችንከፍርሃታችን መላቀቅ፡፡ ወጣቶቻችን እንደ አንድ እናት ኢትዮጵያ ልጆች መዋደድ እንዳለባቸው ከመንገራችን በፊትከውስጣችን ጥላቻን ማጥፋት፡፡ ከራሳችን ጋር መተማመን ለመፍጠር መቻል እንድንበቃ አስቀድመን ከምቾት ከልላችን፤ከምቾት ስብስባችን፤ ከምቾት አምባችንና ጎሳችን መላቀቅ፤ ቀደም ሲል ልናደርገው ሲገባን በችልታ ሳናደርገውየቀረውን ተግባር ለመፈጸም ዝግጁ መሆን አለብን፡፡  ማንኛቸውንም ጉዳይ ማድረግና መፈጸም የሚኖርብን እውነትና ትክክል ስለሆነ ብቻ እንጂ ከሌሎች ስለተፈቀደልን ወይም ስለተከለከልን ሊሆን ጨርሶ አይገባም፡፡ ጆርጅ ኦረዌል እንዳለው ‹‹በዓለም አቀፍ ማታለል ወቅት፤ እውነትን ገልጦ መናገር የእምቢታ ተግባር ተደርጎ ይታያል›› እንዲያ ከሆነም፤ ሁላችንም እምቢተኞች ሆነን ስልጣን ላይ ለተኮፈሱት፤ አቅመቢስ ለሆኑት፤ጉልበታቸውንና ሃይላቸውን ለተነጠቁት፤ ለየእራሳችንም እውነቱን ልንናገር ይገባል፡፡

ለአቻ ጉማሬ ወገኖቼ ሚዛናዊ ለመሆን፤ ለግፈኞች እውነቱን መናገር አንዳችም ለውጥ አያስገኝም በሚል እምነት ዝምለማለት መምረጣቸውን ይናገራሉ፡፡ ለግፈኞች እውነትን መናገር ጊዜ ማጥፋት ነው ይላሉ፡፡ ግፈኞች የሚያዳምጡትምሆነ ለመስማት ፈቃደኛ የሚሆኑት የመሳርያ ጩኸትን ብቻ በመሆኑ፤ ከነሱ ጋር ስለእውነት መናገር መመከሩ ከንቱድካም ነው ይላሉ፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ እኔ ልዩነት አለኝ፡፡ ለነጻነት፤ ለዴሞክራሲ፤ለሰብአዊ መብት በሚደረግ ትግል፤ መናገር የሰዎችን ሕሊናና ልብ ከጠመንጃ፤ ከመድፍ፤ ከጦር አውሮፕላን በበለጠ ያሸንፋል፡፡ ለዚህም ታሪክ እራሱ ምስክር ነው፡፡አሜሪካ በቪየትናም ለሽንፈት የተዳረገው የጦር አውሮፕላን፤የጦር መሳርያ፤ ቴክኒካዊ ብቃት፤ ወይም የገንዘብ አቅም በማጣቱ አልነበረም፡፡ አሜሪካ በጦርነቱ ለሽንፈት የተዳረገው የቪየትናማዊያንን ልብን ሕሊና ለማሸነፍ ባለመብቃቱ ነው፡፡

ሕሊናንና ልብን ለማሸነፍ በሚካሄድ ጦርነት ቃላት በጣሙን የጠነከሩ መሳርያዎች ናቸው፡፡ቃላት እንደምንፈጥራቸውና ገጣጥመን እንደምንጠቀምባቸው ቀላል አይደሉም፡፡ቃላት እጅጉን ሃያል ናቸው፡፡ቃላት ጨለማውን ያበራሉ፤የተጨፈነን አይን፤ የታሸጉ ዓይኖችን፤የተደፈኑ ጆሮዎችን፤ የተለጎሙ አፎችን ይከፍታሉ፡፡ ቃላትያነሳሳሉ፤ያሳውቃሉ፤ ሕይወት ይዘራሉ፡፡ በታሪክ ከፍተኛ ቦታዎች ከተሰጡት አንዱ የሆነው የጦር መሪ ናፖሊዮን ቦናፓርቴ፤ከጠብመንጃ ይልቅ ቃላቶችን አምርሮ ይፈራ ነበር፡፡ ለዚህ ነው ‹‹ከአንድሺህ ጦር መሳርያዎች፤አራት የጠላት ጋዜጦች ሊፈሩ ይገባል›› (ወይም ከሺ ጦረኛ አንድ ጋዜጠኛ ይፈራል) ያለው፡፡ ለዚህ ነው እኔም፤ ውድ የተሳካላችሁ ምሁራን ወዳጆቼም ሆኑ ሌሎችምበምር የዴሞክራሲ፤ የነጻነት፤ የሰብአዊ መብት፤ የሕግ የበላይነት መከበር፤ ደጋፊዎች ነን የሚሉት ሁሉ መነጋር፤ደግሞም መናገር፤ መናገር አሁንም መናገር ያለባቸውና ከዝምታ መጋረጃ ጀርባ ተጠቅልለው መሸሸግ የለባቸውም የምለው፡፡ እኔ የምለው፤ ዕውነትን ለግፈኞች ተናገሩ ነው::   እምነትን በሰብአዊ  መብት መለኮትነት፤ በዘር አክራሪነት ክፉነት ላይ አሳምኑ፤በግፊት፤በወንጀል ድርጊት ፊት፤ስልጣናቸውን አላግባብ በሚጠቀሙና ሕዝባዊ መብቶችን በመግፈፍ ለእኩይ ምግባር በተሰለፉ ፊት ጨርሶ ለዝምታ ቦታ አትስጡ፡፡

ከአቦሸማኔዎች ጋር መተማመንን መገንባት በጣሙን አስፈላጊ ነው፡፡ በጉማሬዎችና በአቦሸማኔዎች መሃል ያለው የትውልድ ክፍተት ጉዳይ አይደለም፡፡ያለው የመተማመን ክፍተት ነው፡፡የግምት ክፍተት፤የመግባባት ክፍተት፤ ከፍ ያለ የርህራሄ ክፍተት አለ፡፡ አቦሸማኔዎችንና ጉማሬዎችን የሚከፋፍላቸውን ክፍተት ለመዝጋት በርካታ ድልድዮች መሰራትአለባቸው፡፡

የ ”አቦጉማሬ” ትውልድ ትንሳኤ

‹‹አዲስ›› የ “አቦጉማሬ” ትውልድ አየመጣ ነው:: “አቦጉማሬ” አስተሳሰቡን፤ድርጊቱን፤ ጸባዩን ሁሉ እንደ አቦሸማኔ ለማድረግ የሚጥር  ማናቸዉም ሰው ነው፡፡ የጉማሬዎችን ገደብ እያወቀ ግን ለአንድ ግብ በአንድ ዓላማ አብሮ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ አቦሸማኔም: አቦጉማሬ ነው፡፡ “አቦጉማሬዎች” ድልድይ ሰሪዎች ናቸው፡፡ትውልድን ለማቀላቀል ወጣቱን ከባለእድሜው ጋር ለማድረግ ድልድይ ይሰራሉ፡፡ዴሞክራሲን፤ነጻነትን፤ ሰብአዊ መብትን ለማስከበር የሚጥሩ ሰዎችን ለማገናኘት ድልድይ ይሰራሉ፡፡ በዘር ገደል  የተከፋፈሉትን ለማገናኘት አግድመት ድልድይ በመስራት ከታሰሩበት የዘር ወህኒ ቤት ደሴት ያሸጋገራሉ ያገናኛሉ፡፡ የቋንቋ ሰርጥን  ሃይማኖትን እና ክልልንን ያቀራርባሉ፡፡ ድሃውን ከሃብታሙ ለማቀራረብ ጥራሉ፡፡ የብሔራዊ አንድነትን ድልድይ በመገንባት ሁሉንም ያስማማሉ፡፡ በሃገር ውስጥ ያለውን ወጣት በዲያስፖራ ካለው ወጣት ጋር ለማስተሳሰር ድልድይ ይሰራሉ፡፡ “አቦጉማሬዎች” ማህበራዊና ፖለቲካዊ  አውታር በመፍጠር ለወጣቱ የፈረጠመ ጉልበት ይሰጡታል፡፡

አንተስ አቦጉማሬ ነህ ወይስ ጉማሬ?

አቦጉማሬ የምትሆነው እምንትህ፡-

ወጣቱ ትውልድ የሃገሪቱ የወደፊት ተስፋ መሆኑንና ባለእድሜዎች ደግሞ የሃገሪቱ ያለፈ ጊዜ መሆናቸውን ካመንክ፤

መጪው ትውልድም ጊዜም በጣም የተሻለና እጅጉንም አስፈላጊነቱን ካመንክ፤

የሰው ዋጋው የሚወሰነው ከስሙ/ስሟ ጋር በሚለጠፈው ተቀጥላ ሳይሆን ወገኑ ለሆነው ሰብአዊ ፍጡር ስለ ሰብአዊ

መብቱ መከበር ለመቆም ባለው ቆራጥ ወገናዊነት ፤ጥሩ ባህሪ፤ትህትና፤ ህዝባዊ ተግባር፤ ትብብር፤ የሰው ችግር

የሚገባው፤ይቅር ባይ፤ ታማኝነት፤ክብር፤ ሃሳባዊነት፤ተጣማሪነት፤ እና ግልጽነት ያለው በመሆኑ ሊሆን ይገባል የሚል

ከሆነ ነው::

አቦጉማሬ የምትሆነው ሁኔታህ

ግልጽ አእምሮ፤ተለዋጭ፤እና ትሁት ስትሆን፤

ከተለያዩ እድሜ ካላቸው፤ ከተለያዩ ዘር፤ ሃይማኖት፤ ጾታ፤ እና ቋንቋ ተናጋሪዎች ጋር አዲስ ሃሳቦችን

የምትቀበልና ለመግባባት የምትችል ከሆነ፤

ከምቾት አምባህ ወጥተህ አስቸጋሪ ምርጫ ውስጥ ለመቀላቀል ፈቃደኛ ከሆንክ፤

ያልከውን የምትሆንና የምትለውን ለመሆን በቆራጥነት የምትቆም እንጂ በመዘላበድና በአሉባልታ፤ በአገም ጠቀም ጊዜ የማታጠፋ ከሆንክ፤

ከነገ ይልቅ በዛሬው ለመጠቀም ፈቃደኛና ዝግጁ ከሆንክ፤

ወጣቱንም ሆነ ሌሎችን በጥፋታቸው ከመውቀስህ በፊት በፈጸምከው ድክመት እራስህን ለመውቀስ ዝግጁ ከሆንክ፤

ያለፈውን አጉል ትምህርት በመርሳት አዲስ ትምህርት ለመማር ጉጉ ከሆንክ፤

ምቹ ጊዜ በማጣት ከማማረር ምቹውን ጊዜ ለማግኘት የምትጥር ከሆንክ፤

ሁኔታዎችንና እምንት ለማዳበር የሚችለውን ለማንጸበራቅ እንጂ የማይቻለወን የማታማርር ከሆንክ፤

ዓለም በማያቋርጥና በፈጣን ለውጥ ላይ መሆኗን በመገንዘብ ለመለወጥ ባለመቻልህ ተወቃሹ አንተው ብቻ እንጂ ሌላ

አለመኖሩን ከተገነዘብክ ነው፡፡

*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):

http://open.salon.com/blog/almariam/2013/01/27/ethiopia_rise_of_the_chee-hippo_generation

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::) ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

Leave a Reply