We are learning that the division within the ruling junta EPRDF is deepening by the day and by the hour as they squabble over who will replace Meles Zenawi continues. Making things even more complicated is that widow of the late dictator, Azeb Mesfin, is refusing to vacate the prime minister’s residence until a new prime minister is selected. The EPRDF 180-member council is called to replace Meles next week, but some thing may explode before the meeting, according to observers in Addis Ababa.
Author Tesfaye Gebreab has this (tongue-in-cheek) advise to his former comrades:
የኢህአዴግ የስልጣን ሽኩቻ ተባብሶ በመቀጠሉ የአመራር አባላቱ ዝግ ስብሰባ ላይ ስለመሆናቸው እየተሰማ ነው። ይህን ሽኩቻ ከህዝብ ጆሮ ለመሰወር ሲባል ስለ ኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ በቴሌቪዥን የተላለፈው ቀሽም ድራማ ነበር። የአመራር አባላቱ እጃቸውን እያወጡ ድምፅ ሲሰጡ በቲቪ ይታያል። በምን ጉዳይ ላይ ነው ተከራክረው በድምፅ ወሰኑት? አልተገለፀም። ከኢህአዴግ ነባር ልምድ አንፃር፣ ከስብሰባው በፊት ጋዜጠኞች ገብተው ምስል ቀርፀው እንዲወጡ እንደሚደረግ አውቃለሁ። ከዚያም በሮችና መስኮቶች ተዘግተው ስብሰባው ይቀጥላል።
ሆነው ሆኖ፣ የመለስ ሞት ከተጠበቀው ጊዜ ፈጥኖ የመጣ ነበርና ጓዶች ያልተዘጋጁበት ገጥሟቸዋል። መለስ ጷግሜ ላይ ወደ አገርቤት ተመልሶ ለእንቁጣጣሽ ዋዜማ የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት፣ እስርቤቱን ባዶ ያደርገዋል ተብሎ እየተጠበቀ እሱ ግን እንደወጣ ቀረ። እንግዲህ ህይወት መቀጠሏ አልቀረም። በችግር ጊዜ መረዳዳት ያለ ነውና፣ የቀድሞ ጓደኞቼ ምናልባት ከሰሙኝ አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮችን እዚህ ላስቀምጥ።
የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ለሃይለማርያም ከመስጠት የተሻለ ምንም አማራጭ የለም። በዚህ ጉዳይ ላይ ልዩነቶች እየጠበቡ ስለመጡ ይህ ችግር አይመስለኝም። ርግጥ ነው፣ ሁሉም የአባል ድርጅቶች ሃይለማርያምን የሚፈልጉበት የየራሳቸው ምክንያት አላቸው። በጥቅሉ ግን ‘ቢያንስ ሃይሌ አይከዳም።’ ተብሎ ይታሰባል። ሃይለማርያም ወንበሩን የሚረከብ ከሆነ የራሱን ካቢኔ ለመቋቋም መጠየቁ መረጃ አለ። መረጃው ግን አጠራጠሮኛል። ሃይሌ ከጀርባ የሚገፋው ከሌለ ብቻውን ያን ያህል አይዳፈርም። ስለቡድን አሰራር ደህና አድርገው አጥምቀውታልና፣ በአንጋፋዎቹ እየተመከረ ስራውን ሊሰራ ራሱን አሰናድቶአል። በባህርይው ለስላሳ በመሆኑ ትእዛዝ ይጥሳል ተብሎ አይጠበቅም። ህወሃት ሃይለማርያምን በደንብ እየተቆጣጠረ ለማሰራት፣ ከአንጋፎቹ አንዱን አማካሪ አድርጎ መሾም ነው። አርከበ እቁባይ፣ አባይ ፀሃዬ፣ ስዩም መስፍን የሚሉ አሉ። በውጭ ግንኙነት ልምድ ስላለው ስዩም ይሻላል። አባይ ፀሃዬ የጀመረውን ይጨርስ። በተለይ የዋልድባ ነገር ከስኳር ምርቱ ይልቅ ከጎንደር – ትግራይ ድንበር ጋር የተያያዘ የመሬት ባለቤትነት ጉዳይ ስላለበት፣ ያንን ዳር ማድረስ ይገባልና አባይ ፀሃዬን መንካት አይገባም። … [read the full text here]