Skip to content

በቀልድ ምርጫ መሳተፍ ትርጉሙ ምንድ ነው?

ከይልማ በቀለ

PDF

ውድ ወንድሜ አቶ ግርማ ካሳ ያቀረቡትን ጽሁፍ በአዲስ ቮይስ ድረ ገጽ ላይ አንብቤዋለሁ፡1 አቶ ግርማ ካሳ በየጊዜው በዳያስፖራ ድረ ገፆች ላይ በአለው የአገራችን ሁኔታ የሚጽፉትን ተከታትዬ አነበዋለሁ። ጊዜአቸውን ውስደው፤ በጥሞና አስበው የሚአወጡት ጽሁፍ አንባቢዎቸቸውን ስለ ውድ አገራችን እንድናስብ ያበረታታናል ብየ አምናለሁ።

ዛሬ ግን አኔ ማተኮር የፈለጉት ሰሞኑን በጻፉት “የፊታችን ምርጫ ቀልድ ነው – መድረኩ ግን መሳተፍ ይበጀዋል” በተባለው ላይ ነው ። (ይህን ሊንክ ቢጫኑ የአቶ ግርማን ጽሁፍ ለማንበብ ይችላሉ)

ጽሁፉን የሚጀምሩት ‘ሕወሃት ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ለማድረግይዘጋጃል ታዛቢዎች አዲስ አበባ ገብተዋል፣ መድርክ፣ መኢአድ፣ ኢዳፓ፣ የምርጫ ዘመቻው አጧጥፈውታል ብለው ነው። አስደሳች ጉዳይ ነው።

ስለ ዳያስፖራው ደ ግሞ ሲናገሩ ግንቦት ሰባትናአንዳንድ ተቋዋሚዎች ‘ምርጫውን ሕወሃት ስላሸነፈው ያለመሳተፍና እራስን ማግለል ‘የሚል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፍተዋል’ ይላሉ። እነፕሮፈሰር መስፍንና ደጋፊዎቻችው ደግሞ እንዴት ወ/ሮ (ሊቀመንበር) ብርቱካን ታስራ ምርጫ ይገባል የማለት ጥያቄ እያነሱ መሆናችቸውን ይገለፃሉ።

የፅሁፋቸውም አላማ ውይይት ለማምጣት መሆኑን ይገልጹና መደምደሚያው ላይ ‘በምርጫው መሳተፍ አይገባም የሚል አቋም የሚይዙ ወገኖች ካሉ ደግሞ የመከራከሪያ ነጥባቸውን ለመስማት ዝግጁዎች ነን። አንድ ሁለት ብለው የምርጫውን ቦይኮት ጥቅም ያስርዱን። ያላቸውን አማራጮች ያቅርቡልን። መክሰስ፣መተቸት፣መሳደብ በጣም ቀላል ነው። መፍትሄ ማምጣት ግን ፍፁም የተለየ ነገር ነው። ሌሎች ድርጅቶች የሚሰሩትን ማጣጣል አንድ ነገር ነው። ሰርቶ ማሳየት ግን ሌላ ነገር ነው’ ብለው ሃይል በተሞላው ግሳፄ ይዘጋሉ።

በጣም ጥሩ አቶ ግርማ እኔም በበኩሌ በጣም እስማማለሁ። በኔ አስተሳስብ ይሄ ጽሁፍ ለመጀመሪያ ጌዜ የመድረኩን አላማ ከማድበስበስ አልፍ በግልጽ ያወጣ ነው ብዬ አምናለሁ።መድረኩ ምን ይፈልጋል ይሚለውን ጥያቄ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚመልስ ይመስላል።ባይመልስም ይሞክራል።

ወደ ዋናው ቁም ነገሩ እንሂድና ጽሁፉ የሕወሃትን መንግስት ተቋሚዎች በሙሉ የምንስማማባቸውን ነጥቦች ሲያቀርብ ዋና ብሎ የሚያስማማንም በቀይ ያስምርዋል ‘የ2002 ምርጫን ከምንም መሳፍርት ሚዛን ፍትሓዊና ዲሞክራሲያዌሊባል አይችልም’ ክዚህም አልፎ ያ ለውን ችግር ሲያብራሩ የወ/ት (ሊቀመንበር) ብርቱካን ያለ አግባብ መታስር፤ ብግልፅ የምናውቀው ሁለት እጩዎች መገደል፣ በምርጫው ምክንያት የብዙ ወገኖች መጎሳቆልናየመነግስት ሰርራተኞች በማስገደድ የመሃላፊርማ መደረጉን ገልፆ ‘ይህ ሁሉ ምን ያህል ምርጫው ጫወታ መሆኑንበግልጽ የሚያሳይ ነው’ ይላል።

ትንታነውን በመቀጠልም ሕውሃት እስክ አርባ ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች በታዛቢነት የሚያገለግሉ አባሎቹን (ካድሬ) መለምሏል ማለትም ይላሉ አቶ ግርማ ‘የምርጫውን ውጤት የሚወስነው ደግሞ ድምጽ ስጭው ሳይሆን ድምጽ ቆጣሪው ነው ቢባል ሕወሃት የሚያደርገው ምርጫ በምንም ስፈርት ንፃናዲሞክራሲያዊ ሊሆን አይችልም ብሎ በሩን ይቀረቅራል።

ውድ አንባቢ ሆይ፣ ታድያስ ክርክሩ ምን ላይ ነው ብለው ትንሽ ቢቸገሩ አያስደንቅም። ምክንያቱም በፀሃፊው አንጋገር ሕውሃት ወይም የአቶ መለስ ድርጅት የዋናው ተቃራኒ ፓርቲ ሊቀመንበርን በግፍ አስሮ፤ የፓርላማ እጩዎችን ገድሎ፣ከሚኖሩበት አፈናቅሎ፤ ስልጣኑን በመጠቀም ስራትኞችንየባርነት ቃል ኪዳን አስፈርሞና ካድሬዎቹን የምርጫ ታዛቢ ብሎ ሹሞ ለይስሙላና ፈረንጆችን ለመደለል በሚያደረገው ምርጫ ላይ መሳተፍ ተገቢ ነው ብልው ክርክራቸውን ያቀርባሉ፣ስምንት ነጥቦችም ያስቀምጣሉ።

‘ክርክሩና አለመስምማማቱ የሚመጣው’ ይላሉ ፀሓፊው ‘ምርጫው …ኢፍትሃዊና ዴሞክራሲያ ሆኖም፣ሕወሃት/ኢሕአዴግ በቀላሉ አጭበርብሮ ተመረጥኩኝ ብሎ የሚያውጅበት ሁኔታ ስፊ ቢሆንም፣ ክመርጫው እራሳቸንን ማግለል ንው የሚበጀው ወይንስ በምርጫው ገፍቶ መሄድ? በሚለው ላይ ንው።

ፀሃፊው የሚሉን በምንም አይነት መንገድ የአቶ መለስ መንግስት የመሸነፍ ሃሳብ የለውም፤ መሬትና ሰማይ ቢገናኛአይሸነፍም፣ ግን ቢሆንም ምን አለበት ገብተን ብንሸነፍ ነው።አቶ መለስ ‘አይናችሁን ጨፍኑ ላታልላችሁ ፈልጋለሁ’ ሲሉ ኩታ ማቀበል እንዴት መልካም ይሆናል ውድ ወዳጄ?

ግድ የለም እሺ ብለን እስቲ ፀሃፊው የዘረዘሩትን ስምንት ንጥቦች እንመልከታቸው። በመጀመሪያ የወያኔው መንግሥት ከምርጫው ማግስት አሽነፍኩ ብሎ ሲያውጅ፣ ይላሉ ፀሃፊው፣ የም እራብ መንግስታትና ሰብ አዊ መብት ድርጅቶች ጥቂት ያወግዙና ይቀበሉታል፣ ስለዚህ ‘መድረኩ ከምርጫው ቢወጣ የሚያገኘው አንዳች ፋይዳና ጥቅም አይኖርም’።ትንሽ ግራ የሚያጋባ አነጋገር ነው። ምርጫው የሚካሄደው በኢትዮጵያኖች ለኢትዮጵያንከሆነ የፈረንጆች መቀበልና አለመቀበል ብዚህ ውስጥ ምን አገባው። በሕወሃት መንግስትን ሕገ ወጥ አገዛዝ እሳትየሚነደው ኢትዮጵያዊ ነው ወይስ ፈረንጅ? ታድያ መድረኩ መጨነቅ ያለበት ስለ ሕዝቡ ወይስ ስለራሱ? ትላንት ኬንያ ውስጥ የተጭበረበረ ምርጫ ሲካሄድ ፈረንጆቹኮ ተቀብለውት ሕዝቡ ነው እኮ አይሆንም ያለው። እስቲ በታሪክ ተበዳዩ ሳይጮህዳኝነት የተጠራበት ጊዜ ወይንም ቦታ ይነገረን?

በሁለተኛ ደረጃ ሕወሃት መኢአድንና፣ ኢዳፓን የመሳሰሉ ምርከኞች ስላሉት መድረኩ ብቻውን ይቀራል ስለዚህ መሳተፉ ይበጃል ነው። በጣም ደካማ ክርክር ይመስላል። ለመሆኑ ሕወሃት መቼ አጃቢ አጥትቶ ያውቃል? ጥያቄው አጃቢነት ለማን ጠቀመ ቢሆን ጥሩ ይመስላል። አልበቃ ተብሎ ደግሞ የደቡብ አፍሪካ ትግል ይጠቀሳል። ታድያ እኮእነ ኔልሰን ማንዴላ፣ ስቲቭን ቢኮያስተማሩን ሌላ ነው። በስላም ይመረጣል ካልሆነም በሰደፍ እንጅ ኩታ አቀብሉኝ አይኔን ልሸፍን አልወጣቸውም።

በአራተኛ ደረጃ መድረኩ እራሱን ቢያገል አገዛዙ ፀረ ሰላምና ሽብርተኛ በማለት ሕጋዊንቱን ይነጥቀዋል ስለዚሀበግልጽ መንቀሳቀስ፣ስብሰባዎች ሰላማዊ ሠልፎች ማናቸውንም ዝግጅት ማድረግ አይችልም፣ ጽ/ቤቱም ይዘጋል ይላሉ።ችግሩ የህገወጥ መንግስትን ባሕሪን ካለም መገንዘብ የመጣ ይመስላል። የፓርቲው ሕጋዊነት እኮ በህገ መንግስቱ ላይ የተመሰረተ ነው እንጅ በገዥው በጎ ፈቃድ የተሰጠ አይደለም፣ ስለዚህ የመድረኩ ስራ ገዥው የራሱን ህግ እንዲያከብር ማስገደድ ነው እንጂ እንደ ቄጠማ መሽመድመድ መሆን የለበትም።እውነቱ ግን መድረኩ ዛሬ ሕጋዊ ሆኖ ከላይ የተጠቀሱትን መች አደረገና? ለሊቀመንበርዋ አንድ አመት እስራት የሻማ ማብራት ዝግጅት ዝግ ቤት ውስጥ የተደረገው በሕገመንግስቱ የተፈቀደውን ለማስከበር ወደ ሁዋላ ስለተባለ አይደለም? በተራ ካድሬ ስብሰባ የሚከለከለው ፣ሽማግሌ አሮጊት የሚደበደበው ሃቅ ነውኮ።

አምስተኛው ነጥብ ለቁጥር የገባ ይመስላለ። መድረኩ አሁን ‘የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ምርጫውም ካለቀ ብኋላእንዲቅጥሉ መደረግ አለበት’ ይላል። ችግሩ ግን አሁን በምርጫ ሰበብ ፈረንጆቹ ባሉበት እንኳን ያለ ሕወሃት ፈቃድ መሰባሰ ያልቻለ ታድያስ ከምርጫው በኋላ የሚሆን ይመሰላለ? ታዛቢ ይፍረድ። ‘ኢሓአዴግ አሽነፈ ማለት ለሚቀጥሉት አምስት አመታት ይገዛል ማለት አይደለም’ ሲሉ ምን ማለታችው ይሆን?

ስድስተኛው ስለ ፈረንጆች መቀበል አለመቀበል ሰለሆን መጀመሪያው ላይ ያየነው መሰለኝ።ሰባተኛው ነጥብ በእውነት ላይ የተመረኮዘ አይመስልም። በመላው ፁሁፉ ሊቀመንበር ብርቱካን የምትጠራው ወ/ት ብርቱካን ተብላ መሆኑምክንያቱ አልገባኝም። ሆኖም መድረኩም ቢሆን አንድነት የሊቀመንበሯ አንደኛ ተሟጋች ናቸው ማለት እውነትን እንደማጣመም ይቆጠራል። በቅርብ ጊዜ እንኹአንሕመሟን ለአለም ያስታወቁት ወዳጆቿ ናችው እንጂ ጓዶችዋ ነን ባይዎች አይደሉም።በዳያስፖራውም የሊቀመንበሯን ጉዳይ በትጋትና ባለመሰልቸት የሚያካሂዱት በፈቃደኝነት የተቋቋሙት ድርጅቶች ናቸው እንጂ በሰሜን አሜሪካ ያለው የ አንድነት ደጋፊ ቡድን አይደለም።

በስምንተኛ ቁጥር ላይ በተጠቀሰው አስተሳሰብ መስጥት ትንሽይችግራል። እኔእንደማውቀው ጌታ እግዚአብሄር ያለው እኔም እንድረዳችሁ መጀመሪያ እራሳችሁን እርዱ መሰለኝ። ታድያ እጅ አጣምሮ ቁጭ ብሎ ‘ተአምር’ መጠበቅየት ያ ደርሳል? ማንም ኢትዮጵያዊ ይሄንን ምርጫ ፀሃፊው እንዳሉት ‘እንደ ቀልድና ጫወታ’ አይወስደውም። በሌላ በኩል አቶ ግርማ “የፊታችን ምርጫ ቀልድ ነው” ብለው ሲተቹ ብዙዎቻቸን የምንስማማ ነን ብዬ አምናለሁ። በርግጡ ደግሞ የአቶ መለስ መንግስት ግን በሕዝቡ ብሶት ላይ እየቀለደ መሆኑንየአለም ህዝብ የሚያውቀው ይመስለኛል።

በኔ አስተሳሰብ ‘መድረክ’ በምርጫው ለመሳተፍ ሙሉመበት አለው ብየ አመናለሁ። የመድረክ መሳተፍ ግንየኢትዮጵያ ሕዝብ ካለበት መከራ የሚያወጣ መፍቻ ቁልፍ አለው ብየ አላምንም።የአገራችን ሰው ሲተረት ‘የማያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያሰታወቃል’ ይላሉ። የመደረክም ጉዳይ እንደዛው ሁኖ አግኝቸዋለሁ። ባንድ በኩል ‘የሰላማዊ ትግል’ እያካሄድን ነው ይሉናል። ጠጋ ብሎ ሲታይ ግን ከመጽሃፉ አንድ ገጽ ብቻ ያነበቡ ይመስላሉ፣ ይኽውም ምርጫ ላይ ብቻ ያተኮረ ይመስላል። ታድያእኮ ‘የሰላማዊ ትግል’ እነማሃታማ ጋንዲ፣ማርቲንሉተር ኪንግ፣ ኔልሰን ማንዴላ ያስተማሩን ልዩ ነው። እነሱ የተጠቀሙት እኮ ‘ካሮትና፣ዱላ’ የተባለውን መንገድ መሰለኝ።መድረኩ ብዙ ካሮት የጫነ ይመስላል ምናለ ዱላው ቢጠፋ አርጩሜ እንኳን ቢይዝ።

ሊቀ መንበሯ ወንጀለኛ ነች፣ እሺ- ሰበሳብ አየፈቀድም፣ እሺ- ተወዳዳሪዎች ይገደላሉ፣ እሺ- ወዘተ ወዘተ።

መቸስ አንድ ነገር ጥሩም ነው ወይም መጥፎ ለመባለ መሞከር አለበት። እነ አቶ መለስ ስልጣን ከተፈናጠጡ ይኽው ወደ አሥራ ስምንት አመት ሆኖታል። አሁን የሚደረገው ምርጫ አራተኛው ይመስለኛል።የኔ ጥያቄ የተቋዋሚው ጎራ ነን እያሉ የአቶ መለስ ፓርላማ ውስጥ የተሳተፉ አንዳንድ አሉ፣ እስቲ እንደው ለእነዚህ አዛውንቶች ስራ ከመስጠት በላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ትርፍ አገኘ? እስቲ አሥራ ስምንት አመት አብሮ ከመስራት ያመጡትን ጥቅም ይንገሩን? እስቲ ያሳለፉት አንድ ሕግ ካለ ይጥቀሱልን? በማንም ያልተመርጠ ካድሬ መጫወቻ ከመሆንና ለሕወሃት ሌጅትማሲ ከመስጠት በስተቀር ሌላምንየሚያሳዩት አለ?

ከራሳችንና ከአለም ሕዝቦች ታሪክ ብንማር የሚከፋ አይመስለኝም። ለምሳሌ ፋሽሽት ጣልያን ውድ ሃገራችንን የደፍረ ጊዜ ቆይ እስቲ መጀመሪያ እንደራደርና ቀስ ብለን ሰጥ ብለን ተገዝተን እናስወጣዋለን አላልንም።

አባቶታችን፣ እናቶታችን ጎበዝ ተነሳ አገርና ቤት ተደፍሮአል ነው ያሉት። አይ አሁን አቅም የለንም ቀስ ብለን እስከምንደራጅ መጠበቅ ይሻላል አልወጣችውም። ለነፃነት ቀጠሮ አይያዝም። ነውር ነው።

ታድያስ ምድረኩ የሚለን ያለፈው አሥራ ስመንት አምት የተሞከረወንና ምንም ውጤት ያለመጣውን ለመስራት እድል ስጡን ንው? ዛሬ በምርጫው ያላሳዩትን አሞት ነገ ደሞዝተኛና ባለስልጣን ሲሆኑ ከየት ያመጡታል? የፈረንጆች አባባል ‘ምራ፣ ተከተል ውይም ከመንገዱ ውጣ’ የሚባለው እዚህ ቦታ ያለው አነጋገር መሰለኝ።

መደረኩን መለካም እድል እመኝለታለሁ። የመድረኩ መሪዎችን ቸሩ ፈጣሪአችን ይጠብቃቸው እላለሁ። ከሕወሃት ጋር መደራደር የነብር ጭራ እንደ መያዝ ነው፣ መጨረሻው የሚያምር አይመስለም።

3 thoughts on “በቀልድ ምርጫ መሳተፍ ትርጉሙ ምንድ ነው?

  1. Selam Elias,
    Plz make sure that you also post an update or two about the hunger strike by Chris Flaherty on his desperate but admirable action to bring attention to the plight of specially Bertukan and the whole Ethiopians under the yoke of vampire TPLf with all its goons.
    I did not see on single article from ER on the hunger strike that is now ongoing since 3 days. This is simply NOT fair!!!

    I personally, like million others, gave up on the so called peaceful struggle years ago after it proved to be a silly credo that will never be able to confront Weyane TPLF head on.
    I mean it as a conclusive statement when I say that the peaceful struggle has my sympathy but zero support.

    All our contributions should normally go to an address where guns with real bullets are ready for the rumble until all weyane parasites drop dead and our motherland is saved.

    If we want Ethiopia to live, we must be also ready to DIE for her!

    Signed: Demfelat

  2. This writer is jealous of the success of the homegrown opposition parties like MEDREK and AEUP. He found some weaknesses in Girma’s writing to ridicule the effort of the opposition and show contempt to their supporters in Ethiopia that are coming out in droves to listen to them.

Leave a Reply