The Ethiopian People’s Patriotic Front (EPPF) recently held its general assembly meeting and made a number of major decisions that affect its activities inside the country and around the world. One of the major decisions the general assembly made was to elect 17 new central committee members from the Diaspora and streamline its activities around the world. This was done to eliminate once and for all any doubt as to who is in charge of EPPF in the Diaspora, which was plagued by confusion and other problems.
The following are statements released by EPPF (Amharic):
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር
ሚያዝያ 6 ቀን 2010 (እ.አ.አ.)
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር (ኢህአግ) ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በቅርቡ በተሳካ ሁኔታ አካሂዶ ድርጅቱ ባለፉት 10 ዓመታት ያካሄደውን እንቅስቃሴ ከገመገመ በኋላ የወደፊት የስራ እቅዶች አውጥቶ፥ እንዲሁም የአመራር አባላትን ምርጫ አካሂዶ ተጠናቋል። በዚሁም መሰረት አዲስ የማዕከላዊ ኮሚቴና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መርጧል።
ድርጅታዊ መዋቅርን በተመለከተ ጠቅላላ ጉባኤው ከወሰናቸው ውሳኔዎች አንዱ የግንባሩ ህገማህበር ተሻሽሎ ማዕከላዊ ኮሚቴው በዳያስፖራ ያሉ ኢትዮጵያውያንን እንዲያካትት ያደረገው ነው። በዚህም መሰራት ከአሜሪካ፥ ከአውሮፓና ከሌሎችህም አህጉራት በጠቅላላው 17 ተጠሪዎች የኢህአግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ተመርጠው ገብተዋል። እነዚህ 17 ተጠሪዎች በዳያስፖራ ያለውን የድርጅቱን እንቅስቃሴ እንዲያስተባብሩ ከጠቅላላ ጉባኤ ሃላፊነት ተቀብለው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
የውጭው አካል ከግንባሩ ጠቅላላ ጉባኤ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የመጀመሪያውን ስብሰባ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ አካሂዶ የስራ ክፍፍልና እቅዶች አውጥቷል። በቀጣይነትም የውጭው አካል ተከታታይ ስብሰባዎች በማድረግ ዝርዝር የስራ እቅዶች አውጥቶ ለህዝብ ይፋ ያደርጋል።
ግንባሩ በተለይ ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች ዋናዎቹ የፊታችን ግንቦት ወር የሚደረገውን የወያኔ የተጭበረበረ ምርጫ ማጋለጥና ኢህአግ ሀገር ውስጥ የሚያካሂደው እንቅስቃሴ በይበልጥ እንዲጠናከር አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ ይሆናል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ከግንባሩ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠውን መግለጫ መመልከት ይችላሉ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
ለተጨማሪ መረጃ፤ አቶ ደምስ በለጠ፥ የፕሬስ መምሪያ ሃላፊ
ስልክ ቁጥር፤ 202 251 2301
* * * * *
ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ከተመሰረተ አንስቶ አገርን የማዳን አኩሪ ተግባራትን በተለያየ መስክ ያደረገ ሲሆን፣ ከዚህ በላቀና በተደራጀ መልኩ በግንባሩና በአለም አቀፍ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገርና ህዝብን ለመታደግ በሚደረገው ትግል ካለፉት አመታት የበለጠና የተጠናከረ ህዝብ አቀፍ ስራ ለመስራት ከመጋቢት 22 እስከ 25/ 2002 አ.ም በተካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ መሰረት ቀጥሏል።
የኢህአግ ሰራዊት በወያኔ ላይ እየወሰደ ያለውን ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ ከእስካሁኑ በላቀ ሁኔታ ወያኔው የሚመካበትን የታጠቀ የግፍ ሃይል ለማንኮታኮት እየሰራ ይገኛል።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወያኔን ለማስወገድ በሚካሄደው እንቅስቃሴ ቀላል የማይባል ሚና ተጫውተዋል። ይሁን እንጅ ተሳትፉቸውንና ጥረታቸውን በማዋሃድና አንድ አቅጣጫ በማስያዝ ረገድ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም የተፈለገውን ያህል ውጤት አላስገኘም። ድርጃታችን ኢ.ህ.አ.ግ ይህን በመረዳት ከውጭ በተመረጡ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ከነሱም መካከል በሰብሳቢው በምክትል ሰብሳቢው እና በዋና ፀሃፊው አስተባባሪነትና አመራር ሰጭነት ሲሆን 14ቱ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎች ነዋሪነታቸውን በውጭ ያደረጉ ወገኖች ሁሉ በተመቻቸው አንድ ወጥ መንገድ ስር በመሰባሰብ እና የሚሰጠውን አገራዊ ተልእኮ በመፈፀምና በማስፈፀም አገርና ህዝብን እያወደመ የሚገኘውን አንባገነኑን የወያኔ ቡድን ይበቃል ልንለው ይገባል።
በተለያየ መንገድ በኢ.ህ.አ.ግ ስም ይንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች ህዝብን ከማወናበድ ተግባር ተቆጥበው በተመቻቸው መንገድ ውስጥ ገብተው እንዲንቀሳቀሱና በጉባኤው በተላለፈው ውሳኔ መሰረት arbegnochginbar.com ሌላ በኢህአግ ስም የተከፈቱ ድረ-ገፆች ህገ-ወጥ መሆናቸውን እያሳወቅን ድርጅታችን በወታደራዊ በፖለቲካና በዲፕሎማሲ… ያለውን ሃይል በመጠቀም ተግቶ ይሰራል።
ወያኔው እየተዘጋጀለት የሚገኘውን የይስሙላ ምርጫ ምእራባውያንም ቢሆኑ እውነታውን የተገነዘቡበትና ፊታቸውን ያዞሩበት ወቀት በመሆኑ በዚህ አጋጣሚ ኢትዮጵያዊ የሆንን ወገኖች ሁሉ ጎጠኛውን አገዛዝ ከስር መሰረቱ ለማስወገድ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አንድ አካል ሆነን አገራችን ኢትዮጵያን ከገባችበት አዘቅት ልናወጣት ይገባል።
6 thoughts on “EPPF streamlines its operations (update)”
EPPF is now reviving the dead spirit of our trademark “Nationalism” I hope one day your movement will come to an achievement that can turn around the future of our beloved country into a nation we will once again be proud of like we are proud by our ancient history and leaders.
Viva eppf. ye Qurt qen Lijoch!
Only eppf knows what it takes to bring down the tplf mafias from minilik palace.
Please tell us who are country representatives so we start contributing!
Hello Elias,
Thank you for the PDF.
Good day
This is a good strat, let us unite behind the EPRDF to kick off the the Meles regime, the ENEMY OF THE ETHIOPIAN people.
The PDF is more of a press release and brief. The mentioned web site in this post, arbegnochginbar.com,although appearing legitmate, and may be an extention of eppfonline.org, its lack of PDF format prevents reading for some of us.
please be strong ,there are so many Ethiopians ready to join due to unfair and destructive activities of weyane .