በሁሉም የአገሪቱ ቀበሌዎች በእያንዳንዳቸው 300 እጩዎች እንዲቀርቡ የሚል መመርያ በማውጣት ተቃዋሚዎችን ከጫወታ ውጭ ካደረገ በኋላ በግዳጅና በማባበያ ለአዲስ አበባ ብቻ 32 ሺህ እጩዎችን ያቀረበው ወያኔ አስቀድሞ ላወቀው የምርጫ ውጤት ለእጩዎቹ ሲሰጥ የሰነበተውን የህዝብ አስተዳደር ስልጠና አጠናቀቀ፡፡
በሁሉም ክፍለ ከተሞች በመሰጠት ላይ የነበረው ስልጠና አንድምታ አሁን ካሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንዳቸውም የተባለውን እጩዎች አሃዝ ያህል ማቅረብ ባለመቻላቸው ወሳኙ ጉዳይ ለ2002ቱ (2010) ምርጫ ራስን ከማዘጋጀት ባለፈ ቀጣዩ ‹‹ውድድር›› አሳሳቢ ያልነበረበት መሆኑ ተመልክቷል፡፡