በተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የመስራቾች ፊርማ ማሰባሰብ በነገው እለት ይጀመራል፡፡
ወደተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በሚደረገው በዚህ የመስራች አባላት ፊርማ የማሰባሰብ ሂደት ወ/ሪት ብርቱካን፤ አቶ ሙሉነህ፤ መቶ አለቃ አለማሁ የኔነህ (አስተባባሪው)፤አቶ መሃመድ አሊ እና ሌሎች የስራ አስፈጻሚ አባላት ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን በዛሬው እለት ርቼ አከባቢ ባለው የፓርቲው ጽ/ቤት በተደረገው ማብራርያና የቅድመ ዝግጅት ውይይት በሂደቱ የሚሳተፉት አባላት ማንኛውንም መስዋእትነት ለመጋፈጥ መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የምርጫ ቦርድ የድጋፍ ደብዳቤ ለመጻፍ የተለያዩ ሰበቦችን ሲያስቀምጥ ከቆየ በኋላ እምቢታውን መግለጹ ይታወሳል፡፡