Skip to content

ምርጫ ቦርድ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችን በሰበቦች ማመላለስ ጀመረ

በወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራው የቀድሞው የቅንጅት አመራር ‹አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ› በሚል አዲስ ስያሜ ፓርቲ ለማቋቋም ከምርጫ ቦርድ ህግ ውጭ በቅድሚያ ስያሜውን እንዲያቀርብ በተጠየቀው መሰረት ከትናንት በስቲያ ማመልከቻውን ቢያቀርብም እስከዛሬ ባሉት ቀናት ‹በደብዳቤው ላይ የሚፈርም ሰው የለም› በሚል ሰበብ የመስራች አባላት ፊርማ ማሰባሰቢያ ፈቃዱን ሊሰጣቸው እንዳልቻለ ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ አመራሮች ፈቃዱን በአስቸኳይ በማግኘት በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በመጓዝ አባላት የማደራጀትና መስራች አባላትን የማሰባሰብ እቅድ ቢኖራቸውም ብዙዎች እንደገመቱት ምርጫ ቦርድ አሳማኝ ባልሆኑ ምክንያቶች ሂደቱን ማራዘም መጀመሩ ሁኔታውን አሳሳቢ አድርጎታል፡፡ ደብዳቤውን ለማግኘት አመራሩ ለነገ መቀጠሩንም ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡

Leave a Reply