Patriotic Ethiopians in Los Angeles confronted and chased away the Woyanne ambassador and cadres during the Fairfax Little Ethiopia Street Festival on September 4. Read the report in Amharic below from the anti-Woyanne action organizers. Woyanne junta members and supporters must be confronted every where around the world in a similar manner by patriotic Ethiopians.
እንደሚታወቀው በ9/4/2011 በሎስ አንጀለስ ከተማ የሊትል ኢትዮጵያን አመታዊ በዓል ለማክበር ዝግጅት ሲደረግ ከርሞ ነበር። በዚህ በዓል ላይ ወያኔ ድንኳን ሊከራይ አይችልም በሚል አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንና የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ሲከራከሩ ነበር የሰነበቱት ሆኖም ግን እስካሁን በሚሰራበት ህግ ማንንም መከልከል አይቻልም ፤ ሁላችሁም ተሳተፉ፤ ተቃውሟችሁንም በሰላማዊ መንገድ እስከሆነ ድረስ የማቅረብ መብታችሁ የተጠበቀ ነው በሚል ስምምነት ተደርጎ እኛም በቂ ዝግጅት አድርገን ትናንትና በቦታው ተገኘን። በነገራችን ላይ፤ የበዓሉን አዘጋጅ ኮሚቴ በስራ በማገዝም ትብብር አድርገናል
የድንኳን ምደባው በእጣ ነበር። እጣው ያለምንም አድሎና ግልጽና ለቁጥጥር አመች በሆነ መንገድ ነበር የተዝጋጀው።
የድንኳኑ አመዳደብ ጎደሎ ቁጥር በአንድ በኩል፤ ሙሉ ቁጥር በሌላ በኩል እንዲሆን ተደርጎ ነበር የታሰበው፤ በዚህ መሰረት እጣው ሲመዘዝ ለኛ የደረስን 6 ቁጥር ሲሆን ለወያኔ የደረሰው 8 ቁጥር ነበር። ስለዚ የእኛና የወያኔ ድንኳን ምሰሶው በአንድላይ የታሰር ነበር። ይህ አጋጣሚ ብዙውን ህዝብ፤ ፍረንጆችን ሁሉ ሳይቀር ያስደነቅ ነበር። እኛን ደግሞ እጅግ ያሰደሰተ አጋጣሚ ነበር። አምባሳደር ተብየው ዘሪሁን ረታ አበደ፤ ስማይ ሊነካ ደረሰ፤ የአዘጋጅ ኮሚቴው እኛን እንዲያስነሳለት ጠየቀ አልሆነም፤ ፖሊስ ጠራ፤ አልሆነም። ያለው አማራጭ የሚደርስበትን የውግዘት ናዳ ተቀብሎ መቀመጥ አለበለዚያ ጥሎ መሄድ ነበር።
እኛ ድንኳናችን ወያኔ ከዚህ በፊት በገደላችው ስዎች ምስልና አሁን በርሐብ ምክንያት አጽማቸው ገጦ በወጣ ህጻናት ሸበብነው። በአሁኑ ሰዓት ያለውን ርሐብ የሚያጋልጥ የቪዲዮ ክሊፕ በፕላዝማ ስክሪን ደቅነን ነበር።
በርካታ ስለርሐቡ ምክንያት የሚግልጹ ጽሁፎች ነበሩን። ልዩ ልዩ ወያኔንና ስርዓቱን የሚያጋልጡ መፈክሮች ተዝጋጅተው በአርበኞች እጅ ተይዘው ነበር። የዚህ ግሩፕ ሎጎ በአዋቂዎች ተሰርቶ በድንኳኑ ውስጥ ተገትሮ ነበር። ምድረ ጨሰች፤ ወያኔ ጥጥ አጥቶ እንጅ ጀሮውን በጥጥ መድፈን ይፈልግ ነበር።
እኛ ቀደም ብለን ደህንነታችን እንዲጠበቅልን ለፖሊስ አመልክተን ስለነበር አንድ ፖሊስ የኛን ድህንነት እንዲጠብቀ ተመድቦ አይዟችሁ እያለ በአካባቢው ያንዣብብ ነበር። እኛም ጨዋነት በሞላው አንድበት ወያኔን ልክ ልኩን መንገራችን ቀጠልን። በወያኔ ድንኳን አካባቢ አንድም ስወ ተውር ማለት አልቻለም። አንዳንድ ፈረንጆች ሂደው አነጋግረው ወደኛ ዘወር ሲሉ ፊታቸው በሐዝን ይዋጣል ምክንያቱም ወያኔ የሚያሳያቸው የትዋበ ህንጻ፤ የአባይ ፏፏቴና የቱሪስት ቦታዎችን ሲሆን እኛ ደግሞ አሁን በተጨባች ኢትዮጵያ ወስጥ ምን እየሆነ እንድሆን ነበር። ተኩረት በሚስብ አቀራረብ አርበኞች እየተባበሩ ባደረጉት ቅስቀሳ የበዓሉን ተሳታፊ አይን ስቧል።
ወያኔ ከዉኃ የገባች አይጥ መስሎ ሲንቆራጠጥ ነበር የዋለው። ቦንድም አልተሸጠ፤ ብሮሸርም አልታደለ። አራት ስዎች ብቻ ነበሩ አምባሳደር ተብዬውን አጅበው የዋሉ። ከአጃቢዎች ውስጥ ሁለቱ ከዚህ በፊት ከነበሩበት ድርጅት ወንጅል ሰርተው የሄዱ ናቸው። መቸም ወያኔ ውንጀለኛና የወንጀለኛ ዋሻ ነው፤ እውነተኛ ቦታቸውን አግኝተዋል።
በመጨረሻም ወያኔ ድንኳኑን ዘግቶ ለመሄድ ወሰነ። እቃውን ጠቅልሎ ሲወጣ ጉዳት እንዳይደርስበት ስለሰጋ በአካባቢው ያሉ ፖሊሶችን ጠርቶ ተጠብቆ ወጣ። እኛም መፈክራችን እያቀለጥን፤ ወያኔና ውሻ ወደ ቤት እያልን ሽኜናቸው።
የማቻል ሆኖ ነው እንጅ “ክቡር አምባሳደሩ” በመትረየስ ቢያስጨርሱን በወደዱ ነበር ነገር ግን ሎስ አንጀለስ 6 ኪሎ ባለመሆኑ ተርፈናል።
የተቃውሞው ተሳታፊዎች በሎስ አንጀለስ ኗሪ የሆኑና በሳንዲያጎ የሚገኙ የኦጋዴን ተወላጆች ኢትይዮጵያዊያዊያንና አሜሪካዊያን ለፍትህና ለዴሞክራሲ በሚል ጥላ ስር ነበር።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር