የሱዳን ጦር መንደር አቃጠለ፣ ኢትዮጵያውያን ታሥረው ወደ ሱዳን ተወሰዱ

ከኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

[pdf]

ሚያዚያ 18 ቀን 2000 ዓ. ም. (April 26, 2008)

ሀ) ሰኞ ሚያዚያ 13 ቀን 2000 ዓ. ም. ከጥዋቱ አራት ሰዓት (April 21. 2008 @ 10:00 A.M.) ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሱዳን ጦር ሠራዊት ቋራ ወረዳ ነፍስ ገበያ የተባለውን ከፍተኛ የርሻ አካባቢ በድንገተኛ በመውረርና የአካባቢውን ሕዝብ በማሸበር፣

1ኛ 24 የርሻ መንደሮችን በእሳት አቃጠለ

2ኛ 34 ኢትዮጵያውያኖችን ይዞ በማሠር ወደ ሱዳን ወሰደ። ከነዚህም ውስጥ አቶ መሐሪ የተባሉት ሰው የአንዱ የተቃጠለ የርሻ ቦታ ባለቤት ሲሆኑ 33 ደግሞ በርሻ ቦታዎች ተቀጥረው የሚሠሩ ዘበኞች፣ አሠሪዎችና የቀን ሠራተኞች ናቸው።

3ኛ ጦሩ አንድ ትራክተር ይዞ ከመሔዱ ሌላ የአካባቢው ሕዝብ የሚገለገልበትን አንድ የእህል ወፍጮ በእሳት Aቃጥሏል።

ለ) ዓርብ ሚያዚያ 17 ቀን 2000 ዓ. ም. ጦሩ ወደ ነፍስ ገበያ በመመለስ በአንድ ባልተቃጠለ የርሻ መንደር ላይ በደንብ የተደራጀና የታጠቀ የፖሊስ ካምፕ መሥርቶ ተመልሷል።

ሐ) የአካባቢው አራሾች በየአቅጣጫው እየተሰደዱ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት በቋራና በጎንደር መካከል ያለው የኢሐዴግ አግአዚ ጦር ደግሞ ለሚሸሹት ገበሬዎች በሱዳን ጦር ላይ ጦርነት ከከፈታችሁ እኛ በስተጀርባችሁ ጠብቀን ነው የምንጨርሳችሁ በማለት ሌላ የሽብር መልእክት በማስተላለፍ ላይ ይገኛል።

በየጊዜው የሚከሰቱትን ሁኔታዎች እየተከታተልን መግለጫዎችን እናወጣለን፣ የአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ይህንን ግፍን አስመልክቶ በምናደርገው እንቅስቃሴ ትብብራችሁን እንጠይቃለ።

የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ለዘለዓለም በልጆቿ ይጠበቃል!
We’ll reclaim our country

ከኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ
e-mail:- [email protected]