Ato Beriso Negussie, Ato Eshetu Teklehaimanot and several other Ethiopians have been murdered in the town of Kore, about 60 km from Shashemene.
In Kore and the surrounding villages, over one hundred homes have been burned and many more have been looted by armed Muslim men. Muslim neighbors of the victims were not attacked.
Thousands of residents of Kore and near by villages are currently taking refuge in Shashemene.
The refugees are living in shelters under terrible condition. No humanitarian group have visited them so far.
The violence was incited by Meles Zenawi’s cadres.
More from German Radion Amharic Service:
ቆሬ፧ በአርሲ የክርስቲያኖች መጨፍጨፍና የአንድ ካህን ተማጽኖ፧
ኢትዮጵያ ውስጥ፧ በአርሲ፧ ኮፈሌ ወረዳ፧ በቆሬ ከተማ ኅዳር 7 እና 8 ቀን፧ 1998 ዓ ም፧ ታጣቂ ሙስሊሞች፧ በክርስቲያኖች ላይ ዘምተው፧ ብዙ ሰዎች መገደላቸውና አያሌ ቤቶች መቃጠላቸው ተመለከተ። በጦርና በጎራዴ፧ በአሠቃቂ ሁኔታ ከተገደሉት መካከል 4 አረጋውያን ክርስቲያኖችና አንድ የ 7ኛ ክፍል ተማሪ ይገኙበታል። አረጋውያኑን፧ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ በጸሎት ላይ እንዳሉ ያረዱአቸው ታጣቂዎች በተጨማሪ፧ የአይሻ ማርያምን ቤተ-ክርስቲያን ቤንዚን አርከፍክፈው ከንዋዬ ቅዱሳትና ንብረት ጋር ማቃጠላቸውን በስልክ የገለጹልን፧ የቤተ-ክርስቲያኒቱ አገልጋይ የነበሩትና እንደርሳቸው አገላለጽ በተዓምር፧ እንደ አናንያ፧ አዛርያና ሚሳዬል ከቤተሰባቸው ጋር ከ«እቶን እሳት« የተረፉት ቄስ አበበ ፈንቴ ናቸው። አረመኔያዊ እርምጃ የወሰዱት ታጣቂዎች፧ ከክርስቲያኑ ወገኑ ጋር ተከባብሮ በሰላም መኖር የሚወደውን ኢትዮጵያዊውን የሙስሊም ማኅበረሰብ የሚወክሉ እንዳልሆኑ ታውቋል።
የተጠቀሰው አሠቃቂ እርምጃ፧ ባስቸኳይ እንዲገታና ሰላም እንዲሠፍን፧ ለተጎዱትም ባፋጣኝ እርዳታ እንዲደርስ ፧ በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ፧ የዓለም ኅብረተሰብም ጭምር እንዲያውቀው አድርጉልን ሲሉም፧ ቄስ አበበ ፈንቴ ተማጽነዋል።