ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
“የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) የተባለውን ድርጅት የመሰረቱትን አገሮች ሁኔታ ቀረብ በማለት በምመለከትበት ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ሁኔታ ከእነዚህ አገሮች ከበርካታዎቹ የባሰ መጥፎ ነው የሚለውን ለመቀበል እቸገራለሁ፡፡” ይህ አባባል የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ሊቀመንበር የሆኑት ማዳም ክሌሬ ሾርት በአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት ቦርድ እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መረጃ ወይም አገልግሎት ለመስጠት ዕጩ የኮሚቴ አባላት ለሆኑት ለአሊ ኢድሪሳ፣ ፌይዝ ዋዲሺ እና ጂን ክላውዴ ካቴንዴ ለተባሉት በጻፉት “ግልጽ ድብዳቤ” የተንጸባረቀው አመክንዮአዊ መደምደሚያ የሰጡበት ብያኔ ነበር፡፡ የድርጅቱ ሊቀመንበር በሆኑት ሴትዮ ኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት ድርጅት አባል እንድትሆን ያላቸውን ጽኑ አቋም በማከል የተጻፈው አጭር ግራ አጋቢና አስፈሪ “ግልጽ ደብዳቤ” ኢትዮጵያ አባል እንድትሆን የሚወተዉት ነው:: አንደሴትየዋም አፃጻፍ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት ጋር “አባል ሆኖ ለመስራት ለሲቪል ማህበረሰብ አባላት በቂ ቦታ መኖር አለመኖሩን እና የሲቪል ማህበረሰብ ተሳትፎ ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ከማንም ጣልቃገብነት ነጻ መሆናቸው መረጋገጥ ይኖርበታል” የሚል ነበር፡፡
የማዳም ሾርት “ግልጽ ደብዳቤ” ያልታሰበበት እና ድፍረት የተቀላቀለበት፣ እብሪተኛ ባህሪ የተንጸባረቀበት፣ ክብር የጎደለው አቀራረብ እና ፍጹም ትምከት የተሞላበት መልዕክትን የሚያስተላልፍ ነበር፡፡ ማዳም ሾርት ኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽ አባል እንድትሆን “የሲቪል ማህበረሰብ ባለድርሻ አካላትን” በኃይል በማስፈራራት ለማሳመን እያቀረቡት ባለው “ስሜታዊነት የተቀላቀለበት” የልመና ተማጽዕኖ በጣም ረዥም ርቀቶችን ተጉዘዋል፡፡ ማዳም ሾርት ኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት አባል መሆን እንዳትችል በዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች መሰረተቢስ ተቃውሞና ሴራ አንዳለ በአዙሪት ጠቁመዋል የሳሳ ድብቅ ክስ አቅርበዋል፡፡ ማዳም ሾርት ልዩ ፍላጎት ባላቸው ቡድኖች “እርባና የለሽ ጠንካራ የተቃውሞ ድምጾች ተጽዕኖ ሳቢያ በደንብ ታስቦበት እና ሆን ተብሎ ሆኖም ግን ‘የደቡቡ ያለም ህዝብ ምን መስራት እንዳለበት የሰሜኑ ያለም ህዝብ እምነቱን የሚጭንበት አካሄድ ነው” በማለት ክሳቸውን አቅርበዋል፡፡ እነዚህ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ፍጹም አይን ባወጣ መልኩ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ሰርሰረው ገብተው ድምጾቻቸውን ከፍ አድርገው በማሰማት የኢትዮጵያን የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት አንዳያገኙ ይጥራሉ በማለት ወንጅለዋል፡፡ ማዳም ሾርት ለሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችም እንዲህ የሚል መረጃ ሰጥተዋል፣ “የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ መስፈርት አስጠባቂ ድርጅት አይደለም፣ የእኛ ስራ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት ጋር እና በእነርሱ አካባቢ ሊያሰራ የሚችል በቂ የሆነ ቦታ መኖር አለመኖሩን እና በአምራች ዘርፉ ለህዝቡ ጠቀሜታ ዙሪያ ባለው መልክ ሽግግር እንዲኖር እገዛ እየተደረገ መሆን አለመሆኑን ማረጋገጥ ብቻ ነው“ ብለዋል፡፡
ማዳምዋ ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ በኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄ ላይ ድርጅታቸው ያለውን የመወሰን ወይም ያለመወሰን ጉዳይን አስመልክቶ ያለውን የወደፊቱን መጥፎ ሁኔታ በመተንበይ እንዲህ የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፣ “የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት በአምራች ዘርፉ መሻሻልን ለሚፈልጉ ለሁሉም አገሮች የሚያገለግል አንድ ዓይነት መስፈርት ያለው ዓለም ዓቀፋዊ ጥምረት ነው፣ ወይም ደግሞ በዘመቻ በሚመሩ ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች የሚመራ ተቋም ነው፡፡“ በአንድ አስገራሚ በሆነ አጋጣሚ ማዳም ሾርት ክብርን በሚያዋርድ መልክ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች “የዘመቻ አድራጊዎች መሳሪያ” እንዳይሆኑ እና “ከጠንካራ የልዩ ፍላጎት ቡድኖች አስፈጻሚ ድምጾች” የሰላ ስለት ተወካዮች እንዲታቀቡ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ እንዲያውም ማዳምዋ ከዚህ ጠንከር ባለ መልኩ ሲያሽሟጥጡ “አመጸኞች ከቅዱስ ፓውሎስ ካቴድራል ውጭ አካባቢውን በመያዝ በእራሴ ሀገር በኃይል በሚባረሩበት“ ጊዜ እንኳ በሚያሳፍር መልኩ በፍርኃት ቆፈን በመዋጥ በዝምታ መታለፉ፣ “የጓንታናሞ መኖር እና ማሰቃየትን መፈጸሙ እየታወቀ… በዩናይትድ ስቴትስ አቤቱታ እየቀረበ ጆሮ ዳባ ልበስ መባሉ“ በግልጽ እየታዬ “ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ከማያሰሙት“ የሞራል ዝቅጠት ያለባቸው ተወካዮች በማለት በስም እየጠቀሱ እና አሳፋሪ በማለት ወርፈዋቸዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ በመቀጠል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች እና “የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለድርሻ አካላት” “ወደ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት አባልነት መግባት እንዲሁም በአካባቢያዊ የተያዙ ተግባራት ቀጣይነት ባለው መልክ እንዲሻሻሉ ማበረታታት ማስቻል“ ዓይነት “አቀራረብ” መያዝ እንዳለባቸው ሰፊ ዲስኩር አድርገዋል፡፡ የሞራል እኩልነት አመክንዮን በማንሳት “በኢትዮጵያ ያሉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሁኔታ በሌሎች አገሮች ከሚገኙ በርካታ ተመሳሳይ ድርጅቶች በተለየ መልክ መጥፎነት አይስተዋልባቸውም” በማለት ማዳምዋ እራሳቸውን አወድሰዋል፡፡ ማዳም ሾርት ያላቸውን አመለካከት ለማስረገጥ በሚል በኢትዮጵያ እና በሌሎች ሀገሮች መካከል ያለውን ደካማ የሰብአዊ መብት አያያዝ በማነጻጸር የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት ረዥም የሰብአዊ መብት ረገጣ እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማጥፋት ረገድ ያለው የአያያዝ ምዝገባ በእጅጉ በኢትዮጵያ ካለው የሚበልጥ ቢሆንም እንኳ በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል የሚያደርገው የሰብአዊ መብት ረገጣ የተሻለ የሞራል ተቀባይነት እንዳለው ለማሳመን ታትረዋል፡፡ ማዳምዋ ለእራሳቸው ስብዕና የሞራል ልዕልና በመስጠት ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች እንዲህ በማለት ማረጋገጫ ሰጥተዋል፣ “ለኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለሌሎች አዲስ አባላት ማለትም ቦርዱ ለሲቪል ማህበረሰቡ በቂ ቦታ መኖር አመኖሩን እና በትክክልም ለስራዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰሩ ለመሆናቸው ክትትል እንደሚያደርግ ግልጽ አድርገዋል፡፡ እንዲህ በማለትም ጠንካራ የሆነ ትችት ሰንዝረዋል፣ “የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነትን ጥረቶች ለማደናቀፍ ልዩ አጀንዳ ይዘው ለሌላ ጉዳይ መጠቀሚያነት ከሚንቀሳቀሱ ኃይሎች የቱንም ያህል ጠቃሚ ቢሆኑም እንኳ ነቅተን መጠበቅ ይኖርብናል“ ብለዋል፡፡
የማዳም ሾርት እራስን አዋቂ አስመስሎ ማቅረብ እና ኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት አባል እንዳትሆን በሀሰት ውንጀላ ተቃውሞ እያካሄዱ ናቸው በሚል ምክንያት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን ትንሽ ዘወር ባለ መልኩ ማውገዛቸው ለማመን በሚያስቸግር መልኩ ንቀት የተሞላበት እና አስደንጋጭ ሁኔታ ነበር፡፡ ማዳምዋ የንቀት ዲስኩራቸውን በመቀጠል የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት ከሚሰሩት ስራዎች በስተቀር ሌሎች በጨቋኝ መንግስታት አገሮች ውስጥ የሚሰሩ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ የሀሰት መረጃ የታጨቀበት ነው በማለት በጅምላ አስታውሰዋል፡፡ እንዲህ ሲሉ ሀሳባቸውን ያጠናክራሉ፣ “የእኛ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለድርሻ አካላት አሁን ባለው አስቸጋሪ ሁኔታ እየሰሩ እና ሁልጊዜ ጨቋኝ የከባቢ ሁኔታዎችን ለማሻሻል እያደረጉ ያሉትን ጥረት በጣም አድርጌ አደንቃለሁ“ ሆኖም ግን ይላሉ፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት ስራቸውን “ቦታ በመስጠት እና የእኛ ድርጅቶች ባይኖሩ ኖሮ ለእነዚህ ለመሻሻል ዘመቻ ለሚክፍቱብን ድርጅቶች ክፍት ሊሆን የማይችል ማዕቀፍ እንደነበር“ ማወቅ እና ምስጋና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ማዳም ሾርት ኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት አባል እንዳትሆን ሲቃወሙ በቆዩት የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ለመሰንዘር ረዥሙን ካራቸውን/ቢላዋቸውን አዘጋጅተዋል፡፡ ማዳም ሾርት የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት “መስማት ያለበት… ግልጽ እና ከዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ድምጽ ይልቅ በኢትዮጵያ ያሉ የተባበሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ድምጽ“ መሆን እንዳለበት የሚጠይቅ ክብር የጎደለው ደንታቢስነት የተንጸባረቀበት በሀሰት እና እብሪት የተሞላ አስተያየት መዝግበዋል፡፡
የማዳም ሾርት “በስሜታዊነት የተሞላ“ “ግልጽ ደብዳቤ” የግላቸው የማይናወጥ እምነታቸው መገለጫ ወይም ደግሞ የአስተሳሰብ ዘይቢያቸው ነው ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ነው!
የማዳም ሾርት “ግልጽ ደብዳቤ” የEITIን የመመስረቻ ደንብ አንቀጽ 12ን ይጻረራል፤
ማዳም ሾርት “ግልጽ ደብዳቤ” በማተም እና በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል በወገነ መልኩ “በስሜታዊነት የተሞላ“ የጥላቻ ስብከት ላይ ተዘፍቀው በመገኘታቸው የEITIን የመመስረቻ ደንብ በግልጽ ደፍጥጠውታል፡፡ የEITI ሊቀመንበር ዋና ዋና የስራ ተግባራት በEITI “የመመስረቻ ደንብ” በዝርዝር የተቀመጡ ሲሆን የሚከተሉትን ያካትታል፣ “ለEITI የቦርድ አባላት ዘገባዎችን ያቀርባል፣ ጉባኤዎችን እና የአባላት ስብሰባዎችን ያቀርባል፣ የውጨ ጉዳይን በሚመከት የEITIን የቦርድ አባላት በመወከል ይሰራል፣ የEITI የቦርድ አባላት ውሳኔዎች በጽ/ቤቱ ተግባራዊ መሆናቸውን በሚመለከት ክትትል ያደርጋል፣ እንዲሁም በEITI ባለድርሻ አካላት መካከል የትብብር ግንኙነቶች እንዲጠናከሩ ጥረት ያደርጋል“፡፡ ሆኖም ግን ለፓርቲ ቅስቀሳ ማድረግ፣ በአገር ደረጃ አባል ለመሆን እንዲቻል መገናኛ ብዙሃንን መሰረት ባደረገ መልኩ የማግባባት ስራ መስራት፣ ደብዳቤ መጻፍ እና በድረገጽ መስመር ተጠቅሞ አቤቱታ ማቅረብ እንዲሁም ለEITI ዕጩ አባል ለመሆን ለሚያመለክቱ ድርጅቶች የህዝብ ግንኙነት የዘመቻ ስራዎችን ማከናወን በማዳምዋ ግልጽ የስራ ተግባራት እና ኃላፊነት ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ብቻ ሳይሆን የEITIን የዓላማ ጽናት በጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚያስገባ ያልታሰበ አደጋን የሚያስከትል ክስተት አንደሚሆን የተረጋገጠ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ላለው የገዥው አካል ወገንተኛ በመሆን ጠንካራ የህዝብ ግንኙነት ዘመቻዎችን በመጀመር ማዳም ሾርት ህገወጥ በሆነ መልክ ከተሰጣቸው ስልጣን በላይ በመሄድ እና ከጥምረቶች እና ከህዝብ ጋር በአደባባይ በመመካከር ሆን ብለው የአባላትን የከፈለህን አትም ሂደት በመከተል በEITI ለተወከሉ አካሎች ኃላፊነት የተሰጠውን በህግ በመከልከል ከአግባብ ውጭ በመሄድ ላይ ናቸው፡፡ ማዳምዋ “ግልጽ ደብዳቤ” በማተም የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችን እና የከፈለህን አትም መርህ በመከተል በዓለም አቀፋዊ የጥላቻ እና የብስጭት እሰጥ አገባ በመክተት የድርጀቱን ስብዕና በማዋረድ እና የሙያ፣ የፍትሀዊነት እና የብቃት ማነስ በነጻነት የመዳኘት ሰብዕናቸውን ከጥያቄ ምልክት ውስጥ አስገብቶታል፡፡ “ስሜታዊነት በተሞላበት” መንገድ በኢትዮጵያ በስልጣን ላያ ያለውን ገዥ አካል ለማገዝ በሚል ጭፍን ፍላጎት ማዳም ሾርት EITIን ወደ ፖለቲካዊ የውዝግብ ማዕቀፍ ውስጥ በማስገባት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ክብር በማኮሰስ የተቀባይነት ደረጃውን አሳንሰውታል፡፡ የማዳም ሾርት ግልጽ ደብዳቤ ስልጣንን እና ኃላፊነትን ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ በመጠቀም የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችን እና ከእርሳቸው ጋር የሀሳብ ስምምነት የሌላቸውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በኃይል በማስፈራራት እጅ በመጠምዘዝ ዓላማን ለማሳካት ከሚያደርጉት ከንቱ መፍጨርጨር የዘለለ አይሆንም፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችን አሳንሶ የማየት አባዜ፣
የማዳም ሾርት ስሜታዊነት የተሞላበት ብስጭት መገለጫ ስለሆኑት የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች ወይም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መናገር አልፈልግልም፡፡ ሆኖም ግን እንደ የሰብአዊ መብት ተሟጋችነቴ ማዳም ሾርት እነዚህን ተቋማት እንደ ወጣት ወሮበላዎች ቆጥረው በአደባባይ ለማዋረድ የመንቀሳቀሳቸውን እውነታ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የተሰማኝን ጥልቅ ቅሬታ ለመግለጽ በማሰብ ነው፡፡ የእርሳቸው ሌሎችን አሳንሶ የማየት ድምጸት እና በሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች ላይ የሚያሳዩት ፍጹም የሆነ ንቀት ትዕግስትን ይፈታተናል፣ አስደንጋጭ እና አሳፋሪም ነው፡፡ ማዳምዋ በሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች ላይ እያሳዩ ያለው ንቀት ተወካዮቹ አሻንጉሊቶች ለእራሳቸው የማያስቡ እንዲሁም ስራዎቻቸውን በትክክል ለመስራት ሌሎች የሚያውቁ የተማሩ የሰለጠኑ ሞግዚቶች እንደሚያስፈልጋቸው በመፈረጅ እየቀለዱ ያሉ ሴት ናቸው፡፡ እውነት ለመናገር እነዚህን ድርጅቶች ተራ ግንዛቤ ያላቸው፣ ማንም እንደፈለገው በቀላሉ የሚያሽከረክራቸው፣ በተሳሳተ መንገድ የሚመራቸው፣ በሞራለቢስ ጭራቆች የሚታለሉ እና በስም የለሽ ድርጅቶች እና ድብቅ ዓላማቸውም EITIን በሾኬ ጠልፈው እነዚህን ድርጅቶች [“የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ?] ተሟጋቾች መሳሪያ” ለማድረግ ነውን?፡፡ የማዳም ሾርት ንቀት የተሞላበት እና የሙያዊ ብቃትን ያልተላበሰ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ያንቋሸሸ “ግልጽ ድብዳቤ” የሚረሳ ሊሆን አይችልም፡፡
ኢትዮጵያ የEITI አባል እንዳትሆን ተቃውሞ የሚያሰሙ ዘረኞች ናቸውን?
የማዳም ሾርት ግልጽ ደብዳቤ ኢትዮጵያ የEITI አባል እንዳትሆን የሚቃወሙ ድርጅቶች በእርግጠኝነት “የሰሜኖቹ ለደቡቦቹ ምን መስራት እንዳለባቸው ለአእምሯቸው የሚነግሩ ናቸው” በማለት በኮሽታ መልክ ለመወንጀል ተፍጨርጭሯል፡፡ ሁሉም “የሰሜኖቹ ህዝቦች ለደቡቦቹ ህዝቦች ምን መስራት እንዳለባቸው ለአእምሯቸው የመናገር” ሀሳብ “እነዚያ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ሆኖም ግን ኢትዮጵያ የEITI አባል እንዳትሆን የሚቃወሙ አጉራዘለል ተሳዳቢ ዘረኞች ናቸው!“ የሚለውን የዋህ እና ለስለስ ያለ አባባልን ያስታውሳል፡፡
የ”ሰሜን ደቡብ” (የዓለም ህዝብን የመክፈል የንግግር ዘይቤ) በይፋ ወጥተው ምን ለማለት እንደፈለጉ በቅጡ መናገር የማይችሉ የሞራል ብቃት የሌላቸው ሰዎች ያለፈበት ፋሽን ነው፡፡ ይህ የንግግር ዘይቤ ከሰብአዊ መብት ጋር ተያይዞ በሚቀርብበት ጊዜ ደግሞ በቀላሉ የሚያስተላልፈው መልዕክት መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶችን መርሆዎች በአፍሪካ እና በሌሎች ከአፍሪካ ውጭ ባሉ አገሮች እንዲተገበሩ የሚፈልጉት የምዕራባውያን ሰባዊ መብት ድረጅቶች የአውሮፓዊ እሴቶችን እና መርሆዎችን በሌሎች ላይ በእብሪት ለመጫን የሚደረግ ጥረት አስተሳሰብ የተሞላበት አሽሙራው አነጋገር ነው፡፡ የ”ሰሜን ደቡብ” የንግግር ዘይቤን ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በመግለጽ ማዳም ሾርት ኢትዮጵያ የEITI አባል እንዳትሆን የሚቃወሙ “ነጮች ለጥቁር ኢትዮጵያውያን እና ለሌሎች የአፍሪካ ህዝቦች የእራሳቸውን ጉዳይ እንዴት መምራት እንደሚችሉ“ ለማሳየት ከሚደረግ የክርክር ጭብጥ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
እኔ እንዲህ ባለ አባታዊ (የበለጠ ግልጽ ለማድረግ “እናታዊ”) እና ግልጽነት በጎደለው መልኩ ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን ስም እያነሱ ጥላሸት ለመቀባት እየተደረገ ባለው ደርጊት አፍራለሁ፡፡ ማዳም ሾርት በቅርቡ ያረፉት አቶ መለስ ዜናዊ በሰብአዊ መብት ጥበቃ አያያዛቸው ጉድለት ምክንያት ወቀሳ ሲደርስባቸው ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ እነዚህ “የኒዎሊበራል” አቀንቃኞች ውንጀላ ነው በማለት አላስፈላጊ ትንተና በመስጠት መሰረተ ቢስ የሆነ ትችት ይሰጡ እንደነበረው ሁሉ እኒህ ማዳምም የእርሳቸውን የንቀት የገደል ማሚቶ በማስተጋባት ላይ ይገኛሉ፡፡ አቶ መለስ እንዲህ በማለት ትንተና ይሰጡ ነበር፣ “ዴሞክራሲ፣ መልካም አስተዳደር፣ ግልጽነት እና ሙስናን መዋጋት ለማንኛውም አገር በተለይም በመልማት ላይ ላሉ አገሮች ጥሩ ዓላማዎች እንደሆኑ እናምናለን፡፡ ኒዎሊበራል እየተባለ ከሚጠራው የርዕዮት ዓለም ፍልስፍና ጋር ልዩነቶች ያሉን ቢሆንም ይህንን ፍልስፍና ገና ከመጀመሪያው በእኛ ላይ ለመጫን ይፈልጋሉ፡፡ ይኸ ተግባራዊ ይሆናል ብለን አናምንም፡፡ ተጠያቂነትን በውል መገንዘብ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ነው፡፡ መንግስት ተጠያቂ የሚሆነው ለዜጎቹ እንጅ ለጥቂት ኤምባሲዎች ወይም የውጭ ተዋንያን አይደለም፡፡“ በማለት ደጋግመው ይናገሩ ነበር፡፡
የማዳም ሾርት “ግልጽ ደብዳቤም” አቶ መለስ ሲያራምዱት በነበረው አስተሳሰብ በተመሳሰለ መልኩ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት እንዲከበር የሚፈልጉትን በኒዎሊበራል የባህል የእጅ አዙር ቅኝ ገዥዎች ብለው በመፈረጅ ማረጋገጫ ይሰጣል፡፡ የማዳምዋ መሰረታዊ በኃይል የመንጠቅ አባዜ እንደሚንጸባረቀው በEITI በኩል ጥቂት (ብዙ) ላላ ያሉ ነገሮችን በመውሰድ የአስተዳደራዊ ተግዳሮት ጉዳዮችን በሙሉ ለዚያው አገር “ውስጣዊ” ተቋማት መተው የሚል ነው፡፡ የማዳምዋ ዕቅድ በኢትዮጵያ ያለው ገዥውን አካል “ለEITI አባልነት የሚመጥን በእራሱ የሚያሟላውን መስፈርት” አምጣ ብሎ በመቀበል የገዥው አካል ተጠያቂነት የቱንም ያህል በጠበበ መልክ ለመያዝ በማሰብ ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ ማዳምዋ ገዥው አካል የEITI የአባልነት መስፈርቶች ያሟላ በማስመሰል “ትርጉም ያለው ስራ” እንደሰሩ እንዲቆጠርላቸው በመፈለግ ከንቱ ውዳሴን ለማትረፍ ይፈልጋሉ፡፡ በእራሱ ክብር እምነት የጣለ እና ፍጹም በሆነ የተጠያቂነት ማዕቀፍ ውስጥ እራሱን ያስቀመጠ ድርጅት እንዲህ “የላላ ተጠያቂነት“ እንዲያመጣ እና እንዲተገብር ማሰብ በጣም አስቂኝ ጉዳይ ነው፡፡
በሁሉም ህዝብ ዘንድ በአንድ ዓይነት የሰብአዊ መብት ጥበቃ መስፈርት በተግባር ላይ እንዲውል የሚታገሉትን እና ለተፈጻሚነቱ በጽናት የሚቆሙትን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን እና ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ወገኖችን በዘረኝነት የሚፈርጇቸውን ሀሳቦች ሁሉ በጽናት በመቆም እንዲወገዱ እታገላለሁ፡፡ ጥቁር፣ ቡናማ ወይም ቢጫ የሰብአዊ መብቶች ይኖራሉ የሚል እምነት የለኝም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ለአፍሪካውያን ልዩ ባህሪ ያለው በነጻ የመደራጀት ወይም የመናገር መብት የሚባል ነገር የለም፣ እንዲኖርም አይፈለግም፡፡ የፕሬስ ነጻነት በአሜሪካ ባንዲራ ተጠቅልሎ አይመጣም፡፡ ወይም ደግሞ መደቡ ቀይ በሆነ ሰማያዊ ቀለም መስቀል በተለጠፈበት ባንዲራ አይመጣም፡፡ የዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብት ድንጋጌ፣ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች እና ሌሎች የመብት ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የፈረመ ማንኛውም አገር ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መስፈርት መከበር ተገዥ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ዋና ተልዕኮ መሆን ያለበት ጉዳይ ያ ነው፡፡ እነዚህ ድርጅቶች በየትኛውም የዓለም ክፍል ያለ እያንዳንዱ ሰው ሰብአዊ መብት አለው/አላት፣ ምክንያቱም እርሱ/ሷ ሰብአዊ ፍጡር ነው/ናት፡፡ ይህም የሚሆነው በእያንዳንዳቸው ዘር፣ ቀለም፣ ጾታ፣ ኃይማኖት፣ ቋንቋ፣ አገር ወይም ሌላ የመመደቢያ መስፈርት በመኖሩ ምክንያትም አይደለም፣ የሰብአዊ መብት ከእነዚህ ሁሉ መመዘኛዎች የጸዳ እና የማይነካካ ለብቻው በእውኑ ዓለም ቆሞ የሚከበር የሰዎች ጸጋ እና መንፈስ ነው፡፡
የኢትዮጵያን ለEITI አባልነት ጥያቄ “በሰሜን ደቡብ የአስተሳብ ቅኝት” ከፋፋይ እይታ ለመገምገም ከቀረበ ሀሳብ የበለጠ ዘረኛ እና ለኢትዮያውያን ጥልቅ ንቀት እና ክብር ከሚሰጥ አስተሳሰብ በላይ አለን? እኔ እንደ ግለሰብ በግሌ ሁለት ዓይነት የሰብአዊ መበት መስፈርቶች መኖር አለባቸው፣ እናም ኢትዮጵያ “በደቡቡ” መስፈርት መለካት አለባት የሚለው ማንኛውም አስተሳሰብ ያመኛል፡፡ የሰብአዊ መብት ጥበቃን በሚመለከት “በሰሜን ደቡብ የአስተሳብ ቅኝት” ቅርኝት ያላቸው ሰዎች አስተሳሰብ ሲመዘን “በሰሜን” ያሉ ሰዎች ለሰብአዊ መብቶች መከበር እውነተኛ ስምምነት መኖሩን ሲያመላክት “በደቡብ” የሚኖሩት ደግሞ በተቃራኒው ለሰብአዊ መብት ጥበቃ እውነተኛ ያልሆነ ያነሰ ስምምነት አላቸው በሚል ይወቀሳሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ ከዚህ መነሻ ሀሳብ ዙሪያ ሲቃኝ የማዳም ሾርት “ግልጽ ድብዳቤ” ጥልቀት ባለው መልክ የሚሞግተው እና ተማጽዕኖ የሚያቀርበው በአፍሪካ የሰብአዊ መብት መከበር ተጨባጭ ሁኔታ ሲነሳ “በሰሜን” ያሉት የጉዳዩ አቀንቃኞች የይስሙላ እና በተግባር የማይውል የሰብአዊ መብት ጥበቃ የበዓል ዝግጅት ሽር ጉድ ከማድረግ ያለፈ ውኃ የሚቋጥር ስራ እንደማያከናውኑ በተጨባጭ ያመላክታል፡፡
የEITI ሊቀመንበር ወይስ በኢትዮጵያ ላለው ገዥው አካል ወገንተኛ ወትዋች?
ማዳም ሾርት በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል የEITI ድርጅት አባል እንዲሆን ለEITI የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያገኝ ስሜታዊነት በተንጸባረቀበት መልኩ ሲጠይቁ እና ሲለምኑ እንደቆዩ ተናግረዋል፡፡ የማዳምዋን “ግልጽ ደብዳቤ” ገና መጀመሪያ እንዳነበብኩት የነበረኝ ምላሽ ለገዥው አካል ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ሲያገለግል በቆየው በዋሽንግተኑ ወትዋች/lobbyist በዲኤልኤ ፓይፐር/DLA Piper ድርጅት የተጻፈ ነበር የመሰለኝ፡፡ የተጻፈው ግልጹ ደብዳቤ ለእራሳቸው ፍላጎቶች እና ዓላማዎች ሲሉ ብዙውን ጊዜ በወትዋች ድርጅቶች ከሚታተሙ እና ከሚጻፉ ድብዳቤዎች እና ጋዜያጣዊ መግጫዎች በምንም ዓይነት መልኩ የሚይለዩ ሆነው አይታዩም፡፡ የማዳም ሾርት ደብዳቤ ነገሮችን አጋኖ የማቅረብ፣ ማብራሪያዎችን የመስጠት፣ ምክር የመሰንዘር እና ለእራስ ጠቀሜታ ሲባል የሚደረግ የልመና ተማጽእኖ የታጨቁበት ድብልቅ ስሜትን ያካተተ ደብዳቤ ነው፡፡ ደብዳቤው አወዛጋቢ የሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በሚከሰቱበት ጊዜ የስራ ኃላፊዎች ውሳኔ መስጠት እንዲችሉ እንዲያግዟቸው እንደሚጻፉት ደብዳቤዎች ዓይነት ሁሉንም ዓይነት የተለመዱ መካተት ያለባቸው ሙያዊ ጽሁፎች ወትዋች ደብዳቤዎች ዘይቤን ነቅሶ የያዘ ነው፡፡
እንደ ወትዋች ደብዳቤ የማዳም ሾርት “ግልጽ ደብዳቤ” ቀስ በማለት የእራሱን ዜጎች ከሰብአዊነት በወረደ መልክ ሁልጊዜ በማዋረድ ላይ ያለውን የገዥ አካል ሰብአዊነትን የተላበሰ በማስመሰል በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል “በሌሎች ፈጻሚ አገሮች” ከሚገኙት ገዥ አካሎች “የከፋ አይደለም” የሚለውን የሁልጊዜ መዝሙር ሀሳብ ኢላማ በማድረግ ለማጠናከር ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ “ብዙዎቹ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለድርሻ አካላት የሰሯቸውን ስራዎች የሚያሳንስ እና የሚያኮስስ” ሆኖ እንዲያውም እነዚህ ድርጅቶች ቀደም ሲል ሊያገኟቸው የማይችሉ የነበሩትን አሁን በአጋጣሚው ተጠቅመው ለሰብአዊ መብቶች መሻሻል የሚያደርጓቸው ዘመቻዎች በቂ ቦታ እና ምህዳር እንዲያገኙ በመደረጉ ሊያመሰግኑ እንደሚገባ ይጠይቃል፡፡ ስለሰብአዊ መብት የሚሟገቱ ድርጅቶችን እና አትዮጵያ የEITI አባል እንዳትሆን የሚቃወሙትን የእራሳቸው በዘረኝነት መሞላት ብቻ ሳይሆን የዘረኝት ሁሉ ጎተራ የሆኑ “በሰሜን ደቡብ የአስተሳብ ቅኝት” ተመርተው ምን መስራት እንዳለባቸው መመሪያ የሚሰጡ ናቸው በማለት ጥላሸት ይቀባሉ፡፡ ደብዳቤው በአገራቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ የሚታገሉትን ይተቻል፣ ያገላል፣ እናም ወገናዊነትን ያሳያል በተለይም ሰብአዊ መብቶች እየተጣሱ እያዩ የሚተውትን፣ ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ረጋጭ አገር በመሆኗ የEITI አባል እንዳትሆን የሚቃወሙትን ሁሉ ይተቻል፣ EITI የኢትዮጵያ ዲያስፖራን የሚቃወመውን ሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ድምጽ ከመስማት ይልቅ በኢትዮጵያ ያሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ግልጽ እና የተባበረ ድምጽ መስማት እንዳለባቸው ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ደብዳቤው ማዕከልነት ያለው ቦታ እንዲያዝ አጥብቆ ይጠይቃል፡፡ “ለዚህም ነው አስቀድሜ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበር ድርጅቶች ከEITI ጋር ለመስራት በቂ ቦታ ያለ የሌለ መሆኑ መረጋገጥ ያለበት እና ለአባልነት የሚያበቁ መስፈርቶች ግልጽ እና ቀላል መሆን እንዳለባቸው አስቀድሜ ስሜታዊነት በተቀላቀለበት መልኩ እምነቴን የገለጽኩት፡፡” ደብዳቤው “EITI ለአብዛኛው ክፍት የሆነ ሆኖም ግን የአባልነት መስፈርቱን በእራሱ ለማሟላት ግን ትርጉም ያለው ውጤት መኖር እንዳለበት ሀሳብ በማቅረብ የኢትዮጵያን የአባልነት ጥያቄ በሀሳብ ሜዳ ላይ እንዲዋልል ያደርጋል…”
እኔ ብዙ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን፣ ደብዳቤዎችን እና በዋሽንግተን ዲ.ሲ በገዥው አካል ከፍተኛ የሆነ ክፍያ በሚከፈላቸው ወትዋቾች የታተሙ ሰነዶችን ለበርካታ ዓመታት አንብቢያለሁ፡፡ ለዲኤልኤ ፒአይፒር/DLA Piper ያሉት ነገሮች እንዳሉ ሆኖ ማዳም ሾርት የፃፉት የግልፅ ደብዳቤ የውትወታ ስራ ለዲኤልኤ ፒአይፒርን ያንክዋስሰዋል ያስከነዳዋል ለማለት እችላለሁ!
የኢትዮጵያን አባልነት ለመቀበል ወይም ውድቅ ለማድረግ ከሚሰጠው ውሳኔ አንጻር የEITI መንፈስ በትክክለኛው ሚዛን ላይ ነውን? የኢትዮጵያ ለEITI የአባልነት ጥያቄ ውድቅ ቢደረግ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ሊጠፉ ይችላሉን?
“ግልጽ ደብዳቤ” በሚለው የማዳም ሾርት ደብዳቤ መሰረት የEITI እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህልውና የተንጠለጠለው ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል እንድትሆን የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘት ወይም ደግሞ ውድቅ ከመደረጉ ላይ ነው፡፡ ማዳምዋ የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ስለኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄ ጉዳይ ያለው አቋም “EITI ደረጃውን የጠበቀ ዓለም አቀፍ ጥምረት ሆኖ የማምርት ማሻሻያ ለሚፈልጉ ሁሉንም አገሮች ለማገልገል የቆመ ድርጅት ወይም ደግሞ በዘመቻ አራጋቢዎች የሚባረር ድርጅት ነው” በማለት የትወና ክርክራቸውን አቅርበዋል፡፡ እንዲህ በማለትም የትንበያ ነብይነታቸውን ለማሳየት ሞክረዋል፣ “ኢትዮጵያን ከድርጅቱ የአባልነት ጥያቄ ውድቅ ማድረግ ማለት የኢትዮጵያን የሲቪል ማህበረሰብ የትም እንዳይሄድ ማድረግ ማለት ነው“ ይደልዎ! የመጨረሻው የምጽዓት ቀን ቀርቧልን!?
የኢትዮጵያ ለድርጅቱ የአባልነት ጥያቄ ለሁለተኛ ጊዜ ውድቅ ቢደረግ EITI በአደገኛ ሁኔታ የማይቀር ውድቀትን ሊከናነብ ይችላልን? የኢትዮጵያ የድርጅቱ የአባልነት ጥያቄ ውድቅ ቢደረግ EITI የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች “የዘመቻ መሳሪያ” ሰለባ ሊሆን ይችላልን?
EITI እ.ኤ.አ. በ2002 ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ አባል ባልነበረችበት ጊዜም ቢሆን ምንም ነገር ሳይደርስበት ህልውናውን ጠብቆ ኖሯል፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 ደረጃውን ካሻሻለ በኋላ ጠንካራ ድርጅት ሆኖ ወጥቷል፡፡ ከፍተኛ የሞራል ብቃት ክብር እና ዉጤታማነትን (ይህ ከወ/ሮ ክላሬ “ግልጽ ድብዳቤ” በኋላ ቀጣይነት የሚኖረው ለመሆኑ እርግጠኛ ባልሆንም) ለማስከበር ችሏል፡፡
በእርግጥ ለመነጋገር የማዳም ሾርት ግልጽ ደብዳቤ የሄኒ ፔኒኒን ተረት (መሬት የምት ጭር ዶሮ ተረት) ያስታዉሰኛል:: አንድ ግኡዝ የሆነ ነገር የሄኒ ፔኒኒን ከላይ ከጭንቅላቷ ላይ ይመታታል፡፡ “ሰማይ ወደቀ! ሰማይ ወደቀ” አያለች በየመንገዱ ሮጠች:: ሰማይ አልወደቀም፣ አይወድቅምም እንዲሁም የኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄ በEITI ውሳኔ ለሁለተኛ ጊዜ ውድቅ ቢደረግ ሰማይ አይወድቅም፡፡
የማዳም ሾርት የEITI የአባልነት መመዘንያ፣
የማዳም ሾርት “በግልጽ ደብዳቢያቸው” ለEITI የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት ለማግኘት ሶስት ጣት ያላቸው መስፈርቶች እንዳሉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ እነርሱም፣ 1ኛ) ስሜታዊነት በተቀላቀለበት መልኩ እጩ አባላትን ለመቀበል በአመልካቹ አገር ከEITI ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል በቂ የሆነ ምህዳር መኖሩ በግልጽ እና በቀላል ሁኔታ መታየት አለበት፣ 2ኛ) የሲቪል ማህበረሰብ ተሳትፎ ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ከማንም ተጽዕኖ የጸዳ መሆኑን ማመሳከሪያ እና ማረጋገጫ መኖሩ፣ 3ኛ) ማመሳከሪያነትን ለመወሰን “ለመሻሻል ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል” የሚሉ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ከEITI ጋር አብሮ ለመስራት በቂ ምህዳር አለን?
“በቂ ምህዳር” ማለት በእርግጠኝነት ምን ማለት ነው? የ ማዳም ሾርት ዘወር ያለ ሀሳብ የEITI ሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች “ልዩ ፍላጎት ባላቸው ቡድኖች ጠንካራ ድምጾች” እና ከሰብአዊ መብት ተሟጋች “ዘማቾች” ቁጥጥር ስር በመሆን የምሁራዊ ልዕልናቸውን በቅጣት መልክ በማንሳት “በቂ ምህዳር” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ውስብስብ በሆነ መልኩ የሚወስኑበት ሁኔታ ነው፡፡ የማዳም ሾርት የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች “በቂ ምህዳር” የማርቲን ሉተር ኪንግን ቅሬታ እነዚያ የነጮች ሊበራል ቀሳውስት ለለውጥ “እንዲቆይ” የተማጽዕኖ ልመና ያደረጉበትን አጋጣሚ አስታወሰኝ:: ይህንኑ ጉዳይ በማስመልከት ማርቲን ሉተር እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “ለበርካታ ዓመታት እስከ አሁንም ድረስ ‘ቆይ!’ የሚለውን ቃል ስሰማ ነበር፡፡ ይህ በእያንዳንዱ ጥቁር ሰው ጆሮ በሚሰቀጥጥ መልኩ በማንቃጨል ላይ ይገኛል፣ ይህ ሁልጊዜ ‘ቆይ’ የሚለው ‘ፍጹም’ የሚል ትርጉም ይዟል፡፡“
የማዳም ሾርት ለኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች “በቂ ምህዳር” ውስጣዊ አስተሳሰብ ሲመዘን በቂ ምህዳር እስኪገኝ ድረስ “ቆይ” ማለት ነውን? ገዥው አካል በቂ ምህዳር ለማዘጋጀት እስኪወስን ድረስ ቆይ ማለት ነው የእርሳቸው ትንተና፡፡ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምን ያህል ምህዳርስ ነው በቂ የሚሆነው ወይም ደግሞ ከበቂ በላይ የሚሆነው? መቸስ ነው በኢትዮጵያ ላሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች “በቂ ምህዳር” እየተባለ የሚደሰኮረው በቂ ያልሆነ የሚሆነው? “በቂ ምህዳር” ማለት “ፍጹም ማለት” ነውን? በቂ መቸ ነው በቂ የሚሆነው?
በማዳም ሾርት ደብዳቤ የቀረበው “በቂ ምህዳር” ጠቅላላ ሀሳብ ተጨምቆ ሲታይ አንዳንድ ሰዎች እንደሚያምኑበት ምንም ዓይነት እውነት የለም፣ ያለው የስህተቶች ቀጣይነት ደረጃ ብቻ ነው የሚለውን የተለመደውን የስብዕና አንጻራዊነት ጨለምተኝነትን የሚያንጸባርቅ ሆኖ ይገኛል፡፡ በተግባራዊ መልኩ ይህ ማለት “ልክ በቂ ምህዳር” በአንጻራዊነት መልኩ ሲታይ ምንም ዓይነት ምህዳር በሌለበት ወቅት ሲታሰብ ጥሩ ነው እንደማለት ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ መሰረት ያደረገው ለውስጣዊ ፍላጎቶች እርካታ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በአቋራጭ መንገድ የሚፈልጉትን ነገር ማግኘትን እንደመርህ መተግበር በስብዕና መርሆዎች ላይ ድልን የሚቀዳጅ ይሆናል፡፡ የዚህ ዓይነቱ አንጻራዊ የስብዕና እብሪተኛ መንገድ የህሊናችንን ውጥረት ለማርገብ የማሰብ ዓይነት እና ትክክለኛውን ነገር በትክክለኛው ጊዜ እንዳናደርግ ሽባ የሚያደርገን አስተሳሰብ ነው፡፡ የዚህ ዓይነቱ አንጻራዊ ስብዕና ጭራቃዊነት ድርጊትን ፊት ለፊት እንዳንጋፈጥ የሚከለክለን እና የጭራቃዊነት መሰሪዎችን እንዲሁም ከእራሳችን ህሊና ጋር የስብዕና ልዕልና ላይ ዝቅጠትን በመያዝ የጭራቃዊነት ሰለባዎችን ስናወግዝ ያ ሁኔታ የስብዕና ዝቅጠት መሰረት ነው፡፡ የዚህ ዓይነቱ አንጻራዊ ስብዕና የእውነት መርሆዎችን በመጨፍለቅ በአቋራጭ መንገድ ያለምንም መዘግየት ከውሸት መድረክ ላይ ያለምንም ሀፍረት ፊጥ በማለት አስመሳይ የመርህ ተከታይ እንድንሆን ያደርጋል፡፡
ማዳም ሾርት “ስለበቂ ምህዳር” ያወራሉ፣ እኔ ግን ስለ ነጻ ምህዳር እናገራለሁ… ነጻ ምህዳር ለማሰብ፣ ለማምለክ፣ ለመጻፍ እና ለመደራጀት፡፡ “ምህዳር” በሚለው ላይ በጣም ስሜታዊ ሆኘ ከሆነ ታላቅ ይቅርታ እጠይቃለሁ:: ማዳም ሾርት ለኢትዮጵያውያን/ት “በቂ ምህዳር” በሚለው እርካታን አግኝተው ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ ግን በፍጹም፡፡ ከሁሉም በላይ ማዳም ሾርት መገንዘብ ያለባቸው ነገር በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን/ት “ምህዳርን” ከምንም ነገር በላይ የሚፈልጉት መሆናቸውን ነው፡፡ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ኢትዮጵያውያን/ት እንደ ከብት መንጋ “ክልል” (ክልሊስታንስ) እየተባለ በሚጠራው የአፓርታይድ ባንቱስታንስ ዘመናዊ መገለጫ በሆነው ስርዓት እጅ ከወርች ተጠርንፈው ይገኛሉ፡፡ በሀገራቸው ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላው ቦታ እንዲንቀሳቀሱ ይገደዳሉ፣ ምክንያቱም ትክክለኛ ያልሆነው የጎሳ ዘር ናችሁ ተብሎ ይነገራቸዋል፡፡ አያት ቅድመ አያቶቻቸው ለሺህ ዓመታት ሲኖሩበት ከነበረው ቦታ በግዳጅ እንዲለቅቁ ይደረጋሉ ምክንያቱም ያ ቦታ የሳውዲ አረቢያ እና የህንድ ህዝቦችን ለመመገብ አዝዕርት እንዲያመርቱበት ይፈለጋል፡፡ ኢትዮጵያውያን/ት ለእራሱ ብቻ ክብር በመስጠት የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑትን የኤሌክትሮኒክ መረጃ ምንጮችን በሚከልክል ገዥ አካል መዳፍ ስር ወድቀው ይገኛሉ፡፡ በቂ ቦታ/ምህዳር? የለም ነጻ ቦታ/ምህዳር!
በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰቡ ተሳትፎ ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ከማንም ጣልቃገብነት የጸዳ ነውን?
ማዳም ሾርት በኢትዮጵያ ስላለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሁኔታ በአጠቃላይ ክህደት የሚያሳዩ ወይም ደግሞ ሆን ብለው ጆሮ ዳባ ልበስ ያሉ ይመስላሉ፡፡ EITI “የኢትዮጵያን ሲቪል ማህበረሰብ ግልጽ እና የተባበረ ድምጽ ማዳመጥ እንዳለበት” አጥብቀው ይማጸናሉ፡፡ ስለየትኛው የተባበረ የሲቪል ማህበረሰብ ድምጽ ነው ማዳም ሾርት የሚናገሩት?
ከሁለት ሳምንታት በፊት የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2013 ስለነበረው አጠቃላይ ሀገራዊ የሰብአዊ መብት አያያዝ ሁኔታ የሚከተለውን ዘገባ አቅርቧል፣ “ከሰብአዊ መብት ጋር በተያያዘ መልኩ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአሳሪው ህግ ምክንያት ስራዎቻቸው ተስተጓጉለዋል፡፡ እ.ኤ.አ ጁላይ 2012 የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የበጎ አድራጎት እና ማህበራት አዋጅ ህግ ሆኖ ከወጣ በኋላ የሲቪል ማህበረሰቡ ምህዳር ‘በፈጣን ሁኔታ ጠቧል’ በማለት ያደረባቸውን ስጋት ገልጸዋል፡፡“ ያ ዘገባ የሚከተለውን ማጠቃለያ በመስጠት ደምድሟል፣ “ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት የወጣው አዋጅ ወደ ተግባር በመሸጋገሩ ምክንያት መንግስት የሰቪል ማህበረሰቡን እና መንገስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን (መያድ) የስራ እንቅስቃሴዎችን መገደቡን ቀጥሎበታል፡፡“ ማዳም ሾርት የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት መምሪያ እና የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ስላቀረቡት ዘገባ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ነውን እየተናገሩ ያሉት? ማዳም ሾርት ገዥው አካል ከዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች እና ከሌሎች እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ገንዘብ ለማግበስበስ እንዲመቸው ለደጋፊዎቹ ዕቅድ በመንደፍ ስለማስመሰያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ነው እየጠቀሱ ያሉት?
“የነጻ፣ ፍትሀዊ እና ከማንም ጣልቃ ገብነት የጸዳ ባህሪ” ያላቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን “የተባበረ የሲቪል ማህበረሰብ ድምጽ” ለማዳመጥ በተማጽዕኖ ልመና የሚለካ አይደለም፣ ሆኖም ግን በውል ተጢኖ በተዘረጋ የአሰራር ስርዓት እንጅ፡፡ የፖለቲካ ስርዓት አስተዳደሩ የሲቪክ ምህዳሩን ለማስፋት እና ሀብቶችን ለመጠቀም የሚያስችል ህጋዊ ማዕቀፍ ይፈቅዳልን? በአሁኑ ጊዜ ያለው የፖለቲከ ስርዓት አስተዳደር ያለውን የፖለቲካ እና የፍትህ ስርዓት በማሻሻል የህብረተሰቡን ደህንነት በመጠበቅ ፍትሀዊነትን ማረጋገጥ ይችላልን? የፖለቲካ ስርዓት አስተዳደሩ ጠንካራ፣ ቀልጣፋ፣ በኃይል የተሞሉ እና ብዝሀነትን የተላበሱ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት፣ ቡድኖች እና ጥምረቶች እንዲንቀሳቀሱ የመፍቀድ ወኔ አለውን? የማህበረሰብ ባለድርሻ አካላት የኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ለፖሊሲ ውሳኔ ውጤቶች ተጠያቂ ተዋንያን እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን ሊፈጥር ይችላልን? በአሁኑ ጊዜ ተገልለው ለሚገኙት የህብረተሰብ ክፍሎች ልዩ ትኩረት በመስጠት እያንዳንዱ ግለሰብ ተጠቃሚ የሚሆንበትን አግባብ ተግባራዊ ሊያደርግ ይችላልን?
ከዚህ በላይ የቀረቡት አንዳቸውም ጥያቄዎች በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል ስለበጎ አድራጎት እና ማህበራት ህግ አዎንታዊ መልስ ሊሰጥ አይችልም፡፡ ከሙሉ ክብር ጋር የማዳም ሾርት ባለሙሉ ስልጣን በኢትዮጵያ ነጻ፣ ፍትሀዊ እና ከማንም ጣልቃገብነት የጸዳ “የተባበረ የሲቪል ማህበረሰብ ድምጽ” መስፈርትን ያካተተ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት መኖራቸውን ለመወሰን የሚያደርጉት የተማጽዕኖ ልመና የማዳምዋን ምሁራዊ ክህሎት አጠያያቂነት ጥያቄ በማንሳት ብቻ የሚዘለል ሳይሆን በጣም ተራ የሆነ ኃላፊነትን የሚጠይቅ እውነታን መርምሮ ሀሳባቸውን ለህዝብ በማቅረብ ረገድ ያላቸውን ችሎታ ከታላቅ ጥርጣሬ ላይ የሚጥል ነው፡፡
ከገዥው አካል አያያዝ አንጻር በኢትዮጵያ ያሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች “ቀጣይነት ያለው መሻሻል” እንዲያሳዩ ምን መካተት አለበት?
ማዳም ሾርት ለEITI አባልነት በአሁኑ ጊዜ ካሉት የመምረጫ መስፈርቶች መካከል ድርጅቱ “ቀጣይነት ያለው መሻሻል” መስፈርት ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለበት በመሞገት ላይ ናቸው፡፡ እውነታው ግን ገዥው አካል ቀጣይነት ያለው መሻሻል ለማሳየት በመጀመሪያ ያስገባው የአባልነት ጥያቄ ውድቅ ከተደረገ ሶስት ዓመታት አልፈዋል፡፡ ቀጣይነት ያለው መሻሻል አላሳየም ይልቁንም ቀጣይነት ያለው የኋሊዮሽ ጉዞውን ቀጥሎበታል፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 መጀመሪያ አካባቢ ብዛታቸው 4,600 የነበረው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ብዙዎቹ እንዲከስሙ ተደርገው በመንገዳገድ ላይ የሚገኙ 1,400 ብቻ ሆነው ተገኙ፡፡ ከመክስም የተረፉት ወደ 30 በመቶ ብቻ መሆናቸው ሲታይ ሁኔታው አስደንጋጭ መሆኑን ያመላክታል፡፡ መረጃዎቼ እንደሚያስረዱት በህይወት ከተረፉት ድርጅቶች መካከልም የአብዛኞቹ ድርጅቶች የሰው ኃይል 90 በመቶ ወይም በበለጠ ቅናሽ አሳዬ፡፡“ በተመሳሳይ ዓመት ገዥው አካል ቀደም ሲል የተቋቋሙትን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤን እና የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበርን የእነዚህን ሁለት ጠንካራ ተቋማት አቅማቸውን ለማሽመድመድ በማሰብ ዓላማቸው እና የሚፈጽሟቸው ተግባራት ከህግ አግባብ ውጭ ነው በማለት ወንጅሎ የባንክ ሂሳቦቻቸውን በመዝጋት ንብረቶቻቸውን አገደ፡፡
እ.ኤ.አ በ2012 ገዥው አካል አስር መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን/NGOs ከአዋጁ በተጻራሪ መንገድ ሲንቀሳቀሱ አገኘኋቸው በሚል ሰበብ መዝጋቱን እና የሌሎች 17 የሚሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጉዳይ በመጣራት ላይ ያለ መሆኑን ተናገረ፡፡ ገዥው አካል እርምጃውን በመቀጠል 400 የሚሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከአዋጁ በተጻራሪ እየተንቀሳቀሱ ነው የሚል ሰበብ ከሰጠ በኋላ በቀጣይ አስፈላጊ እርምጃ እንደሚወስድባቸው በማስረገጥ ዝቷል፡፡ እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2012 ሄንሪክ ቦል ፋውንዴሽን/Heinrich Boll Foundation የተባለ በዴሞክራሲ እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የሚሰራ የጀርመን አገር መንግሰታዊ ያልሆነ እርዳታ ሰጭ ድርጅት ንብረቱን ሸክፎ በሚሰራቸው ስራዎች ላይ የተጣሉትን እገዳዎች በመቃወም ከሀገር ለቅቆ ወጣ፡፡
እ.ኤ.አ በፌብሯሪ 2013 ገዥው አካል በሶስት መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ ማለትም አንድ ኢውሮ/ One Euro፣ የእስላም ባህላዊ እና የምርምር ማዕከል/the Islmaic Cultural and Research Center፣ እና የጎሄ ህጻናት፣ ወጣቶች እና ሴቶች የልማት ድርጅት/the Gohe Child, Youth and Women Development Organization የተባሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን “ህገወጥ የኃይማኖት እንቅስቃሴ” ማድረግ የሚል ክስ በማቅረብ ስራቸውን በማቆም ከሀገር እንዲለቅቁ አድርጓል፡፡ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ2013 “በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት/US Agency for International Development የገንዘብ ድጋፍ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት 29 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ 27ቱ ከአዋጁ ህግ በተጻራሪ መልኩ የሚንቀሳቀሱ ናቸው ብሎ ፈርጇቸዋል፡፡“
እንደ ፖሊሲ ትንተና ተማሪ በጊዜ ሂደት የሚከሰቱ “ቀጣይነት ያላቸው መሻሻሎች”/continuous improvements፣ “እመርታዊ”/Incremental improvements መሻሻሎች ልዩ ጠቀሜታ ያላቸው እና ባልተጠበቀ ጊዜ የሚከሰቱ እና “ዘለቄታዊ መሻሻሎች”/breakthrough improvements በአንድ ጊዜ የሚከሰቱ ለሚሉት መሻሻሎች በቂ ግንዛቤ አለኝ፡፡ ማዳም ሾርት የገዥውን አካል ቀጣይነት ያለው መሻሻል አንድ መገለጫ እንኳ መጥቀስ ይችላሉን? ወይም ደግሞ ባለፉት ሶስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት አንጻር ቀጣይነት ያላቸውን መሻሻሎች የሚያመላክቱ ምን ምን ተግባራት እንደተከናወኑ መግለጽ ይችላሉን? ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በተያያዘ መልኩ ስለእመርታዊ እና ዘለቄታዊ መሻሻሎች በገዥው አካል የተከናወነ ቅንጣት ድርጊት ካለ ማዳም ሾርት ሊጠቁምን ይችላሉን?
እውነታው ሲታይ ግን ገዥው አካል እስከ አሁንም ድረስ በአገሪቱ ያሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን እየወነጀላቸው እና እንዳይንቀሳቀሱ አፍኖ ይዟቸው ነው ያለው፡፡ ከገዥው አካል አስቸጋሪው የበጎ አድራጎት እና ማህበራት አዋጅ “ቀጣይነት ያለው መሻሻል” መጠበቅ ከአፓርታይድ ህጎች “ቀጣይነት ያለው መሻሻልን” እንደ መጠበቅ ይቆጠራል፡፡ ጥቂት ህጎች እና ፖሊሲዎች በጣም መጥፎ የጥራት ደረጃ ያለባቸው ሲሆኑ ብቸኛው “ቀጣይነት ያለው መሻሻል” በእነዚህ ህጎች እና ፖሊሲዎች ላይ ለማድረግ ከተፈለገ እርባናየለሽ መሆናቸውን በመገንዘብ ቀጣይነት ባለው መንገድ ማስወገድ ነው! የማዳም ሾርት “ቀጣይነት ያለው መሻሻል” ክርክር ስለ አባልነት አቀባበል መስፈርት እንደነበረ መታየት ይኖርበታል… ሆን ተብሎ የተፈበረከ ዘገባ፣ የሀሰት እና የማሳሳቻ ክርክር ከጊዜ ብዛት መጥፎ ህግ ጥሩ ሊሆን ይችላል፡፡ መጥፎ ህጎች እንደ ጥሩ ወይን ጠጅ አይደሉም፣ ጊዜ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የበለጠ መጥፎ እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡
ፍትሀዊ ያልሆነ ጥቃት በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ላይ መውሰድ?
ማዳም ሾርት የእጃቸውን ቡጢ ለኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ በማሳየት EITI “የተቃውሞ ድምጾችን ከኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ” እንዳይቀበል የሚጠይቅ ተማጽዕኖ አቅርበዋል፡፡ ማዳምዋ የሚያደርጓቸው ንግግሮች ሁሉ ከገዥው አካል ታማኝ ሎሌዎች እና ጽኑ ደጋፊዎች አመለካከት ጋር ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ እኔ እና ሌሎች ብዙዎች የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን/ት ኤችአር/HR 2003 (ኢትዮጵያ፡ የዴሞክራሲ እና የተጠያቂነት ህግ 2007) የተባለው የሰብአዊ መብት ሰነድ በዩናይትድ አሜሪካ ኮንግረስ እንዲያልፍ አስከታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ድረስ በመውረድ ቅስቀሳ እያደረግን ባለንበት ጊዜ፣ ገዥው አካል፣ የእርሱ ደጋፊዎች እና ወትዋቾች ልሳናችንን ለመዝጋት አንደበታችንን ለማሰር ለብዙ ጊዙ ጠንክረው ይሰሩ ነበር፡፡ ያኔ “ጽንፈኛ ዲያስፖራ” ብለው ጠሩን፣ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ለስለስ ባለ አሰያየም “የተቃዋሚ ድምጾች” ተብለን በመጠራት ላይ እንገኛለን፡፡ የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን/ት ድምጾች ዝም ሊሉ ይችላሉ፣ እንዲሁም ጸጥ እንዲሉ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን የማንሰማ ደንቆሮዎች አይደለንም፡፡ የማዳም ሾርትን መልዕክቶች ደርሰዉናል፡፡ ስለስም አወጣጣችን ብዙም የሚያሳስበን ጉዳይ አይደለም፣ ምክንያቱም ተቃዋሚ ድምጾች ወይም “ጽንፈኞች” መሆናችን ለነጻነት እና ለሰብአዊ መብቶች መከበር የምናደርጋቸው ትግሎች ሞገሳችን እንጅ ውርደት ሊሆን ከቶውንም አይችልም፡፡
በማዳም ሾርት የንቀት እና የእብሪት ንግግር የተሰደቡ እና ክብራቸው የተዋረደ መስሎ የሚሰማቸው ኢትዮጵያውያን/ት የዲያስፖራ አባላት ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ በማዳምዋ ቀስቃሽ፣ ቆጥቋጭ ንግግሮች ተበሳጭተው ላለመናገር ዝም ያሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ይህንን ልንረዳው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ማዳም ሾርት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ድምጾች ምንም ነገር አያመጡም በማለት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አውጀዋል፡፡ በእርግጥም በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል በአገሪቱ ያሉትን የተቃውሞ ድምጾች ዝም ማሰኘቱ በቂ አይደለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ማዳም ሾርት “የተቃውሞ ድምጾችን ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ” ላይ ለማስወገድ ግልጽ የሆነ የመጨቆኛ የማግባባት ስራ እየሰሩ ስለሆነ ጸጥ የሚለውን የህዝብ ብዛት ከፍ ያደርገዋል፡፡
ማዳም ሾርት በአንድ ጠብታ ብዕራቸው የሚሊዮኖችን ኢትዮጵያውያን/ት የዲያስፖራ ድምጾች ጸጥ ለማድረግ እና ደብዛቸውን ለማጥፋት የሚያስችል በእብሪት የተሞላ የስብዕና ስልጣን ከየት አመጡት? ምናልባትም እንደዚህ ዓይነቱ እብሪት ለከፍተኞቹ እና ለጠንካራዎቹ ታላቅ የቢሮ ሞገስን የሚሰጥ ይሆናል፡፡ የማዳም ሾርት የማንአህሎኝነት ዓይነት ታዓይታን የሚያንጸባርቅ እብሪተኝነት ቁጣን ሊያጠናክር እና የቃላት ቀስቶቹ ዒላማ ከሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች ያልሰለጠነ እርምጃ እንዲወስዱ ሊጋብዝ ይችል ይሆናል የሚል ፍርሃት አለኝ፡፡ በመጨረሻም በEITI ላይ ጥላቻ እንዲቀፈቀፍ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ያም ሆነ ይህ ማዳም ሾርት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብን ይቅርታ የመጠየቅ ዕዳ አለባቸው፡፡
በማዳም ሾርት በመረጃ ድህነት የታጀበ አሳዛኝ መግለጫ እና የይሆናል “ግልጽ ደብዳቤ” ምንም ዓይነት ግላዊ ጥላቻን አልይዝም፡፡ “የደንቆሮዎችን ደምጾች” ለመስማት እገደዳለሁ (በእርግጥም እንድደነቁር):: ለበርካታ ዓመታት ለእብሪተኛ ደንቆሮዎች ከኒው ሀምሻየር የጣራ ባልጩት ድንጋይ ላይ ውኃ ከማስሰስ ጋር ተመሳሳይነት ውጤት ካላቸው ጋር እውነትን ለመናገር ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ፡፡ ከሁለት ሳምንታት በፊት “በኢትዮጵያ የማዕድን ሙስናን ለመሸፋፈን የሚደረግ ሸፍጥ” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችቴ በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል ከEITI ጋር የስልታዊ ባህሪን በመላበስ እና ድርጅቱን በተሳሳተ መንገድ ለመምራት በመሞከር በማዕድኑ ዘርፍ ሙስናን ህጋዊ ለማድረግ ይችላል በሚል ተጨባጭነት ባላቸው አሃዛዊ መረጃዎች የተደገፈ ክርክር አቅርቤ ነበር፡፡ ለትንታኒየ መረጃዎች እና የክርክሬ ጭብጥ የተገኘው ከዓለም ባንክ ዳጎስ ያለ ዘገባ ነው፡፡
ማዳም ሾርት እንዲያውቁት የምፈልገው የእኔ ዲያስፖራ ድምጽ አልተሰማም የሚል የተለየ የሚያሳስበኝ ነገር የለም፡፡ በተደጋጋሚ ስናገረው እንደነበረው ሁሉ ስለሰብአዊ መብት እና ስለየህግ የበላይነት፣ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላለው ገዥው አካል እና ለአፋሽ አጎብዳጅ የባዶ ፕሮፓጋንዳ ሰባኪዎቹ እንዲሁም ለታማኝ ሎሌዎቹ ማስተማር ምንም ዓይነት መስማት እና መናገር ለማይችሉ ዱዳ አሕዛቦች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እየጠቀሱ ለመስበክ እንደመሞከር ወይም ደግሞ በተጠረበ የባልጩት ድንጋይ ላይ ውኃ እንደ ማፍሰስ ይቆጠራል፡፡ ላልሰማ እችላለሁ ሆኖም ግን በማዳም ሾርት የብዕር ጠብታ ልሳኔ ሊዘጋ አይችልም፡፡ የኦማር ክሃያምን ግጥሞች በመዋስ፣ ”ተንቀሳቃሹ ጣቴ መጻፉን ይቀጥላል፣ እናም መጻፍ፣ ይንቀሳቀሳል፣ ወይም እምነቱን ይገልጻል ወይም ይጽፋል፣ግማሽ መስመር እንደገና አልሰርዝም፡፡“
ለማዳም ሾርት ለጋስ እሆናለሁ እናም የእርሳቸውን የንቀት እርባናየለሽ ትችት ዊሊያም ቡክለይ እንዳሉት ሁሉ፣ “የተባበሩት የሲቪል ማህበረሰብ በኢትዮጵያን መስማት እና የተቃውሞ ድምጾችን ከዲያስፖራ ኢትዮጵያ ማስቀረት የሚሉትን የጻፉትን በእርግጠኝነት ያምኑበታል ብዬ የማዳም ሾርትን የብሩህ አዕምሮ ባለቤትነትን ከግምት ውስጥ በማስገባት ዘለፋ አልፈጽምም፡፡“ ሆኖም ግን ከማርቲን ምልከታ በመውሰድ ለመንፈሴ እረፍትን እሻለሁ፣ “ደህና ምግባር ካላቸው ሰዎች የተወሰደው ጥልቀት የሌለው ግንዛቤ ጤናማ ካልሆኑ ሰዎች የተወሰደው ፍጹም ግንዛቤ ያልተደረገበት የበለጠ ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡“
አንድ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ድምጽ የብዙ ዲያስፖራ ድምጾችን እንደሚወክል ሁሉ ማዳም ሾርት እራሳቸውን በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት የፖሊሲ ክርክር ላይ እንዲያስገቡ ደስተኛ እሆናለሁ፡፡ የማዳምዋን ሀሳብ እና “በግልጽ ደብዳቤ” መብታቸውን መግለጻቸውን እንደማከብር ግልጽ ማድረግ እፈልጋለሁ በብዙ ነገር ላይ የምስማማ ቢሆንም፡፡ ማዳም ሾርት ሀሳባቸውን እንዲገልጹ እና አለመስማማታችንን በመስማማት ለመቋጨት ሁሉም ኢትዮጵያዊ/ያት መብታቸውን እንዲያከብርላቸው እማጸናለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ለEITI የአባልነት ጥያቄ ከማቅረቡ ጋር በተያያዘ መልኩ ከማዳም ሾርት ጋር ያለኝ ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ ማዳም ሾርት እና እኔ የምንጋራው የሆነ ነገር አለ፡፡ ኃይለኛ ስሜታዊነት፡፡ ማዳምዋ በኢትዮጵያ ያለውን ገዥ አካል በማወደስ በኩል “ስሜታዊ” ናቸው፡፡ እኔም እንደዚሁ በተመሳሳይ መልኩ በገዥው አካል የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማዳከምና በማጥፋት እረገድ፣ ነጻ ጋዜጠኞችን ወደ እስር ቤት ዘብጥያ በመወርወሩ እረገድ እና ሁሉንም የፖለቲካ ምህዳር በመዝጋቱ ሁኔታ ላይ ስሜታዊ ነኝ፡፡ ማንኛችን በትክክለኛው መንገድ ላይ እንደሆንን ታሪክ የሚበይን ይሆናል፡፡
ማዳም ሾርት EITI “የኢትዮጵያን ዲያስፖራ የተቃውሞ ድምጾች” ከቁም ነገር እንዳያስገባቸው ምክር ቢለግሱም ቅሉ ከአምባገነናዊነት ጋር ሰላም ማውረድ እና ለአምባገነኖች ለመጥፎ ባህሪያቸው ሽልማት በመስጠት የበለጠ ድፍረት እንዲሰማቸው እና የበለጠ በሰለባዎቻቸው ላይ ስቃይ እና መከራ እንዲያበዙ የሚያግዟቸው ስለሆኑ ማዳምዋን የታሪክን ድምጽ እንዳይረሱት እመክራቸዋለሁ፡፡ ሰላም ማውረድ ለአምባገነኖች ሰብአዊነትን አያላብሳቸውም፣ እንዲያውም ልባቸው እንዲደነድን ያደርጋቸዋል፣ እናም አመክንዮአቸውን እንዲህ በማለት ያጠናክረዋል፣ “አንድ ባገኙ ቁጥር የበለጠ ያብጣሉ፡፡“
ከሁሉ ህዝቦች በላይ ማዳም ሾርት ማስታወስ ያለባቸው ነገር፣ “በአሁኑ ጊዜ ሰላምን ማቀንቀን“ ወደ አስቸጋሪ ጦርነት መርቷል፡፡ ሰላም ማውረድ እንደ “በቂ ምህዳር“ (አንዳንድ ጊዜም ምህዳር ለእድገት እየተባለ እንደሚጠራ እገምታለሁ) ከተገለጸ የሰብአዊ መብቶችን በአቋራጭ መንገድ ለፖለቲካ ፍጆታ በአደገኛ ሁኔታ መጠቀም እና መከራ እና ስቃይ የሚያስከትሉት ሙሉ ውጤት የሚያግዝ ከሆነ በኢትዮጵያ በክልል ተጠርንፈው ያሉትን ክልሊስታንስ ማዳም ሾርት ማስታወስ ይኖርባቸዋል፡፡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተጠያቂነትን እና ግልጽነትን በውሸት ለመተግበር ሲነሱ በሰው ዘር ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን አለማየት ይጀምራሉ፣ ሰላም አቀንቃኝ ብቻ አይሆኑም ነገር ግን ከእውነታው በፊት እና በኋላ የመለዋወጫ መሳሪያ ሆነው ይቀርባሉ::
ወይ ጉድ ረሰቸው ላልፍ አኮ ነበር!
የገዥው አካል ለEITI አባል ለመሆን ያቀረበው ማመልከቻ ምንድን ነው? በዚህ ላይ ትችት በመስጠት ጊዜዬን አላባክንም፡፡ በደንብ ካጠናሁት በሁዋላ ፍሬ ከርስኪ እርባናየለሽ ማመልከቻ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ የአባልነት ጥያቄው 25 ገጾችን ያካተተ አሳፋሪ የህትመት ግድፈቶች የታጨቁበት እና የቃላት አመራረጥ ስህተቶች የተንጸባረቁበት ማመልከቻሰነድ ነው፡፡
በአባልነት ጥያቄው ላይ ያሉት ብዙዎቹ ነገሮች በእርባነየለሽ ዓለም ላይ ትርጉም ይሰጣሉ፡፡ የማመልከቻ ጥያቄውን ይዘት በመረመርኩበት ጊዜ በጸጥታ ሳቅሁ፡፡ የአሊስን እንቆቅልሽ በአልስ የአስደናቂ ነገሮች መሬት ላይ አስታወሰኝ፡፡ “የእራሴ የግል ዓለም ያለኝ ከሆነ” አለች አሊስ፣ “ሁሉም ነገር ትርጉም አልባ ይሆናል፡፡ ማንኛውም ነገር እንደነበረ አይሆንም ምክንያቱም ሁሉም ነገር ያልነበረውን ነው የሚሆነው፡፡ በተቃራኒው ሲታይ አሁን የሆነው ወደፊት ላይሆን ይችላል እናም አሁን ያልሆነው ወደፊት ሊሆን ይችላል፡፡ አያችሁ?“ ዝብርቅርቅ ያለ ማመልከቻ ነው::
ለእራሱ ክብር የሚሰጥ የአስተዳደር ባለስልጣን ወይም ደግሞ ገዥ አካል ለEITI የአባልነት ጥያቄው ተቀባይነት እንዲያገኝ ሊያቀርበው በቂ ማመልከቻ አይደለም፣ በእርግጥ ለቀልድ የቀረበ ካልሆነ በስተቀር፡፡ ምናልባትም በገዥው አካል የአባልነት ጥያቄ ላይ በEITI ጭካኔ የተሞላበት ቀልድ መሆኑን የሚያሳየው “የኢትዮጵያ ብሄራዊ የጋዜጠኞች ማህበር”ን ባካተተ መልኩ የኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት የሚያገኝ እና የሚጸድቅ ከሆነ የEITI ፕሮቶኮል በትክክል እየተተገበረ መሆኑን የሚቆጣጠር አምስት አባላት ያሉት ከአገር ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ተመልካች ቡድን ይቋቋማል፡፡ አዎ! የኢትዮጵያ ብሄራዊ የጋዜጠኞች ማህበር? ድንበርየለሽ የጋዜጠኞች ተሟጋች ድርጅት “ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ጋዜጠኞችን በማሰር ሁለተኛዋ አገር“ በማለት ገልጿታል፡፡ ይህ ለEITI የቦርድ አባለት የአዕምሮ ብቃት ምን ዓይነት ዘለፋ ነው! ማዳም ሾርት የEITI የቦርዱ አባላት የኢትዮጵያን ብሄራዊ የጋዜጠኞች ማህበርን ነው በኢትጵያ ዉስጥ “ግልጽ ድምጽ መስማት አለባቸው የሚሉት ማህበረ ሰብ?
የአባልነት ማመልከቻው በእራሱ ግልጽ ያልሆኑ እና አደናጋሪ ቃላት የታጨቁበት ነው፡፡ ጥቂት ምሳሌዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፣ “በእርግጥ ቦርዱ ተጠቅሷል አዋጅ ቁጥር 621/2009 EITIን በኢትዮጵያ ለመተግበር የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራትን እንቅስቃሴ ይጎዳል፡፡ ቢሆንም በግልጽ ለቦርዱ ገልጸነው እንደነበረው ቦርዱ በደንብ በተለየ መልኩ ካላስቀመጠው በስተቀር አዋጁ ምንም ነገር አይደለም ወይም ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተሳትፎ ለEITI አባልነት ማመልከት ህጎች በኢትዮጵያ፡፡“ ምን ለማለት ተፈልጎ ነው?! የአባልነት ማመልከቻ ጥያቄው እንዲህ ይላል፣ “የኢትዮጵያ ማመልከቻ የEITI የተፈረመ በሚመለከት ለይቷል ወይም በቦርዱ የተያዘ ቢሆንም መንግስት በድርጅቱ ጥበቃ ስር ሆኖ የድርጀቱን በቀጣይነት የድርጅቱን ክብር ለመጠበቅ በከፍተኛ ደረጃ ይሰራል፡፡“ ጉድፈላ! በቀጣይነትም እንደዚህ በማለት ያብራራል፣ “በመሆኑም በEITI የጥበቃ ተነሳሽነት ብዙ ወርክሾፖች እና ስልጠናዎች ይደረጋሉ ለባለድርሻ አካላት ስለግልጽነት እና ስለተፈጥሮ ሀብት ጉዳዮች ያለምንም ገደብ መናገር እንዲችሉ እና መብታቸውን ለመጠቀም ግንዛቢያቸውን ለማስቻል ለመግባባት እና እርስ በእርስ ለመተባበር ስለተፈጥሮ ሀብት ጉዳዮች በድፍረት በከፍተኛ የEITI ስብሰባ ላይ በሌሎች ለመነጋገር“፡፡ “በእራሳቸው ዓለም ለሚኖሩ ብቻ” ትርጉም የሚሰጥ የፍሬ ከርስኪ ስነጽሁፍ ተምሳሌት ነው አንጂ ሌላ ሰው ሊገነዘበው አይችልም
በሰልልጣን ላይ ላሉ እውነትን ለሚናገሩ እና ስልጣናቸውን አላግባብ በሚጠቀሙ ላይ በመናገር በእራሴ ኩራት ይሰማኛል፡፡ የገዥው አካል የEITI አባልነት ማመልከቻ ጥያቄ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ሊገባኝ ባይችልም ሁሉንም በአንድ ቃል ማስቀመጥ ይቻላል፣ ሆኖም ግን ከእብሪት የጀመረ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡
ማዳም ሾርት ከኃላፊነት ቦታዎ በእራስዎ ፈቃድ መልቀቅ አለብዎት!
የእራሳቸውን ግልጽ ደብዳቤ በማተም ማዳም ሾርት በEITI የቦርድ አባላት ላይ ታማኝነት የጎደለው ስራ ሰርተዋል፡፡ ከአቅማቸው በላይ ተንጠራርተዋል እናም በEITI የመመስረቻ ደንብ አንቀጽ 12 ስር በግልጽ የተመለከተውን በመተላለፍ ከስልጣን ገደባቸው በላይ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ የEITIን ተቋማዊ ፍላጎት በመጫን ለአንድ ገዥ አካል የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘት ሲሉ የእራሳቸውን ግላዊ ጠንካራ ጥረት በማድረግ በጥቅም ግጭት ውስጥ እራሳቸውን ዘፍቀው ተገኝተዋል፡፡ ማዳም ሾርት ኃላፊነት በጎደለው መልኩ የአንድን የእጩ አባልነት አቅራቢ አገር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ብሄራዊ ባለድርሻ አካላት ሆን ብለው ለጉዳት በመዳረጋቸው EITIን በዓለም አቀፍ ውዝግብ ውስጥ እንዲዘፈቅ አድርገዋል፡፡ ማዳምዋ በድርጅት የውስጥ ጉዳይ በህዝብ ማዕቀፍ ጉዳይ ውስጥ ከህግ አግባብ ውጭ ዘልቀው በመግባት የEITI የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ይፋ እንዲደረጉ የሚጠይቅ የውጭ ቡድንን እንዲገባ በማድረግ በግልጽ ክርክር ለማድረግ መርጠዋል፡፡ ማዳም ሾርት ለአንድ አገር እንደ ወትዋች እና የፓርቲ ቡድናዊነት አሰራርን በማድረግ የEITIን የስብና ብቃት ከጥያቄ ምልክት ውስጥ እንዲገባ አድርገዋል፡፡ በይፋ በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል ተወካይ እና እራሳቸውን እንደ ባለስልጣን በመቁጠር የEITIን የስብዕና ጥያቄ በተጫማሪ ጥያቄ ምልክት ውስጥ እንዲገባ አፍራሽ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ማዳምዋ የድርጅታቸውን ክብር አዋርደዋል፣ እንዲሁም በEITI የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች ላይ ንቀትን እና ውርደትን አምጥተዋል፡፡ በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና በሌሎች ድርጅቶች ላይ አሳፋሪ የስም ማጥፋት ዘመቻ አድርገዋል፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የEITI አባል እንዳይሆን ያስገባውን የአባልነት ማመልከቻ ጥያቄ በEITI ዘንድ ተቀባይነት እንዳያገኝ እየተቃወመ ያለውን የኢትዮጵያ የዲያስፖራ ማህበረሰብ ሰብአዊነትን አንቋሸዋል ጫራቀዊም አድርገው አቅርበዋል፡፡
ማዳም ሾርት እ.ኤ.አ በ2003 ከዓለም አቀፍ ልማት ጸሐፊነት ስልጣናቸው በለቀቁበት ጊዜ የተባበሩት መንግስታት በኢራቅ ህጋዊ መንግስት የማቋቋም ተልዕኮ እንዳለው ቶኒ ብሌር የሀሰት ማረጋገጫ ሰጥተውኛል በማለት በብሌር ላይ ጮኸውባቸው ነበር፡፡ ይህ ሁኔታ አቋሜን እንድለውጥ አያስገድደኝም፡፡ በጣም አዝናለሁ እናም ይቅርታ የእርስዎ ነገር እንዲህ አበቃ፡” ብለው ራሳቸዉን ከሰራ አሰናብተው ነበር::
ስለሆነም በአሁኑ ጊዜ አሜሪካኖች አንደሚተርቱት “ለወንዱ ዳክዬ ጥሩ የሆነው ሁሉ ለሴቷ ዳክዬም ጥሩ ነው፡፡” ማዳም ሾርት በግልጽ ደብዳቢያቸው የፈጸሙት ድርጊት የEITIን የመመስረቻ ደንብ ዓይን ባወጣ መልኩ የመጣስ እና እንደ ድርጅቱ ሊቀመንበርነታቸው የእርሳቸውን የእራስን ኃላፊነት ሆን ብሎ በመዘንጋት በማያገባቸው ተልዕኮ ላይ ተዘፍቀው መገኘት ነው፡፡ “ግልጽ ደብዳቢያቸውን” ወደፊት መግፋት በEITI ያላቸው ስልጣን የሚፍቅድላቸው አይደለም፡፡ ሁላችንም እናዝናለን፣ እናም ይቅርታ በዚህ መንገድ ተጠናቋል፣ ሆኖም ግን ማዳም ክላሬ ሾርት እንደገና ወደኋላ መለስ በማለት ትክክለኛውን ነገር ማድረግ አለባቸው፡፡ማዳም ክላሬ ሾርት አሁን ካሉበት የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) የሊቀመንበርነት ቦታ መልቀቅ አለባቸው፡፡ የተቀመጡበት ወንበር አይመጥናቸውምና!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
መጋቢት 3 ቀን 2006 ዓ.ም