Woyanne goons are intensifying intimidation and harassment against the editor and staff of Feteh, the only independent newspaper remaining in Ethiopia. Last night Feteh editor Temesgen Desalegn’s residence was surrounded by Woyanne police. Another editor, Hailemeskel Beshewamyele, was also harassed and his phone’s SIM card was confiscated by Woyanne thugs. The purpose of such intensified harassment is to shut down the newspaper. The following update is posted on Feteh’s website:
በትላንትናው እለት በ11/04/04ዓ.ም ለፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ርዮት አለሙ መከላከያ ምስክር ሆኖ በመቅረብ የመሰከረላት የፍትህ አዘጋጅ ሀይለመስቅል በሸዋምየለ ከምሽቱ 12፡30 ላይ ቢሮ በር ላይ የደህንነት ሰራተኛ ነን ያሉ 3 ግለሰቦች ሲም ካርዱን ከነጠቁ በኋላ ከባድ ማስፈራራያ አድርሰውብታል፡፡
በዚሁ እለት ከምሽቱ 2 ሰአት ላይ የፍትህ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ እና ሀይለመስቀል በሸዋምየለ ከቢሮ ወጥተው ሲሄዱ በርከት ያሉ የደህንነት አባላቶች ሲከታተሏቸው ከቆዩ በኋላ ሁለቱም ጋዜጠኞች ወደ ተመስገን መኖሪያ ቤት ሲሄዱ የሚከታተሏቸው ሰዎችም አብረው በመሄድ አካባቢውን ከበው ያደሩ ሲሆን በማግስቱም /ዛሬ 12/04/04/ መከታተሉ የቀጠለ እንደሆነ ታወቋል፡፡ አሁን እየተደረገ ያለው ማስፈራሪያና ክትትል ከመጠን ያለፈ ከመሆኑም በላይ በስራቸው ላይ ጫና እያሳደረባቸው መሆኑን ለፍትህ ድህረ ገፅ ገልጸዋል፡፡