Abebe Tola, one of the most prominent columnist and satirist in Ethiopia, was forced to leave his country this week. Abebe, who uses the pen name Abe Tokichaw, told AddisNeger that he didn’t even have the chance to say goodbye to his family before fleeing to escape an imminent arrest. The following is a brief interview with AddisNeger:
አዲስ ነገር፡- በድንገት አገርህን ለቀህ ለመውጣት ምክንያትህ ምንድን ነው?
አበበ ፡- ባለፉት ስድስት ወራት በይፋ ከመንግስት ጋር እንድተባበር ሲወተውተኝ እና ሲከታተለኝ የነበረው የደኅንነት ሰው በእኔ ተስፋ መቁረጡንና እኔን እስር ቤት ለመወርወር መወሰኑን ነገረኝ፡፡ በዚህም ምክንያት ቤተሰቤን ሳልሰናበት በድንገት አገሬን ለመልቀቅ ተገድጃለሁ፡፡ ያው “ከመግባት መውጣት” ይሻላል ብዬ ነው
አዲስ ነገር፡- ከመንግሥት ጋር በምን መልኩ እንድትተባበር ነበር ደኅንነቱ ይወተውቱህ የነበረው ?
አበበ ፡- ግልጽ የሆነ ነገር የለም ነገር ግን “Double agent ሆነህ ከእኛ ጋር” ስራ ይልኝ ነበር፡፡
አዲስ ነገር ፡- አቤ እዚህ ላይ ግልፅ አድርገው፤ ለሌላ አካል የደኅንነት ስራ ትሰራለህ ብለው ይጠረጥሩህ ነበር
አበበ ፡- መጠርጠር ብቻ ሳይሆን መረጃም አለን ብለውኛል፡፡ ይሁንና እኔ ከጸሐፊነት ውጪ ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ የለኝም፡፡ ስሰራ የነበረውም ለመንግሥት የሚጠቅም እንደነበር ነው የማምነው፡፡ እጽፋልሁ፡፡ በጽሑፌም የታችኛውን ኅብረተሰብ ሮሮ አሰማለሁ፡፡ ይህንንም ነው ለመንግሥት ይጠቅማል የምልህ እንጂ የማንም ኤጀንት አይደለሁም፤ የመሆን ፍላጎትም የለኝም፡፡
አዲስ ነገር ፡- በቅርቡ በአሸባሪነት ከተፈረጁት ሰዎች ጋር ካለህ የስራ ግንኙነትና ቅርርብ አንፃር የደረሰብህ ተፅእኖ አለ?
አበበ ፡- በአሽባሪነት ከተፈረጁት ጋዜጠኞች ጋር መገናኘት ቀርቶ ቤተስቦቻቸውን መጠየቅ ፈታኝ ነው፡፡ ይሁንና የሚደርስብኝን የመፈረጅ አደጋ ችላ በማለት በተደጋጋሚ ታሳሪዎቹንም ሆነ ቤተሰቦቻቸውን እጠይቅ ነበር፡፡
አዲስ ነገር፦ የስደትን የመጀመሪያ ቀኖች ከባድነት ስለምንረዳ ከዚህ በላይ አንጠይቅህም። እንኳን ደኅና መጣህ፤ ሥራህን ከስደት እንድትቀጥል እንመኛለን። የሚፈልጉት ዝምታህን ነው፤ ዝምታህን አትስጣቸው።