Federal Police Joint Anti-Terror Task Force in Ethiopia has caught the suspect that is responsible for causing the death of 9 ruling party musicians.
The suspect, a 2-year-old bird named Al’ula, has been positively identified by the driver of the bus that crashed on its way to South Sudan carrying over 25 members of the TPLF musical group.
The driver, fighting back tears, told investigators that the bird barged into the bus and savagely attacked him causing him to lose control. The bird was assisted by an ox, the driver said. The ox is yet to be apprehended.
The suspect, Al’ula, has been brought to Maikelawi Jail in Addis Ababa today for interrogation. Initial investigation indicates that Al’ula has received extensive terror training in Eritrea, according to TPLF regime spokesperson Bereket Simon.
Reporter has the following report in Amharic:
በአዲሷ ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያን ባህል ለማስተዋወቅ በመጓዝ ላይ የነበሩት በብዛት የሕወሓት ታዋቂ ታጋዮች የሚገኙበት የአርቲስቶች ቡድን በገጠመው የተሽከርካሪ አደጋ የዘጠኙ ሕይወት አልፏል፡፡ የሟቾቹ የቀብር ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት መቀሌ ውስጥ በሚገኘው ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ይፈጸማል፡፡
ከቆቦ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ልዩ ስሙ ኾርማት በመባል በሚታወቀው አካባቢ አደጋ የገጠመው አርቲስቶችን የያዘው አውቶብስ የመገልበጥ አደጋ የገጠመው፣ አሞራ በሾፌሩ መስኮት በኩል መግባቱን ተከትሎ መሆኑን የአካባቢው የሪፖርተር ምንጮች ተናግረዋል፡፡
ባለፈው ሰኞ ከማለዳው ሦስት ሰዓት ላይ አደጋ የገጠመው ይኼው አውቶቡስ፣ በከፍተኛ ፍጥነት ሲጓዝ የነበረ ሲሆን፣ ሾፌሩ አሞራውን ለማስወጣት ሲታገል ድንገት መንገዱ ላይ በሬ ገብቶበት ድልድይ ውስጥ የመግባት አደጋ እንዳጋጠመው ለማወቅ ተችሏል፡፡
በጎንደር በኩል ወደ ደቡብ ሱዳን ለማምራት ያቀደው ይኼው የትግራይ የባህል ቡድን፣ በሕወሓት 17 የትጥቅ ትግል ዓመታት በታጋዮችና በተለይ ደግሞ በትግራይ ሕዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆኑ የትግል ሥራዎች በማቅረብ የሚታወቁት ይገኙባቸዋል፡፡ በአደጋው ሕይወታቸው ያለፉ ታጋዮች ብርሃነ ገብረ መስቀል (ጋኖ)፣ ለተመስቀል ገብረ ሕይወት፣ ብርሃነ ገብረ ሕይወት (ሃንደበት)፣ ብርሃነ ዓምዳይ (ኩናማ)፣ ኃይለ ገብረ ሥላሴና ተኪኤ ተስፋ ማርያም ይገኙበታል፡፡ እንዲሁም ወጣት አርቲስቶች ብርሃነ ገብረ ሚካኤል፣ አሸናፊ መንግሥቱና ሃፍቶም ገብረ ማርያም ሕይወታቸው በአደጋው ካለፉት መካከል ይገኙበታል፡፡
የአካባቢው ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ጉዳት ከደረሰባቸው 17 አርቲስቶች መካከል 10 ከፍተኛ ጉዳት፣ 6ቱ መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆኑ፣ የአንዱ አርቲስት ሕይወት የመትረፍ ዕድሉ አጠራጣሪ ነው፡፡
ጉዳት የደረሰባቸው አርቲስቶች ተገቢው የሕክምና አገልግሎት እየተደረገላቸው ሲሆን፣ የትግራይ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ የክልሉ ባለሥልጣናት የጠየቁዋቸው መሆኑንና የሟች ቤተሰቦችንም እንዳፅናኗቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡