The Kinijit Support Group in Dallas, Texas, has issued the follwing statement opposing the illegal land give away of Ethiopian land to Sudan.
መሐል ዳር እንዳይሆን
ከዳላስ ቅንጅት ድጋፍ ቻፕተር የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ህዝብ ፀር እና ባላንጣ የሆነው የወያኔ ኢሀአዴግ ፋሽስታዊ አስተዳደር ገና ከመነሻው የጀመረውን አገርንና ህዝብን የመከፋፈል አባዜ በመቀጠል ለዘመናት ተከባብሮ፤ ተስማምቶና ተግባብቶ የኖረውንና በጋራ መተሳሰብ ፤ መረዳዳት እና በጽኑ ወዳጅነት ላይ የተገነባውን የኢትዮጵያ ህዝብ እንድነት ለመናድ በጎሳ እና በዘር እየከፋፈለ እንዱ ወገን ከሌላው ጋር እንዲጋጭ እና ህዝቡ እርስ በርሱ እንዳይተማመን ለማድረግ የሚሽርበው ሴራ እና እፀያፌ ድርጊት በሰፊው ቀጥሎ ባለበት ባሁኑ ወቅት ይኽው እረመኔ መንግስት በህዝቡ ላይ የግፍ እገዛዝ ቀንበሩን ከጫነበት ጊዜ እንስቶ እስካሁን ህዝቡን ብፋሽስታዊ እገዛዙ ከማሰቃየቱም ሌላ እገርን ቆርሶ ለባእዳን የመስጠት ደባውንም ቀጥሎበታል።
ሁላችንም እንደምናውቀው ከዚህ በፊት ኤርትራንና የባህር ክልላችንን ያለምንም ህዘበ-ውሳኔ በራሱ ፈቃድ ብቻ ለፈጣሪዎቹ ለኤርትራ ገንጣዮች አሳልፎ በመስጠቱ ይኽው ዛሬ በባህር ንግድና በወደቦቿ ታዋቂ የነበረችው ሐገራችን ወደበ-አልባ ሆና የጎረቤት አገሮችን ወደቦች በመጠቀም ለነዚህ ሀገራት የወደብ ግልጋሎት ፣ የ ጉሙሩክ እና ኤክሳይዝ ቀረጥ ሲሳይ ለመሆን በቅታለች ። ይህም ብቻ አይደለም ወያኔ የሰሜናዊ ትግራይ ግዛት የሆነውንና ከሁሉም የኢትዮጵያ ግዛቶች የተውጣጡ ከ 70 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን መ ለዮ ለባሾች የተሰውበትን ባድመን አስመልከቶ ከሻብያ ጋር በተነሳው የግዛት ይገባኛልጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት በሄግ ተሰይሞ በነበረው አለም አቀፍ ፍርድ ቤት፣ ወያኔ ያለበቂ ጥናት ዝግጅትና ማስረጃ ለይስሙላ ብቻ ለክርክር በመቅረቡ እነሆ የዓለም እቀፉ ፍርድ ቤት ባድመ የኤርትራ ግዛት እንደሆነች አድርጎ ፈርዳል።
ይህ በእንዲህ እያለ ሰሞኑን ደግሞ አንድ አስገራሚና አሳዛኝም የሆነ ጉዳይ ተፈጥሮ በሐገር ውስጥም ሆነ በዓልም ዙሬያ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በሰፊው እያነጋገረ እያስቆጣና ምናልባትም ኢትዮጵያውያን በዘረኛው አገዛዝ ላይ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የማያዳግም እርምጃ እንዲውስዱ እየገፋፋ ይገኛል፣ ይኸውም ጉድይ የ 1600 ኪ/ሜ ርዝመትና ከ 30-50 ኪ/ሜ የጎን ስፋት ያለውንና ከሰሜናዊ ጎንደር አካባቢ ጅምሮ አስከ ጋምቤላ ድረስ የሚዘልቀውን የኢትዮጵያ ለም መሬት ለሱዳን መንግስት አሳልፎ መስጠቱ ነው። ይህ አይነቱ የወያኔ ተግባር ከ ሐገር ክህደት ወንጀል ተነጥሎ የሚታይ አይደለም። ውያኔ ዝም ከተባለና በዚሁ ከቀጠለ እገሪቷን በየአቅጣጫው ቆራርጦና በጣጥሶ በመቸብቸብ መሃል ዳር እንዲሆን ካማድርግ አይመለስም። ስለሆንም “መሃል ዳር እንዳይሆን” መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደቀድሞው ሁሉ ዛሬም እምቢ ለሃገሬ ለዳር ድንበሬ ብሎ ክንዱንና አንድነቱን አስተባብሮ በግፈኛው አገዛዝ ላይ መነሳቱና የግዛት አንድነቱንና ሰብአዊ ክብሩን ከማስጠበቅ ሌላ አማራጭ ይኖረዋል ብሎ መገመት የዋህነት ይሆናል።
በዳላስ እና ፎርትዎርዝ የቅንጅት ለአንድነትና ለ ዲሞክራሲ ፓርቲ ድጋፍ ቻፕተር በወያኔ መልካም ፈቃድ ለሱዳን የተሰጠውን የኢትዮጵንያ ግዛት በሚመለከት ይህ ድርጊት ፍጹም ሃላፊነት የጎደለውና ከሃገር ክህደት ወንጀል ተለይቶ የማይታይ በሃገር ላይ የተፈጸመ ደባ መሆኑን በማመን የከረረ ተቃውሞውን ያሰማል ። ከዚህም በተጨማሪ ይህን አምባገነናዊ የወያኔ ኢህአዴግ አሳፋሪና በሃገር ዳር ድንበር ላይ የተቃጣ ሴራ ለማጋለጥ እና የሱዳን መንግስትም በህገወጥ መንገድ ከያዘው የኢትዮጵያ ግዛት በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ በሚደረገው ሁለገብ ጥረትና ትግል ሁሉ የበኩሉን ድርሻ በቆራጥነት ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን አበክሮ አየገለፀ፣ በሐገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሐገር የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ መለዮ ለባሽ ይህንን የወያኔ አሳፋሪ ድርጊት ለማጋለጥ እና በህገ-ወጥ መንገድ ግዛታችንን የያዘው የሱዳን ጦርም አካባቢን ለቆ እንዲወጣና ከመሬታችው ላይ በግፍ የተነሱትና የደረሱበት ያልታወቀው ወገኖቻችን ወደ ነበሩበት ቀያቸው እንዲመለሱ ለማስቻል ከመቸውም ጊዜ ይልቅ አሁን የተባበረ ክንዳችንን በወያኔው ዘረኛ አገዛዝ ላይ ማንሳት እንደሚገባ ለማስገንዘብ ይወዳል።
ድል ለ ኢትዮጵያ ህዝብ!!!!
በዳልስ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ድጋፍ ቻፕተር
ዳላስ ሜይ10/2008