Statement from the Association of Ethiopian Air Force Officers on the death sentence by the Woyanne kangaroo court against air force officer.
ቂም በቀል ወይስ ፍትህ ?
በአለም አቀፉ መድረክ የተባበሩት መንግስታትን አርማ አጥልቆ በኮንጎ ለተሰለፈው ሰራዊት ከፍተኛ የሎጅስቲክ አቅርቦት ሥራን ያከናውን የነበረው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ወደር ላልተገኘለት ጀግንነቱና ለዓለም ሰላም መከበር አስተዋፅኦው የዘመኑ ድንቅ አየር ኃይል በመባል ወገንን አኩርቷል ።
በጐረቤት ሶማልያ ለደረሰው የውሃ መጥለቅለቅ አደጋም በአስደናቂ ፍጥነት ደርሶ ከህይወት ማዳኑ ተግባር ጐን ለጐን ምግብና መድሃኒት ለተጐጂው በማቅረብ ለአካባቢው ህዝቦች ጭምር አለኝታነቱን አስመስክሯል ።
ለዘመናት አገራችንን ኢላማ አድርጐ የያዛትን የአካባቢያዊ ሰላም ማጣት ሥጋት ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ በእብሪት የተቃጣብንን ወረራ በግምባር ቀደምትነት በመሰለፍ የአየር ክልላችንን ከማስከበር አልፎ በምድር ለተሰለፈው የወገን ሰራዊት የቅርብ ረዳት ሲሆን ለጠላቶቻችን ደግሞ የማይፈታ ቅዠት በመሆን ዛሬ ድረስ አለ ።
በቅርቡም የአሁኑ ገዢ ፓርቲ ከኤርትራ ጋር በአደረገው ግጭት በመጨረሻው ጦርነት ለቀድሞው የአየር ኃይል ሰራዊት ጥሪ በማቅረቡ ለአገሩ ሁሌ ቀናኢ የሆነው የአየር ኃይል አባላት በሰጡት ፈጣን ምላሽ የተመረጡ ወታደራዊ ኢላማዎችን በብቃት በመደምሰስ በአገር ላይ ሊደርስ የነበረውን ውርደት በአጭር ቀናት ሊቀለብሰው እንደቻለ የምናስታውሰው ነው ።
ይሁን እንጂ የአየር ኃይሉን የሃገርና የወገን አለኝታነት ፤ በተጨማሪም ኢትዮጵያዊ ጀግንነትን ለማኮስመንና ለማጥፋት በስመ ጥሩው የአየር ኃይል በራሪዎች ላይ የብቀላ ክስ በመመስረት እነሆ እንደተራ ነፍሰ ገዳይ ለሞትና ለእድሜ ልክ እስራት ፍርድ በቅተዋል ።
የአሁኑ ገዢ ፓርቲ በተቃዋሚነት ዘመኑ አለም አቀፋዊ የጦርነት ህግን በመተላለፍ ሰላማዊ ሰዎችን በከለላነት (Human shield) በመጠቀም ሆን ብሎ ካሜራውን አዘጋጅቶ ታንክና መድፉን ወደ ሰላማዊ ሰዎች ወረዳ ይዞ በመግባት በጊዜው በስልጣን ላይ ለነበረውም መንግስት የተሳሳተ መረጃ እንዲደርሰው በማድረግ የአቀናበረውን ፊልም በአለም ላይ እንደቸበቸበና የአለምንም ህዝበ እንዳወናበደበት ከቀድሞው የህውሃት መስራች መሪዎች የተጋለጠ ደባ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጢር በሆነበት በአሁኑ ሰዓት ለ18 አመታት ያለ አንዳች ፍርድ በማጎሪያው እንዲማቅቁ ያደረጋቸውን እንቁ የአገር ሃብት በራሪዎችን፤በተጨማሪም ለሃገራቸው የአየር ክልል መከበር ህይወታቸውን ካጡ ከ20 አመታት በላይ ያስቆጠሩትን ሰማዕታትን
በአፅማቸው ላይ የሞት ፍርድ መፍረዱ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያሳዘነ ጉዳይ ነው።
በሄሮሺማና ናጋሳኪ የአየር ድብደባ ተዋናይ የነበሩት በራሪዎች እንደማንኛውም ወታደራዊ ግዳጅ ፈፃሚ ለፈፀሙት ጀብዱ እስከመጨረሻው በብሄራዊ ጀግንነታቸው::