ቅንጅት በአዲሱ ቢሮው ስራ ጀመረ

ቢሮ ከመከራየት ጋር በተያያዘ በወያኔ ካድሬዎች ከፍተኛ ፈተና ገጥሞት የነበረውና በቅርቡ ወሳኝ የላእላይ ም/ቤት ስብሰባውን ያከናወነው በወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራው የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ በቂርቆስ ክ/ከተማ ርቼ አከባቢ በተከራየው ቢሮ ዛሬ ስራ ጀመረ፡፡

ፓርቲው ከዚህ በፊት ይገለገልበት የነበረውን ቢሮ የወያኔ ካድሬዎች በአከራዩዋ ግለሰብ ላይ ያደርሱ በነበረው ማስፈራርያ ለመልቀቅ የተገደዱ ሲሆን የአዲሱ ጽ/ቤት አከራዮች በእንደዚህ አይነቱ ህገ ወጥ የማስፈራራት ተግባር ተሸንፈው የአቋም ለውጥ እንደማያደርጉ ቢሮውን ለተከራዩት የአመራር አካላት ገልጸዋል፡፡

አመራሩ የ6 ወር ክፍያውን በህጋዊ ውል ካከናወነ በኋላ በዛሬው እለት የቢሮ መገልገያዎችን በማስገባት ስራውን የጀመረ ሲሆን ይህም ድርጅታዊ ስራዎችን በአንድ ማእከል በማከናወን ይፈጠር የነበረውን እክል እንደሚቀንሰው አንድ የአመራር አባል ገልጸዋል፡፡