­

አቶ አባይነህ የጠሩት የላእላይ ም/ቤት ስብሰባ አባላት ባለመገኘታቸው ሳይካሄድ ቀረ

የቅንጅት አርማና ስያሜ ለሌላ በመሰጠቱ በፓርቲው ስም ከዚህ በኋላ መንቀሳቀስ አይቻልም በማለት ምርጫ ቦርድ በማስጠንቀቁና ‹ቀጣዩ የትግል ጉዞ› ምን መሆን አለበት በሚሉት አጀንዳዎች ዙርያ ለላእላይ ም/ቤት አባላት በዛሬው እለት አቶ አባይነህ ብርሃኑ ያቀረቡት የስብሰባ ጥሪ ጥቂት የቀድሞ መኢአድ አባላት ብቻ በመገኘታቸው ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

በተጠባባቂ ሊቀመንበርነት ስልጣን ከፓርቲው ህገ ደንብ ውጭ በተሾሙት በአቶ አባይነህ የሚመራው ቡድን በርካታ ደጋፊዎች አሉን ባለው ደሴ፤ ባህር ዳርና ጎንደር በመሄድ በምርጫ 97 ወቅት የቅንጅት ተመራጭ የነበሩ ግለሰቦችን በየቤታቸው በመሄድ ለማነጋገር እያደረገ የነበረው ጥረት ተቃውሞ በገጠመው ማግስት የጠራው የላእላይ ም/ቤት ስብሰባ የተወሰኑ አባላትን ብቻ ማግኘቱ የቡድኑን ዘላቂነት አጠያያቂ አድርጎታል፡፡