እነ ብርትካን ሚዴቅሳና የቅንጅት የሥ/አ ኮሚቴ አባላት በዛሬው እለት ሊሰጡት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ በሶስት ሆቴሎች አዳራሽ በመከልከሉ በወረቀት የተፃፈውን መግለጫ ሰተው ተበተኑ፡፡
እንደ ኢትዮጵያውያን ሰአት አቆጣጠር ከቐኑ በ 8 ሰዓት ላይ ሞተራ እየተባለበሚጠራው ሆቴል መግለጫ እንዳለ የተነገራቸው ጋዜጠኖች ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ እንደገና ተደወለና አዳራሹ አሳማኝ ያልሆነ ምክኒያት ተሰጥቶ ብሩ እንዲመለስላቸው መደረጉ ታውቀል፡፡
በተጨማሪም ኪንግስ የባለውን ሆቴል አዳራሽ በተመሳሳይ መልኩ የተከለከሉ ሲሆን በመጨረሻ ዮርዳኖስ የተባለ ካሳንቺስ አካባቢ የሚገኝ ሆቴል ከቀኑ በ9፡30 መግለጫው እንደሚሰጥ ተነገረ፡፡
ወደ 20 የሚሆኑ ጋዜጠኞችና አንዳንድ የቅንጅቱ አባላትም በቦታው ተገኙ፡፡
የመግለጫውን መሰጠት በመጠባበቅ ላይእነዳለን ከፖሊስ ተደውሎ ስብሰባው መደረግ እነደማይቻል ከፖሊስ ተደውሎ መታዘዛቸውነና ስሰባውን አደርጋለሁ ብሎ የሚል ና አልወጣም ብሎ የሚያስቸግር ካለ የፖሊስ ሃይል እነደሚላክ እንደተገለጸላቸው ሰራተቹ ገለጹልን፡፡
ምናልባት የተደወለው ስልክ ከፖሊስ ሳይሆን ከሊላ ቦታ እንደሆነ ጠይቀናቸው ምልስ ሲሰጡ፤ የፖሊስ ጣቢያውን ስልክ ያውቁት ስለነበር መልሰው ሲደውሉ ተመሳሳይ መልስ ስለተሰጣቸው ስብሰባውን እንደማይፈቅዱ በመግለጽ የተቀበልነውን ብር እንመልሳለን ብለዋል፡፡
አንድ ፖሊስና ሲቪል ለባሽ ወደ አካባቢው በመምጣት ስለሺ ማነው ብለው ከጠየቁ በሃላ ስብሰባውን ማነው የከለከለው ሲሉ ተደምጠዋል ነገር ግን ሲቪል ለባሹ ቀደም ሲል ወደ ሆቴሉ በመግባት ፖሊስ መሆኑን ከገለጸ በሃላ ስብሰባው ህገ ወጥ ስለሆነ እናዳይደረግ ሲል ትእዛዝ አስተላልፋል ፡፡
ከሆቴሉ እንዲወጡ የተደረጉት ጋዜጠኞችና አንዳንድ አባላት ከሆቴሉ ፊት ለፊት ለ20 ደቂቃ ያክል ሰብሰብ ብለው ከቆሙ በሃላ ብርቱካን ሚዴቅሳ ፣ሙሉነህ ኢዩኤል ፣ስለሺ ጠና፣ታምራት ታረቀኝ እና ሌሎች አባላት መተዋል፡፡
ወደ ሆቴሉም ገብተው መከልከሉን ጋረጋገጡ በሃላ በወረቀት የያዙትን መግለጫ ለጋዜጠኞች ሰጥተው ተመልሰዋል፡፡
በትናንትናው እለትም እነ ብርቱካን በመኢአድ ጽህፈት ቤት ስብሰባ እንዳያካሂዱ መከልከላቸው ይታወሳል፡፡