ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
ወገኖቼ! የተጻፈ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ነውና ከመንፈሳውያን መጽሐፍቶቻችንም ሆነ ከአለማውያን መጻሕፍት የምንጠቅሳቸው እድሜአችን እስኪያልቅ ብንናግራቸው የማያልቁ ብዙ ብዙ ትዝታዎች አሉን፡፡ በቤተ መንግስትም ሆነ በቤተ ክህነታችን ተዝቆ በማያልቀው
እርማችን የገደልናቸው፤ ነገር ግን ምላሳችንን ገልብጠን ዛሬ ለምንዘራው እርም ይረዳን ዘንድ በበጎ ምግባር በገዛ አፋችን የምንጠቅሳቸው ቅዱሳን አባቶች ደም እየከሰሰን ነው፡፡ ይሁን እንጅ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው፤ እኔም ስለገዳይነትና ስለገደልናቸው ወገኖቻችን አይደለም ማለት የምፈልገው፡፡ ማተኮር የምፈልገው ከዚህ በፊት በፈጸምነው በደል ስለተሸከምነው እርም፤ አሁን በዚች ደቂቃም እያቦካን እንደቂጣ ስለምንጋግረው እርም፤ ከዚህ እርም ልንጸዳበት ስለምንችልበት መንገድና ሌላ እርም ከመፈጸም እድንቆጠብ ሊረዳን ስለሚችለው ሃይማኖታዊና ባህላዊ ሐብታችን ነው፡፡ እንዲሆን የምፍለገውም ከዚህ ቀደም ከገባንበት እርም ሕሊናቸን ሳይጸዳ በሌላ እርም ውስጥ ገብተን በመዋኘት መላ ሕይወታችንን በከንቱ እንዳናባክን፤ የተጠጋንበትን ጉባኤ ሁሉም እየበከልን እርምን እንደወረርሽኝ በሽታ ማሰራጨቱን እንድናቆም ነው… ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
(You can download Amharic font here)