ወደ አሜሪካ ጉዞ የሚያደርጉት አራት የቅንጅት አመራሮች ከስቴት ዲፓርትመንት ክሊራንስ መጣላቸው፡፡ ለፓርቲው መሪ አቶ ኃይሉ ሻውል ግን ክሊራንሱ እንዳልመጣላቸው ታውቋል፡፡
በትናንትናው እለት አዲስ አበባ ከሚገኘው አሜሪካን ኢምባሲ ተደውሎ ወ/ት ብርቱኳን ሚዴቅሳ: ዶር ኃይሉ አርአያ: አቶ ግዛቸው ሽፈራው እና አቶ ብሩክ ከበደ ከስቴት ዲፓርትመንት ክሊራንስ እንደመጣላቸው ሲነገራቸው አቶ ኃይሉ ሻውል ግን የተባሉት ነገር የለም፡፡
ምንጮች እንደጠቆሙት አመራሮቹ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወደ ኤምባሲ መሄዳቸውን ቪዛም እንዳገኙ የገለፁ ሲሆን አቶ ኃይሉ ሻውልን በሚመለከት በዛሬና በነገ መካከል ስቴት ዲፓርትመንቱ ክሊራንስ ሊልክ ይችላል የሚል ግምት መኖሩን ነው፡፡