Former president of Ethiopia Mengistu Hailemariam writes a new book — a memoir — that is expected to be released in a few weeks.
Woyanne journalist and publisher Amare Aregawi is also releasing a new book soon, according to Tesfaye Gebreab. It would be interesting to read what he says about his arch nemesis Al Amoudi.
Mengistu’s books is a tell-all account of his 17 years of bloody rule, Ethiopian Review has learned. However, Tesfaye, in his report below, expresses doubt as to how much Mengistu will reveal. We will find out soon.
No matter what, it is a good thing that books and memoirs are being written by Ethiopians who have played a role in shaping the country’s history — whether their role was good or bad.
Aregawi Berhe’s recently released book, A Political History of the Tigray People’s Liberation Front, is one such book.
I recently met with Tesfaye Gebreab in Asmara where he is currently doing research for his new book. It happens that Woyanne has a lot of secrets burried in Eritrea. Tesfaye hopes to release his book, “Ye Derasiw Mastawesha,” in January 2010. If you think “Ye Gazetegnaw Mastawesha” was a shocker, wait until you read the new book. It lays bare some of Woyanne’s most closely guarded secrets. – Elias Kifle
ዜና መፃህፍት – ከተስፋዬ ገብረአብ
ሁለት ዜናዎች ሰማሁ።
መንግስቱ ሃይለማርያምና እና አማረ አረጋዊ መፃህፍት ፅፈዋል። እንደሰማሁት የሁለቱም መፃህፍት ማተሚያ ቤት ገብተዋል። ድንቅ ነው!
ምን ፅፈው ይሆን?
ኮሎኔል መንግስቱ እንዲያው የአበሻ ነገር ካለሆነበት፤ ያበጠው ይፈንዳ፤ ያላበጠው ይበጥ! ብሎ ሁሉን እንደወረደ ቢነግረን አዲስ የግልፅነት አብዮት ማፈንዳት ይችል ነበር። እንደሰማሁት ከሆነ ግን መንጌ ቴክሱ አሁንም በጥቁር አንሶላ ራሱን ለመሸፋፈን ሞክሮአል። ረቂቅ ፅሁፉን ያነበቡ ሰዎች እንደሚሉት ኮሎኔሉ ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ግልፅ ለመሆን ቢሞክርም ገና ልቡን ከፍቶ ሁሉን ሊነግረን ዝግጁ አይደለም። የሆነው ሆኖ መፅሃፉ ታትሞ እሳከነበው ቸኩያለሁ።
የቀድሞ ወዳጄ አማረ አረጋዊም እንዲሁ፤ “አደገኛ መፅሃፍ ፅፌያለሁ” ብሎ ለጋራ ወዳጃችን ነግሮታል። አማረ እንደተናገረው ሁሉን ፍርጥርጥ አድርጎ ፅፎ ከሆነ፣ ሊደብቀን ካልፈለገ በቀር፤ ብዙ ምስጢርና አዲስ ነገር ሊነግረን እንደሚችል ተስፋ አለኝ። ምክንያቱም አማረ ከህወሃት ነባር ታጋዮች አንዱ የነበረ፤ በፕሮፓጋንዳው ክፍል ከመለስ ዜናዊና ከአለምሰገድ ገብረአምላክ ጋር በተመጣጣኝ አቅምና ስልጣን ላይ የነበረ፤ አሁንም ከህወሃት ያሻውን መረጃ ማግኘት የሚችል በመሆኑ ብዙ ያውቃል ብቻ ሳይሆን ሁሉን ያውቃል! ጥሩ የስነፅሁፍ ችሎታ እንዳለውም አውቃለሁ። በአናቱ ደግሞ ፈሪ አይደለም።
የሆነው ሆኖ በቅርቡ ሁለት መፃህፍት የምናገኝ ከሆነ ጠቃሚ ነው። መልካም ንባብ ለሁላችን!