ADDIS ABABA, ETHIOPIA — Tens of thousands of people are lined up starting early Sunday morning to buy tickets for Teddy Afro’s concert tonight.
This concert, which will be held at the Addis Ababa Stadium, will be the first one for Teddy since he was released from prison last August.
The popular singer was thrown in jail for 2 years by the Woyanne tribal junta after being falsely accused of hit-and-run accident which claimed the life of a homeless man.
Awramba Times has the following report (Amharic):
አውራምባ ታይምስ (አዲስ አበባ)፡- ከእስር ከተለቀቀ በኋላ የመጀመሪያው የሆነውና ዛሬ ምሽት ከ12፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚካሄደውን የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ኮንሰርት ለመታደም ከአዲስ አበባና ከመላው አገሪቱ የተሰባሰበ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ከንጋት አንስቶ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ተጥለቅልቋል፡፡
በሺህ የሚቆጠሩ የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ የኮንሰርቱን ትኬት ለማግኘት ብዙ ጥረት ቢያደርጉም አውራምባ ታይምስ ያነጋገራቸው የኮንሰርቱ የፕሮሞሽን ኃላፊ አቶ ምትኩ ግርማ ግን ‹ትኬት አስቀድመን አንሸጥም የትኬት ሽያጩ የሚከናወነው ኮንሰርቱ በሚካሄድበት ዕለት በስታዲየም ነው ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ትኬቱ በህገወጥ መንገድ ዋጋው እንዳያሻቅብ ነው› ማለታቸው ይታወሳል፡፡ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከጧት ጀምሮ ከባድ ዝናብ እየጣለ ቢሆንም በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የኮንሰርቱ ታዳሚዎች ግን ለዝናቡ ቦታ ሳይሰጡ በረጃጅም ሰልፎች እየተጠባበቁ ነው፡፡