It is reported that Beyonce Knowles will not perform at Al Amoudi’s millennium party in Addis Ababa. Instead, the Black Eyed Peas band from the U.S. will perform, according to the organizers. The Black Eyed Peas web site has also posted the band’s planned event in Addis Ababa.
Reuters and other media had reported that Beyonce, Janet Jacksom and 50Cent would perform at the millennium party, but there is no explanation available yet as to why these singers pulled out.
At least two Ethiopian human rights advocacy groups, Tegbar and SCOEPP, had sent warnings to Beyonce and others not to come to Addis Ababa for the millennium, saying that Ethiopia today is not a place to party; “t is a place where the people are being massacred, tortured, raped, and terrorized.”
More details in Amharic below…
ቢዮንሴ ለሚሌኒየም በኢትዮጵያ አትገኝም
ለኢትዮጵያውያን ዕስራ ዓመት (ሚሌኒየም) በአል አልአሙዲ ቦሌ ባስገነባው ማስጨፈሪያ ላይ መጥታ ትዘፍናለች ተብሎ ሲነገርላት የነበረችው ቢዮንሴ እንደማትገኝ ታወቀ፡፡ በምትኩ “ብላክ አይድ ፒስ” የተባሉ አቀንቃኞች እንደሚመጡም ተነግሯል፡፡
ከቦሌ መንገድ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ሲገባ በስተ ግራ በኩል ባለው የተንጣለለ መሬት ላይ ከስድስት ወራት በፊት ኤም ኤ የተባለ የማስታወቂያ ድርጅት ለሚሌኒየሙ የስደስት ወር ፌስቲቫል ለማዘጋጀት አካባቢውን የማስተካከል ስራ ጀመረ፡፡ “እኔ እያለሁ” ያሉት አቶ አብነት ገ/መስቀልና ሼክ መሐመድ አልአሙዲን እሱን አስነስተው ብዙ ብር ሊያመጣ የሚችል አዳራሽና መድረክ ማሰራት ጀመሩ፡፡ በዋዜማውም ታዋቂ የውጭ አቀንቃኞች ይመጣሉ ተብሎ መወራት ጀመረ፡፡ አንዷም ቢዮንሴ ነበረች፡፡
ሰሞኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንደገለጹትም በዋዜማው ለሚደረገው ለዚህ ዝግጀትም ቢዮንሴ እንደማትገኝና በምትኩ “ብላክ አይድ ፒስ” የተባሉ አቀንቃኞች እንደሚገኙና ኢትዮጵያውያን ዘፋኞች እንደሚጋበዙ ተገልጿል፡፡ ለዚህ ዝግጅት መግቢያ የተመደበውም ለአንድ ሰው 1600,00 የኢትዮጵያ ብር ነው፡፡
በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ስታዲየም ዝግጅት ለማዘጋጀት ገንዘብ ከፍሎ የነበረ አንድ ድርጅት ስታዲየሙ “ሕብር” የተባለ ዝግጅት ይዘጋጅበታል ተብሎ እንደተከለከለ ለማወቅ ተችሏል፡፡ መስቀል አደባባይ ላይ “ቴስት ኦፍ አዲስ” በግለሰቦች ሊዘጋጅ የነበረው ዝግጅትም መሰረዙ የሚታወስ ነው፡፡