Ethiopia’s fake patriarch send his goons after bishops

Addis Ababa, Ethiopia — It is reported that last night several unknown individuals have attacked at least three bishops of the Ethiopian Orthodox church who are thought to be opponents of the fake patriarch of Ethiopia, Aba Gebremedhin (formerly known as Aba Paulos), who was installed by the Woyanne tribal regime.

According to the Amharic online journal, Deje Selam, those who were attacked include Abune Fanuel, Abune Qerlos and Abune Epifanios.

Read more at Deje Selam. Click here.


ዛሬ ረቡዕ ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው ያለውን የመብራት መጥፋት ተገን ያደረጉ ሰዎች በብፁዓን አባቶች ላይ አደጋ መጣላቸው ተሰማ።

የደጀ ሰላም ምንጮች እንደተናገሩት ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ባለፈው ጊዜ ማንነታቸው ለጊዜው ያልታወቀ ሰዎች የብፁዓን አባቶችን መኖሪያ በመደብደብ፣ በር ገንጥሎ በመግባት አደጋ ማድረሳቸው ሲታወቅ ይህ ዜና በተጠናቀረበት ወቅት አባቶች ላይ የደረሰው አደጋ ምን እንደሆነ፣ የተጎዱትስ አባቶች ምን እንደገጠማቸው አልታወቀም። ምንጮቻችን እንደተናገሩት ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ሳይሆኑ አይቀሩም፣ ሲጮሁና “አድኑኝ” ሲሉ ተሰምተዋል ተብሏል።

ፓትርያርኩን በመቃወሙ ዘርፍ ስብሰባዎችን ሲመሩ የሰነበቱት የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ መኖሪያ በር ከተሰበረ በሁዋላ ብፁዕነታቸው የመኝታ ቤታቸውን በር ቆልፈው ከአደጋው አምልጠዋል ተብሏል። ማንነታቸውን ለጊዜው ያላወቅነው አንድ አባት ግን ችግር ሳይደርስባቸው አልቀረም። እኚሁ አባት “ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ናቸው፤ ታፍነው ሳይወሰዱ አልቀሩም” ሲሉ ምንጮቻችን ጥቆማ ሰጥተዋል። ይህንኑ ያወቁ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መግባታቸውም ታውቋል።

በሌላም በኩል ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ውጪ ቃሊቲ አካባቢ ባለው መኖሪያቸው የሚኖሩት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የጥቃቱ ኢላማ የነበሩ ሲሆን አደጋ ጣዮቹ በራቸውን በተደጋጋሚ ከደበደቡ በሁዋላ፣ በጥበቃ ሠራተኞቻቸው መኖር ከአደጋው አምልጠዋል ተብሏል። ብፁዕነታቸውም ወደ ፖሊስ ዘንድ በመሄድ ቃላቸውን ሰጥተው ተመልሰዋል።

የዛሬው አደጋ ኢላማ የሆኑት አባቶች የፓትርያርኩ ተቃዋሚዎችና በዛሬው ስብሰባ ላይ ጠንካራ ሐሳብ የሰነዘሩት ናቸው ተብሏል። ነገሩ በርግጥም በተባለው መልኩ ተፈጽሞ ከሆነ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ አደጋ ላይ የመሆኗ የመጨረሻ ምልክት ይሆናል ማለት ነው።

አባቶች አካላዊ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ታወቀ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 16/2009)

ረቡዕ ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው ያለውን የመብራት መጥፋት ተገን ያደረጉ ሰዎች በብፁዓን አባቶች ላይ አደጋ ለመጣል በተደረገው ሙከራ ከንብረት ውድመትና አባቶችን ከማጎሳቆል ባለፈ አካላዊ ጉዳት በሚያደርስ መልኩ አደጋ የደረሰበት አባት እንደሌለ ታወቀ።

ብዙ የጥበቃ ሠራተኞች በሚተራመሱበት የቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የብፁዓን አበው መኖሪያ ሕንጻ ላይ በተሰነዘረው በዚህ አደጋ የቅዱስ ሲኖዶስ መብት አስጠባቂነቱን ስብሰባ በመምራት ላይ የሚገኙት የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ቤት በሮች ከተሰባበሩ በሁዋላ እርሳቸው ግን በእግዚአብሔር ቸርነት ሲተርፉ በተመሳሳይ መልኩም የብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ቤት በር ተሰባብሯል ተብሏል።

ከሌሎቹ በተለየ የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ቤት ለአደጋ የተጋለጠበት ምክንያት የአባቶች ፊርማ ያረፈበት ቃለ ጉባዔ እርሳቸው ዘንድ ስለሚገኝ ሊሆን እንደሚችል ምንጮቻችን አብራርተዋል። ከርሳቸው በተጨማሪ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ለተወሰነ ጊዜ “ታፍነው፣ ማስፈራሪያና ዛቻ” ደርሶባቸው ተለቀዋል የተባለ ሲሆን ሌሎች ምንጮች በበኩላቸው ምንም እንዳልደረሰባቸው ይናገራሉ።

ይህ ሁሉ ሲሆን የግቢው የጥበቃ ክፍል ምን ይሠራ እንደነበር፣ የት እንደነበር ገና ምርመራ ያስፈልገዋል። አደጋውና በር- ሰበራው ለጆሮም ለዓይንም የማይሰወር፣ እንኳን የጥበቃ ሠራተኞች ራሳቸው ፓትርያርኩም ሊሰሙት የሚችሉት እንደሆነ ተገልጿል። አባቶች ስለ ቤተ ክርስቲያን ያላቸውን አቋም በመግለጻቸው ብቻ ጥበቃ ሊደረግላቸው ሲገባ ለአደጋ በሚጋለጡበት ሁኔታ መተዋቸው የተደፈረችው ቤተ ክርስቲያን መሆኗን ያሳያል ተብሏል። አደጋው መድረሱን ያወቁ አንድ አባት ለጥበቃ ሰዎች ቢናገሩም የሚደርስ ሰው አለመገኘቱ ሲታወቅ መንግሥት በእምነት ደረጃ የሃይማኖት አባቶች፣ በዜግነት ደረጃ አረጋውያን የሆኑ አቅመ ደካማ ዜጎቹን ለመጠበቅ አለመቻሉ አነጋግሯል።

ዛሬ ጠዋት አባቶች በአካል በተገናኙበት ወቅት ስለ ጤንነታቸውና ስለ አጠቃላዩ ሁኔታ ሲነጋገሩ መታየታቸው ታውቋል። በዚህ የመንፈስ መረበሽና የሴኪዉሪቲ እጦት መንፈስ ምን ዓይነት ስብሰባ ሊያኪያሂዱ እንደሚችሉ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል። በዚህ ወንጀል ውስጥ ሊሳተፉና ሊመሩ የሚችሉ እነማን ሊሆኑ ይችላሉ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የራሳቸውን መላምት የሚሰጡ ምንጮቻችን እንደሚናገሩት በፓትርያርኩ መሪነት እርሳቸውን ተገን አድርገው የሚንቀሳቀሱት ማፊያ ቡድኖች፣ በተለይም የእጅጋየሁ በየነና የቅዱስነታቸው የወንድም ልጅ የሆነው የያሬድ ጋሻ ጃግሬዎች ሳይሆኑ አልቀሩም ይላሉ። ሌሎችም በበኩላቸው መንግሥት የሚጫወተው ድራማ ወይም በቁልቢ ብር የተገዙ የደህንነት ሠራተኞች የሚሰሩት ሕገ ወጥ ድርጊት ይሆናል ሲሉ ግምታቸውን ይናገራሉ።

በትናንት ረቡዕ ስብሰባ ፓትርያርኩ “ሕገ ቤተ ክርስቲያን የምትሉትን አልቀበልም፣ የማንም ዱርዬ የሠራው ነው፣ … ሲኖዶሱ ተጠሪነቱ ለፓትርያርኩ ነው” የሚለው ክርክራቸው ከከሸፈ ወዲህ በትልቅ የተስፋ መቁረጥ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። ነገሩ በዚህ ካለቀ ችግር ውስጥ የሚገባው የፓትርያርኩና የማፊያዉ ቡድን ወደ ጥቃት የተሸጋገረው ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ተብሎ ተገምቷል። ሲኖዶሱ በመንግሥት ባለሥልጣናት አሸማጋይነት የጀመረው ስብሰባ ዛሬም ቀጥሎ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እግድና በሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ ለመነጋገር ቀጠሮ ነበረው።