Ato Gebremedhin erects statue for himself

Aba Paulos statueAto Gebremedhin (formerly Aba Paulos, also commonly knows as Aba Diabilos), who claims to be the patriarch of Ethiopia,  has just erected a massive statue for himself in the center of Ethiopia’s capital Addis Ababa. Aba Diabilos builds statue for himself — like Saddam Hussein — while ancient Ethiopian monasteries and churches are currently falling apart due to lack of funds. This is indeed one of the saddest moments in the history of Ethiopian Orthodox Church.

The following is a commentary regarding the statue and other developments in the Church.

መንፈስ ቅዱስን ካሳዘኑ፥ ቅድስናን ከጣሉ ተሳዳቢዎች ጋር መወያየት አይጠቅምም

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ለሚመራው በሰደት ላይ ለሚገኘው ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን (ኢት.ኦር.ተዋ.ቤተክርስቲያን) ቅዱስ ሲኖዶስ ምንም እንኳ ቀኖናና ህገ ቤተክርስቲያን በመጣሱና ቤተክርስቲያኗ በአምባገነናዊ የመንፈስ ድቀት በተጎናጸፉ ዘረኛ ቤተክርስቲያኗ መሪ ቤተክርስቲያኗ በካህናቷ በምዕመናኗ ላይ እየተሰራ ያለውን ግፍ አስቀድማችሁ ያወገዛችሁ ብትሆኑም ምናልባት ቀኖና ጣሾች በንስሃ ተመልሰው ልብ ገዝተው ቤተክርስቲያኗ ወደቀደመችበት የአንድነትና የፍቅር መንፈስ ተመልሳ ህገ ቤተክርስቲያን ሊጠበቅና የቀደመ ቦታዋን ትይዛለች በሚል ቅን የእውነት እምነት “ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነው፣ እነሆም ያማረ ነው ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስ እስከ አሮን ቂም በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው። በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርምኒኤም ጠል ነው። በዚያ እግዚያብሔር በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዟልና” መዝሙር 132 በሚለው መሪ የእግዚያብሔር ቃል በህብረት በፍቅር ከወንድሞች ጋር ተቀምጦ ለመወያየት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ስለ ቤተክርስቲያን አንደነት ስትሉ ሰሞኑን ከጁላይ 24, 2010 ወዘተ… ጀመሮ ባሉት ቀናት ለውይይት ለመቀመጥ ተዘጋጅታችኋል።

አዎ እርቅ ያስፈልጋል የናፈቀንና የራቀብን ነገር ነው። ሆኖም ሰሞኑን አምባገነኑ በክህደት እባጭ በሞት አፋፍ የሚገኙት የቤተክርስቲያኗ የውድቀትና የድቀት ምልክት አባ ጳውሎስ ጭራሽ የምን ቀኖና ቤተክርስቲያን፥ የፈለኩትን ከማድረግ የሚያስቆመኝ የለም በሚል የቤተክርስቲያኒቷ ዋይታ እንዲጨምር፥ መሸከም እስኪያቅታት፥ እስከሚጨንቃት፥ ወደማትወጣበት አዘቅት በመጣል ህገ ቤተክርስቲያኗን በመጣል የክርስቶስ በሆነችው ቤተክርስቲያናችን ላይ ቀልድ፣ ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ንስጥሮሱ አባ ጳሎስ ምንም እንኳ በስራቸው ከሞቱ የቆዩ ቢሆንም “ከሞትኩ ቆይቻለሁ፥ እናንተ ግን አይገባችሁም፣ ለኔ ከመስገድ በቀር” በሚል የንስጥሮሱ አባ ጳውሎስ መታሰቢያ ጣኦት ሐምሌ 4 ቀን 2002 ዓ.ም. በቦሌ አቆሙ። አይ ድፍረት!!!

አባ ንስጥሮስ ጳውሎስ ቀደም ብሎ ከሎስ አንጀለስ ጀምሮ የተወገዙ ቢሆንም ህይወታቸው በጨለማ ተጋርዶ በዚህ ቀደሙ ሳይፀፀቱበት ዛሬም ቀኖና ቤተክርስቲያንን በመጣስ በቤተክርስቲያን ትምህርት፣ ታሪክና ትውፊት የሌለ “በላይ በሰማይ፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውሃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረፀውን ምስል ለአንተ አታድርግ ዘፀአት 20፡ 4-5” የሚለውን በመተላለፍ፣ የኦርየንታል አብያተክርስቲያናትን ትውፊት በድፍረት በመጣስ አስደንጋጭ ክህደት ስለሆነና የቤተክርስቲኡኗን መፅሃፍት የእውነት ምስክርነት የሚፃረር በመሆኑ፣ ትንሳዔ ሙታንን የሚያስረሳ ነውረና ስራ በመስራት ላይ ካሉት ከጣኦቱ ከንስጥሮሱ አባ ጳውሎስ ጋር በግል የምታደርጉትን “የእርቅ” ውይይት ከቤተክርስቲያኗ የወደፊት ትክክለኛ ጉዞ አንፃር በመመርመር ከንስጥሮሱ አባ ጵውሎስ የግል ግጥር ሰራተኞች ጋር የምታደርጉትን ውይይት በመሰረዝና በመገናናኛ ብዙሃን በማሳወቅ አዲስ አበባ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዲስ ልብ ገዝቶ ሁሉንም የሚወክሉ አምኖበት ወስኖ በመለያየት ቁንጮነትና መሰሪነት በስድብና ከክፉ ባሕርያቸው አድራጎታቸው ከማይጠረጠሩት ተወካይ ብፁአን አባቶች ጋር ታደርጉት ዘንድ እናሳስባለን። አዲስ አበባ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ሳይመክርበት ከሚመጡት አራት ሰዎች ውስጥ፤

1. አባ ገሪማ የአባ ንስጥሮስ ጳውሎስ እምባ ጠባቂ፥ የመለያየቱ ዋና መሪና ተዋናይ፥ ዛሬም የእርቁ ተቃዋሚ በፓትሪያርክ ላይ ፓትሪያርክ መሾሙን ቀኖና ቤተክርስቲያን መጣሱን የሚደግፉ የጥቅም ሰው ስለመሆናቸው ከዚህ በፊት ለ ቪ.ኦ.ኤ. የሰጡት ቃለ ምልልስ ስላለን በጊዜው በአየር ላይ እናውለዋለን።

2. ሌላው የግል ቅጥረኛ፥ ሰይፈ ይሁዳ ብንለው ይቀላል፥ መቀራረብ እንዳይኖር ብፁዓን አባቶች ላይ ጸያፍ ዘለፋና ቤተክርስቲያንን በማዋረድ በየሬዲዮ የተሳደባቸው መረጃዎች በእጃችን ላይ ይገኛሉ።

3. ንቡረዕድ ኤሊያስ የአባ ንስጥሮስ ጳውሎስ እንባ ጠባቂ ተላላኪ።

4. ብጹዕ አቡነ አትናቲዮስ እውነተኛ አባት በመሆናቸው ለእርሳቸው ያለንን ፍቅርና የመንፈስ ልጅነት ዛሬም በፅናት እንገልፃለንና ልክ ብጹዕ አቡነ አትናቲዮስን የመሳሰሉ ብጹአን አባቶች ጋር አዲስ አበባ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ መክሮበት ብታደርጉ ይሻላልና (የአዲስ አበባው ቅዱስ ሲኖዶስ መጀመሪያ ከራሱ ጋር መታረቅ ይኖርበታል)።

አሁን ለውይይት ከተላኩት ሶስቱ መንፈስ ቅዱስን ካሳዘኑ ቅድስናን የጣሉ ተሳዳቢዎች ለቤተክርስቲያኗ ተለያይታ እንድትኖር መዘውር ከሚዘውሩት ጋር ውይይት ማድረግ የማይጠቅምና በአባ ንስጥሮስ ጳውሎስ ጭምብል የተላኩ “ብለን ነበር፣ እምቢ አሉ” የሚለውን የተለመደ ቅጥፈት ከማለት ያለፈ ለቀኖናና ህገ ቤተክርስቲያን መጠበቅ የሚፈይደው አንዳችም ጉዳይ ስለሌለ ለሌላ ጊዜ ብታስተላልፉት የምዕመንነት ምክራችንን እንለግሳለን።

“ዕርቁ፥ ጠቡ በአባ እከሌና በአባ እከሌ መካከል የተደረገ እጅ የማጨባበጥ ተግባር ሳይሆን ቀኖና ህገ ቤተክርስቲያንን የመጣስና የማቃለል፥ መንፈስ ቅዱስን የማሳዘን ተግባር ነውና የተፈፀመው” ግልፅ ሊሆንና ዛሬ ላለንበት የኢት.ኦር.ተዋ.ቤተክርስቲያን ጉስቁልናና ውርደት ተጠያቂነት ነውና በሁሉም ዘንድ ተወዳችነትና ተፈላጊነት ያላቸው የአዲስ አበባው ቅዱስ ሲኖዶስ አምኖበት ብፅዓን አባቶች ተወክለው ሲመጡ እንደሚደረግ ሆኖ የእርቁ በር ክፍት ቢሆን የተሻለ ነው።

ነፍሳቸውን ይማርልንና አለቃ አያሌው ታምሩ በአንድ ወቅት “ግለሰቡ አባ ንስጥሮ ጳውሎስ ቀኖና ቤተክርስቲያንን የሚፃረሩ የካቶሊክ እምነት አራማጅ ናቸው” በማለት አውግዘዋቸው በመቃብሬም እንዳይገኙ ብለው ነበር። እነሆ በገሃድ ታየ። ጣኦቱ ቤል ንስጥሮ ጳውሎስ ቦሌ ላይ ቆመ። ታዲያ ተዋህዶ ምን ትጠብቃለች? አለን የምትሉትስ የአዲስ አበባ ቅዱስ ሲኖዶስ አባላትስ ምን ትላላችሁ? ወይ ፍርሃት! ወይ አሳምኑን፥ ወይ እናሳምናሁ። አሁን የቦሩ ሜዳን ታሪክ መድገም እንሻለን። መቼም ከጣኦት ጋር ህብረት እንደማይኖራችሁ እርግጠኛ ከመሆን ጋር፡፡ ቸር ይግጠመን።

አምላካችን እግዚያብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ከፀሐዩ ደመቀ፥ ለንደን

FORUM | AMHARIC