Ethiopia: Addis Ababa Police Headquarters robbed

ADDIS ABABA, ETHIOPIA — Unknown individuals have reportedly robbed the Addis Ababa Police Headquarters late last month taking with them over 20 AK-47 automatic rifles, several hand grenades, and ammunition, according to Ginbot 7 Radio.

Such a brazen attack on a police headquarters in Addis Ababa, which is watched by several layers of security agencies — the Federal Police, kebele police, the military, Ministry of Internal Security, and the Addis Ababa police itself — has caused a speculation that the robbery might be an inside job.

More from Ginbot 7 Newspaper [Amhairc]:

ከባድ የጥበቃ ስራ በሚካሄድበት አዲስ አባባ ፖሊስ ጽፈት ቤት ውስጥ የመሳሪያ ዝርፊያ ተካሄደ

የወያኔ የደህንነት፣ የመከላከያና የፖሊስ አባለት ለ24 ሰአት በተጠንቀቅ በሚጠብቋት አዲስ አበባ የመሳሪያ ዝሪፊያ መካሄዱ ፤ ዝሪፊያውም የተካሄደው በፖሊስ ጣቢያው ግቢ ውስጥ መሆኑ ብዙዎችን አስገርሟል።

ጥቅምት 24 ቀን 2002 አም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በአዲስ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በተፈጸመው ዝርፊያ ከ20 በላይ ክላሺንኮቭ ጠመንጃዎችና በርካታ ጥይቶችና ቦምቦች መዘረፋቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል። ዝርፊያው የተፈጸመው በሌሊት ሲሆን፣ የወያኔ ተረኛ ጠባቂ ፖሊሶች ስራቸውን በመስራት ላይ እንደነበሩም ለማወቅ ተችሎአል።

የዘራፊዎቹ ማንነት በውል ባይታወቅም ለዝግጅታችን ሚደርሱን መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ዝርፊያውን የፈጸሙት ራሳቸው የወያኔ ሹመኞች ሳይሆኑ አልቀረም። የወያኔ ባለስልጣናት የተወሰኑ ፖሊሶችን ለማጥቃት በማሰብ ዝርፊያውን ሆን ብለው እንዳቀነባበሩት የሚጠቁሙ መረጃዎች በርካታ ሲሆኑ፣ የግንቦት 7 ድምጽ መረጃውን አጣርቶ ለህዝብ ይፋ ለማድረግ በመስራት ላይ ነው።

በተያያዘ ዜናም ባለፈው ወር ብቻ ከ1500 በላይ ፖሊሶች ስራቸውን በፈቃዳቸው ለቀዋል። ፖሊሶቹ ከወያኔ ጋር አብረው ለመስራት አለመፈለጋቸውን በመግለጽ የመልቀቂያ ደብዳቤ ሲያስገቡ መቆየታቸውን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን፣ ወያኔ በሚለቁ ፖሊሶች ቦታ ታማኝ ተተኪዎችን ካዘጋጀ በሁዋላ የስራ መልቀቂያውን መፍቀዱ ታውቋል። ይህን ተከትሎም ከ1500 በላይ ፖሊሶች ስራቸውን ጥለው መውጣታቸውን ከታማኝ ምንጮች ያገኘው መረጃ አመልክቷል።

ወያኔ በፖሊሶች ላይ ያለው ጥርጣሬ በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ በቅርቡ በጦላይ ወታደራዊ ማስልጠኛ ጣቢያ ግምገማ አካሄዶ በርካታ ፖሊሶችን ማባረሩ የሚታወስ ሲሆን፣ ተመሳሳይ ዙር ግምገማ በቅርቡ እንደሚደረግም ለማወቅ ተችሎአል።

ወታደሮችና ፖሊሶች አገርን በመግደል ላይ ካለው የወያኔ አገዛዝ ጋር በመተባበር ወገናቸውን ከመበደል እንዲታቀቡና የነጻነት ሀይሎችን እንዲቀላቀሉ የግንቦት 7 ሊ/መንበር የሆኑት ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ በአዲስ አመት መልእክታቸው ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ጥሪው በሰራዊቱና በፖሊሶች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኘ መምጣቱን የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ።