የቅንጅትን የትግል አቅጣጫ የሚወስን የስምምነት ፊርማ ተፈጸመ

ለቀናት ሰፊ ውይይት ሲካሄድበት የቆየው ቅንጅትን የትግል አቅጣጫ ይወስናል ተብሎ የታመነበት ስምምነት ፊርማ በቅንጅት ስራ አስፈጻሚ እና ፓርቲውን ወክለው ፓርላማ በገቡት በእነ አቶ ተመስገን መካከል በዛሬው እለት ተፈጸመ፡፡

ዛሬ ከቀኑ በ8፡00 ሰአት ላይ የቅንጅት ስራ አስፈጻሚ ቡድን ባደረገው የአብላጫ ድምጽ ውሳኔ የእነ አቶ ተመስገን ዘውዴ ቡድን ያቀረበው የትግል አቅጣጫ ሃሳብና አመራሩ ያቀረበውን ከተናበቡ በኋላ ተግባራዊ እንዲሆን ተወስኗል፡፡

የስምምነቱ ዝርዝር ሃሳብ ፓርቲው ህጋዊ የሚሆንበት አማራጭ አስመልክቶ የተለያዩ ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን በቀጣይ ሂደት አዲስ ስያሜ ለመውሰድ ወደ ምርጫ ቦርድ የሚኬድበት አማራጭ፤ ይህንን ተከትሎም ፊርማ ማሰባሰብ፤ ከፊርማ ማሰባሰብ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ መጥራትና የፓርቲው አመራር የሚመረጥበትን ዲሞክራሲያዊ አሰራር ያጠቃለለ መሆኑን አንድ የአመራር አባል ለዜና አገልግሎቱ ገልጸዋል፡፡