ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ በጦርነት እየታመሰች ነው

በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ኦሮሚያ ዞን ቦረና ከሃገረ ማርያም 57 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በጉጂዎችና በኮሬ ብሄረሰብ መካከል በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን ሪፖርተራችን ዘገበ፡፤

በአከባቢው በተለያዩ ጊዜያት በወሰንና አከባቢውን ሃብት በመጠቀም መንስኤ ግጭቶች ሲከሰቱ የቆዩ ቢሆንም የአሁኑ ከፍተኛ የሰውና የንብረት ኪሳራ እያደረሰ መሆኑን ተጠቂዎቹን ያነጋገረው ሪፖርተራችን ዘገባ ያመለክታል፡፤

እስካሁን ሁለት የፌዴራል ፖሊስ አባላትና ሌሎች ሁለት የክልል ፖሊስ አባላት በግጭቱ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች ግጭቱን የቀሰቀሱት በአካባቢው የተሰማሩት የወያኔ/ኢህአዴግ ካድሬዎች ናቸው ሲሉ ይከሳሉ:: በሌላ በኩል የዞኑ ባለስልጣናት “ኦንግ የፈጠረው ብጥብጥ ነው” ይላሉ::

የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አባዱላ ገመዳ በክልሉ ያሉ የኦነግ አባላትን ለማስወገድ በሚል ከክልሉ አስተዳዳሪ ጋር የነደፉት የአራት ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ከከሸፈ በኋላ ግጭቶች በከፍተኛ ደረጃ መጨመራቸውን ምንጮቻችን አመልክተዋል፡፡