ወደ አሜሪካና አውሮፓ ጉዞ የሚያደርጉት የቅንጅት አመራሮች ቪዛ አላገኙም

ወደ አሜሪካና አውሮፓ ጉዞ የሚያደርጉት የቅንጅት አመራሮች ቪዛ አላገኙም
ወደ አሜሪካን አገር ጉዞ ለማድረግ በዝግጅት ላይ የነበሩት አምስት የቅንጅት አመራሮች ኢትዮጵያ ከሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ የመውጫ ቪዛ ባለማግኘታቸው ጉዞአቸው ሳይዘገይ እንደማይቀር ተገምቷል፡፡ ወደ አውሮፓ የሚጓዙት ሌሎቹ አምስት አመራሮችም እስካሁን ቪዛ እንዳላገኙ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
ባለፈው እረቡ የግብዣ ወረቀታቸውን በመያዝ ኢትዮጵያ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ያመሩት ኢ/ር ኃይሉ ሻውል፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ዶ/ር ኃይሉ አርአያ አቶ ብሩክ ከበደ እና ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው በአጠቃላይ አምስት የቅንጅት አመራሮች የአሜሪካ መንግሥት የመግቢያ ፍቃድ ስላላከልን እሱን ከላከልን እንሰጣችኋለን ሲሉ መልሰዋቸዋል፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚፈለገውን ክሊራንስ ያልላከ ሲሆን እሱ ተልዕኮ ቪዛ እስኪሰጣቸው ድረስ እየጠበቁ መሆኑ ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ወደ አውሮፓ ጉዞ የሚያደርጉት አቶ ሙሉነህ ኢዩኤል፣ ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም፣ አቶ አባይነህ ብርሃኑ፣ አቶ አስቻለው ከተማና አቶ ክፍሌ ጥግነህ የግብዣ ወረቀት የደረሳቸው ባለፈው ሳምንት ሲሆን ትክክለኛውን ምላሽ የሚያውቁት የፊታችን ሰኞ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡