Detainees accused of plotting coup brutally tortured by police

ADDIS ABABA, ETHIOPIA — The 46 detainees who are currently on trial after being accused by the tribal junta in Ethiopia of trying to overthrow the regime have told the court on Friday that they are being savagely beaten up by security personnel.

One of the accused, Ato Asaminew Tsige, told the court that he has lost sight in one eye from the beatings.

Upon hearing Ato Asaminew’s claim, family members started to cry loudly, prompting the judges to remove every one from the court room except the accused, the prosecutors, the defense lawyers, the police, and some journalists.

Ato Asaminew asked the court to appoint an independent physician to give the detainees medical treatment and investigate the tortures.

An official representing the prison denied the torture charge. The judges hearing the case told the detainees to file their complaints in writing.

More by Tamiru Tsige, a correspondent for The Reporter:

መንግሥትን በሃይልና በአመፅ ለመጣል ሲንቀሳቀሱ ደርሸባቸዋለሁ በሚል የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ክስ ከመሠረተባቸው ተከሳሾች መካከል አንዳንዶቹ በማረሚያ ቤት ውስጥ ድብደባ እንደደረሰባቸው ለፌዴራል ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ኅዳር 4 ቀን 2002 ዓ.ም. አቤቱታ አቀረቡ፡፡ ማረሚያ ቤቱ የቀረበበትን አቤቱታ “የተቋሙን ሥም ለማጥፋት የተደረገ ነው” ሲል አስተባብሏል፡፡

በእነ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ በተከሰሱት 46 ተከሳሾች ላይ የተደመጡትን የመከላከያ ምስክሮች ቃል (880 ገጽ) ከህግ አግባብ ጋር በማገናዘብ ውሳኔ ለመስጠት ለኅዳር 4 ቀን 2002 ዓ.ም. ቀጥሮ የነበረው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት “የ8ኛ፣ 19ኛ፣ 21ኛና የ32ኛ ተከሳሾች ያሰሟቸው ምስክሮች ቃል ባለ መድረሱ ሁሉንም አጠቃለን ኅዳር 8 ቀን 2002 ዓ.ም. የመጨረሻ ውሳኔ እንሰጣለን” ሲል፤ የ28ቱ ተከሳሾች ጠበቃ ተነስተው ደንበኞቻቸው ለፍርድ ቤቱ የሚያመላክቱት አቤቱታ እንዳላቸው ተናገሩ፡፡

ፍርድ ቤቱ “አሁን ምንም አንቀበልም” ሲል፤ 2ኛ ተከሳሽ የሆኑት አቶ አሳምነው ጽጌ በመሀል ተነስተው “በጌታ ስም፣ በምታመልኩት ሥም አዳምጡን እኔ ዓይኔ ጠፍቷል” ሲሉ ችሎቱን የታደሙት ዘመድ አዝማድ የፍርድ ቤቱን አዳራሽ በጩኸት አናወጡት፡፡

ለተወሰነ ደቂቃ ጩኸት በተቀላቀለበት ለቅሶ ተናውጦ የነበረው የፍርድ ቤቱ አዳራሽ ሲረጋጋ፣ “ፍርድ ቤቱ በጩኸትና በሁካታ ሊሰራ ስለማይችልና አቤቱታ አቅራቢዎቹም በተረጋጋና በተስተካከለ መልኩ መናገር ስለማይችሉ ፀጥታ ወሳኝ ነው፡፡ አሁንም ተከሳሾቹ የሚያቀርቡትን አቤቱታ በጥሞና መስማት እንዲቻል፣ ከፖሊስ፣ ጠበቃና ዐቃቤ ሕግ ውጭ ችሎቱን የታደማችሁ ትወጡና በዝግ እንሰማለን” በማለቱ ጋዜጠኞችን ጨምሮ ሁሉም የችሎቱ ታዳሚዎች ወጡ፡፡

ጋዜጠኞች ለዳኞች አመልክተን እንድንገባ ከተፈቀደ በኋላ ተቋርጦ የነበረው “ተደበደብን” ያሉት ተከሳሾች አቤቱታ መደመጥ ጀመረ፡፡

ጥቅምት 27 ቀን 2002 ዓ.ም. ከምሽቱ 12፡10 ሰዓት ሲሆን ለብቻቸው ከታሰሩበት “ትፈለጋለህ” ተብለው ሲጠሩ “የመተኛ ሰዓቴ ነው ለምን” ቢሉም እንደሚፈለጉ በድጋሚ ተነግሯቸው ወደ ሌላ ክፍል ከተወሰዱ በኋላ ግንባራቸውንና ዓይናቸውን ተመትተው ጉዳት እንደደረሰባቸው ለፍርድ ቤቱ በመጀመሪያ አቤቱታቸውን ያሰሙት ሁለተኛ ተከሳሹ አቶ አሳምነው ጽጌ ናቸው፡፡

አቶ አሳምነው ለፍርድ ቤቱ ጨምረው ባሰሙት አቤቱታ በተለይ ግራ ዓይናቸው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበትና ሰው መለየት እንደማይችሉ፣ አንገታቸው ላይ አድርገውት የነበረ ሀብል ሲበጠስ በመጐዳታቸው ከፈሳሽ በስተቀር ምግብ መውሰድ እንደማይችሉ፣ ጥቅምት 28 እና 29 ቀን 2002 ዓ.ም. ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳልተገናኙ ተናግረዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ በሆነ ሐኪም እንዲመረመሩ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አካላት እንዲጐበኛቸው፣ እንደማንኛውም እስረኛ ከሌሎች እስረኞች ጋር ተቀላቅለው እንዲታሰሩ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸውም አመልክተዋል፡፡

“የተደበደበው ፍትሕ ነው” ያሉት አቶ አሳምነው ፍርድ ቤቱ ጥቃት ያደረሱባቸው ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዲያደርግላቸው ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል፡፡

የምግብ ማቆም አድማ አድርገዋል በሚል ከታሰሩበት ክፍል ወደ ሌላ ክፍል ተወስደው እጃቸው በካቴና ከታሰረ በኋላ ጆሮአቸው አካባቢ በደረሰባቸው ድብደባ ጉዳት እንደደረሰባቸው ለፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን ያሰሙት 6ኛ ተከሳሽ ሻለቃ መኮንን ወርቁ ሲሆኑ፣ እርሳቸው ግን ምንም ዓይነት የምግብ ማቆም አድማ አለማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ከማረሚያ ቤት እስረኞቹን በሀላፊነት ይዘው የመጡትን ኃላፊ ስለ ሁኔታው ጠይቋቸው፤ “ይኸንን ነገር የሰማሁት አሁን ነው፡፡ እንደዚህ ያለ ድርጊት በማረሚያ ቤቱ ውስጥ አልተፈፀመም ይኸ ሆን ተብሎ የማረሚያ ቤቱን ሥም ለማጥፋት ነው” በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

“ይኸ ፊት ለፊት የሚታይ ነገር ነው፡፡ የሆነ ችግር እንዳለ ይታያል፡፡ ተፈጥሮ ነው ወይስ ምንድነው?” በማለት ፍርድ ቤቱ ኃላፊውን ጠይቆ፤ ከሠው ጋር ተጣልተው ከሆነ “ተጣልተዋል”፣ ወይም ታመው ከሆነ “ታመዋል” በማለት መጠቆም እንደሚያስፈልግ ገል”ል፡፡

ማንም መመታት እንደሌለበት፣ ጉዳዩ መጣራት እንዳለበት ፍርድ ቤቱ አሳስቦ፣ “ተደብድበናል” ያሉት ተከሳሾች ሁኔታውን በጽሑፍ ለኅዳር 7 ቀን 2002 ዓ.ም. ይዘው እንዲቀርቡ አዟል፡፡

ፍርድ ቤቱ በተከሳሾቹ ላይ ጉዳቱን ያደረሱትንና ጉዳቱ የደረሰበትን ምክንያት የማረሚያ ቤቱ ዋና አስተዳዳሪ አጣርተው ይዘው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ በጉዳዩ ላይ ባለው አቅም አጣርቶ አፋጣኝ ውሳኔ እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

ጉዳዩ እስከሚጣራና ውሳኔው እስከሚሰጥ ድረስ በገለልተኛ ሀኪም ህክምና እንዲደረግላቸውና ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው የጠየቁት ደግሞ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ሲሆኑ፤ “የትና ማነው ገለልተኛ ሀኪም? የሚለውን አጣርተን አፋጣኝ ትዕዛዝ እንሰጣለን” በማለት ፍርድ ቤቱ ምላሽ ሰጥቶ ለኅዳር 7 ቀን 2002 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱ ተጠናቋል፡፡