An Addis Ababa neighborhood honors Bertukan Mideksa

The Ferensay Legacion area residents of Addis Ababa have awared the Vice President of the Coalition for Unity and Democracy Party (Kinijit) Bertukan Mideksa a brand new car on Saturday.

Bertukan MideksaFerensay Legacion is Wzt. Bertukan’s neighborhood. It is also an area that was savagely attacked by Woyanne tanks and Agazi special forces during the Nov. 2005 civil unrest when the residents tried to protect their favorite daughter from being taken away by security forces. To avoid further boodshed, Bertukan surrendered herself to the Woyanne, saving the neighborhood from Mogadishu-like devastation.

Also on Saturday, the Ferensay Legacion residents had organized a luncheon for the Kinijit leaders. Representing the party, Wzt. Bertukan and Prof. Mesfin gave speeches. Kinijit President Hailu Shawel could not attend the luncheon, but he was represented by his son, Shawel Hailu.

Ethiopian Review correspondent in Addis Ababa has filed the following report in Amharic (Amharic font can be downloaded here):

የቅንጅት ምክትል ፕሬዚደንት ብርቱካን ሚደቅሳ መኪና ተሸለሙ 

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ፈረንሳይ ለጋሲዮን እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች የአካባቢያቸው ልጅ ለሆነችው ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ መኪና በመሸለም ደስታቸውን ገለጹ፡፡ በተጨማሪም ከእስር ለተፈቱት የቅንጅት አመራሮች የምሳ ግብዣ አደረጉ፡፡ በግብዣው ላይ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም እና ወ/ት ብርቱካን ንግግር አድርገዋል፡፡

ከቀኑ አምስት ሰአት ጀምሮ ነበር ግብዣውን ያዘጋጁት የአካባቢው ነዋሪዎች ጉድ ጉድ ማለት የጀመሩት፡፡ እንግዶቹ በተጠሩበት 7፡00 ሰአት ሲመጡ ግን አካባቢው በጩኅት ተናወጠ፡፡ ሁሉም ደስታውን በጭብጨባ መግለጽ ጀመረ፡፡

ዝግጅቱ ወደተደረገበት የቀበሌ እድር አዳራሽ ሲገባ አዳራሹ ውስጥ የተሰበሰበው ህዝብ ደስታውን የሚገልጽበት ስሜት ምናልባትም ከምርጫው በሓላ የመጀመሪያው የህዝብ ስሜት ሊባል የሚችል ነበር፡፡ ሁሉም ታዳሚ የቅንጅት አርማ የሆነውን የጣት ምልክት በማውጣት በፉጨት ደስታውን ይገልጻል

አዘጋጆቹ ንግግር ካደረጉ በሓላ የምሳው ግብዣ ሥነስርአት የተከናወነ ሲሆን ኣቶ ኃይሉ ሻውል ባለመገኘታቸው የተዘጋጀላቸውን ስጦታ በልጃቸው አማካኝነት ተሰተቸዋል፡፡

በተጨማሪም ለፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም ስጦታ የተሰጠ ሲሆን ይህ ለሁለቱም የተሰጠው ስጦታ የቅንጅት አርማ የሆነው የጣት ምልክት የተቀረጸበት ዱላ ሲሆን ‹‹በትረ መንግስት›› ሲሉም ሰይመውላቸዋል፡፡

ለአቶ ሙሉነህ ኢዩኤል እና አቶ አለማየሁ ለተባለ የአካባቢቸው ወጣት ተጨማሪ ሥጦታን ከሰጡ በኋላ ለወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ሽልማት እንዳላቸው ተናገሩ፡፡ ህዝቡ ሽልማቱን ለማወቅ በከፍተኛ ጉጉት የጠበቀ ሲሆን ‹‹ጀግና›› ላለት የአካባቢያቸው ልጅ የመኪና ቁልፍ አስረከቡ፡፡ ህዝቡ ደስታውን በጭብጨባ ገለጸ፡፡

ወ/ት ብርቱካን ምን እንደምትናገር የጠፋት በሚመስል ስሜት በሁለት እጆችዋ አርማውን እያሳየች ከወገቧ በመጎንበስ ምስጋናዋን ገልጻለች፡፡ ወደ መኪናዋም በመሄድ የተሸፈነችበትን ጨርቅ ገልጣ ተረክባለች፡፡

አዘጋጆቹም ሽልማታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ‹‹አቅማችን ፈቅዶ ሁላችሁንም ብንሸልም ደሰ ባለን ነበር… ግን ለሁላችሁም የሚሆን አንድ ስጦታ አለን እሱም ልባችን ነው›› ብለዋል፡፡

ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳና ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም ረዘም ያለ ንግግር አድርገው ፕሮግራሙ ተፈጽሟል፡፡