Col. Kassaye Kifle passed away

Colonel Kassaye Kifle Colonel Kassaye Kifle has passed away on July 14, 2009, after receiving medical treatment at St. Thomas Hospital in Nashville, Tennessee.

Friends and family held a memorial service for him at the Debre Keranio Medhanialem Church in Nashville on July 17.

His funeral services will be held at the Debre Libanos Monastery in Ethiopia on July 25, 2009.

Many who had served as officers in the Ethiopian armed forces remember Col. Kassaye as a leader who served his country honorably.

Over during his career he was trained as an aviator in the United States, and aviation commander in the Soviet Union and the Ethiopian Air Force Command Staff College.

As a member of the Ethiopian Army Aviation Unit, he led Assault Helicopter Teams and received medals for bravery.

His contribution to Ethiopia continued as a pilot trainer at Ethiopian Airlines.

Col. Kassaye Kifle is survived by his wife, two children, and two grand children.

(Messages of condolence to the family can be sent to [email protected])

የኮሎኔል ካሣዬ ክፍሌ አጭር የህይወት ታሪክ

ኮሎኔል ካሣዬ ክፍሌ ከእናታቸው ከወይዘሮ ደመቀች አስፋውና ከአባታቸው ከአቶ ክፍሌ ደስታ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 1935 ዓ∙ም∙ በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ::

እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የ 1ኛና የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ኮከበ ፅባህ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኋላ አገራቸውን ለማገልገል በፅኑ ወዳመኑበት ሀረር ጦር አካዳሚ በመግባት ከፍተኛ የውትድርና ትምህርት ቀስመዋል::

ኮሎኔል ካሣዬ ክፍሌ ከሀረር ጦር አካዳሚ ከተመረቁ በኋላ በአርሚ አቪዬሽንና በኢትዮጵያ አየር ኃይል በአውሮፕላን አብራሪነት ለረጅም አመታት አገልግለዋል::

ኮሎኔል ካሣዬ ክፍሌ በስራ ባልደረቦቻቸው ክብርና ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፉ ከመሆናቸው ሌላ በሀገር ፍቅር ስሜታቸውና በቆራጥነታቸው እጅግ ተወዳጅ ነበሩ::

ኮሎኔል ካሣዬ ክፍሌ ከባለቤታቸው ከወይዘሮ ዘሪቱ ዘውገ በሰላምና በፍቅር ለ 27 ዓመታት በጋብቻ ፀንተው የኖሩ ሲሆን ሁለት ልጆች አፍርተዋል::

ኮሎኔል ካሣዬ ክፍሌ ባደረባቸው ፅኑ ህመም በህክምና ሲረዱ ከቆዩ በኋላ በናሽቪል ከተማ ሴንት ቶማስ ሆስፒታል እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሐምሌ 7 ቀን 2001 ዓ∙ም∙ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል:: አስከሬናቸው ወደ ውድ አገራቸው የተላከ ሲሆን በዛሬው እለት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሐምሌ 18 ቀን 2001 ዓ∙ም∙ የቀብር ስነስርዓታቸው በኢትዮጵያ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ይፈፀማል::

ቸሩ ኣምላክ የኚህን ጀግና የኢትዮጵያ ልጅ ነብስ ከፃድቃን መካከል እንዲያኖራት የሁላችንም ፀሎት ነው::