Head of Ethiopia Telecommunication Agency defects

In another blow to the fast decaying regime of the Woyanne tribal junta in Ethiopia, the director of Ethiopian Telecommunication Agency, Ato Eshetu Alemu, has defected in the U.S., according to The Reporter.

Eshetu came to the U.S. to attend a 15-day training in executive telecommunication management. He is the second high level Woyanne regime official to defect in the U.S. this month.

In early July, propaganda chief Bereket Simon’s deputy, Ato Ermias Legesse, has disappeared after arriving in the U.S. on a business trip.

More from The Reporter:


የቴሌ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አሜሪካ ቀሩ

የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ እሸቱ ዓለሙ ለስብሰባ አሜሪካን ሄደው እንደቀሩ ተጠቆመ፡፡ የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቃቸውም ታውቋል፡፡ አቶ እሸቱ ከሚያዝያ 25 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ለ15 ቀናት በኤክስኪዩቲቭ ቴሌኮም ማኔጅመንት ስልጠና ለመሳተፍ አሜሪካ እንደሄዱ ምንጮቻችን፣ ተናግረዋል፡፡

ከ1995 ዓ.ም. ጀምሮ አሜሪካ እስከሄዱበት ቀን ድረስ የኤጀንሲው ዳይሬክተር ሆነው ሲሰሩ የነበሩት አቶ እሸቱ፣ በኢሜል በላኩት መልዕክት በአሜሪካ እንደሚቆዩ ማረጋገጣቸውን ለእሳቸው ቅርበት ያላቸው የሥራ ባልደረቦቻቸው አመልክተዋል፡፡

ከኬሚስትሪ በተጨማሪ በኢንፎርሜሽን ሳይንስ የማስትሬት ዲግሪ እንዳላቸው በፕሮፋይላቸው ላይ የጠቀሱት አቶ እሸቱ የቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ቦርድ አባል ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ቀደም ሲል በሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን የተለያዩ ኃላፊነቶች ላለፉት 7 ዓመታት ሰርተዋል፡፡