A prominent Ethiopian scholar/theologian passed away

Aleqa AyalewAleqa Ayalew Tamiru, a prominent Ethiopian theologian and scholar, passed away on Sunday at his home in Addis Ababa. He was 83 years old.

Aleqa Ayalew was an icon of the Ethiopian Orthodox church who was engaged in a running battle with Aba Gebre-Medhin (formerly Aba Paulos) over fundamental teachings of the Church. He had served as chairman of YeLiqawnt Gubae (council of scholars) until he was forced out by Aba Gebre-Medhin, the gun-totting illegitimate patriarch of the Ethiopian Orthodox Church.

The following is a report from Addis Ababa:


አለቃ አያሌው ታምሩ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ


Aleqa Ayalew Tamiruአለቃ አያሌው በአራት አመታቸው በምስራቅ ጎጃም ዞን ዲማ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን የቤተክህነት ትምህርት የጀመሩ ሲሆን በእድሜ ዘመናቸው ቤተ ክህነትን ሲያገለግሉ የነበሩና በኋላም የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ በነበሩበት ወቅት በ1988 ዓ.ም ከአባ ገ/መድህን (የቀድሞው አቡነ ጳውሎስ) ጋር ቤተክርስቲያኒቱን በሚመለከት ጠንካራ የሃሳብ ልዩነት በመፈጠሩ ወጥተዋል፡፡
ሊቀጠበብት አያሌው ወያኔ በጠመንጃ ሃይል ካስቀመጣቸው ጳጳስ ከአባ ገ/መድህን ጋር ያለመግባባቶች የነበራቸው እንደነበር ወዳጆቻቸው ሲናገሩ በተለይ በ1988 ያለመግባባታቸው ጎልተው መተው ነበር ይላሉ፡፡ ልዩነቶቻቸውም የቅዱስ ሲኖዶስ ተጠሪነቱ ለፓትሪያርኩ ይሁን በሚል አባ ገ/መድህን ሲወስኑ አለቃ አያሌው በበኩላቸው ቅዱስ ሲኖዶስ መመራት ያለበት በመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ጰጳሳቱ በእኩል ተቀምጠው በመግባባት በእኩልነት ነው ሊወስኑ የሚገባቸው በቅዱስ ሲናዶስ ማንም የበላይ ሊሆን አይገባም፡፡ ኃይማኖቱም የሚያዘው ይህንኑ ነው በማለት ሲከራከሩ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ገልፀውልናል፡፡

በተጨማሪም ተጠሪነቱ ለፓትሪያርኩ ተደርጎ የነበረው ቅዱስ ሲኖዶስ “የኢትዮጵ እምነት ስርዓት አምልኮና የውጭ ግንኙነት” በሚል በእንግሊዝኛና በአማርኛ ያሳተመው መጽሃፍ “ክብር ድንግል ማርያምን የሚነካና ሚስጥረ ስላሴን የሚያፋልስ አንቀጽ አለበት” በማለት አለቃ አያሌው ተቃውመትም ሰላማዊ ሰልፍ ተወጥቶበትም ነበር፡፡በዚህ መፅሃፍ ላይ የአለቃ አያሌው ሌላው ልዩነት በወቅቱ እሳቸው የሊቃውንቱ ጉባኤ ሰብሳቢ የነበሩ በመሆናቸው መፅሃፉ የወጣው በሊቃውንቱ ሳይታይ በፓትሪያርኩ ትዕዛዝ ነው የሚልም እንደነበር የሚያስታውሱ ይናገራሉ፡፡ሊቀጠበብት አያሌው ታምሩ ከፆም ብዛት ከፍተኛ የአንጀት ድርቀት ህመም የነበረባቸው ሲሆን ፕሮፌሰር አስራት ወ/የስ ከዚህ አለም በሞት ከመለየታቸው በፊት ሁለት ጊዜ ቀዶጥገና አድርገውላቸዋል፡፡ በተጨማሪም በሌላ ሃኪም ለሶስተኛ ጊዜ ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸው እንደነበር የቅርብ ወዳጆቻቸው ይናገራሉ፡፡በተለይ ከፕሮፌሰር አስራት ወ/የስ ጋር ጠንከር ያለ ወዳጅነት እንደነበራቸው በቅርብ የሚያውቋቸው ያስታውሳሉ፡፡አለቃ አያሌው መጋቢት 23/1916 ዓ/ም ተወልደው በ1920 ዓ.ም የቤተክህነት ትምህርት መማር የጀመሩ ሲሆን በህፃንነታቸው በአካባቢያቸው በገባው የፈንጣጣ ወረርሽኝ ለዓይነ ስውርነት ተዳርገዋል፡፡በብፁእ ቅዱስ ፓትሪያርክ ዘኢትዮጵያ በአቡነ ባስሊዮስ ግዜ ሊቀጠበብት አያሌው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ተ/ኃይማኖት እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የደብረ አማን ፃዲቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆነው ሰርተዋል፡፡አለቃ አያሌው “የኢትዮጵያ እምነት በሶስቱ ህግጋት”“መች ተለመና ከተኩላ ዝምድና”“የፅድቅር፣ ምልጃ፣ ዕርቅና ሰላም”፣ “መልዕክተ መንፈስ ቅዱስ፣ ወላዲት አምላክ ኢትዮጵያ፣” “አባትና መሠረት” እና “የኑሮ መሠረት ለህፃናት” የሚሉ መፅሃፍቶችን ፅፈዋል፡፡አለቃ አያሌው የ12 ልጆች አባት ሲሆኑ የአብዛኞቹ ልጆቻቸው ኑሮ ከኢትዮጵያ ውጪ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡